March 26, 2016

ማንንም የማይፈራው እውሩ መንግሥታችን!!!

(ዲባባ ዘለቀ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት):- ማኅበረ ቅዱሳንኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅበሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል 1 ሳምንት ለማሳየት ያዘጋጀው ዐውደ ርእይ ለዕይታ ለመቅረብ ሰዓታት ሲቀሩትባልታወቀ አካልቀጭን ትዕዛዝ መታገዱን በዘመኑ ፈጣን የመገናኛ መንገዶች ከኢትዮጵያ አልፎ በመላው ዓለም ተሰምቷል።  በእርግጥም የቤተ ክርስቲያኗ ልጆች ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመተባበር የቤተ ክርስቲያኒቱን ገጽታ በሚገባ ለማሳየት፣ ርትዕት የሆነውን ትምህርተ ሃይማኖቷን በሚገባ ለመግለጥ፣ እንዲሁም ምእመናን ሌሎችን ወቃሽ ብቻ ሳይሆኑ ከቤተ ክርስቲያን ባገኙት የልጅነት ጸጋ እንዴት ማገልገል እንደሚችሉ ለማመላከት ይቻል ዘንድ ሌት ተቀን ደክመው ያዘጋጁት መርሐ ግብር በድንገት ሲሰረዝ እንኳን ለአዘጋጆቹ ለማንኛውም የቤተ ክርስቲያን ምእመን አሳዛኝ ነው።

March 16, 2016

ከ”አሜን ባሻገር”ን በዐይነ-ደብተራ አሻግረን ባየናት ጊዜ!

(በአማን ነጸረ በፌስቡክ እንደጻፉት):- መጽሐፊቱ ጓዘ-ብዙ ናት፡፡ ታሪክ፣ፖለቲካ፣የጉዞ ማስታወሻ ትነካካለች--መጽሐፊቷ፡፡ የታሪክ ማጠንጠኛዋ አጼ ምኒልክን ማዕከል ያደርጋል፡፡ ጭብጧአጼ ምኒልክ ያገሪቱን ማዕከላዊና ደቡባዊ ክፍል እስከ ጠረፉ ባስገበሩበት ጊዜ ከብሔር ብሔረሰቦች ቀደምት አበው፡- የሌላውን ብሔር ያልተነኮሰ፣በራሱ የብሔረሰብ አባላት ላይ -ሰብአዊ ድርጊት ያልፈጸመ፣በውስጡ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ያሰፈነ የብሔር ወይም የጎሳ ባላባት ያለው ብሔረሰባዊ ምሁር የምኒልክን አጽም በድንጋይ ይውገርየምትል ሆና ተሰምታኛለች፡፡ መከራከሪያው ቅጣት ማቅለያ ይሆን እንደሆነ እንጅ አንዱ ብሔር በሌላ ብሔር ተወላጅ ባላባት ሲጨቆንና በራሱ ቋንቋ ተናጋሪ ብሔረሰብ ሲጨቆን ስሜቱ እኩል አይመስለኝም፡፡ በዚህ ላይ ያለነው ብሔር-ተኮር ክልላዊ አረደጃጀትና ሕገ-መንግሥታዊ ቁመና በገነነበት ጊዜ ነውና የጨቋኙ ብሔረሰባዊ ማንነትም ለወገናዊ ትረካው አስተዋጽኦ አለው ብዬ አምናለሁ፡፡

March 9, 2016

ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ባሻገርሕዝብና መንግሥት እንዲወያዩ ጥሪ ቀረበ፤ ጸሎትና ምሕላ ታወጀ፤ ስለ ሶሻል ሚዲያና ድርቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ!
 (ደጀ ሰላም፤ ማርች 9/2016፤ የካቲት 30/2008 ዓ.ም )፦ የብፁዕ አቡነ ናትናኤልን እረፍትና ቀብር ተከትሎ ከየሀገረ ሰብከታቸው የመጡ አበው የቅ/ሲኖዶስ አባላትን መሰባሰብ ተከትሎ የተጠራው አስቸኳይ ጉባኤ እንደተካሄደ መዘገቡ ይታወሳል። የተሐድሶ ድረ ገጾች “ማህበረ ቅዱሳን ያስጠራው ስብሰባ ነበረ፤ ከሸፈ” ሲሉ ኦርቶዶክሳውያን የጡመራ መድረኮች ደግሞ ፓትርያርኩ የሚያካሒዱትን የቤተ ክህነቱን አስተዳደርና አሠራር እንዲሁም የቅ/ሲኖዶስን የበላይነት የሚያስተሐቅር ርምጃ እንዲያስተካክሉ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው በሰፊው ዘግበዋል። ከመጋረጃ ጀርባ በዝግ በር ያለው እልህ አስጨራሽ ስብሰባ ካለቀ በኋላ የወጣው መግለጫ ብዙ ቁምነገሮች ይዞ እናገኘዋለን። ከነዚህም ውስጥ ሕዝብና መንግሥት እንዲወያዩ ጥሪ መቅረቡን፤ ጸሎትና ምሕላ መታወጁን፤ ስለ ሶሻል ሚዲያና ድርቁ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ማንሣት ይቻላል።

March 7, 2016

በኢትዮጵያም፣ በአሜሪካም ያለው የተሐድሶ ቡድን ጡንቻውን እያፈረጠመ ነውን?

·        በስደት በሚገኙ አባቶች ጉባኤ አድርገው መግለጫ አውጥተዋል፤
·        “የቤተ ከርስቲያን ችግር” ያሉት በርግጥ ችግር ነውን?
·         ከመካከላቸው ያሉትና በእምነታቸው ነቅ የሌለባቸው አባቶች ለምን ዝምታን መረጡ?
·        “በስደት ባለው ሲኖዶስ ሥር ላሉ አብያተ ክርስቲያናት አገልጋዮችና ምእመናን” ከፍ ያለ ታሪካዊ ጊዜ ነው፤

 (ደጀ ሰላም፤ ማርች 6/2016፤ የካቲት 27/2008 ዓ.ም )፦ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት እና በዋናው ጠቅላይ ቤተክህነት ስር የሚገኙ የተለያዩ ካህናት “ጊዜው ተመችቶናል” በሚል ጦርነት በከፈቱበት በዚህ ወቅት በስደት በሚገኙ አባቶች የሚመራው ቤተ ክህነት አባላት የሆኑ ካህናትም ሰሞኑን ጉባዔ ማድረጋቸውንና የአቋም መግለጫ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል (መግለጫውን በመጨረሻ ያገኙታል):: እነዚሁ “ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ” በሚባለውና በ4ኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ በሚመራው ክፍል ሥር የሚገኙ ካህናት ያደረጉት ጉባዔ ከየካቲት 21-25/2008 ዓ.ም (ከፌብሩዋሪ 29 እስከ ማርች 4/2016 መሆኑ ነው) ድረስ የተካሄደ መሆኑን “ቆሞስ አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ” በሚል ፊርማና ማኅተም የወጣው መግለጫ ያትታል። ታዲያ ስለምን ተነጋገሩ? ውሳኔያቸውስ ምን ይሆን?

March 5, 2016

አባ ማቲያስ:- ከመሳሳም ይቅርታ ይቅደም!


·        "ከካቶሊክ ጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነው" (አባ ማቲያስ ሕዳር 2008)
·        " ከቫቲካን ጋር የነበረንን የቀድሞ ፍቅር(?) እንመልሰዋለን" (አባ ማቲያስ የካቲት 2008)
·         " ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስትያንን የገዛ ቅኝ ገዥ ነው" (አባ ማቲያስ ጥቅምት 2008)
·        ወራሪዋን ቫቲካንን ፍቅር : ልጆቻቸውን ቅኝ ገዥ--- አባት ብሎ ዝም!!

(ዘአዲስ እንደፃፉት):- አባ ማቲያስ በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ትግራይ ሄደው ጉብኝት ማድርጋቸው ይታወሳል:: አዲግራት ላይ የአዲግራቱ የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ቦታ ላይ " ከካቶሊክ ጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነው" በማለት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል:: http://www.addisadmassnews.com/images/Issue-826.pdf

March 3, 2016

"በዛቻና በማስፈራራት የባከኑት የፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ሦስት ዓመታት"

እንደ መግቢያ
       እነሆ የኢትዮጵያ በራሷ መመራት ከጀመረች 57 ዓመት ሊሞላት ጥቂት ወራት ቀራት፡፡ በእነዚህ 57 ዓመታት ውስጥ አሁን በመንበሩ ላይ ያሉትን ሳይጨምር 5 ፓትርያርኮችን አስተናግዳለች፡፡ እነዚህ አባቶች በዘመናቸው በቤተ ክርስቲያንና በምድሪቱ ላይ የራሳቸውን አሻራ አሳርፈው አልፈዋል፡፡
አቡነ ማትያስ ስድስተኛው የቤተ ክርስቲያናችን ፓትርያርክ ሲሆኑ ከቀናት በኋላም ሦስተኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ያከብራሉ፡፡ እኔምመቼም ክፉም ይሁን ደግ ታሪክ ነውና መጻፍ አለበትየሚለውን የአባታችንን ቃል መነሻ በማድረግ ለበዓለ ሢመታቸው መታሰቢያ ይህንን መጣጥፍ አዘጋጀሁ፡፡ (በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ያለው ቃል አቡነ ማትያስ ራሳቸው በኢትኦጵ መጽሔት ላይ ስለ አቡነ ጳውሎስ ጉዳይ ሲጽፉ የተጠቀሙት ነው፡፡) መቼም የቤተ ክህነቱ ሹማምንት የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና እና የሐሳብን ልዕልና አጥብቀው ቢጋፉም፣ አንጻራዊ ነጻነቴን ማለትም ቢያንስ የቤተ ክህነቱ ሠራተኛና የየትኛውም ማኅበር አባል አለመሆኔን ተጠቅሜ ጥቂት ልተንፍስ፡፡

March 2, 2016

ፓትርያርክ ማትያስ:- ከፖፕ ፍራንሲስ ሊማሯቸው የሚችሏቸው ነገሮች

(ማርች 2/2016/ የካቲት 23/2008 ዓ.ም):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ወደ ቫቲካን ጉዞ ማድረጋቸው እና ከሮማማው ፓፓ “ፖፕ ፍራንሲስ” ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው በመገናኛ ብዙኃን ተዘግቧል፡፡ ሲጨባበጡ፣ ትከሻ ለትከሻ ተሳስመው ሰላምታ ሲለዋወጡ፣ ፓትርያርካችን ለፖፕ ፍራንሲስ ማስታወሻ መስቀል እና መጽሐፍ ሲሰጡ ሁሉ አይተናል።
የሁለቱ መሪዎች ዋነኛ የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የክርስቲያኖች መከራ፣ ስደትና የቤተ ክርስቲያን ውድመት እንደሆነ ከፖፑ ንግግር መረዳት ይቻላል። “የክርስቲያኖች የሰማዕትነት ደም የክርስትና ዘር ነው” የሚለውን ታዋቂ ቃል አንስተው ፖፑ ማብራራታቸው ተዘግቧል። ዝርዝሩን መመልከት ለሚሻ ዜናው ወደተዘገበባቸው ሥፍራዎች ጎራ ማለት ይችላል።

የተሐድሶዎች ዓላማና ግብ ለምን ያደናግረናል? ከሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንዴት መማር አቃተን?

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ “ተሐድሶ” (ሪፎርሜሽን) ለማካሔድና በእነርሱ እምነት “ተባላሽቷል” የሚሉትን በመቀየር ገሚስ ፕሮቴስታንት ገሚስ ኦርቶዶክስ መሰል እምነት የመፍጠር ዓላማ መኖሩ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው እውነታ ሆኖ “አለ ወይስ የለም?” በሚል ለምን ግር ይለናል? በሃይማኖታቸው ኦርቶዶክሳዊነት የማይጠረጠሩ ብዙ ሰዎች በዚህ ጉዳይ ልባቸው ይከፈላል። ለማመንም ለመተውም ይቸግራቸዋል። በሌላ አቀራረብ የሚቃወሙትን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ትምህርት ለማስፋፋት የሚጥሩትን ተሐድሶዎቹን ሲረዷቸው ይገኛሉ። ይህ የመደናገርና ግርታ ላይ የመውደቅ አባዜ እጅግ ሥር ከመስደዱ የተነሣ በአገር ቤት ያለችውን ቤተ ክህነት እጅግ እግሯን አስሮ ሊቆጣጠራት ምንም አልቀረውም። ከአገር ቤቱ ተገንጥለን የራሳችን ሲኖዶስ አለን የሚሉትንም አባቶች እንዲሁ መጠቀሚያው አድርጓቸዋል። የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና የሆነው ይህ “ሪፎርሜሽን/ Reformation” የተባለ አፈንጋጭ አስተምህሮ ሊያመጣ የሚችለው ውጤት ለማይታያቸው ምናልባት የዚሁ ችግር ሰለባ የሆነችውን የሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በአጭሩ መጥቀስ አብነት ሊሆን ይችል ይሆን?

March 1, 2016

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል:- በረከትዎ ትድረሰን … እረፍተ አበው ያድርግልዎ

(http://eotcmk.org):- ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐረፉ:: ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በምሥራቅ ትግራይ ክለተ አውላሎ አውራጃ አውዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሕይወት ፀዓዱ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ወለተ ክርስቶስ ቢሻው በ1923 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ዲቁናን ከአቡነ ይስሐቅ፣ ቅስና፣ ቁምስና እና ምንኩስና ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ተቀብለዋል፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)