February 26, 2016

አዎ ማኅበረ ቅዱሳንን ተጠንቀቁ ! ትልቁ "ስጋት" እሱ ነውና(አዲሱ ተስፋዬ ለደጀሰላም እንደጻፉት/ READ IN PDF)
መነሻ

ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ሰንደቅ ጋዜጣ በሚያዝያ 1/2006 ዓ.ም እትሙ ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ያወጣው ቃለ መጠይቅና ተታ ነው [i]:: በዜናው ላይ ስማቸው የተጠቀሰው ሦስቱም አስተያየት ሰዎች "ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ነው:: ስለዚህም መንግት ሊያፈርሰው ነው " የሚለው ወቅታዊ ዜና ምንጩ ከየት እንደሆነ ግልጽ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል :: በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የዝብ ግንኙነት ላፊ አቶ አበበ ወርቁ ጉዳዩን "በሬ ወለደ ነው" ብለው ሲያጣጥሉት የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ደግሞ " የዚህ ወሬ ምንጩ ከየት እንደሆነ አናውቅም” ሲሉ ተመሳሳይ ነገር ተናግረዋል።


ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንዴ?

በ 1955 እ. ኤ. አ የተመሰረተውና መቀመጫውን በኔዘርላድና በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው  Open Doors : Serving Persecuted Christians Worldwide [ii] የተሰኘው ግዙፍ ድርጅት 2013 እ. ኤ. ኣ ባወጣው World Watch List ላይ ክርስቲያኖችን በማሰቃየት በ63 ነጥብ ኢትዮጵያ 15ተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝና ለዚህም ስቃይ ዋና ተዋናይ ከሆኑት አካላት መካከል አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ ጽፎ  ሊስቱንም በመላው ዓለም በትኗል [iii]

ው በመላው ዓለም በድረ ገጽና በተለያዩ ኤለክትሮኒክ ሚድያዎች (hard and soft copy) የተበተነው ሪፖርት ከመስክ የመረጃ ሰራተኞቼ ከምሁራንና ከሰላዮቼ አገኘሁ ባለው መረጃ ረት አቶ መለስ ዜናዊን ሞት ቀደማቸው እን ማኅበረ ቅዱሳንን እንክትክቱን ሊያወጡት አቅደው እንደነበረ ቀጣዩም ዜ ማኅበረ ቅዱሳን የሚገበት ዜ እንደሚሆንና ይም ለተሐድሶዎች አስቸጋሪ ጊዜ ስለሚሆን ከማኅበረ ቅዱሳን እንዲጠበቁ እንዲህ በማለት ያትታል
“The death of Prime Minister Meles Zenawi, who sought to crush Mahibere
Kidusan, the fanatical group inside EOC, is considered a big blow for the renewal movements. Zenawi was not a supporter of those movements, but his actions against Mahibere Kidusan for political survival were considered by the EOC renewal movements as helpful for less squeeze. His replacement, Haile Mariam Desalegn, does not possess the political and religious background required to confront the fanatical group. Mahibere Kidusan is currently riding high and…. In addition to this, the death of the EOC leader is a big shock for the renewal movements as he was reluctant to take action against them. “ [iv]

ው ዓለማቀፋዊ “የክርስቲያኖች ንባ ጠባቂ” ነኝ የሚለው ድርጅት ማኅበረ ቅዱሳን በመንግሥት የደንነት መዋቅር ውስጥ ዘልቆ እንደገባና የመንግሥትን ልጣን በመቆጣጠር በተለይ "የተሐድሶን ቡድን " ለማጥፋት መነሳቱን በዚህ መልኩ ሪፖርቱ ላይ ገልጾታል
(MK) normally monitor the churches. The fanatic group inside the EOC (Mahibere Kidusan) has to be mentioned here. Particularly Open Door Field experts report that the group is now a growing threat for non-traditional protestant churches and renewal movements within the EOC. The group ( MK) allegedly has an ambition to influence and control the government policies to restrict the activities of other religions. There are reports that Mahibere Kidusan has managed to infiltrate the government security and administrative apparatus. In the absence of a powerful leader and the death of a relatively moderate patriarch (late leader of EOC) the next move of the group is nervously watched.[v]

እስካሁያዋጣናልማኅበሩን ለመምታት ጥሩ መላ ነው”  ብለው ያሴሩትማኅበሩ ራት ይወስዳልግብር አይከፍልምሕንጻ ገንብቷል ወዘተ” የሚል ነበርማኅበሩ ራት እንደማይወስድ ሳቡንም በተመሰከረላቸው ሳብ ባለሙያዎች ኦዲት በማስደረጉና ከግብርና መሰል ክፍተቶች የጸዳ መሆኑን በማረጋገጡና የውንጀላ ክፍተት በመጥፋቱ ሌላ ዜማ ጀምረዋልአሁን ደሞ ክሱማኅበሩ መንግሥት ንነት መዋቅር ውስጥ ገብቶ ሊያፈርሰን ነው” የሚል ሆኗል እንደማያዋጣ ያወቁት እኩያን አሁን ደሞ የመጨረሻ ጥይታቸው ተቀይሯልማኅበሩ ፖላቲካ ውስጥ ገብቷል እና መንግሥት ወዮልህ አይነት ዝባዝንኬ

እናም  ማኅበረ ቅዱሳንን ተጠንቀቁ !
ው ሪፖርት  ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገተው፣ ቤተ ክርስቲያንን እየገዘገዙ ላሉ ራሳቸውን ተሐድሶ ብለው ለሰየሙ ውስጠ ተኩላ ወገኖቹ ያስተላለፈው ጥሪ አንድ ነው:: "አክራሪው ማኅበረ ቅዱሳንን እየበረታና እየጠነከረ ስለሄደ የሚቀጥሉት መታት ለተሐድሶዎች እጅግ አስቸጋሪ ነውና ... ማኅበረ ቅዱሳንን ነቅታችሁ ጠብቁ::የሚል። ከዚህም ጋት የመነጨ ይመስላል ግብረ አበሮቻቸው ማኅበረ ቅዱሳንን ለማወክ ያለ የሌለ ይላቸውን አስተባብረው መንጫጫት ከጀመሩ የሰነባበቱት።

Now, in his absence and with the government’s reduced leverage, this fanatic group ( Mahibere Kidusan) appears to be taking charge. The coming months may bring difficult times for the renewal movements inside the EOC...the next move of the group is nervously watched.[vi]

ድርጅት መንደርተኞች የፈጠሩት የሰፈር ቁብ አይደለም:: በመላው ዓለም ኔት-ወርክ ያለው መረተ ሰፊ ድርጅት ነው:: የሚያወጣቸውንም ሪፖርቶች ሚሊዮኖች ያነቡታል:: የኢትዮጵያ “ክርስቲያኖችን ዋይታ” በተመለከተ ያወጣው ጽሑፍ ግን ይገርማል:: ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ክርትስያኖች ተገድለዋል:: ተሳደዋል:: አብያተ ክርስቲያናትም ተቃጥለዋል:: ገዳማትም ተደፍረዋል:: ክርስና ለሚገደው አካል እነዚህ ብዙ የሚያስጽፉ ነበሩ:: ይሄ ሪፖርት ግን ያተኮረው ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ነው:: የማኅበሩም ወንጀሎች ብሎ ሊነረን የሚፈልገው አንድ ነገር "ማኅበረ ቅዱሳንን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ዶግማ አፍርሰው ወደ ሌላ እምነት ድርጅት ለመቀየር የተነሱ ተሐድሶዎችን አላስቀምጥ አለ:: ለተሐድሶ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆነብን የሚል ነው:: እንግዲህ የማኅበሩ ወንጀል ይ ነው::

ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተናገሩትንም አስተያየት ጠምዝዞ "ጠቅላይ ሚኒስሩ ሞት ቀደማቸው እንጂ ሊያፈራርሱት ነበር" በማለት እውነቱን ሳይሆን ምኞቱን ተርኮልናል:: የሚገርመው ማኅበረ ቅዱሳንን በማፍደት ጉልህ ሚና አልተጫወቱምና ተተኪው ጠቅላይ ሚኒትር አቶ ኃይለማርያምን "አቅም ያነሳቸው" እስከማለት ደፍሯል:: ፓትርያርክ ጳውሎስንም ተሐድሶ ላይ እጃቸውን ማንሳት የማይፈልጉ ለዘብተኛ" ሲል አሞግሷቸዋል:: እንደዚህ ድርጅት ዘገባ ከሆነ ቤተ ክርስቲያንን ለመሰርሰር ሰርገው የገቡ መናፍቃን ሰማዕታት ሲሆኑ፣ የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም በሚል ለቤተ ክርስቲያን ትውፊትና እምነት መጠበቅ የሚደክመው ማኅበረ ቅዱሳንን ደግሞ አሸባሪ፣ አክራሪ የሚል የስም ጥላሸት እንዲቀባ ተደርጓል:: እንግዲህ የማበረ ቅዱሳን ወንጀሉ ይ ነው::

ማኅበረ ቅዱሳን ወሳኝ ይል ሆኗል

ከቅርብ ያት ወዲህ ማኅበረ ቅዱሳንን በአክራሪነትና በነውጠኛነት የመፈረጁ አባዜ በአካዳሚክ ጽፎች ላይም እየታየ ነው:: ለምሳሌ የዶክተር ጥበበ እሸቴን የዶክትሬት ማሟያ ጽሑፍ ማንሳት ይቻላል:: ዶክተር ጥበበ በ 1960ዎቹ ውስጥ በነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ተሳትፎ የበራቸው እና በኋላ ደግሞ የፕሮቴስታንቱን ዓለም በመቀላቀል በዛው ድርጅት ውስጥ የአስተዳደር ቦታ እስከመያዝ የደረሱ ሰው ናቸው::

እኚህ ሰው 2009 ላይ The Evangelical Movement in Ethiopia: Resistance and Resilience በሚል ርዕስ የጻፉትን የዶክትሬት ሟሟያ ጽፋቸውን አሳትመዋል[vii]:: በዚህ አወዛጋቢ መጽሐፍ ዶክተር ጥበበ ማበረ ቅዱሳንን militant, aggressive, anti evangelical በማለት ጥላሸት በመቀባት አንባቢን የሚያደናግር አንቀጽ አስፍረዋል:: ያይጥ ምስክሯ ድንቢጥ ነው ነገሩ::
The emergence of a highly aggressive and more militant movement that arose within the Orthodox Church under the name of Mahibere Kidusan in recent years should be seen in multidiscrusive context (Mahibere Kidusan) as a nationalistic and strongly anti-evangelical movement enjoying the backing of some Orthodox conservative intellectuals and elements of the urban youth, the new religious strain is becoming a significant force.” [viii]

ዶክተር ጥበበ ለምን ዓላማና በምን መረጃ militant ( ነውጠኛ) anti evangelical (ረ ወንጌል) እሰከማለት እንደደረሱ ባላውቅም እሳቸውም ግን ገና በ2009 ማኅበረ ቅዱሳን significant force ሆልና አስቡበት ሲሉ አስገንዝበው ነበር:: ምንም እንኳን ዶክተር ጥበበ እሸቴ በዚህ ጥናታዊ ጽፋቸው በርካታ አመኔታ የሚጎድላቸው ነጥቦችን ቢያስነብቡንም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቤተ ክርስያኗን ወደ ሌላ እምነት ድርጅት ለመቀየር በስውር የሚሰሩ የተጠናከሩ ህቡዕ ቡድኖች እንዳሉና ተጽኗቸውም በሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ በየማበራቱ፣ በየአጥቢያ አብያተ ክርናት እንዲሁም በየገዳማቱ ሳይቀር መታየት መጀመሩን የውስጥ አዋቂ በሚመስል ሁኔታ እንዲህ በማለት ገልጸውታል::

Today, many underground movements are operating within Ethiopian Orthodox Church, some with evangelical and others with Pentecostal convictions. … Some of these movements exemplify attempts at religious innovation, though it is hard to plot their trajectories because of their hidden nature and complex character. Such developments are affecting wide ranging areas of the established structure of the Orthodox institutions, such as Sunday Schools, the mahibers, the monastic centers, and even the local churches in major cities. [ix]

የፕሮቴስታንቱ ዓለም ፓስተሮችም ከ34,000 የማያንሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋዶ አብያተ ክርያናት ውስጥ ገብተው ቤተ ክርስቲያኗን ወደ ፕሮቴስታንቱ ዓለም ለመገልበጥ አባላትን እየመለመሉና ልጠና እየሰጡ እንደሆነ በጀብዱ መልክ በአደባባይ እየተናገሩ ነው::
The evangelist is hopeful that the seeds of revival are being planted and nurtured in the estimated 34,000 Orthodox churches in Ethiopia and abroad. So far more than 600 people have successfully completed the two-week course.[x]

አልፎ ተርፎም ማኅበረ ቅዱሳን ባይኖር ኖሮ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ቤተ ክርያኗን ሙሉ ለሙሉ ይቆጣጣራት እንደነበር በይፋ እየጻፉ ነው:: ማኅበረ ቅዱሳንም ላይ ጥርሳቸውን የሚያገጫግጩት ለዚህ እኩይ ዓላማቸው እንቅፋት ስለሆነባቸው ነው

ለዚህም ዓላማቸው ስኬት ማኅበረ ቅዱሳንን ሊያፈስርና ሊበትን የሚችል ዘርፈ ብዙ በመራት ላይ ይገኛሉ:: ቤተ ክህነቱ ውስጥ በገንዘብ የገዟቸው ቅጥረኞቻቸው ማኅበሩን ለማፍረስ የቻሉትን ያህል ሄደዋል:: ግን ከኪሳራ ውጭ ማኅበሩ ላይ ምንም ያመጣው ጉዳት አለመኖሩ ያሳሰባቸው አካላት አሁን ደግሞ ቤተ ክህነቱ ውስጥ ሰግስገው ላስገቧቸው ቅጥረኞቻቸውና በገንዘብ ለገዟቸው ይሁዳዎች የመጨረሻ ትንቅንቅ እንዲያደርጉ እንደላኳቸው በየቀኑ የምናየው ሃቅ ምስክር እየሆነ ነው::

ጋዜጠኛ ተመስገን ዘውዴ የማኅበረ ዱሳን የመጨረሻዎቹ ቀናት በሚል ርዕስ በቅርቡ ባስነበበን ግሩም ጽሑፍ ላይም የማኅበሩ ተቃዋሚዎች ቤተ ክህነት ውስጥ አዳራሽ ተፈቅዶላቸው ስብሰባ ማድረጋቸውንና የአቋም መግለጫ እስከማውጣት መድረሳቸውን እንዲህ ሲል ነበር ያስነበበን
ለመጽሔቱ ዝግጅት ክፍል የደረሰው በድምፅ የተቀረፀ የውይይቱ ሙሉ ክፍል እንደሚያስረዳው፣ ተሰብሳቢዎቹ ማኅበሩን በተመለከተ ያወጡት የአቋም መግለጫ÷ የማኅበሩና የዋነኛ መሥራቾችና አባላት የባንክ አካውንት፣ ቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎች ጨምሮ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች፣ /ቤቶች፣ የንግድ ተቋማት፣ የአክስዮን ተቋማት፣ የንዋያተ ቅድሳት ማምረቻዎችና ማከፋፈያዎች፣ ከቀረጥ ነጻ የገቡና በመግባት ላይ ያሉ ዕቃዎች በሚመለከታቸው የመንግሥት መሥ/ቤቶች እንዲታገዱ በቅ/ሲኖዶስ አማካይነት ደብዳቤ እንዲጻፍ፤ ከምእመናን በቀጥታም ኾነ በተዘዋዋሪ የሚቀበለው ዓሥራት እየፈረጠመበት ስለኾነ እንዳይቀበል ይከልከል፤ የግቢ ጉባኤያት(የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) እርሱ በሚቀርፀው ትምህርት እንዳይወሰዱብን በደንብ መሥራት፤ ተጠሪነቱ ከዋና ሥራ አስኪያጅነቱ ሥር ወጥቶ በሰንበት /ቤቶች /መምሪያ ውስጥ አንድ ንኡስ ክፍል ይኹን የሚሉና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡[xi]

በዚህ የአቋም መግለጫ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው የተሰብሳቢዎቹ አንዱና ዋና ቅድ "የግቢ ጉባኤያት (የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) እርሱ በሚቀርፀው ትምህርት እንዳይወሰዱብን በደንብ መሥራት" የሚል ነውማኅበረ ቅዱሳን ለየግቢ ጉባኤያት ቀርጾ ያዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት እና መማሪያ መጻሕፍቱ በሙሉ ይታወቃሉቢጋሮቹም፣ መጻሕፍቱም በሊቃውንቱ ታይተው የተመረመሩና የታረሙ ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ናቸውእርሱ በሚቀርጸው ትምህርት እንዳይወሰዱብን ማለት ትርጉሙ ምንድነው? እንግዲህ እየተካሄደ ያለው ቤተ ክህነት አፍንጫ ብብት ስር ነው

ማኅበረ ቅዱሳን የኔ ነው ! ያንተ ነው!  ያንቺ ነው! የኛ ነው!

ምንም እንኳን ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ ባታውቅም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አሳሳቢ ፈተና ውስጥ ወድቃለችከአውሮፓና አሜሪካ ድረስ ሳይቀር ድርጎ የሚታሰብላቸው ሆድ አምላዎች የቤተ ክርስቲያንን አባቶችን ክብር በማጉደፍየቤተ ክርስቲያንን ትውፊትና ትምህርት በመገዝገዝ፣ ቤተ ክርስቲያንን ወደ መናፍቃኑ ጎራ ለማስረከብ ሌት ተቀን እየሰሩ ይገኛሉበተለይም ራሳቸውን ተሐድሶ በሚል የሰየሙ ቡድኖች ቤተ ክርስቲያኗን ለማፍረስ ቆርጠው ተነተዋልለዚሁ እኩይ ዓላማቸው መሳካት ማኅበረ ቅዱሳን እንቅፋት ስለሆነባቸው ከምሁር እስከ ተርታው አባል ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዘመቻ ከፍተዋልየማኅበሩን ስም ለማጥፋት በርካታ ብሎጎች ሥራ ላይ ውለዋልብዙ ብር ወጥቶባቸው መጻሕፍት ታትመዋልሊናቸውንና ሃይማኖታቸውን በብር በሸጡ ይሁዳ የቤተ ክህነት ሰዎችም ማኅበሩን ለመምታት ዘርፈ ብዙ ሙከራ ተደርጓልአንዱም ማኅበሩን ለማፍረስ አቅም ባይኖረውም አረቦቹ እንደሚተርቱት ውሾቹ ይጮሃሉ ግመሉ ግን ይጓዛል

እኛስ ለሃይማኖታችን የሚገደን ኦርቶክሳውያንስ ምን እያደረግን ነው? ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን እጅ ነው[xii]የቤተ ክርስቲያን አካል ነው ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር የሚደረግ ትግል ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን ለመጣል የሚደረግ ሰይጣናዊ ትግል ነውማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚታወጅ ጦርነት በሙሉ ቤተ ክርያን ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው በረ ቅዱሳንንም ላማ ውስጥ እንዲገባ ያደረገው ዋነኛ ምክንያት፣ ትውልድ ስለ ኦርቶክሳዊ ማንነቱ የላቀ ግንዛቤ እንዲኖረው ማስተማሩና ከቤተ ክርስቲያን ጎን መቆሙ ነው የማኅበረ ቅዱሳን ጥንካሬ የቤተ ክርስቲያን ጥንካሬ ነውማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚቀሰሩ ጦሮች በሙሉ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚቀሰሩ ጦሮች ናቸው ስለዚህ ማኅበሩ ላይ የሚደረጉ ትንኮሳዎች ቤተ ክርስቲያን ላይ ሚደረጉ ትንኮሳዎች ናቸውና እያንዳንዳችን ኦርቶዶክሳውያን ቆመን ማሰብ አለብን

ማኅበረ ቅዱሳን ይፈርሳል እንዴ ?

“ማኅበረ ቅዱሳን ይፈርሳል” ብለው ለሚቃዡ ሰዎችም እውነታውን አውቀውት ከወዲሁ እርማቸውን እንዲያወጡ ትንሽ ልበልዛሬ እኮ የትኛውም ዓለም ብትሄድ የማኅበረ ቅዱሳን ሴል (Cell) የሌለበት ክፍለ ዓለም የለም ኢትዮጵያ ውስጥ እያንዳንዱ ቀበሌ ድረስ "እምቢ ለቤተክርስቲያኔ" የሚሉ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት አሉልህ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ እያንዳንዱ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ድገት ነቅተው የሚሰሩ የማኅበሩ አባላት አሉየማኅበሩ መመርያ እንደሚያዘው እያንዳንዱ የማኅበር አባል የሰንበት ትምህርት ቤት/ የሰበካ ጉባዔ አባል ነው

የትኛውም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ውስጥ ክርስቲያንን ባላቸው አቅም ለማገልገል ቁርጥ አቋም ያላቸው የማኅበሩ አባላት አሉኢትዮጵያ ውስጥ ያለ የትኛውም የመንግሥትም ሆነ የግል ድርጅት ውስጥ የማኅበሩ አባል የሌለበት የለምእያንዳንዱ ሪያ ቤት ያለ ተቀጣሪ የማኅበረ ቅዱሳን ተጽዕኖና አሻራ የሌለበት የለምየማኅበሩ ቋሚ አባል ባይሆን እንኳን የማኅበሩ ግን ደጋፊ ነው ወይም በዘመኑ ቋንቋ ስትፍቀው ማኅበረ ቅዱሳ ነውማኅበረ ቅዱሳን በየቀኑ ለቤተ ክርያን ጉዳይ የሚንገበገብየሚያስብ ትውልድ ፈጥሯል ይህ ትውልድ ማኅበረ ቅዱሳናዊ ነውቢመረንም ቢዋጠንም

ከኢትዮጵያም ውጭ የማኅበሩ ቅርንጫፍ የሌለበት ቦታ የለምበተለይ በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓዛሬ ዛሬ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ የሚደረጉ የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤያት ከሀገር ውስጡ የማይተናነሱ እየሆኑ ነውበዓረቡ ዓለምና እሲ ያለው የማኅበሩ እድገትም ቀላል አይደለምየትኛውም ክፍለ ዓለም ላይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚገደው በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ዝም የማይል የማኅበረ ቅዱሳን ሕዋስ አለባጭሩ ማኅበሩ global ሆኗልወይ ደግሞ ነፋስ ሆኗል አትይዘው አትጨብጠው። ነፋስ የማይነፍስበት ቦታ እንደሌለ ሁሉ ማኅበሩ የሌለበት ቦታ የለም ማን ነበር ማኅበረ ቅዱሳን ሳብ መስመር ( Imaginary line) ሆኗል ያለውማኅበረ ቅዱሳንን ልዝጋው ብሎ የሚያስብ አላዊ እንኳን ቢመጣ አዲስ አበባና በየዞኑ ያለውን ጽፈት ቤት ሊዘጋ ይችል ይሆናል እንጂ ማኅበረ ቅዱሳንን ማጥፋት አይችልም::  ዋናው የማኅበሩ ሥራ የሚሰራው በያንዳንዷ ደብርበየሰበካ ጉባኤውበየሰንበት ትቤቱበየአባላቱ ቤት ስለሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚያመጣው ለውጥ insignificant ነው

ሰሜን አሜሪካ ያለው ማዕከል ብቻውን አዲስ አበባ ያለው ማስተባበርያ የሚሰራውን ሥራ መሥራት አቅም አለውእድሜ ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዛሬ አሜሪካ ሆነህ በያንዳንዱ ቀበሌ በያንዳንዱ አጥቢያ ያለውን አባል ለቤተ ክርስቲያን ሥራ ማስተባበር ከባድ አይደለም። It is a click or one call away ማኅበሩ በአንድ የጸሎት ቋንቋ የሚናገሩበአንድ የእምነት ልብ የሚመሩእንደ አንድ ቃል ተናገሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ የሆኑ ብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኦርቶክሳውያን ስብስብ ነውና እንዲህ በቀላሉ እንደ አንቧይ ካብ አትንደውም ብትሰረስረውም ረቱ ጠንካራ ለት ነውና አታፈርሰውምከሁሉም በላይ የማኅበሩ ጠባቂ እመብርሃን ናትና ገና ይሄ ማኅበር ያድጋልይሰፋል

ማስገንዘቢያ
ይህ ጽሑፍ የኔ የራሴ የግል ምልከታዬ እንጂ ሌላ ማንንም አይወክልም:: አስተያየት ሊሰጡኝ ከወደዱ በዚህ ኢ ሜይል ይላኩልኝ
redawube@gmail.com
                                                                                                                             ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን። 


[i] http://www.sendeknewspaper.com/images/Sendek-Pics/448/448.pdf
[iii] http://www.opendoors.no/vedlegg/1988472/WWL2013-FullReport-en
[v]  ibid

[vi] Ibid
[vii]  Eshete,Tibebe  The Evangelical Movement in Ethiopia : Resistance and Resilience 2009 Bayor University press
[viii]  Ibid ( page 313)
[ix] Ibid ( page 61)
[x] http://www.charismamag.com/blogs/189-j15/features/africa/530-revival-and-persecution-in-ethiopia
[xi] ፋክት፤ ቅጽ ቁጥር ፴፱፤ መጋቢት ፳፻፮ ..

9 comments:

Anonymous said...

እግዚአብሔር ለቤቱ ከልብ የሚተጋውን እሱ ይጠብቅ እንደኔ
እንደኔ ብዙም ባናወራ እንደትለመደው እግዚአብሔር በውስጥ የሚያውቀውን መልካሙን ሥራ በውስጥ እንድናደርግ ቢሆን ለዚህም አምላከ ቅዱሳን ይርዳን አሜን...

Anonymous said...

እግዚአብሔር ለቤቱ ከልብ የሚተጋውን እሱ ይጠብቅ እንደኔ
እንደኔ ብዙም ባናወራ እንደትለመደው እግዚአብሔር በውስጥ የሚያውቀውን መልካሙን ሥራ በውስጥ እንድናደርግ ቢሆን ለዚህም አምላከ ቅዱሳን ይርዳን አሜን...

Anonymous said...

እግዚአብሔር ለቤቱ ከልብ የሚተጋውን እሱ ይጠብቅ እንደኔ
እንደኔ ብዙም ባናወራ እንደትለመደው እግዚአብሔር በውስጥ የሚያውቀውን መልካሙን ሥራ በውስጥ እንድናደርግ ቢሆን ለዚህም አምላከ ቅዱሳን ይርዳን አሜን...

Anonymous said...

What is your intention? Are you in MK side or not? I think you are against, that is marvelous and smart to fight MK.

Anonymous said...

ጌታው አትጠራጠር፡፡አሁን አንተ እንደምትለው ሌሎች የቤ/ክህነት መዋቅሮችን ደፍጥጠው ለቤ/ክ ያላት ማኅበረቅዱሳን ብቻ እንደሆነ የሚያስቡት አመራሮችም ጭምር ከሆኑ መንግሥትን እንዳትጠብቅ ራሳችን ኦርቶዶክሳውያን የቤ/ክ ልጆች አክራሪነታችሁን በአደባባይ አውጀን እንታገላችኋለን፡፡ሲጀመር ማኅበሩ አጋዥ እንጅ ምትክ አልባ የቤ/ክ መሰረት አይደለም፡፡አስተውል!! ከማኅበሩም በፊት በተጋድሎ የኖረች ቤ/ክ ያለማኅበሩ አትኖርም ብሎ ማሰብ እውት ሳይሆን ዝቅጠት ነው፡፡እሱን ለዐባላቶቻችሁ ንገሩ፡፡ ግራኝን ስለገደልን ካቶሊክ ሁኑ እንዳሉን የካቶሊክ ሚሲዮናውያን ተሃድሶን በመዋጋት ስም መላውን የቤ/ክህነት መዋቅር እያጥላሉ በሰንበት በተወሰደ የግቢ ጉባኤ ኮርስ ለሚመጻደቁ አማተሮች ቤ/ክንን አሳልፎ ለመስጠት ጊዜው አልደረሰም፡፡ሌሎች እንደፈለጉ ሊያስቧችሁ ይችላሉ፡፡ በቤ/ክህነት ዙሪያ ሆነን ከእናንተ በብዙ መንገድ በተሻለ መልኩ በየዐውደምህረቱ ወንጌልን እየሰበክን ከመናፍቃን ጋር የምንጋደል የቤ/ክ ልጆች መገናኛ ብዙኃን ስለሌለን ብቻ አስተዋጽኦአችን ተደምስሶ ቤ/ክ ያለማኅበር ህላዊ የላትም ለማሰኘት ከሆላንድ እስከ አውስትራሊያ ምንጭ ብትጠቅስ አንሰማህም፡፡
እውነቱን ልንገርህ፡፡በበኩሌ አሁን በየማኅበራዊ ሚዲያውና በየጋዜጣው የማየው የማኅበረቅዱሳን አባላት ሃይማኖትን በማኅበር የቀየረ አስተሳሰብ በቤ/ክህነቱ ገዥ አስተሳሰብ ሆኖ ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ፡፡መመጻደቅ ግዘፍ ነስቶ በሰው አምሳል ሲሄድ እያየነው እኮ ነው፡፡ያውም የሊቃውንት ጉባኤ ባሏት ቤ/ክ የሺኖዳን መጻህፍት ዳውንሎድ እያደረገ ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ እንዳሉት እያለ የሀገሩን ቤ/ክ አስተምህሮዎች ማቀጨጩን በወጉ ሳይረዳ ዘሎ ቤ/ክህነትን በማነወር ራሱን ሊቅ የሚያሥመስል ጥራዝ ነጠቅ ትውልድ!!ይሄ ትውልድ አልፈላም፡፡አልሰከነም፡፡በህግ ስር ማደርን አልለመደም፡፡ስለሆነም ገና ይፈተናል፡፡በራሱ ጦስ ይፈተናል፡፡ችግሩ ፈተናው ለቤ/ክ የሚተርፍ እየሆነ ነው፡፡እሱ እንዳይሆን ቦታውን ለማስያዝ እየተደረገ ያለው ተጋድሎ ይቀጥላል፡፡ራሳችሁን አታሞኙ፡፡የእናንተን አጉዋጉል ዘመናዊ ት/ት የተጫነው መመጻደቅ ለመቃወም ተሃድሶ መሆን አያስፈልገንም፡፡ተሃድሶን እናንተ ከምትታገሉት በላይ እንታገለዋለን፡፡በዛው ልክ እናንተም ከህግ በታች እንድታድሩ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንታገላለን፡፡ከህግ በታች ባለማደራችሁ ከቤ/ክህነቱ የሚደርስባችሁን ተግሳጽ ሁሉ ከተሃድሶ ጋር እያያዙ አጉል ቲፎዞ የማበራከት አካሄድ ካዋጣችሁ ቀጥሉበት፡፡እኛ ግን ነቅተናል፡፡የውጭውም የሀገርቤቱም የቤ/ክህነት ማኅበረሰብ ተረድቷችኋል፡፡ተሃድሶንም አምርረን እንታገላለን የማኅበረቅዱሳንን አምባገነናዊ አካሄድም እንቃወማለን!!

Anonymous said...

ጌታው አትጠራጠር፡፡አሁን አንተ እንደምትለው ሌሎች የቤ/ክህነት መዋቅሮችን ደፍጥጠው ለቤ/ክ ያላት ማኅበረቅዱሳን ብቻ እንደሆነ የሚያስቡት አመራሮችም ጭምር ከሆኑ መንግሥትን እንዳትጠብቅ ራሳችን ኦርቶዶክሳውያን የቤ/ክ ልጆች አክራሪነታችሁን በአደባባይ አውጀን እንታገላችኋለን፡፡ሲጀመር ማኅበሩ አጋዥ እንጅ ምትክ አልባ የቤ/ክ መሰረት አይደለም፡፡አስተውል!! ከማኅበሩም በፊት በተጋድሎ የኖረች ቤ/ክ ያለማኅበሩ አትኖርም ብሎ ማሰብ እውት ሳይሆን ዝቅጠት ነው፡፡እሱን ለዐባላቶቻችሁ ንገሩ፡፡ ግራኝን ስለገደልን ካቶሊክ ሁኑ እንዳሉን የካቶሊክ ሚሲዮናውያን ተሃድሶን በመዋጋት ስም መላውን የቤ/ክህነት መዋቅር እያጥላሉ በሰንበት በተወሰደ የግቢ ጉባኤ ኮርስ ለሚመጻደቁ አማተሮች ቤ/ክንን አሳልፎ ለመስጠት ጊዜው አልደረሰም፡፡ሌሎች እንደፈለጉ ሊያስቧችሁ ይችላሉ፡፡ በቤ/ክህነት ዙሪያ ሆነን ከእናንተ በብዙ መንገድ በተሻለ መልኩ በየዐውደምህረቱ ወንጌልን እየሰበክን ከመናፍቃን ጋር የምንጋደል የቤ/ክ ልጆች መገናኛ ብዙኃን ስለሌለን ብቻ አስተዋጽኦአችን ተደምስሶ ቤ/ክ ያለማኅበር ህላዊ የላትም ለማሰኘት ከሆላንድ እስከ አውስትራሊያ ምንጭ ብትጠቅስ አንሰማህም፡፡
እውነቱን ልንገርህ፡፡በበኩሌ አሁን በየማኅበራዊ ሚዲያውና በየጋዜጣው የማየው የማኅበረቅዱሳን አባላት ሃይማኖትን በማኅበር የቀየረ አስተሳሰብ በቤ/ክህነቱ ገዥ አስተሳሰብ ሆኖ ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ፡፡መመጻደቅ ግዘፍ ነስቶ በሰው አምሳል ሲሄድ እያየነው እኮ ነው፡፡ያውም የሊቃውንት ጉባኤ ባሏት ቤ/ክ የሺኖዳን መጻህፍት ዳውንሎድ እያደረገ ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ እንዳሉት እያለ የሀገሩን ቤ/ክ አስተምህሮዎች ማቀጨጩን በወጉ ሳይረዳ ዘሎ ቤ/ክህነትን በማነወር ራሱን ሊቅ የሚያሥመስል ጥራዝ ነጠቅ ትውልድ!!ይሄ ትውልድ አልፈላም፡፡አልሰከነም፡፡በህግ ስር ማደርን አልለመደም፡፡ስለሆነም ገና ይፈተናል፡፡በራሱ ጦስ ይፈተናል፡፡ችግሩ ፈተናው ለቤ/ክ የሚተርፍ እየሆነ ነው፡፡እሱ እንዳይሆን ቦታውን ለማስያዝ እየተደረገ ያለው ተጋድሎ ይቀጥላል፡፡ራሳችሁን አታሞኙ፡፡የእናንተን አጉዋጉል ዘመናዊ ት/ት የተጫነው መመጻደቅ ለመቃወም ተሃድሶ መሆን አያስፈልገንም፡፡ተሃድሶን እናንተ ከምትታገሉት በላይ እንታገለዋለን፡፡በዛው ልክ እናንተም ከህግ በታች እንድታድሩ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንታገላለን፡፡ከህግ በታች ባለማደራችሁ ከቤ/ክህነቱ የሚደርስባችሁን ተግሳጽ ሁሉ ከተሃድሶ ጋር እያያዙ አጉል ቲፎዞ የማበራከት አካሄድ ካዋጣችሁ ቀጥሉበት፡፡እኛ ግን ነቅተናል፡፡የውጭውም የሀገርቤቱም የቤ/ክህነት ማኅበረሰብ ተረድቷችኋል፡፡ተሃድሶንም አምርረን እንታገላለን የማኅበረቅዱሳንን አምባገነናዊ አካሄድም እንቃወማለን!!

Anonymous said...

chere were yasemah berta wendemie amlkak bderebu yabertah tewachew menafik byimeta egna lhaymanotachen mawek aneterem neber ahunem yzih tose EGZIHABHAIR EGNAN BTEBEBU LIBERTAN FELIGO NEW ENA AYZOACHEHU eneberta ktach bdenb yesera elalehu chere were amitalen

Anonymous said...

ይህን ጽሁፍ እኔ እንዳነበብኩት ከሆነ በጣም ጥሩ መረጃ ነው ወደፊትም እንደዚህ አይነት መረጃዎችን ማድረስህን ቀጥል በርታ እግዚአብሄር አምላክ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡ ይህ ነው ዕውነቱ………..

Unknown said...

አንድ ሁሌ የምንጠቅሳት ጥቅስ አለች ለስንፍና የምትመች " ዲያብሎስ ቀስቱን ጨረሰ ቤተክርስቲያንን አልጎዳትም " የምትል ወገኖቼ እንንቃ የማህበረ ቅዱሳን ጠላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጠላት ነውና ።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)