June 21, 2016

በአሜሪካ/በውጩ ዓለም ያሉት አባቶች ወዴየት እያመሩ ነው?!


(ተረፈ ወርቁ):- "... እንደው እነዚህ በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች እንደምንም ብለው ተጠናክረው በአገራችን በኢትዮጵያ በእነርሱ በሚመራው በአሜሪካው "ሲኖዶስ" ሥር ያለ/የሚመራ አንድ እንኳን ቤተ ክርስቲያን መመሥረት ቢችሉ በየቦታው ተበታትኖ ያለውን የተሃድሶ እንቅስቃሴ አንድ ማድረግ መምራት ይቻል ነበር እኮ ...።"

ይህ ቁጭት፣ ምሬት አዘል ቃል በአንድ  ወቅት የኢትዮጵያን ቤ/ን እናድሳለን ብለው ከተነሡ ሰዎች መካከል ማህበር አቋቁሞና ከአንዳንድ ስለ ሃይማኖታቸው በቂ የሆነ መሠረት ከሌላቸውና የእውነት ዕውቀትን በፍቅር ካልተቀበሉና እንደ "ዘመነ መሳፍንቱ" - የባላባቶች ዘመን "አወዳሽና አንጋሽ" ፈላጊ በሆኑ ባለ ጠጋዎች፣ ወይዛዝርት፣ ነጋዴዎች ምጽዋትና እንዲሁም ከውጭ አገር በሚላክለት ዶላር (በተለይ ከዱባይና ከአሜሪካ) በዐሥር ሺዎች የሚገመት ዘመናዊ ቤት/አዳራሽ ተከራይቶ የተሐድሶን እንቅስቃሴ ለማስፋፋት ላለፉት 20 ዓመታት እየደከመ ያለ ሰው የተናገረው ምሬት ያዘለ ቃል ነው። ለነገሩ ይህ ማህበር በነጋ ጠባ ራሳቸውን በሾሙ በጎበዝ አለቆች የሥልጣን ይገባኛልና በጥቅም ግጭት ሲፈርስ ሲሠራ የኖረ፣ እንዳሰቡትና እንዳለሙት እንኳን የኢትዮጵያን ቤ/ን ሊወርሱ ቀርቶ የሕልም ዳቦቸውን እየገመጡ በቀቢፀ ተስፋ ተውጠው ነው ያሉት።

June 13, 2016

የማኅበረ ቅዱሳን የ፭ኛ ዙር ዐውደ ርእይ አጭር ቅኝትእንደ መንደርደሪያ

(ተረፈ ወርቁ):- ከጥቂት ዓመታት በፊት የለንደኑ ተነባቢ መጽሔት ‹‹ዘታይምስ›› ስለ ሩሲያዊው፣ የዓለማችን ታላቅ የፖለቲካ ሰው ቭላድሚር ፑቲን ሃይማኖተኝነት አስመልክቶ አንድ ሰፋ ያለ ዘገባ ይዞ ወጥቶ ነበር፡፡ ዘታይምስ ይህን ዘገባ ይዞ የወጣበት ምክንያት ደግሞ በወቅቱ የሩሲያ ጠቅላይ / የነበሩት፣ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በእስራኤል ይፋዊ ጉብኝት ያደርጉ ስለነበር ነው፡፡

June 12, 2016

የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዕርቀ ሰላም እና የዘመናችን ፖለቲካ


መግቢያ

(ዲባባ ዘለቀ):- በሀገራችን የፖለቲካ ሥርዓት ለውጥ ግርግር የሁልጊዜ ተጠቂ የሆነችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት መከራ በመቀበል ኖራለች።  የሩቁን ትተን የቅርቡን እንኳን ብናነሳ በኢጣልያ ወረራ ወቅት ስለሀገር ሉዓላዊነት የመሰከሩና ህዝቡ ለወራሪው እንዳይገዛ ያወገዙ ሁለት ብጹዓን ኣባቶች (ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና ብፁዕ አቡነ ሚካኤል) በመትረየስ ጥይት ተደብደበው ተገደሉ። እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ መነኮሳትና ካህናት በየገዳማቱና አድባራቱ በግፍ ተጨፈጨፉ። 1966 አብዮት ማግሥት ፓትርያርኳ በግፍ እና በአረመኔያዊ ጭካኔ በሲባጎ ታንቀው በደርግ ኮማንዶዎች ተገደሉ።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)