February 9, 2013

ሁሉንም ጊዜ ይፍታው


(ገብሩ ለክርስቶስ በተለይ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት/PDF)፦ “ወሰብአ ኢትዮጵያ ኢይሢሙ ላዕሌሆሙ ሊቀ ጳጳሳት እማእምራኒሄሙ  ወኢበሥምረተ ርእሶሙ፡፡ እስመ ጳጳሶሙ ይከውን እምታእተ እዴሁ  ለበዓለ  እስክንድርያ   ዘይደልዎ  ይሢም ላዕሌሆሙ ሊቀ  እምኀቤሁ  ዘውእቱ  መትሕተ ሊቀ  ጳጳሳት”፤ ትርጉም የኢትዮጵያ  ሰዎች ከዐዋቂዎቻቸው ወገን በራሳቸውም ፈቃድ ሊቀ ጳጳሳትን ለራሳቸው አይሹሙ፡፡ ጳጳሳቸው ከእስክንድርያ በዓለ መንበር ሥልጣን በታች ነውና፡፡ ከሊቀ ጳጳሳት በታች የሆነውን ሊቀ ጳጳስ  ከእነርሱ ወገን ሊሾምላቸው የሚገባው እርሱ ነው፡፡” (ፍትሐ .ነገ አንቀጽ 2 ቁ 50)::
ይህ ግብጻውን ትዮጵያ ራን ችላ በራ ፓትርያክ ስትመራ ላለማየት በማሰብ እንደጨመሩት የሚነገርለት የፍት ነገሥት ቃል ነው፡፡ አንዳንዶች ይህን ሕግ ማክበር ነበረብን ከራሳን ፓትርያርክ መምረት አይገባንም ነብር  ይላሉ፡፡ለዚህም  ፕትርክናውን  ከተቀበልን  ጊዜ  ጀምሮ  ያሳለፍናቸውን  ፈተናዎች  እንደምሳሌ  ይጠቅሳሉ፡፡ሌሎች ደግሞ  ይህ የፍትሐ ነገሥት ሕግ  በግብጻውያን እደተጨመረ በመጥቀስ  የፕትርክና ሥልጣን ፈተና  የገጠመው መንግሥታት  ባመጡብን  ግልጽ የሆነ ተፅዕኖ  እንጂ  ሳይገባን  ቀርቶ/ለኢትዮጵያውያን የተከለከለ ሆኖ/አይደለም ይላሉ፡፡የዝሆን ጥርስ፣ወርቁን፣ብሩን ለግብጻውያን እየገበርን በሥራቸው ከመኖር ነጻ መውጣታችን መልካም ሆኖ ሳለ ችግር የፈጠረብን  የመንግሥታት  ተጽዕኖ  ነው  በማለት  ያስረዳሉ፡፡

ኢትዮጵያ የራ ጳጳስ እንዲኖራት ያቀረበችው ጥያቄ
ታሪክ እንደሚነግረን  በ11ኛው  መቶ ክፍለ ዘመን የነገሠው  ቅዱስ  ሐርቤ ወስመ ጥምቀቱ ገብረ ማርያም ኢትዮጵያን ዞረው የሚያስተምሩ የሚቀድሱ የሚባርኩ አር ቆሞሳት የኤስ ቆጶስነት ዕረግ እንዲሰጣቸው ዳግማዊ ገብርኤል  የእስክንድርያውን ፓትርያርክ ጠይቆ ነበር፡፡ የካይሮ ቅዱስ ሲኖዶስ ለጥያቄው ቀና መልስ ስላልሰጠው ጉዳዩ በእንጥልጥል  ቀርል፡፡ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽም ላይ አ ሐንስ ኢትዮጵውያን ቆሞሳት ተመው ኤጲስ ቆጶሳት  እንዲሆኑላቸው የእስክንድርውን ፓትርያርክ ቄርሎስ ሁለተኛን ጠይቀው ነበር፡፡ አሁንም ከእስክንድርያ ቀና መልስ  አልተገኘም፡፡ አጼ ሐንስ በዚህ ምክንያት  ከአርመን ቤተ ክርስቲያን  መጻጻፍም ጀምረው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ማርቆስ አባታችን እስክን እናታችን ከሚለው ውፊት መራቅ መሆኑ ስለተሰማቸው  ጉዳዩን ትተውታል፡፡

በ1921  እና 1922  ዓ.ም  ለመጀመሪያ ጊዜ  አራት በካይሮ አንድ በአዲስ አበባ በድምሩ  አምስት ቆሞሳት ኤጲስ ቆጶስ ሆነው ተሾሙ፡፡ሊቀ ጳጳስ ሆኖ እንዲያገለግልም  ግብጻዊው  ቄርሎስ  ከካይሮ  ወደ  ኢትዮጵያ  መጣ፡፡በ1928  ዓ.ም  ፋሽስት ኢጣልያ  በኢትዮጵያ  ላይ ወረራ  ባካሄደበት  ወቅት ሊቀ ጳጳሱ አቡነ  ቄርሎስ  ያለ በቂ ምክንያት  ብፁዕ  አቡነ አብሃምን ወክለው  ወደ ሮም ሄዱ፡፡ ከዚያም  የተጠየቁት ጥያቄ ስላልተሳካ  ከሮም ወደ ካይሮ በዚያው ተመለሱ፡፡

በጣልያን  ወረራ  ወቅት  በኢትዮጵያውያንና  በግብጽ  አብያተ  ክርስቲያናት  መካከል  ቅራኔ  ተፈጥሮ ነበር፡፡ ይህም ቅራኔ  ያለ ግብጻውያን እውቅና ኢትዮጵውያን ሹመት መስጠት በመቀጠላቸው  ምክንያት  የመጣ  ነበር፡፡ ፋሽስት ኢጣልያ  ሙሉ  ለሙሉ  ሀገር  ለቆ  ከወጣ  ከጥቂት  ዓመታት  በላ   በ1940  ዓ.ም  የኢትዮጵያ ቤተ ክህነት ልዑካን ወደ ካሮ በመሔድ ከግብጽ ሲኖዶስ ጋር ያላቸውን ቅራኔ በመነጋገር  ፈትተዋል፡፡ በዚህም ወቅት አምስት ሊቃነ ጳጳሳት ተሹመው   ኤጲስ ቆጶስ ሲሆኑ በ1943 የሊቀ ጵጵስና ማዕረግም ተገኝል፡፡ ቆይቶም ይህ የሰላም ውይይት በመቀጠሉ ምክንያት  በ1951   ዓ.ም ብፁዕ  አቡነ  ባስልዮስ  የመጀመሪያው  የኢትዮጵያ  ፓትርያርክ  ሆነው   በቄርሎስ   ስድስተኛው በካይሮ  መንበረ  ማርቆስ ተሹመዋል፡፡ በዚህ የሹመት ሥነ ርዓት ላይ ግርማዊ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ተገኝተው ነበር፡፡ የፕትርክናው ሥልጣን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አባቶች እየተሾሙበት እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ በዚህም በ1951 ዓ.ም ከተሙት ከመጀመሪያው ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ጀምሮ ወደ አምስት የሚደርሱ ፓትርያርኮችንም አፈራርቀናል፡፡ የእነዚህ ፓትርያርኮቻች የሥልጣን  ዘመን  እንደሚከተለው ነው፡፡

የፓትርያርኮቻችን  የሥልጣን ዘመንና  የሾሙአቸው ሊቃነ ጳጳሳት ብዛት
1-     ብፁዕ  ወቅዱስ  አቡነ ባስልዮስ  ፓትርያርክ   ከ1951-1963  ዓ.ም
2-    ብፁዕ  ወቅዱስ  አቡነ  ቴዎፍሎስ  ፓትርያርክ  ከ1963-1968  ዓ.ም
3-    ብፁዕ  ወቅዱስ  አቡነ  ተክለ ሃይማኖት ፓትርያርክ  ከ1968-1980  ዓ.ም
4-    ብፁዕ  ወቅዱስ  አቡነ  መርቆርዮስ  ፓትርያርክ  1980-1983 ዓ.ም
5-    ብፁዕ  ወቅዱስ  አቡነ  ጳውሎስ   ፓትርያርክ   ከ1984-2004  ዓ.ም  

በእነዚህ  አባቶች  የፕትርክና  ዘመን  የተሾሙ  ሊቃነ ጳጳሳት  ቁጥር ደግሞ  ይህንን ይመስላል
1-     ብፁዕ  ወቅዱስ  አቡነ ባስልዮስ - ራ ሰባት
2-    ብፁዕ  ወቅዱስ  አቡነ  ቴዎፍሎስ - ዘጠኝ
3-    ብፁዕ  ወቅዱስ  አቡነ  ተክለ ሃይማኖት - ሃያ ስምንት
4-    ብፁዕ  ወቅዱስ  አቡነ  መርቆርዮስ - ስድስት  በሀገር  ቤት  አስራ  ሦስት  በውጭው  ሲኖዶስ 
5-    ብፁዕ  ወቅዱስ  አቡነ  ጳውሎስ - አርባ ዘጠኝ

በሁለቱም ሲኖዶስ በድምሩ መቶ ሃያ ሁለት ጳጳሳት የተሾሙ ሲሆን በሞት ከተለዩ አባቶች ውጭ የተቀሩት አሁንም ቤተ ክርስቲያንን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ጳጳሳትን በብዛት በመሾም የሚታወቁት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲሆኑ በመቀጠልም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ይከተላሉ፡፡

የጵጵስና  ማዕረግ
የጵጵስና ማዕረግ በቤተ ክርስቲያን  የመጨረሻው የሥልጣንና  የላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኝ  እንደመሆኑ  አመራረጡም ሆነ ሹመት አሰጣጡ በጥንቃቄ የሚካሔድ ነው፡፡ ለዚህ ማዕረግ የሚታጭ አባት ቢቻል በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ዕውቀት የበለፀገ፣ ቅዳሴውን፣ ቅኔውን፣ ትርሜውን፣ ቋቋሙን የዘለቀ ተርጉሞ  አመስጥሮ ምዕመናን የሚያስተምር የሚመክር  ሊሆን  ይገባዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ደግሞ በምግባር የተመሰከረለት፣ ምዕመናንን በመንፈሳዊ ሥነ ምግባር እንዲበረቱ  በጎ ጎዳናን የሚመራ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህ በተግባር ሲታይ ግን ብዙ ብርቱ አባቶች ቢኖሩንም የአንዳንዶቹ ሕይወት ጥያቄ የሚያስነሳበት ሁኔታ አለ፡፡ መልሱን ለእግዚአብሔር ትተናል፡፡
የመንግሥት  ጣልቃ  ገብነት
ፕትርክና ወደ ኢትዮጵያ ካመጣን ለፉት ሃምሳ አራት መታት ጀምሮ መንግሥታት ጣልቃ ከመግባት አላረፉም፡፡ የሚሾሙ ፓትርያርኮች ከእነርሱ  ጋር  ተስማምተው እንዲዙ  ለማድረግ  በግልጽ ሲሰሩ ታይተዋል፡፡ ብፁዕ  ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ከንጉሡ ጋር  መስማማት፣ ብፁዕ  ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ለንጉሡ ከነበራቸው  አክብሮትና  ፍቅር  የተነሣ  ከደርግ  መንግሥት ጋር መጋጨት እንዲሁም መታሠር እና መገደል ለዚህ ምስክር ይሆነናል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት  ከወታደራዊው መንግሥት  ላለመስማማት  ላለመጣላትም  ባደረጉት ጥረት የገጠማቸው  ፈተና  እና ራሳቸውን በጾም  በጸሎት  ቀጥተው  ያለፉበት ሕይወት፣ ብፁዕ  ወቅዱስ  አቡነ መርቆርዮስ ከወታደራዊው መንግሥት ጋር በነበራቸው መቀራረብ  ምክንያት ሥልጣን ሲለቅ በኢሕአዴግ መንግሥት የቀረበላቸው ሥልጣን ይልቀቁ የሚል ግፊት በዚህም  ያለበቂ  ምክንያት ሥልጣኑን ለቀው እንዲሰደዱ የሆኑበት ሕይወት፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ  ጳውሎስ ከኢሕአዴግ መንግሥት ጋር የነበራቸው ግልጽ መቀራረብ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ  የፈጠረው አሉታዊ ተጽዕኖ ለችግሩ ማሳያ የሚሆን ታላቅ  ምስክር ነው፡፡

ዛሬ  ይህ  ተፅዕኖ  መጣብን ችግር  ምክንያት አባቶቻችን ለሁለት ተከፍለዋል፡፡ የተሐድሶ እምነት አራማጆች በየሥፍራው  እንደ ልባቸው  እንዲፈነጩ ሆነዋል፡፡ ሙስና ሥርዓት አልበኝነት ዘረኝነት እና ኢ-ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባሮች በቤተ ክርስቲያናችን  ተንሰራፍታል፡፡ ዘረኝነት ማን አለብኝ ባይነት ከላይ እስከ ታች  እንዲዳረሰ  ሆል፡፡ ቤተ ክርስቲኒቱ በውጭም  ሆነ በውስጥ ለተሰለፉባት ጠላቶች አመቺ  ሆና እንድትገኝ  ሆናለች፡፡ ብዙዎች  ይህንን ተመልክተው መጪውን ዘመን  ያለፈውን ቁስል የምንሽርበት እንዲሆን እየተመኙ  ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ካለፉት ሁሉ በከፋ በግልጽ በሚታይ መልኩ ስድስተኛውንም ፓትርያርክም  በመንግሥት  ተዕኖ ሥር ሆነን ለመምረጥ እየተዘጋጀን ነው፡፡ በዚህ  በያዝነው የየካቲት ወር ሁሉም ነገር ይፋ ይሆናል፡፡ አሳዛኝ የታሪክ ድግግሞሽ  ይከሰታል፡፡ ከትናንቱ ያልተማርንበት ሌላ አዲስ የፈተና ዘመንም እንጀምራለን፡፡

በዓለ ሲመት በየካቲት ወር?
የስድስተኛው ፓትርያርክ የአስመራጭ ኮሚቴ ይፋ እንዳደረገው  የምርጫ  ውጤት የካቲት  ሃያ አንድ ይፋ ይሆንና የካቲት  ሃያ አራት በዓለ ሲመት ይከበራል፡፡ የስድስተኛው ፓትርያር በዓለ ሲመት የካቲት ሃያ አራት ሆኖም በየዓመቱ  ይቀጥላል፡፡ የሚገርመው በመጪው ዓመት የካቲት አራ ሰባት የዳዴ ም  መጀመሩ ነው፡፡ በ2007  ዓ.ም ደግሞ የዳዴ ም መግቢያ የካቲት ዘጠኝ  ይሆናል፡፡ ስለዚህ  በዓለ ሲመት በሑዳዴ ሊከበር ነው ማለት ይሆናል፡፡ አንዳንድ አባቶች ይህን አስበው ምርጫው ከሑዳዴ ም  በላ ለምን አይሆንም የሚል ጥያቄ  ቢያቀርቡም የሚሰማቸው አላገኙም፡፡ በችኮላ  እና  በሩጫ  ወደ   ምርጫው  ተገስግል፡፡ እንዲህ በጥድፊያ ዘነገሮቹን መፈጠም የተፈለገው ከየት በመጣ ትዕዛዝ ይሆን?

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን
  
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)