March 19, 2013

"30 000 ኢትዮጵያውያንን ለጨፈጨፈው ለግራዚያኒ የተሠራውን ኃውልት መቃወም ያስከብራል!" (ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ)


                                               www.globalallianceforethiopia.org
        ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ - የኢትዮጵያ ጉዳይ
                  4002 Blacksmith Drive, Garland, TX 75044, USA
                              መጋቢት 9 ቀን 2005 ዓ/ም
መግለጫ (PDF)
30 000 ኢትዮጵያውያንን ለጨፈጨፈው ለግራዚያኒ የተሠራውን ኃውልት መቃወም ያስከብራል!
በኢጣልያ፤ ከሮማ ወደ ምሥራቅ ደቡብ በምትገኝ፤ አፊሌ በምትሰኝ ትንሽ ከተማ፤ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” ለተሰኘው፤ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ ነሐሴ 4 ቀን 2004 ዓ/ም የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት የተመረቀለትን የክብር መታሰቢያና መናፈሻ በመቃወም፤ እስከ የኢጣልያ ኤምባሲ ድረስ ሰላማዊ ሰልፍ ለማከናወን መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ/ም ስድስት ኪሎ የተሰበሰቡትን 43 ሰዎች፤ ዶር. ያዕቆብ ኃይለማርያምን ጭምር፤ ፖሊስ አፍሶ ማሰሩና በማግስቱ፤ መጋቢት 9 ቀን 2005 ዓ/ም መልቀቁ ታውቋል።

አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን፤ ከነዚሁ ውስጥ በሶስት ቀኖች ብቻ፤ በአዲስ አበባ ከተማ 30፣000 ሕዝብ ላስጨፈጨፈው፤ እነአቡነ ጴጥሮስን፤ የደብረ ሊባኖስን መነኮሳትና ሌሎችንም በጭካኔ ለረፈረፈ፤ እንዲሁም 2000 ቤተክርስቲያኖችንንና 525፣000 ቤቶችን ላስወደመው፤ በተጨማሪም በብዙ አይሮፕላኖች ባስነሰነሰው የመርዝ ጋዝ ብዙ ሕዝብ ከመግደሉ በላይ እጅግ የከፋ የአካባቢ ብክለትና 14 ሚሊዮን እንስሶችን ላወደመው የጦር ወንጀለኛ፤ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ የተሠራውን መታሰቢያ መቃወም ለሐገር የሚያኮራና የሚያስመሰግን እንጂ የሚያሳስር አይደለም።

እንደሚታወቀው፤ ለዚህ ዓመት የየካቲት 12 ክብረ-በዓል፤ የፋሺሽቶችን የጦር ወንጀልና የግራዚያኒን መታሰቢያ በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ፤ 30 ከተሞች፤ ማለት፤ ሮማ፤ ኒውዮርክ፤ ዋሺንግተን ዲ.ሲ.፤ አትላንታ፤ ቴል አቪቭ፤ ወዘተ.  የሚገኙ የብዙ ሐገሮች ዜጎች፤ ኢጣልያውያን ጭምር፤ ሰላማዊ ሰልፎች፤ ስብሰባዎች፤ ጸሎቶች አከናውነዋል። አዲስ አበባም የከተማው አስተዳደርና የኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበር በእለቱ ለክብረ-በዓሉ መታሰቢያ ማከናወናቸው ታውቋል።

ስለዚህ፤ በኢጣልያ ለጦር ወንጀለኛው ለግራዚያኒ መታሰቢያ እስከ መሥራት የደረሰ የፋሺሽት መንሰራራት ሊያሳስበንና ሊያስቆጨን የሚገባው፤ ዋናዎቹ የግፉ ተበዳዮች የሆንነው እኛ ኢትዮጵያውያን በመሆናችን፤ ሐገራችን አሁንም እየጠበቀች ያለችውን ፍትሕ እንድታገኝ በሰላማዊ ሰልፍ ለኢጣልያ መንግሥት ማስገንዘብ የሚደገፍ እንጂ የሚያሳስር መሆን የለበትም።
በመጨረሻም፤ ኢትዮጵያ ለተፈጸመባት እጅግ መራርና ከባድ ግፍ እስካሁን ድረስ ተገቢውን ፍትሕ ስላላገኘች፤ ድርጅታችን ለሚከተሉት ዓላማዎች እየተንቀሳቀሰ ነው፤

          (ሀ) የኢጣልያ መንግሥት፤ የጦር ወንጀለኛውን የግራዚያንን መታሰቢያ እንዲያስወግድ፤
          (ለ) በቫቲካንና በኢጣልያ መንግሥቶች ይዞታ የሚገኙ የኢትዮጵያ ንብረቶች እንዲመለሱ፤
          (ሐ) የኢጣልያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ተገቢውን ካሣ እንዲከፍል፤
          (መ) ቫቲካን፤ ከፋሺሽት ኢጣልያ ጋር ተባብራ በተፈጸመው ወንጀል፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤
          (ሠ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጦር ወንጀሉን እንዲመዘግብ ነው።

ሐገራችን ላይ ለተፈጸመው የጦር ግፍ በሰብአዊ መብት መከበር የሚያምን ሁሉ በሚያከናውነው የተባበረና የጠነከረ ጥረት ተገቢው ፍትሕ ይገኛል።
                                   
                                                                                                

14 comments:

Anonymous said...

Yes we do have to demonstrate and oppose fascism which killed many thousands of Ethiopians including monks and Abunes (Abune Petros, Abune Micael) and destroy churches and monasteries. Tne Vatican Church which bless the war against Ethiopia is now again praising Adolf Hitler must stop supporting and also request an excuse the Ethiopian people. Go ahead

Anonymous said...

enante eko Deje selam sayhon DEJE SHIBIR neber malet yeneberebachuh,huket neger feligachuh post taregalachuh,yematrebu ere sile fetari eski be tsom enkuwan le nefs yemihon neger awru.yikir yibelachuh.

Anonymous said...

Maferia nhei ,kiber le yekatit 12 sematat.Ethiopia lezelalem be kiber tenure Amen!!!.

Anonymous said...

selam yebza wegnot endamen senbetahu ande nager lenager metym tefekdolgaltu gen gen yehne ye abey tome be masemelkat enkan adersatu malet enkan yektahuale kedanemihiretn betam new yetazebkatu belo soby new ena yekr beyatualhge egzabhr kenate gar yehne

Hailu said...

Yes, We should remeber our martyrs.
30,000 of fathers and mothers died in 3 days in Addis Ababa. Aune Petros and scores of monks at the Debre Libanos were masacred by Graziani.

Who in the world does not demonstrate against the erection of fascist Graziani? None, other than decendants of the bandas.

May God bless the souls of the Martyrs who were vicitmized by the fascist Graziani.

Melkam Abiy Tsome.

Anonymous said...

If you want to protest Graziani's statue, go to Rome and protest. That is where it is. Why protest in Ethiopia? Unless you want to use the excuse to create chaos.

Anonymous said...

I appreciate, u raised this point. but you should also bring any related issue or other stuffs.Ende it is long time eko yihe post ketederege

Kidist A

Anonymous said...

Hello,

Sitting at my desk at work, I just turn to this page a couple times a day. But nowadays you guys been silent. Be active, continue with your blog by serving us information. I really like this website,and the unique style of writing.

Stay relevant Deje Selam!

Its me said...

አእምሮ ላለው ባንዳ ላልሆነ ኢትዮጵያዊ ያሰከብራል ለቀረው ግን

Anonymous said...

ደጀ ሰላም ሆይ ወዴት ነሽ ? ? ? ? ? ? ? ?

Anonymous said...

ኸረ እንዴት ነው? በጤና ነው የጠፋችሁት? ምንድን ነው ነገሩ?

Anonymous said...

no more news for Dejeselam anymore since March 19. I guess the sources or lines of stealing information has been shut down for dejeselam.

Anonymous said...

what happened to deje selam? No more News. what is going on?

Anonymous said...

What happen dejeselamoch. There is no update on your blog. Pls we need new information about our church. Come on! sile graziyanai keteletefe sint gizew new...pls come up with new information. Enewodachehualen!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)