April 5, 2014

“እንዳያዝን፣ የከተማዋን ጥፋት ያይ ዘንድ አልወድለትም"


( አረጋዊ ለደጀሰላም እንደጻፉት መጋቢት 27/2006 ዓ.ም፤ April 5/2014/ PDF)፦ ታላቁ የእግዚአብሔር ነቢይ የማይቀረውን የኢየሩሳሌምን ጥፋትና በከላውዴዎን ንጉስ እጅ፣ ለከለዳውያን ሠራዊትና፣ ለባቢሎን ሕዝብ ተላልፋ መሰጠቷን እግዚአብሔር ራሱ በተረዳ ነገር በገለጠለት ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ልብሱን ቀዶ፣ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ፣ በቤተ መቅደስ ውስጥ ከባሮክ ጋር እያለቀሱ ተቀመጡ፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ እግዚአብሔርንም ሁለት ታላቅ ነገሮች ለመነው። ጉዳዮቹም፦  
፩ኛ. ተሰውረው እግዚአብሔርን ስለሚያገለግሉባቸው ንዋያተ ቅድሳት ዕጣ ፈንታ  እና
፪ኛ. ስለ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ጉዳይ ነበር፡፡
 
ኤርምያስም እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ ጌታዬ ሆይ፤ እለምንሃለሁ፣ ሕዝቡን ብዙ ዘመን ለጠበቃቸው፣ እኔን ባሪያህ ኤርምያስንም ከሃገሩ ሰው ሁሉ ይልቅ ለጠበቀኝ ለኢትዮጵያዊው ለአቤሜሌክ የማደርገውን ግለጥልኝ፡፡ እርሱ ከረግረግ ጒድጓድ አወጣኝ፣ እንዳያዝን የከተማዋን ጥፋት ያይ ዘንድ አልወድለትም” (ተረፈ ባሮክ ፪፥ ፰-፱)።
ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ በነቢዩ በኤርምያስ እንደተመሰከረለት በዚያ ዘመን ከነበረ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም የኢየሩሳሌም ነዋሪ ይልቅ የከተማዋ ለባዕዳን ወረራ ተላልፋ መሰጠት እና ከዚያም ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የጥፋት ዘመን ቢመለከት እጅግ የሚያዝንና በኃዘኑም አብዝቶ የሚጎዳ መሆኑን ነበር፡፡
እንግዲህ ነቢዩ  ኤርምያስ “…. እንዳያዝን የከተማዋን ጥፋት ያይ ዘንድ አልወድለትም” ብሎ እንደማለደለትና የኃያሉ የእግዚአብሔር ቸርነት ተደርጎለት አቤሜሌክ እንደዋዛ ለ66 ዓመታት አንቀላፍቶ የወዳጆቹን የእስራኤላውያንን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሚወዳትን የኢየሩሳሌምን በጠላት መወረርና መጥፋቷን ሳያይ ቀርቷል፡፡
አባቶቻችን እንኳንስ ለታላቋ ውድ ሀገራቸው ለኢትዮጵያ አንድነት እና ነጻነት፣ ለቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናቸው ልዕልና እና ክብር ይቅርና በፍቅርና በሰላም ለተወዳጇቸው ሁሉ ከራስ በላይ የሚታመኑ የልብ ወዳጅ የሚሆኑ እና የወዳጆቻቸውን ጥፋት በቸልታ የማይመለከቱ የእውነትና የደግነት አውራ መሆናቸውን በብዙ የተከበሩና የታመኑ የዓለማችን ታሪካዊ መዛግብት ላይ ሰፍሮ እናገኛለን፡፡ ይልቁንም በታላቁ መጽሐፍ፡፡
እውነት ነው! እነዛ ቅዱሳንና ጽኑዓን አባቶቻችን በዘመናቸው ከተነሱባቸው ሀገር አፍራሽ፣ ሃይማኖት ለዋጭና፣ ታሪክ አቆሻሽ የሀገር ውስጥና የባዕዳን ጠላቶች ጋር ተጋድለው፣ ኊልቆ መሣፍርት የሌለው ውድ ሕይወታቸውንና ንብረታቸውን ሰውተው እነሆ ዛሬ እኛ በታላቅ ክብርና ሞገስ የምንኖርባትን ብቸኛዋን የክርስቲያን ደሴት አውርሰውናል።
እነሆ ዛሬ ሌላ እውነትም አለን፤ 
ዛሬ በእኛ ዘመን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በጠና ታማለች፡፡ አዎ የመናፍቃንና የኢአማንያን የተቀናጀና የተቀነባበረ የጥቃት ዘመቻ ተከፍቶባታል፡፡ የማይተባበሩት ተባብረውባት፣ አንድ የማይሆኑት በአንድነት ዘምተውባት፣ በቤቷ የተሰገሰጉት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ከዘመኑ አብዮታዊ ዲሞክራሲያውያን ጋር አብረው እነሆ ሊያጠፏት ዘምተውባታል፡፡
ታላቋ ሀገራችን ኢትዮጵያም እንዲሁ ተዘምቶባታል፡፡ ለፍቅር ሳይሆን ለጥላቻ፣ ለእርቅ ሳይሆን ለበቀል፣ ወደ አንድነት ሳይሆን ወደ መበታተን የሚወስዳት የእነ ዮዲትና ግራኝ ውላጆች፣ የእነ ሞሶሎኒ ደባና ሴራ ራሱን አዘምኖና አደራጅቶ በማን አለብኝነት ዳግም ህልውናዋ ላይ ተዘምቶባታል፡፡

እነሆ ዛሬ፤
፨ ለእኛ እንደ አቤሜሌክ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን እና የታላቋን ኢትዮጵያ ሀገራችን ከተደቀነባቸው የወል ጥፋት የሚሰውረን እንደ ኤርምያስ ያለ ነቢይ ከወዴት እናገኝ ይሆን? እንደ ጻድቁ አባታችን እንደ አቡነ ጴጥሮስ ተዋሕዶን ለተኩላ፣ ኢትዮጵያን ለባንዳ አሳልፈን እንዳንሰጥ የሚገዝተን ጀግና መሪ ወዴት እናመጣ ይሆን?
፨ ዛሬ እንደ ቀደሙት አባቶቻችን ትናንት የክርስትና መሰረት እና ደሴት ለነበሩት ዛሬ ግን በግፍ የሚረግፉትን የሶርያና የግብጽ ክርስቲያን ወንድሞቻችንን መታደግ ባንችልም፤
፨ በሀገራችን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ በቃጠሎ ሲወድሙ፣ ካህናቱና ምዕመኑ በቀያቸው እንደ በግ ሲታረዱና በግፍ ሲሳደዱ፣ ግድ የሚለው የቤተ ክርስቲያን መሪ እንዲሁም የዜጎቹ መሳደድ የሚያሳስበውና ሀገራዊ ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት እና ተቋም የኖራል በሚልና ለችግሮች ሁሉ ተገቢው መፍትሔ በሚመለከተው አካል ይሰጣል በሚል በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በክርስቲያናዊ ሆደ ሰፊነት ፍትህን በትዕግስት መጠበቃችን፤
፨ ቅዱስ ሲኖዶሱ በመንግሥት ባለሥልጣናት ሲደፈርና ብፁዓን አባቶቻችን በዘመኑ ጋጠወጦች ሲጎሸሙና ሲዋከቡ፣ ይልቁንም ለዘመናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሁለት ሲኖዶስ ስር እንድትቆይ ያደረጋትን ውጫዊ ሴራ ለማክሸፍ አባቶቻችን በተጉ ጊዜ በመንግሥት አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነትና በቤተ ክህነቱ ውስጥ በተሰገሰጉ የፕሮስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች ደባ የዕርቁ ሂደት ሲከሽፍ እያየን እንዳላየን ማለፋችን፤  
፨ ይልቁንም በአለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ቤተ ክርስቲያናችን ከየአቅጣጫው ከተጋረጡባት የመናፍቃን የተቀነባበረ ወረራና ጥቃት፣ ከአክራሪ እስልምና ጅሃዳዊ ዘመቻ፣ በእቅፏ ተሰግስገው ከሚገዘግዟትና  በጎጥ ተደራጅተው ከሚቦጠቡጧት ሙሰኛ ካድሬዎች ዘረፋ ከመታደግ መዘግየታችን፤ ወዘተ ያሳበየው የጥፋት ሃይል፤

በሌላ በኩል፤
፨ ጥንታዊ ገዳማቶቻችን በቀለብ፣ በአልባሳት፣ በውኃ፣ በመብራት፣ በንዋየ ቅድሳት፣ ወዘተ እጥረት እንዳይዘጉና ቅዱሳን አባቶችና እናቶቻችን እንዳይሰደዱ፤ የአብነት ጉባዔያት በመምህራን ደሞዝ፣ በተማሪዎች ቀለብና አልባሳት ማጣት ተማሪዎች እንዳይበተኑና ቤተ ክርስቲያናችን ተተኪ እንዳታጣ፤
፨ ይልቁንም በሀገራችን ከተማሪው አብዮት ጋር ተያይዞ በተከሰተውና ዘመን በወለደው የግራ ዘመም የፖለቲካ አስተሳሰብ ምክንያት ከክርስቲያናዊ ሕይወት በተጻራሪው የሚሄደውንና እንደዋዛ የተፈጠረውን የትውልድ ክፍተት ለመሙላት፣ እንዲሁም ወጣቱን ትውልድ ከተጀመረው የክህደት ቁልቁለት ለመታደግ በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ሌት ከቀን እየባዘነ ያደራጀ፣ ያስተማረና፣ ቤተ ክርስቲያን የወላድ መሐን እንዳትሆን የታደገን ክፍል፤
፨ አንዳንድ አምባገነን የመንግሥት ባለሥልጣናት በተለያዩ መድረኮች ያለ ስሙ ስም፣ ያለ ምግባሩ ምግባር በመስጠት ለመወንጀል ሲሞክሩ በዝምታ መመልከታችን ቤተ ክርስቲያናችንን በሚመሩት አባቶቻችን ጭምር ሲነገር መስማታችን አስደንጋጭ ከመሆኑም ባሻገር መጭውን ጊዜ ከወዲሁ በአንድነትና በጥንቃቄ እንድንመረምርና የመፍትሄ አቅጣጫም እንድናስቀምጥ የግድ የሚል ሆኖ ይሰማኛል፡፡
ስለሆነም ሁላችን የተዋሕዶ ልጆች በአንድነት በማኅበረ ቅዱሳን አባላትና አመራሮች ላይ የተከፈተውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በማውገዝና በመንግሥትና በቤተ ክህነቱ ውስጥ ተሰግስገው በሚገኙ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች አማካኝነት እየተወሰደባቸው ያለውን የማዋከብና የማሸማቀቅ እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም አስፈላጊውን የተቀናጀ እንቅስቃሴ ከወዲሁ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ካልሆነ የአቤሜሌክ የልጅ ልጆች የሀገራችንና የቤተ ክርስቲያናችንን ጥፋት በዓይናችን ከማየት ማን ይታደገን ይሆን?

በመጨረሻም፤
ምን አልባት ለዘመናት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ሰፍኖ የኖረው እና እንደ ታሪካዊ እርግማንና ውርደት የምቆጥረው በአባቶቻችን ላይ የተፈፀመው የመከፋፈልና የማሰደድ ስትራቴጂ በማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ላይም ለመድገም መታሰቡና የማኅበሩንም ቢሮ ለመዝጋት ብሎም በተለጣፊ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች ለመተካት የተጠነሰሰው ሴራና በቅርቡም በኢቴቪ እየተሰራነው የሚባለው “ማኅበረ-ቅዱሳናዊ ሐረካት” ፊልም ለሚያመጣው ውዝፍ መዘዝ ብቸኛው ተጠያቂ አሁን በሥልጣን ላይ የሚገኘው የሀገሪቱ መንግሥትና የመንግሥቱን አመራር በበላይነት የያዘው ኢሕአዴግ ብቻ መሆኑን ከወዲሁ ማስገንዘብም ማሳሰብም ወደድኩ፡፡
  
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መጋቢት ፳፩, ፻፪፲፬

6 comments:

Anonymous said...

Pls PDF

Anonymous said...

PDF

Anonymous said...

Brothers and sisters believe me who ever behind this devilish act will pay the price. We will win; we are the Son and Daughter of Almighty God. We are the winner of the fight by his name. The story of Goliyad and David will be a very good example for this. We may seem small and powerless, but we are capable of winning everybody by his name. Not by arms, not by bad mouthing, but by making our church and Christianity life flourish in each and every day of our life. All of us should bear in mind that, our fathers have been crucified, tortured, and obliged to live in catacomb, we are their son, we will pay every price to be paid for his name by his name and we will be the winner with love

Anonymous said...

Brothers and sisters believe me who ever behind this devilish act will pay the price. We will win; we are the Son and Daughter of Almighty God. We are the winner of the fight by his name. The story of Goliyad and David will be a very good example for this. We may seem small and powerless, but we are capable of winning everybody by his name. Not by arms, not by bad mouthing, but by making our church and Christianity life flourish in each and every day of our life. All of us should bear in mind that, our fathers have been crucified, tortured, and obliged to live in catacomb, we are their son, we will pay every price to be paid for his name by his name and we will be the winner with love

Anonymous said...

ይሄንን ልብን የሚመሰጥና ማንነትን የሚያስታውስ ጽሑፍ ላስነበበን፥ የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር
ዕውቀትን ያብዛለት። ለእኛም ላነበብነውን በልባችን ይጻፍልን። በተግባር ለመፈጸም ያብቃን።
ቸሩ መዳኃኒዓለም ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንና ሀገራችንን ኢትዮዽያን ይጠብቅልን።
አሜን።

Anonymous said...

ጌታ ሆይ የኢየሩሳሌምን ጥፋት አታሳየን ማህበሩንም ጠብቅልን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)