ደጀ ሰላምን በኢሜይል

በዚህች የጡመራ መድረካችን የምናቀርባቸው ዜናዎች፣ ሐተታዎችም ሆኑ ሪፖርታዦች ከአንባብያኑ ከእናንተ ከደጀ ሰላማውያን መድረሳቸውን ማረጋገጥ እንፈልጋለን። ሰው መቸም “ያዘጋጀውን ሲበሉለት፣ የወለደውን ሲስሙለት” ነውና ደስታው ይህንን ለማድረግ ዘወትርም እንሞክራለን። እነሆ አሁንም የደጀ ሰላም ዝግጅቶች በወጡ ቁጥር ያለምንም ችግር እንዲደርሷችሁ እና ለወደፊቱም ለማስቀመጥ ብትፈልጉት ቀላል ይሆንላችሁ ዘንድ አዲስ የኢ-ሜይል አቅርቦት ጀምረናል። ቀላል እና ሦስት ደረጃ ያለው ነው።
1ኛ. ኢሜይሎትን በባዶ ቦታው ያስገባሉ፣
2ኛ. ደጀ ሰላም “አውቶማቲካሊ” ኢሜይሉን ያስገቡት እርሶ መሆን አለመሆን ለማረጋገጥ አንዲት መልእክት በኢሜይሎ ይልክሎታል፤ እንዲህ ይላል፦
Hello there,
You recently requested an email subscription to
ደጀ ሰላም Deje Selam. We can't
wait to send the updates you want via email, so please click the following
link to activate your subscription immediately:
http://feedburner.google.com/fb/a/mailconfirm?k=2IvbETeZ9pqJBR

(If the link above does not appear clickable or does not open a browser
window when you click it, copy it and paste it into your web browser's
Location bar.)

3ኛ. ኢሜይሉ እንደደረሰዎት “አዎን እኔ ነኝ” ብለው ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ምልክት የሚመስለውን (http://feedburner.google.com/fb/a/mailconfirm?k=2IvbETeZ9pqJBR ) ምልክት ሲጫኑና ሲያረጋግጡልን ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ በኢሜይሎት መላክ እንጀምራለን።

በቀላሉ “ፕሪንት” ለማድረግም ሆነ ለሰዎች ለመላክ ይችላሉ። ነቢዩ “ሕዝቤ እውቀት ከማጣት የተነሣ ጠፋ” እንዳለው እኛም “እውቀት በማግኘት እንድን/ እንተርፍ” ዘንድ እንወቅ፣ እንጠይቅ።

ወደ መጦመሪያችን የፊት ገጽ (ሆም ፔጅ http://www.dejeselam.org/) ይሂዱና ኢ-ሜይሎትን ያስገቡ።

ድረ ገፁን ሲከፍቱ በግራ በኩል ያገኙታል።

ቸር ወሬ ያሰማን


Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)