April 2, 2014

“ለነሱ (ለማ/ቅዱሳን) የተሰጠው ስም ለእኔም ይገባኛል”ለነሱ (ለማ/ቅዱሳን) የተሰጠው ስም ለእኔም ይገባኛል
(ክቡር አቶ ግርማ ሰይፉ፤ የፓርላማ አባል)
ክቡር ሆይ
አኔ የአንድ እምነት አንድ ሀገር አራማጅ ነኝ መንግ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዘመቻ ጀመረ በሚል እሰጥ አገባ እንደበዛ አውቃለሁ፡፡ በሌለኝ መረጃ የእኔን ስም እየጠቀሱ ሰዎች ፖስት እንደሚያደርጉ ከሰዎች ብሰማም የእኔ ፌስ ቡክ ይህን አልገለፀልኝም፡፡ ለማኛውም መንግሥት በእምነት ላይ ዘመቻ ሲጀምር በኦርቶዶክስ ላይ በማኅበረ ቅዱሳን መስመር እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒሰትር አቶ መለስ ይህን አሰመልክተው ለሰጡት አሰተያየት የሰጠሁትን ምላሽ በድጋሚ ላጋራችሁ፡፡ ይህ ነው የእኔ አቋም፡፡ ይህ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ከገጠመ እሰየው ነው፡፡ ለነሱ የተሰጠው ስም ለእኔም ይገባኛል፡፡ የሰጠሁት ምላሽ እንደወረደ ይህን ይመስል ነበር፡፡


ብዙ ጉዳዮች እንደተርጓሚው እንደሚሆን መገመት ይቻላል ነገር ግን አንድ እምነት አንድ ሀገር ማለት ግን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንተረጎሙት ሳይሆን፤ አንድ ሰው ሊኖረው የሚገባው አንድ ምነት ብቻ ነው (ሰኞ፤ ዕሮብና አርብ ሙስሊም ማክሰኞ፤ ሀሙስና ቅዳ ክርስቲያን፤ ወዘተ መሆን አይቻልም) ይህ ደግሞ አምላካዊ ቃል ነው (እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝ ሲል) ይህ አምላካዊ ቃል ደግም የሚሰራው ለሚያምኑበት ነው፡፡ ቃልቻ ቤት እየሄዳችሁ ቤተ ክርስቲያን አትምጡ ማለት ነው፡፡ ሊኖረን የሚገባው አንድ እምነት ነው፡፡ በእርግጠኝነት ሙስሊም ሆኖም ክርስቲያን መሆን አይቻልም ለዚህ ይህ ለአንድ እምነት የመገዛት ፍልስፍና የሁ የእምነት ዘርፎች መለያ ነው፡፡ ጥንቆላ ብቻ ነው ይህንን የሚፈቅደው ይህ ደግም በሁሉም እምነቶች የተወገዘ የመጥፎ መንፈስ ነው፡፡ ለዚህ እኔ ያለኝ አንድ እምነት ብቻ ነው፡፡ መፍክሬም ነው፡፡

ከአንድ እምነት ጋር ተያይዛ የመጣችው የአንድ ሀገር ጉዳይ ነው፡፡ ይህ በእርግጥ አከራካሪ ነው፡፡ አንድ አንድ ሀገሮች ጥምር ዜግነትን የሚፈቅዱ አሉ ይህም ሆኖ እኔ በግሌ ኢትዮጵያ ከምትባል ሀገር በሰተቀር ሌላ ሀገር የለኝም- እንዲኖረኝም አልፈልግም ይህን አቋሜን ገልፅ ግን እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስል ሌሎች ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም አለ ተብሎ ልከሰስ አይገባም፡፡ አንድ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊ ሊሆን እንደሚችል ብዥታ ኖሮብኝ አያውቅም ወይም የሌላ ክርስትና እምነት ተከታዮች ኢትዮጵያዊ ንደሆኑ አልጠራጠርም፡፡ -አማኒያንም ቢሆኑ፡፡

አንድ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለችኝ ብዬ ነው ለዚህች ሀገር እድገት (ሁሉ አቀፍ እድገት ማለቴ ነው) የሚከፈል መሰዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ የሆኑኩት፡፡ ሌላ አማራጭ የለኝም - አማራጭ ያለው ግን ካልተመቸው ወደዛኛ ሊሄድ ይችላል፡፡ ሁለት ጉርጓድ ያላት አይጥ እንደሚባለው፡፡ እኔ ግን ሀገሬ አንድ እና አንድ ነች፡፡ ኢትዮጵያ፡፡ ይህ ማለት ግን በምንም መመዘኛ ይህች ሀገር የኔ ብቻ ነች ማለት አይቻልም፡፡ አይሆንምም፡፡ እኔ የአንድ እምነት እና አንድ ሀገር ባለቤት ነኝ፡፡ምንጭ፦ የፌስቡክ ገጻቸው።
 

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)