February 25, 2013

ሽማግሌዎች ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን አነጋገሩ፤ አስመራጩ መግለጫ ሰጠ


(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 18/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 25/2013/ PDF)፦ ቅዳሜ የካቲት 16/2005 ዓ.ም ቀርበው በአብዛኛው የቅ/ሲኖዶስ አባላት ይሁንታ አግኝተዋል የተባሉት አስምት ሊቃነ ጳጳሳት በመጪው ሐሙስ ለሚካሄደው የፓትርያርክ ምርጫ ያለፉ መሆናቸውን አስመራጭ ኮሚቴው ዛሬ በጋዜጣዊ መግለጫው ገልጿል።


ከፍተኛ ታቃውሞና የከረረ ተግሳጽ የደረሰባቸውን አቡነ ማትያስ ዘኢየሩሳሌምን ጨምሮ ሌሎቹ አራት አባቶች የተካተቱበት የአስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማ ለቅ/ሲኖዶስ ቢቀርብም ተጨማሪም ተቀናሽም ሳይደረግበት መጽደቁ ዛሬ ይፋ ሆኗል። በዚህም መሠረት ሐሙስ በሚደረገው ምርጫ ከፍተኛ ቁጥር የሚያገኘው ተወዳዳሪ ስድስተኛ ፓትርያርክ ተብሎ ይሾማል ማለት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ስድስተኛውን ፓትርያርክ ምርጫ ተከትሎ ሰሞኑን የተፈጠረውን  አለመግባባት ለመፍታት የአስመራጭ  ኮሚቴው  ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከሌሎች ብፁዐን ሊቃነ  ጳጳሳት ጋር በመሆን  የምርጫውን  ሒደት የታቃወሙትን ብጹዕ አቡነ ሳሙኤልን ማነጋገሩን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለደጀ ሰላም ገልጸዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ለማነጋገር ያደረጉት ሙከራም በብፁዕነታቸው በአካባቢው አለመኖር ምክንያት ሳይሳካ መቅረቱን እነዚሁ ውስጥ አዋቂዎች አስረድተዋል።

በምርጫው ላይ ያነሱትን የዘገየ ነው የተባለ ተቃውሞ እንዲያቀዘቅዙ ለማግባባትና ምርጫው በተጀመረው መሠረት እንዲጠናቀቅ ለማሸማገል የተላኩት አባቶች የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሐሳብ ለማስቀየር የቻሉ አይመስልም። ብጹዕነታቸው በተቃውሟቸው በመግፋት በቅዳሜ የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ያንጸባረቁትን ሐሳብ ደግመውላቸዋል ተብሏል። እንዲያውም አስመራጩ ኮሚቴ መግለጫውን ካወጣ እነርሱም (አቡነ ሳሙኤልና አቡነ አብርሃም?) በበኩላቸው ተቃውሟቸውን በመግለጫ ይፋ እንደሚያደርጉ ለሽማግሌዎቹ አስረድተዋቸዋል ሲሉ ምንጮቻችን ያብራራሉ። ይሁን እንጂ አስመራጭ ኮሚቴው በያዘው ሐሳብ በመግፋት በቅዳሜው ስብሰባ ያስጸደቃቸውን አመስት አባቶች እና አጠቃለይ የጥቆማውን ሒደት በመግለጽ ዋነኛውን ክፍል የምርጫ ጉዞ አጠናቋል።

ይኸው ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት በዛሬው ዕለት እንደተገለጸው በነዚህ ሦስት ቀናት ብፁዓን አባቶችን ጨምሮ ምእመኑ በሙሉ ጉዳዩን በጾም በጸሎት እንዲያስብና የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲጠይቅ አስመራጭ ኮሚቴው አሳስቧል። ምርጫው ካርድ በመጣል እንጂ እንደ አበው ሥርዓት ዕጣ በማውጣት እንዳልሆነ፣ ይህ ሐሳብ በምርጫ ደንብ ማጽደቁ ወቅት ውድቅ እንደተደረገ፣ ይህንን ሐሳብ ያቀረቡ አባቶች ተሰሚነት እንዳላገኙ ይልቁንም “ምርጫው ልክ በመንግሥት እንደሚደረገው በካርድ ይሁን” የሚል ሐሳብ እንደተንጸባረቀ መዘገቡ ይታወሳል። በርግጥ በዕጣ ቢሆንና ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቁ ቢባል እንዴት ባማረ፣ እንዴትስ ሃይማኖታዊ በመሰለ ነበር። የመንግሥት እጅ ለሚዋኝበት፣ ፈቃደ ቤተ መንግሥት ፈጻሚ ሞገስ ለሚያገኝበት፣ ሁሉም ወገን “አባቴ ነው፣ ይደልዎ፣ መመረጥ ይገባዋል” ለማይልበት ምርጫ በጾምና በጸሎት አስቡን ማለት ሰውን ለመፈታተን እና ሃይማኖታዊ መስሎ ለመታት ካልሆነ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ነው።

ከዚህ አስቀድመን በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ዘኢየሩሳሌም ፓትርያርክ እንዲሆኑ የመንግሥት ዓላማ መሆኑን ምንጮችን ጠቅሰን ዘግበን ነበር። በወቅቱ በግልም በሚዲያ ደረጃም ይህ የደጀ ሰላም ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን ለመጠቆም ብዙ መልእክቶች ደርሰውን ነበር። ጊዜው ሲደርስ እየሆነ ያለው ይኸው ይመስላል።

ደጀ ሰላም ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ላይ ተቃውሞ የላትም። ለሃይማኖታቸው ተቆርቋሪ፣ በብዙ ሰዎችም ዘንድ የመሰገኑ ንፁህ መነኩሴ መሆናቸውን የሚሰጠውን ምስክርነት ደጀ ሰላምም ታውቃለች። የምርጫው ሒደት ትክክል አይደለም ማለት አቡነ ማቲያስ መጥፎ ናቸው እንደማለት መቆጠር የለበትም። ሌለቾዩን ብፁዓን አባቶች አሠራራቸውን በየጊዜው እያየን ሊመሰገኑ ሲገባቸው የምናመሰግናቸው፣ ትክክል አይደሉም ብለን በምናስብበት ወቅት የምንቃወማቸው በዚያ ወቅት ባራመዱት ዓላማ ምክንያት ብቻ ነው።

ከዚህ በፊት አቡነ ሳሙኤልንና አቡነ አብርሃምን ታደንቁ ነበር አሁን ለምን የያዙትን አቋም አልተቀበላችሁም ለሚሉን የምንሰጠው መልስ ይኼው ነው። አቡነ ሳሙኤል በተለይ የቀድሞው ፓትርያርክ ያራምዱት በነበረው አውዳሚ እንቅስቃሴ ላይ በነበራቸው ተቃውሞ፣ ሙስናን ለማጥፋት ባደረጉት ትግል እኛም ደግፈናቸዋል። አሁንም ለዚያ እንቅስቃሴያቸው ያለን አክብሮት ትልቅ ነው። አቡነ አብርሃምም አሜሪካ በነበሩበት ወቅት ለሠጡት ትልቅ አገልግሎት ስናመሰግናቸው ቆይተናል፣ አሁንም እናመሰግናቸዋለን። ሁለቱም አባቶች ዕርቀ ሰላሙን በተመለከተ ባራዱት አቋም ደግሞ እንኮንናቸዋለን። ተሳስተዋል እንላለን።

ከዚህ ባሻገር ምርጫውን በተመለከተ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንዳለበት መግለጻቸው ትክክል ነው። ስንቃወመው የነበረው፣ አሁንም የምንቃወመው ተግባር ነው። በዕጣ መሆኑን ስንመኝበት ከነበረው ምክንያት አንዱ ለእግዚአብሔር ፈቃድ የተመቸ ሥራ መሥራት እንዲቻል ነበር። አልሆነም። በካርድ የሚመረጠው አባት ማንም ይሁን ማን “የመንግሥት ወገን” ተደርጎ መቆጠሩ አይቀርለትም። ያሳዝናል።
ቸር ወሬ ያሰማን አሜን

14 comments:

Anonymous said...

በዕጣም ሆነ በምርጫ እግዚአብሔር በፈቀደው ጥሩ አባት ይስጠን። አሜን

ቴክሳስ

Anonymous said...

በድርቶ ላይ አዲስ ጨርቅ እንዲሉ ለኔ ሌላው በአባ ጳውሎስ ማለት ናቸው::
የሚገርመው ምርጫ ሳይደረግ ስለ አቡነ ማትያስ ይህን ሁለ ከተባለ እኔና መሰሎቸ የምንቃወመው ስርአቱን ነው እንጂ እንደ አባት በአባ ጳውሎስን አይደለም። ወደድንም ጠላንም የትግራይ ባሪያወች እነሱም የኛ ቅኝ ገዥወች ከሆን 21 አመት አልፎናል።

Unknown said...

''በዕጣም ሆነ በምርጫ እግዚአብሔር በፈቀደው ጥሩ አባት ይስጠን። አሜን

ቴክሳስ''የቴክሳሣሱ ወገኔ ፤ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ምርጫ የቅዱስ እግዚአብሔር ምርጫ ሊሆን አይችልም !ለምን ጨለማን ከብርሃን ጋር ያለማፈራረቅ ሊያኖሩት ይሞክራሉ ? ይህ እኮ የተፈጥሮን ሕግ ለመቀየር እንደ መሞከር ነው። ለምን ነው ሀቁን እያወቅነው ለማለት ስንል በቻ አስመሳይነትን የምናንጸባርቀው ? በእውነት ከክርስቲያኖች የሚጠበቅ ነው ? አባ ማትያስ የአገዛዙን መመዘኛ በሁሉም ነገር ስለሚያሙዋሉ የአባ ጳውሎስን አልጋ የሚወርሱት እርሳቸው መሆናቸውን ሁላችንም የምናውቀው ሀቅ ስለሆነ፥ ይህን ደፍሮ መናገር ነብይነተን የሚጠይቅ አይደለም። በዚህ አገዛዝ ዘመን ''ወርቃማ'' ከሚሉት ዘር ውጭ በማንኛውም ሥልጣን ቁልፍ ቦታ ላይ ወሳኝ ለመሆን ሊቀመጥ መመዘኛውን አያሟላም !

Anonymous said...

I read all these comments regarding this issue, it looks like a copy and paste comment. we know exactly TPLF's involvment on the election and on other internal issues but I don't like the way you support Abune Merkorios. if this chruch is to be in its worst time after Gragn Mohamed the contibuition is not only Abune Paulos's and Woyane but also Abune Merkorios's too. He was elected and was supported by Derg, all Ethiopia knows this, now he and his supporters are against the government's involvement. this is like when you steal something I call you a THIEF and when I still something I am the best.
read John 8:7:
"He that is without sin among you, let him first cast a stone at her."
I think our Bishops have never understood what Jesus said in this word. why is he not appearing in public addressing his messages and blessings? may be this moment would be good for him also. "yegebeya giri giri leleba yamechal". Please check what happened in the Catholic chruch recently, the Pope has resigned due to so many internal bad reasons- I think this is a sense of responsability, I think our Bishops should learn something from this. if we had had such bishops with a sense of responsability our chruch would have been........ Let God and his virgin mother help the chruch. please pray.

Anonymous said...

Geta Eyesus kirstos Medhanialemim eko Esraelawi new wegenoch! Bessiga awo Esraelawi new. Engidi Ethiopiawi amlak liyawm non-tigree felguwa! Are tewu the semayawi new!? YEmishomew hulu yegd and bota mewled alebet. Hulum Amara kilil/Tigray kilil liweledko aychilim. Demo keTigray hizb 95% yemihonew kirstiyan( Orthodoxawi) New ena beprobability hig enquan bnayew, menfesawi abatoch keza yemewtat edilachew sefi new. Kale fetari fekad andach yemihon yelem ena yemimeretew manim yhun man yegeta tewekay new. Bayfekidko geta, eyandandachinin negen layasayen ychilal. Zerna mender kotariwoch ebakachu adeb gizu. Beza lay lela kilil yetewelede yerash zer lihon ychilal. Alyam ante kilil yetewelede yelela zer. Emenegn wedaje manim bishom aymechihm. Ante rasihim bitishom enquan.

Anonymous said...

በመሠረቱ ይህ ሲመተ ፓትርያርክ ከእርቅ በፊት መደረጉ በራሱ አማኙን ብቻም ሳይሆን የበጎቹን ባለቤት እግዚአብሔርንም የሚያሳዝን ነው፡፡

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ምርጫው አያስፈልግም እርቅ ይቅደም ያልነው አንሶ አሁን ደግሞ ፍጹም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ፍጹም ሐዋርያዊ ባልሆነ አሠራር ምርጫው በካርድ ይሁን ማለት በ1997ዓ.ም ኢሕአዴግ የሕዝብን ድምጽ ሠርቆ ራሱን እንዳስጌጠበት ነው፡፡ ለመሆኑ እሳትና ውሃ ይኸውልህ እጅህን ወደሚበጅህ የሚለው ታላቅ በነጻነትና በፈቃድ የመወሰን ዴሞክራሲያዊ መብት በራእየ ዮሐንስ ተሰጥቶ እያለ ኢሕአዴግ በካርድ ምረጡ ብሎ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን ለቤተክርስቲያን ማስተማሩ የአባቶቻችንን ተጠያቂነት፣ እግዚአብሔርን በእውነት በሚፈልጉት ምዕመናን ዘንድ ምን አባት አለን ዛሬም እረኛ የሌለው በግ ሆነን ተበትነናል ማስባሉ አይቀርም፡፡

ካርድ ለምርጫ? አሳፋሪ፣ አሳፋሪ፣ አሳፋሪ አስጸያፊ ኢ ቀኖናዊ፣ ኢ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፡፡

Anonymous said...

Yekedemut 5 papasat yeteshomutimko be mircha new. Ante kalawek ei-kenonawi new mallet adelem. Eski yminakewn enawra. Abune mMerkoryosna kesachew yekedemut patriyarkoch hulu yeteshomut bemrcha new. Kemefredih befit yemiyakutin teyk.

Hailu said...

No matter how it is directed, the so called election is a drama devoid of any spirituality.

As long as the legitimate Patriarch, His Holiness Abune Merkorios is alive, any election, no matter how well managed and better directed than it is now by the TPLF, it remains illegal.

So, who cares about this madness as to who will emerge as the star actor of this drama? It doesn’t matter whether it is Aba matias, Aba Elsa, or anyone. It is illegal and unspiritual per the cannon law of the Orthodox Church.

Anonymous said...

አንዳንድ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ሰወች ጉዳዩን ከአባ ጳውሎስ እና ከብጽእ ወቅዱስ አቡነ መርቀሪዮስ ጋር እያመሳሰሉ ያምታታሉ። እኛ ስርአቱንና የስርአቱን አራማጆች እንዲሁም ሆዳሞችን ነው የተቃወምነው። አባቶችን በዘር አደራጂቶ የሁላችሁም የበላይ እኔ ትግሬው ነኝ የሚለውን ስርአት ነው የምንዋጋው ። ተስፈኞች ለሆዳቸው ይደሩ፡ እኛ ግን እውነትን ይዘን ከብጽእ ወቅዱስ አቡነ መርቀሪዮስ እውነተኛ ቅዱስ ፓትሪያሪክ ጋር እግዚአብሄርን በፍቅር የማንም ክፉ ዘረኛ ማላገጫ ሳንሆን እግዚአብሄርን እናመልካለን ብርሀን ከጨለማ ጋር ህብረት የለውም።ገለልተኛ መሆን ከዚህ ላይ ያበቃል ወያኔ ወይም ፀረ ወያኔ መምረጥ የግድ ይላል።

Anonymous said...

እባካችሁ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ምርጫው ትክክል አካሄድ እንዳልሆነ ድምጻችን እናሰማ :: እነ አባ አብርሃም አባ ሳሙዔል ተቀምጠው ተከራክረው የአተፉትን ጥፋት ዛሬ ይሄው መመለስ አቅቷቸው እርር ድብን ይላሉ :: እርቅ ይቅደም ቢባል አይሆንም ብለው ሞገቱ ምርጫው በኢጣ ይሁን ቢባል አንገታችን ለሰይፍ አሉ :: ይህ እስኪሆን ድረስ ምናልባት ከእኛ አይወጣም ብለው አስበው ነበር :: ቤተ ክርስቲያንን ግን ቀብሯት እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ :: እናም ውገኞቼ እኔ መንግስትን በምንም መንገድ ተጠያቂ አላደርግም የእናውቹ ጳጳሳት ትብየዎች ናቸው እኮ ቤተ ክርስቲያንን እያደሟት ያሉት::የዛፎችን ምሳሌ መመልከት በቂ ነው :: ዛፎች ተሰብስበው በምሳር /መጥረቢያ / ላይ ስብሰባ አደርጉ ከተሰብሳቢዎች በእድሜ ጤና ያለው ታላቅ ዛፍ ተነስቶ መጥረቢያ /ምሳሩ/ ምን አደረገን የእኛው ጠማማ እጄታ ነው መሳሪያ ሆኖ የምያስቆርጠን አለ ይባላል :: እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ ስለ ደጋጎቹ ስል :: ሌላ ምን ይባላል ::

Anonymous said...

መቼስ ብዙው ጦመርተኛው ውጭ፤ ከውጭም በምድረ አሜሪካ ያለን ስንሆን፤ በተለይ ደግሞ አንዳንድ "ጥርሳቸውን ነክሰው"ና "ለሃይማኖቷና ለሥረዓቷ ተጨንቀው" አስተያየት የሰጡትን ሳስተውል ግን እንደው ግርም ይለኛል...
- እንደው ጫማ አጫመው ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ሲያስቀድሱ ...ያልተጨነቁ
- እንደው የጥዋት ቁርስ በልተው ቤተ ክርስቲያን ሲገቡና ሲዘምሩ...ያላፈሩ
- ቤተ ክርስቲያናቸውን በፈረቃ ለፖለቲካ ስራ ፈቅደው...የተዳፈሩ ደፋሮች
-.... አፍቃሪ አባ...እገሌ ወይም አባ ... ሆነው የሙጥኝ ያሉ..
- "አዎ፤ የስደተኛ ቤተ ክርስቲያን ነው የኛ" ሲሉ..
- አዝማሪዎችን በቅኔ ማህሌቱ ላይ ሲያዘልሉ... ለfund raising ፤ ለሌላም ሲያደርጉ ...ያላፈሩ/ ደፋሮች
- የቤተ ክርስቲያን አባል ለመሆን የሚፈልገውን የቦርድን ይሁንታን ሲያስጠይቁ... አረ ስንቱ
-
-
** አረ በየትኛው የሞራል መስፈርት ነው? በሀገር ያሉ አባቶችን፤ ቤት ክርስቲያንና ሥርአቷን "የሚገመግሙት"? **
-
- ላላወቀሽ ታጠኚ
ግድ የለም እዚሁ በተግ.ማው ላይ ማሰብ ይበቃል።
አልያ እንመጥንም።/ k-eyqirta gar

ቴክሳስ

Anonymous said...

ከቴክሳስ feb 26-2013 8:23 የጻፍከው /ሽ / አስትያየቱ አሁን ቤተ ክርስቲያን ያለችበትንና መወያያ የሆነውን ነገር ይተመለከትከው አልመሰለኝም ::ወይም የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ አላስጭነቀህም ልበል ይሆን ? ከይቅርታ ጋር በአሁኑ ሰዓት ውጭ ስላሉት አብያተ ክርስቲያናት ወይ ደግሞ ስለ ሁለቱ ሲኖዶሶች አይደለም የሚያስጨንቀን ያን የተነጋገርንበት ግዜ አለፈ እኮ :: ምንም አዝነን ብንቀርም :: አሁን ትልቁ ጉዳይ ቤተ ክርስቲያንን የሚመራ አባት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ስርዓትና ትውፊት ይመርጥ ነው ጥያቄው ::አንተ እንዳልከው የቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ እየፈረሰ ነው አክብሮ የሚያስከብር አባት እና አሰራር ይኑረን ነው ጥያቄው:: ከዚህ አንጻር ሁሉም የምንገበገበው አሁን እየተደረገ ያለው ስርዓተ ምርጫ ትክክል አይደለም ነው ::ብዙ የምለው ነገር ነበረ ግን ምን ዋጋ አለው ::

Unknown said...

ከቴክሳስ ሁነህ ስደተኛ አባቶችን በመንቀፍ አስተያየት የሰጠኸው ወገን ፣ አባባልህ ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በዘመነ ሥጋዌው በዚህ ዓለም በአካል በነበረበት ጊዜ ሲታገሉት የነበሩትን ፈሪሳውያንን መስለህ ታየኽኝ። በቤተ መቅደስ ባሕታዊ ፈቃደ ሥላሴን የገደሉትን ፥ በቁማቸው የጣዖት ሃውልት ያቆሙትን ''ብፁዕ ወቅዱስ'' እያሉ የሚጠሩትን ''ብፁአን'' እያልክ እየጠራህ ''ጫማ ተጫሙ፥ አዝማሪዎችን አስጨፈሩ፥ ቁርስ በልተው ዘመሩ...''የሚል ክስ ታቀርባለህ። የሥላሴን ሕንፃ ሰውን ማፍረስ እንደ ኃጢአት ሳትቆጥረው ጥቃቅኑን ነገር እንደ ታላቅ ኃጢአት ኣድርገህ ስደተኛ አባቶችን ለመንቀፍ እንደ መረጃ አድርገህ ማቅረብህ ፈሪሳውያኑን አስመስሎሃል። ወገኔ ፤ እስቲ ስለፈሪሳውያን ምንነት የሚገልፀውን ማቴዎስ 23፤ 1-36፥ ማርቆስ 12፤ 38-40፥ ሉቃስ 11 ፤ 37-መጨረሻው ያለውን ተመልከት። ራስህን ከዚህ ጋር አመሳክረውና እውነተኛ ማንነትህን እወቀው ። አዝማሪዎች በቤተ ክርስቲያን መዘመራቸውንም ነቅፈሃል። ለመሆኑ ''አዝማሪ ''የሚለው ቃል ''ዘመረ'' ከሚለው ግስ እንደወጣ ታውቃለህ ? ጥያቄው ለማን ነው የዘመሩት ወይም የዘፈኑት ነው። ልበ አምላክ ዳዊት በታቦተ ሕጉ ፊት እንደ ዘፈነ እስቲ 2ኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 6 ከቁጥር 1 ጀምረህ ያለውን ተመልከተው። 'ማኅሌት ፥ መዝሙር ፥ ዘፈን ' የሚለው ነገር ሁሉ ምሥጢሩ ያው ምሥጋና ማለት ነው። የሚለየው ማንን ለማመስገን ነው በሚለው ጥያቄ ላይ ብቻ ነው እንጅ በቃላቶቹ አይደለም። እስቲ ለማንኛውም ''ድንቁርና ለድፍረት ፥ ዐቃቤ ንዋይ ለክህደት ይመቻል'' የሚለው አንተን እንዳያጠቃህ የእውቀትና የጥበብ እንዲሁም የእመነት ምንጭ የሆኑትን መጻሕፍት አንብበህ ተረዳ።

Anonymous said...

sorry I did agree with your idea. 4mi kemihon hezeb wist yeteshale haymanotena selale ...le patriyac Ene
yeteshale wetader selehone yetoru azashe
yeteshale yetemare selehonu wager meriyoch
Arif keld new Esu yakale lehulum geze alew

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)