(በፀሐፊው ፈቃድ ከፌስቡክ ተወስዶ የተለጠፈ)፦ ዛሬ ግንቦት 27 የ30ኛው የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፡፡ እንደሌሎቹ የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርኮች ሁሉ ይህንን አባትም የትሩፋቱንና የዕውቀቱን ዜና በሰሙ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ያለፍቃዱ ይዘውት ሊቀ ጵጵስና ሾሙት፡፡ የዕለቱ ስንክሳር “ወደረሰ ድርሳናተ ብዙኃተ ወአቀመ እግዚአብሔር በመዋዕሊሁ ቀርነ ቤተ ክርስቲያን” እንዲል በዘመነ ፕትርክናውም ብዙ ድርሳናትን የደረሰና የቤተ ክርስቲያንን ስልጣን ያጸና አባት ነው፡፡
June 4, 2014
May 31, 2014
"የሲኖዶስ ጉባኤ በፓትርያርኩና ጳጳሳቱ ፍጥጫ ተቋጨ"
ማውጫ፦
From Contributors
Posted by
DejeS ZeTewahedo
·
ጳጳሳት የፓትርያርኩን የማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ማሻሻያ ቅድመ ኹኔታ አልተቀበሉትም::
·
‹‹ቅድመ ኹኔታው የማኅበሩን አገልግሎት የሚያቀጭጭና በሒደትም የሚያስቆም ነው›› /ታዛቢዎች/
(አዲስ አድማስ ጋዜጣ):- የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅን እንደ አንድ አጀንዳ የያዘው የዘንድሮው የሲኖዶሱ የርክበ ካህናት ጉባኤ ከረቂቁ ጋር በተያያዘ በፓትርያርኩና በሊቃነ ጳጳሳቱ መካከል በተፈጠረ ፍጥጫ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ የፍጥጫው መንሥኤ፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተሠየመው የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ አጥኚ ኮሚቴ ያዘጋጀው የማሻሻያ ረቂቅ በዝርዝር ከመታየቱ አስቀድሞ ፓትርያርኩ ለውይይቱ እንደ ቅድመ ኹኔታ ያቀረቧቸው ነጥቦች በአብዛኛው የጉባኤው አባላት የገጠመው ተቃውሞ እንደኾነ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡May 5, 2014
ሚ ላዕሌነ፤ ምን ገዶን?
ማውጫ፦
ምልከታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(መሪጌታ ዘድንግል ለደጀ-ሰላም እንደጻፉት/ PDF)
ቅዱስ ያዕቆብ
ዘሥሩግ “አሜሃ ይከውን ኃዘን ዘኢይበቊዕ ኃዘን = ያን ጊዜ ኃዘን ይሆናል ግን የማይጠቅም ኃዘን ነው” እንዳለ የማይጠቅም ኃዘን
የሚያዝኑ ብዙዎች ናቸው። ከነዚያው ዘንድ ቅሉ ይሁዳ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው። ይሁዳ በፈጸመው እኩይ ግብር ኃዘን በተሰማው ጊዜ
የሄደው ወደ ካህናቱ አለቆችና ወደ ሕዝቡ ሽማግሎች ነበር። በደሉንም መናዘዝ የጀመረው በደልን ፀነሰው፣ ወልደውና አሳድገው ለመዓርገ
ሞተ ነፍስ ላደረሱና ላበቁ ፈሪሳውያን ነበር። በማቴዎስ 23፥15
“አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፣ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት
ወዮላችሁ” ተብሎ እንደተጻፈ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ይሁዳን በክፉ ግብራቸው አጥምቀው የነሱ ፈጻሜ ፈቃድ/ፈቃድ ፈጻሚ ለማድረግ ብዙ
ደክመዋል። ጨርሶ የድኅነት በር እንዳይከፈትለት አድርገው ለገሃነም ዳርገውታል። “ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም”
እንዳለ ወንጌለ ዮሐንስ። (ዮሐ 16፥12)
April 19, 2014
ትንሣኤ ዘክርስቶስ - የክርስቶስ ትንሳኤ
ማውጫ፦
From Contributors
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት በመቃብር፤
- ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት የሞላው እንዴት ነው?፤
- እንዴት ተነሣ?
- ለምን በአዲስ መቃብር ተቀበረ?
- እንዴት በዝግ መቃብር ተነሣ?
- መቃብሩን ማን ከፈተው?
(መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ
ሺፈራው/ PDF):- ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ÷ ይኸውም በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረትን ሊያስቀርልን ነው፡፡ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረደ÷ ይኸውም በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ይሰብክላቸው ዘንድ ነው፡፡ መለኮት፥ በተዋሕዶ፥ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ ለዚህ ነው፥ መቃብር ሥጋን ሊያስቀረው ያልቻለው፤ ሲኦልም ነፍስን ማስቀረት አልተቻለውም፡፡
April 18, 2014
“የራስ ቅል የሚሉት ሥፍራ” (በአለቃ አያሌው ታምሩ)
ማውጫ፦
DS Videos
Posted by
DejeS ZeTewahedo
ሌሎች ጽሑፎቻቸውን፣ ቃለ ምልልሶቻቸውን እና ትምህርቶቻቸውን ለማግኘት በስማቸው የተሰየመውን ድረ ገጽ (http://www.aleqayalewtamiru.org/) ይጎብኙ።
April 16, 2014
ሰሙነ ሕማማት - ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
ማውጫ፦
From Contributors
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ - መጋቢት/፳፻፪ ዓ.ም):- ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት ፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት ፤ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት ፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው - ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።
April 10, 2014
መንግስት ማኅበረ ቅዱሳንን በአክራሪነት አልፈረጅኩም አለ
ማውጫ፦
From Contributors
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- “በይፋ አክራሪ ናችሁ ያለን አካል የለም” (አቶ ተስፋዬ ቢሆነኝ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ፀሐፊ)
(ሰንደቅ ጋዜጣ፤ ሚያዚያ 1/2006 ዓ.ም፤ ኤፕሪል 9/2014)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በ1994 ዓ.ም ፀድቆ በተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተቋቋመው ማኅበረ ቅዱሳንን የኢትዮጵያ መንግሥት በአክራሪነት አለመፈረጁን አስታወቀ። በሌላ በኩል ማኅበረ ቅዱሳን በበኩሉ በይፋ በአክራሪነት የፈረጀው አካል እንደሌለም አስታወቀ።
Subscribe to:
Posts (Atom)
Blog Archive
Must Read Documents
"1/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት/ የመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ጽ/ቤት አስተዳዳራዊ እና መዋቅራዊ ችግሮች የዳሰሰ ምልከታ"
አዘጋጅ፡- ልዑልሰገድ ግርማ የጠ/ቤ/ክ/ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ
Click HERE to read.
2/ የቅ/ሲኖዶስ የጥቅምት 2004 ዓ.ም አጀንዳዎች እና ውሳኔዎች፤ እንዲሁም ተያያዥ ዶኩመንቶች:: Click HERE to read and scroll down to (Page 5-20).
አዘጋጅ፡- ልዑልሰገድ ግርማ የጠ/ቤ/ክ/ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ
Click HERE to read.
2/ የቅ/ሲኖዶስ የጥቅምት 2004 ዓ.ም አጀንዳዎች እና ውሳኔዎች፤ እንዲሁም ተያያዥ ዶኩመንቶች:: Click HERE to read and scroll down to (Page 5-20).
