March 1, 2016

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል:- በረከትዎ ትድረሰን … እረፍተ አበው ያድርግልዎ

(http://eotcmk.org):- ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐረፉ:: ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በምሥራቅ ትግራይ ክለተ አውላሎ አውራጃ አውዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሕይወት ፀዓዱ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ወለተ ክርስቶስ ቢሻው በ1923 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ዲቁናን ከአቡነ ይስሐቅ፣ ቅስና፣ ቁምስና እና ምንኩስና ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ተቀብለዋል፡፡

ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የትግራይ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ተብለው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከ30 ዓመታት በላይ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው በማገልገል ላይ ሳሉ የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ዐርፈዋል፡፡
ሥርዓተ ቀብራቸው ሐሙስ የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም በሀገረ ስብከታቸው ራሳቸው በገደሙትና ከፍተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት ሲሰጡበት በነበረው ደብር ቅዱስ ደብረ መዓዛ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ይፈጸማል፡፡
                                                                                                                  
 የአባታችንን ነፍስ ከደጋጎቹ አበው ጋር ያድርግልን
አሜን።
         

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)