April 4, 2014

“የሚቀብሯትን የምትቀብር ቤተክርስቲያን!”

  (By “Abel Sog Sos”)
እስኪ እውነቱን እንነጋገር!
አሁን ባለንበት ዘመን ሃገርን ስለመውደድ የምንማረው/የተማርነው ከየት ነው? ከቤተ እምነቶች ወይስ ከስነ ዜጋና ስነ ምግባር ወይም "ሲቪክስ" ኮርስ? የጸረ ሙስና ኮሚሽን ሳይቋቋም ማን ነበር የራስ ያልሆነን ስላለመውሰድ ያስተማረው? አሁንስ ቢሆን? የሃይማኖት ተቋማት አይደሉምን?

እድሜ ለማኅበረ ቅዱሳንና ወጣቱ በየግቢጉባዔያቱ ተኮትኩቶ ባይወጣ ምን ይውጠን ነበር? አገሩ ሁሉ ሙሰኛ በሙሰኛ ይሆን አልነበር! (መንግስት እንዲያውም ቢያውቅበት ሊደግፈው ይገባ ነበር፤ የ'ርሱን ስራ ማኅበረ ቅዱሳን እየሰራለት ስለሆነ!)

በመልካም ገጽታ ግንባታ (የተዋስኳት ከኢቲቪ ነው።) ከመንግስት ባልተናነሰ የሃገር ሃብት የሆኑ ቅዱሳት መካናትን ጠብቆ በማቆዬት የአንበሳውን ድርሻ ማኅበረ ቅዱሳን አይወስድም?

የእናት ጡት ነካሽ ፖለቲከኛ ሁላ ዛሬ ማኅበሩን አፍርሰው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የተኩላ መፈንጫ ለማድረግ ከላይ ታች ማለቱን ተያይዘውታል፤ ቤተክህነቱ ውስጥ በተሰገሰጉ "አማኝ መሳይ" ካድሬዎች በኩል።

በጣም የሚገርመኝ ነገር ቢኖር በቁም ሳሉ ሊያፈርሷት የታተሩ ሁሉ በኋላ ግብአተ መሬታቸው እንደ ሥላሴ ባሉ ታላላቅ ካቴድራልና አድባራት ሲፈጸም "እገሌ ታላቅ ሰው ነበሩ። እትት እትት" ተብሎላቸው ይቀበራሉ። የሚቀብሯትን የምትቀብር ቤተክርስቲያን!

ማኅበረ ቅዱሳንን መቅበር ማሰብ ከብርቱውና ኃያሉ አምላክ ጋር መታገል ነው፤ እግዚአብሔር ወድዶና ፈቅዶ የመሰረተው ማኅበር ነውና።2 comments:

Anonymous said...

igziabher mahibere kidusanin yibark(andrew kemoyale)

ሐይለገብርኤል said...

በዓለም ላይ ብቸኛዋና የምቀብሯትን የምትቀብር ይቺ በ ጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የታነፀቸውና ሐዋርያት የተጋደሉላት ፃድቃን ሰማዕታት ደማቸውን ያፈሰሱላት በእመቤታችን አማላጅነትና በቅዱሳን መላእክት ተራዳይነት ዛሬ እኛ ያለንባት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ናት::

ግን ጃል አይገርምም ????
እግዚአብሔር የቤተክርስቲያን ጠላቶችንና ለምእመኑ ነፍስ የማይራሩትን ያሳፈርልን ያስታግስልን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)