March 29, 2014

“አይቴ ሀለዉ ቀደምት ጳጳሳት”?(ደጀ ሰላም፣ መጋቢት 20/2006 ዓ.ም፤ ማርች 29/2014/ PDF)፦ ሥርዓተ ቅዳሴውን ለመምራት  ተሰይመው ለተመለከታቸው ከረጅሙ ነጭ ጽህማቸው  ጋር ውብ  የሆነውን  መረዋ  ድምጽ ሲሰማ ምድራዊ  ሳይሆን  ከሰማይ የተገለጠ መልአክ ይመስሉ ነበር፡፡ ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተለየ ፍቅር ስለነበራቸው በተጋበዙበት መድረክ ሁሉ አክብረው በሰዓቱ ይገኛሉ፡፡ ለማስተማር ከተነሱም በትርጋሜ  የተዋዛ  ምስር አዘል ትምህርታቸውን ለምእመናን ቀምመው ያቀርባሉ፡፡ ለሃይማኖት ያላቸውን ቀናዊነት ለመረዳት በትምህርታቸው መግቢያ  የሚናገሩትን  መልእክት መስማት ብቻ በቂ ነው፡፡ ይህ የመግቢያ መልእክታቸው ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ልተበረዘች ያልተከለሰች  መሆን የሚስረዱበት በተለያዩ ዘመናት የተነሱባትን መናፍቃን በመጥቀስ እነዚህ ሁሉ ያልበረዛት ያልከለሳት መሆናን የሚገልጹበት ነው፡፡ እናም በጥዑም አንደበታቸው ስለቤተ ክርስቲያን ሲናገሩ ለሰማቸው  የሊቃውንቱ ዘመን የእነ እትናቴዎስ ዘመን የሃይማኖት ቅናት በውስጣቸው እንዳለ ይረዳል፡፡ ብፁዕ አቡነ ቶማስ፡፡

March 28, 2014

ብፁዕ አቡነ ቶማስ የሃይማኖት ገበሬ አርፈዋል? ተተኪው ቶማስ ከየት ይገኛል?(ደጀ ሰላም፣ መጋቢት 19/2006 ዓ.ም፤ ማርች 28/2014/ PDF)፦ በዚህ የዘመነ ብላ ተባላ፣ ጸረ ሊቃውንት እና መፍቀሬ ተሐድሶ ዘመን በቤተ ክህነት ከቁንጮው እስከ ግርጌው ባሉ በልቶ አደሮች ሲገፉ ከኖሩት አባቶች መካከል አንዱ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ነበሩ። አፈር ይቅለላቸው። ዕረፍታቸው እጅግ ቢያሳዝነንም ማንም ከዚያ ስለማይቀር የምንጸጸትበት አይደለም። እንዲህ የተማሩ ሊቃውንት እንደ ተርታ ሰው ወደጎን ተገፍተው ዳዊት ባልደገመ አፋቸው ነገረ ቤተ ክርስቲያንን የሚዘነጥሉ፣ ንብረቷን የሚዘርፉ፣ አሰረ ክህነታቸውን ያልጠበቁ ሰዎች የሚፏንኑበት እንዲሁም በፖለቲካ ቀረቤታቸው የቤተ ክርስቲያን ሳይሆኑ መቅደሷን የሚረመርሙ ሰዎች የሰለጠኑበት ዘመን መሆኑ ግን ያሳዝነናል። ሐዘን ብቻ ባይበቃም።

March 26, 2014

ብፁዕ አቡነ ቶማስ ዐረፉ

abuna tomas 2
ማስተካከያ፦ ከዚህ ቀጥሎ በተለጠፈው የማ/ቅዱሳን ድረ ገጽ ዜና ብፁዕ አቡነ ቶማስ የተሾሙት በ1972 ዓ.ም ነው የሚለው ግንቦት 1979 ዓ.ም በሚለው እንዲስተካከል በትህትና እያስገነዘብን ዜናው የደጀ ሰላም ባለመሆኑ እንዳለ መተዉን መምረጣችንን እናስታውቃለን። አስተያት ለሰጣችሁን ደጀ ሰላማውያን በተለይም ለመልአከ ሳሌም አባ ገ/ኪዳን ሺፈራው (በፌስቡክ እርማቱን ስለሰጡን) ልባዊ ምሥጋናችንን እናቀርባለን።
 
(MKWebsite):- የምእራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ቶማስ ዐረፉ:: የቀድሞ ስማቸው አባ መዘምር ተገኝ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ጥር 14 ቀን 1932 ዓ.ም ጎጃም ደጋ ዳሞት ዝቋላ አርባዕቱ እንስሳ ተወለዱ፡፡

March 25, 2014

ከ5ኛው ፓትርያርክ ግድፈቶች መካከል አሁንም እንዳይደገሙ መታሰብ ያለባቸው ነጥቦች

ታሪክ ራሱን ይደግማል። እነሆ ዛሬም በድጋሚ አነሣነው።
 (ደጀ ሰላም፤ የካቲት 26/2005 ዓ.ም፤ ማርች 5/2013/ PDF)ይህ ጽሑፍ “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ወእጬጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱምና የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ለሰላም የክብር ፕሬዚደንት፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሟቸው ዐበይት ችግሮች፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና ዋና አንገብጋቢ ችግሮች እና መፍትሔዎች፦ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ” (ግንቦት 2001 ዓ.ም፤ ከገጽ 3-9) በሚል ርዕስ ከዚህ በፊት (August 5/2009) ያቀረብነውን ለተሾሙት አዲስ ፓትርያርክ ተሞክሮ ይሆኑ ዘንድ ያቀናበርነው ነው። 

ቤተ ክህነቱን ከሙሰኞችና ከጎሰኞች የማጥራት ዘመቻው ይሳካ ይሆን?!(ደጀ ሰላም፣ መጋቢት 14/2006 ዓ.ም፤ ማርች 24/2014/ PDF በፍቅር ለይኩን):- ባለፈው ሳምንት ‹‹የፓትርያርኩ የለውጥ ተስፋዎች ወዴት ገቡ?›› በሚል አቶ መብራቱ መርሳ የተባሉ ግለሰብ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ፓትርያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ በቤተ ክህነቱ ተቋም የተንሰራፋውን ሙሰኝነትንና ጎጠኝነትን በተመለከተ የተማፅኖ ጦማራቸውን በሪፖርተር ጋዜጣ በኩል ለቅዱስ ፓትርያርኩ ይደርስ ዘንድ አቅርበው ነበር፡፡ እኚህ ግለሰብም ባቀረቡት የተማፅኖ ደብዳቤያቸው ዋና አሳብም፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ የነገሠውን አድር ባይነት፣ ዘረኝነት/ጎጠኝነትና ሙስና ለማጥፋት በአደባባይ ቃል የገቡበትን ዘመቻቸውን አጠንክረው እንዲቀጥሉበትና ፍሬውን በተግባር እንዲያሳዩ የሚጠይቅ ነው፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)