- ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት በመቃብር፤
- ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት የሞላው እንዴት ነው?፤
- እንዴት ተነሣ?
- ለምን በአዲስ መቃብር ተቀበረ?
- እንዴት በዝግ መቃብር ተነሣ?
- መቃብሩን ማን ከፈተው?
(መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ
ሺፈራው/ PDF):- ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ÷ ይኸውም በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረትን ሊያስቀርልን ነው፡፡ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረደ÷ ይኸውም በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ይሰብክላቸው ዘንድ ነው፡፡ መለኮት፥ በተዋሕዶ፥ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ ለዚህ ነው፥ መቃብር ሥጋን ሊያስቀረው ያልቻለው፤ ሲኦልም ነፍስን ማስቀረት አልተቻለውም፡፡