March 26, 2014

ብፁዕ አቡነ ቶማስ ዐረፉ

abuna tomas 2
ማስተካከያ፦ ከዚህ ቀጥሎ በተለጠፈው የማ/ቅዱሳን ድረ ገጽ ዜና ብፁዕ አቡነ ቶማስ የተሾሙት በ1972 ዓ.ም ነው የሚለው ግንቦት 1979 ዓ.ም በሚለው እንዲስተካከል በትህትና እያስገነዘብን ዜናው የደጀ ሰላም ባለመሆኑ እንዳለ መተዉን መምረጣችንን እናስታውቃለን። አስተያት ለሰጣችሁን ደጀ ሰላማውያን በተለይም ለመልአከ ሳሌም አባ ገ/ኪዳን ሺፈራው (በፌስቡክ እርማቱን ስለሰጡን) ልባዊ ምሥጋናችንን እናቀርባለን።
 
(MKWebsite):- የምእራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ቶማስ ዐረፉ:: የቀድሞ ስማቸው አባ መዘምር ተገኝ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ጥር 14 ቀን 1932 ዓ.ም ጎጃም ደጋ ዳሞት ዝቋላ አርባዕቱ እንስሳ ተወለዱ፡፡

መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን በሚገባ ከተማሩ በኋላ ጸዋትወ ዜማን ከመሪጌታ አንዱዓለምና መሪጌታ ካሣ ይልማ ፣ ቅኔ ከመሪጌታ ፈንቴ /ዋሸራ/፣ መጻሕፍተ ሐዲሳትን ከመሪጌታ ብርሃኑ ወልደ ሥላሴ ፣ መጻሕፍተ ሊቃውንትን ከመሪጌታ ቢረሳ ደስታ ተምረዋል፡፡ በዘመናዊ ትምህርትም እስከ 6ኛ ክፍል ፣ የእንግሊዝኛን ቋንቋ በግላቸው የተማሩና የመኪና ጽሕፈት /type writing/ የሚያውቁ ነበሩ፡፡ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ዲቁና ከአቡነ ማርቆስ፣ ቅስና ከአቡነ ባልዮስ፣ ቁምስና ከብፁዕ አቡነ ተክለሃይማኖት ተቀብለዋል፡፡
በደብረ ሊባኖስ ገዳም መጻሕፍተ ሊቃውንትን ረዘም ላለ ጊዜ አስተምረዋል፡፡ በገዳሙ የሠራተኞች ቅርንጫፍ ማኅበር ሲቋቋምም የመጀመሪያው ሊቀ መንበር በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ተዛውረው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በአስተዳዳሪነትና መጻሕፍተ ሓዲሳትንና ሊቃውንትን በማስተማር የሚጠበቅባቸውን ተልእኮ ተወጥተዋል፡፡ ጥር 14 ቀን 1972 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አንብሮተ ዕድ ተሹመው ሰፊ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመመለስ የታእካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና መንበረ መንግሥት ግቢ ገብርኤል ገዳም የበላይ ጠባቂ ሆነው አገልግለዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የምእራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተው፤ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መጋቢት 16 ቀን 2006 ዓ.ም መንበረ ጵጵስናቸው በሚገኝበት በፍኖተ ሠላም ከተማ ዐርፈዋል፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም በዚያው በፍኖተ ሰላም እንደሚፈጸም ይጠበቃል፡፡

4 comments:

Anonymous said...

ማስተካከያ: ብጹእ አባታችን ነፍሳቸውን በገነት ከቅዱሣን ጋር ያሳርፍልን እና በ 1972 ዓም አይደለም የተሾሙት በ1972 ዓም ወደ ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ነው የተመደቡት እናም እስከ 1977 ድረስ አገልግለዋል በማስከተልም ወደ ደብረ ሣህል የካ ሚካኢል በአስተዳዳሪነት ተዘዋውረው አገልግለዋል ደብረ ነጎድጓድ በነበሩበት ወቅትም በወቅቱ እድለኛ ሆኜ ከእግራቸው ስር ሆኜ ቅዳሴ ቀጽዬአለሁና ወደ የካም ሲዘዋወሩ አብሬ በሽኝቱ ተሳታፊም በቅዳሴ ተካፍዬ ነበረ እና ነው አመሰግናለሁ ከመንፈስ ልጃቸው

desalegn said...

Unknown said...

Pipisina yeteqebelut be 1979 a.m. new

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)