April 28, 2016

ስቅለትን በስግደት ወይስ በሙግት?

·         የ2008 ዓ.ም በዓለ ስቅለት በእመቤታችን ቀን ውሏል። እናም ይሰገዳል? ወይስ አይሰገድም?
·         ይኸው ገጠመኝ በ1913 ዓ.ም ተከስቶ በነበረበት ወቅት አበው ጉዳዩን እንዴት ፈቱት?
(መምህር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ):- በተወሰኑ ዓመታት መካከል የስቅለት ዕለት በየጊዜው ዘንድሮ እንደሆነው ሲገጥም ክርክር ይነሳል። አስታውሳለሁ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ ሳለሁ እንዲሁ ስግደት በእመቤታችን ዕለት በመዋሉ ምክንያት በተለያዩ አድባራት ተበታትነን በዓሉን የምናሳልፍ ተማሪዎች እንደየደብሩ አለቃ ስሜት ወይም ግንዛቤ አሳልፈን ተመልሰናል። ማለትም አንዱ ጋር ይሰገዳል አንዱ ጋር አይሰገድም። ይህ ክርክር ዘንድሮም ቀጥሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ የማያዳግም ምላሽ ቢሰጥበት መልካም ነው። በቅድሚያ ጾሙን በጥሩ ሁኔታ የቻላችሁትን ያክል በትጋት ላሳለፋችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ድካም ባለው ተጋድሎዋችሁ ቸርነቱን አክሎበት የልባችሁን መሻት ይስጥልኝ። የጾምና ጸሎታችሁም በረከት ይድረሰን ለብርሃነ ትንሳኤውም በሰላም ያድርሰን እላለሁ።
ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ ዘንድሮ ስቅለት በእመቤታችን ቀን ውሏል። እናም ይሰገዳል? ወይስ አይሰገድም? በሕማማት ውስጥ ከትንሳኤ በፊት ያለችው ቅዳሜ የተሻረች ሰንበት ትባላለች (ቀዳሚት ስዑር) ሃይማኖተ አበው እንደሚያዝዘን በቅዳሜ ቀን መጾም ክልክል ነው። ከቀዳሚት ስዑር በቀር ይላል ስለተሻረች የሕማማትን ቅዳሜ እንጾማታለን በሕማማት ውላለችና። ልክ እንደዚሁ በሕማማት ማንኛውም በዓል ቢውል አይከበርም።

April 21, 2016

ዐውደ ርእዩ ተፈቀደ፤ እኛም "ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ" ብለን ተቀበልን¡¡

 (ዲባባ ዘለቀ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት):- በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፣ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 15-21 ቀን 2008 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማእከል ለ5ኛ ጊዜ ሊያካሔደው የነበረው ዐውደ ርእይ ለእይታ ሊቀርብ ጥቂት ሰዓታት ሲቀር በቀጭን ትእዛዝ ያገደውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ርእይ ፀሐዩ መንግሥታችን መፍቀዱን አስታውቋል።በዚህ ምክንያት ነው ያገድኩትለማለት ያልተገደደው የአጼዎቹ መንግሥት ዛሬም እንዲታይ የፈቀደበትን ምክንያት መጠየቅ ነውር ሆኖ ይልቁንም ስለፈቀዳችሁልን "እናንተን ያቆይልን" ለማለት ዳር ዳር እየተባለ ነው። ወያኔ ላለፉት 25 ዓመታት የሕዝብን ተቃውሞ ሲያስተነፍስ የኖረበትም ስልት ይኸው ነው። ለፓለቲካ ዓላማ ወሳኝ የሆኑ ርምጃዎችን በህገ ወጥነትና በድፍረት ይወስድና ሕዝቡ እንዲንጫጫ ካደረገ በኋላ ትንሽ ዘግየት ብሎ ነገሩን የሚያበርድ ከፊል ምላሽ ይሰጣል። ሕዝቡም "ኧረ ይህንንስ  እነርሱ ቢሆኑ አይደል? እግዚአብሔር ይስጣቸው!" ብሎ አስቀድሞ የጠየቀውን ጥያቄ ዘንግቶት ዝም ይላል። ይህ ስልት ሳይቀየር ለሩብ ምእተ ዓመት መሥራቱ በራሱ ኢትዮጵያውያን ለማታለል የማናስቸግርየዋሕሕዝቦች መሆናችንን የሚያረጋገጥ ይመስለኛል።

April 15, 2016

ኦርቶዶክሱ ራሱን ሁለተኛ ዜጋ ያደረገበት አካሔድ

የሚከተለው ጽሑፍ በዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ ተጽፎ አደባባይ የጡመራ መድረክ (www.adebabay.com) ላይ የወጣ ነው። ደጀ ሰላማውያን ቢያነቡት መልካም ነው በሚል ሐሳብ እነሆ አቅርበነዋል። 
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን

+++++

እንደ ዳራ (Background)


(ኤፍሬም እሸቴ/ ephremeshete@gmail.com/ www.adebabay.com)
ሁለት የባፕቲስት ሚሲዮን እምነት ተከታዮች የሆኑ ፓስተሮች ባለፈው የጥምቀት ሰሞን አገራችንን መጎብኘታቸውን እንዲሁም ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋርም መነጋገራቸውን በፎቶግራፎች አስደገፈው ያወጡት ዜና ያትታል። ዜናውን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ከፍተኛ መነጋገሪያ እንዲሆን ያደረገው የሁለቱ ፓስተሮች ጉብኝት ሳይሆን እንገነባዋለን ያሉት የ50ሺህ አብያተ ጸሎት ጉዳይ እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ናቸው በተባሉት በአፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ላይ (ያውም በፓርላማው መንበራቸው ላይ እንደተሰየሙ) ከዳርና ከዳር ጠምደው ጸሎት ሲያደርጉላቸው የሚያሳየው ፎቶግራፍ ነው። http://www.bpnews.net/46636/layman-plans-for-50000-churches-in-ethiopia

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)