February 24, 2013

የዕጩዎች ምርጫው እንደፈለጉት ያልሆነላቸው ጳጳሳት ሙግት ገጥመዋል

(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 16/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 23/2013/ PDF)የስድስተኛው  ፓትርያርክ  አስመራጭ   ኮሚቴ  በዛሬው   ዕለት  የዕጩዎቹን  ዝርዝር  ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባቀረበበት ወቅት ምርጫው በፈቀዱት መልክ አልሔደላቸውም የተባሉ ጳጳሳት ሙግት ገጥመው መዋላቸውን የደጀ ሰላም ምንጮች ገለፁ።

አምስቱ እጩዎች  መሆን ያለባቸው ብፁዕ  አቡነ  ማትያስ፣  ብፁዕ  አቡነ  ማቴዎስ፣ ብፁዕ  አቡነ   ዮሴፍ፣ ብፁዕ  አቡነ  ሕዝቅኤል እና ብፁዕ  አቡነ  ኤልሳዕ  ናቸው የሚለውን ውሳኔ አስመራጭ ኮሚቴው ካሰማ  በኋላ  አስተያየት የሰጡት እጩ ፓትርያርክ ብፁዕ  አቡነ ማቴዎስ  “በቀደመው የአበው  ገዳማዊ  ሥርዓት  መሠረት  በዕጩነት መግባት  አይገባኝም።  አባቶቼ  ስለ እግዚአብሔር  ብላችሁ እኔን ተዉኝ” ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ ይህንን የትህትና ንግግር  የተመለከቱ አንዳንድ አባቶች “እንዲህ ያለ ትህትና በዚህ ዘመን ማየታችን የሚደንቅ ነው” በማለት ሲናገሩም ተሰምተዋል፡፡ እጩነቱን በአኮቴት እንዲቀበሉ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ግፊት የተደረገባቸው ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በመጨረሻ  የአባቶችን ቃል አድምጠው በዝምታ ተቀብለዋል ተብሏል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሌሎቹ እጩ ፓትርያርኮችም ተመሳሳይ ሐሳብ  ለማንሳት ቢሞክሩም  በቅዱስ  ሲኖዶስ  አባላት  ግፊት  ጉዳዩን ለመቀበል ተገደዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአስመራጭ ኮሚቴው አሠራር፣ ጥቆማና ውሳኔ ትክክል አይደለም በሚል ከረር ያለ ሐሳብ ያሰሙት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና ብፁዕ  አቡነ አብርሃም  በየተራ  ባደረጉት ንግግር በተለይ በብፁዕ  አቡነ  ማትያስ  ለዕጩነት  መቅረብ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደተናገሩት የብፁዕ  አቡነ ማትያስ ዜግነት ጉዳይ ዕልባት ሳያገኝና ነገሩም በሥርዓቱ ሳይጣራ ከዝርዝሩ ውስጥ መግባታቸውን ኮንነዋል። አጠቃላይ የምርጫው ሒደት ትክክል አለመሆኑንም ለማስረዳት ሞክረዋል ተብሏል።

የሁለቱን አባቶች ተቃውሞ ያልተቀበለው ምልዓተ ጉባዔው ይህን ጥያቄ በዚህ ሰዓት ማንሳታቸው ተገቢ አለመሆኑን፣ “ትናንት ምርጫው እንዲካሔድ ስታቻኩሉ የነበራችሁ እናንተ ናችሁ፡፡ ‘ይዋልና ይደር፣ ጉዳዩን በጥሞና እንመልከተው’ ስንላችሁ አይሆንም ብላችሁ አጣደፋችሁት፡፡ አሁን ስምንት መቶ መራጭ መንገድ ከጀመረ በኋላ፣ የውጭ እንግዶች   እየተጠባበቅን ባለንበት ሁኔታ እንዲህ ያለ ግርግር ማንሳት ቤተ ክርስቲያኒቱን  ማዋረድ ነው” የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ተክለ-ስብዕናቸውን በመገንባት፣ የትምህርት ደረጃቸውን ከፍ በማድረግ፣ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን በማስተባበር  የምረጡኝ  ቅስቀሳ ላይ  እንደሰነበቱ ሲነገርባቸው የሰነበተው ብፁዕ  አቡነ ሳሙኤል እና እርሳቸውን ለማስሾም ደፋ ቀና እያሉ ነው፣ የአባቶችን እርቅ አኮላሽተዋል የሚል ወቀሳ የሚሰማባቸው ብፁዕ አቡነ አብርሃም ባለቀ ሰዓት የምርጫው ተቃዋሚ ሆነው መቅረባቸው “የሚያስቡት ለቤተ ክርስቲያኒቱ  ሳይሆን  ለራሳቸው ነው” የሚል አስተያየት እንዳሰጠባቸው ደጀ ሰላማውያን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም 6ኛው ፓትርያርክ ሊሆኑ የሚችሉት ብፁዕ አቡነ ማትያስ ዘኢየሩሳሌም ናቸው የሚለውን ቅድመ ትንበያ ምንጮችን ጠቅሳ ዘገበችው ደጀ ሰላም አረጋዊው አባት ለፓትርያርክነት ቢበቁ ከትህምርትም፣ ከመንፈሳዊነትም፣ ከብስለትም፣ ከልምድም አንጻር የሚበዛባቸው እንደማይሆን ትረዳለች። ዛሬ የተነሣባቸው ተቃውሞም “ይህ ይጎድላቸዋል” ከሚል አንጻር ሳይሆን ከዜግነት ጋር በተገናኘ ነው።

 

በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን የተሐድሶ ቀንደኛ ተከታዮች ከሆኑት ከነ አባ ሰረቀ ጋር ተገናኝቶ የተዘገበባቸውም ሐሰት መሆኑ አረጋዊው አባት የጥቃቱ ሰለባ የሆኑበትን ምክንያት እንድንመረምር ያደርገናል። ደጀ ሰላም ባለፈው ጽሑፏ እንዳለችው ምእመናን ቅዱስ አባታችን ብለው በሙሉ ልብና በፍቅር የሚታዘዙት አባት ይፈልጋሉበርግጥም። ይህንን ለማግኘት ደግሞ በቂም በቀል እና የራስን ደጋፊ በማስሾም ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን የሚበጀውን በመሻት መሆን አለበት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያየን ያለነው ግርግር ግን ቤተ ክህነቱ እና ጥቅመኛ ቡድኖች እንዴት መስመር የለቀቀ መንገድ እየተከሉ መሆኑን የሚያመለክት ነው።

 

ዞሮ ዞሮ የሚሰየመው አባት የቤተ መንግሥቱ ይሁንታ (ኢንዶርስመንት) ያለው፣ ቀድሞ ያለቀ ነገር፣ የተበላ ዕቁብ መሆኑን መዘንጋታቸው ግን ገርሞናል። አሁን ደርሶ ምርጫው ይሸጋገር ማለት ራሳቸው በጀመሩት ጨዋታ መሐል ላይ ደርሶ “ይቋረጥልን” እንደማለት ይሆናል። የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዳይመጣ ተግታችሁ ሰርታችኋል። አንድነቱ ሲቀበር የመጨሻውን ምስማር የመታችሁትን አትርሱት። ተሳክቶላችኋል። ያቺ ያለማችኋትን “ወንበር” ግን ተሸውዳችኋል።

 

በዛሬው ጉባዔ ተቃውሞ በብርቱ የቀረበባቸው አረጋዊው ብፁዕ አቡነ ማትያስ ዘኢየሩሳሌም ጉዳዩን በዝምታ ማለፍ መርጠዋል፡፡ ውይይቱ በዚህ መልኩ  ከተከናወነ በኋላ አምስቱ እጩዎች ጉዳይ የተጠናቀቀ ሲሆን ሰኞ በፊርማ ይቋጫል ተብሏል። ቅ/ሲኖዶሱ ካጸደቀው ዘንዳ የሚቀረው የምርጫውን ሒደት ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ድራማው ይቀጥላል!!!!!

 

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

12 comments:

አክባሪያቸው፣ ግን የማልጠብቀውን ያደረጉ said...

ዞሮ ዞሮ የሚሰየመው አባት የቤተ መንግሥቱ ይሁንታ (ኢንዶርስመንት) ያለው፣ ቀድሞ ያለቀ ነገር፣ የተበላ ዕቁብ መሆኑን መዘንጋታቸው ግን ገርሞናል። አሁን ደርሶ ምርጫው ይሸጋገር ማለት ራሳቸው በጀመሩት ጨዋታ መሐል ላይ ደርሶ “ይቋረጥልን” እንደማለት ይሆናል። የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዳይመጣ ተግታችሁ ሰርታችኋል። አንድነቱ ሲቀበር የመጨሻውን ምስማር የመታችሁትን አትርሱት። ተሳክቶላችኋል። ያቺ ያለማችኋትን “ወንበር” ግን ተሸውዳችኋል።

Anonymous said...

Another Sew Lesew

Anonymous said...

አባት ሆኖ የሚመራ
አባት ሆኖ የሚያሻግር
አባት ሆኖ የሚመግብ
አባት ሆኖ የሚመክር
ባባትነቱ መርቶ የኤርትራን ባህር የሚያሻግር
አባት አጣች እማማ አባት ናፈቃት ሀገሬ
አቃቅማ ያፈራችው የምታፍሰው ያረም ፍሬ (አቃቅማ… እሾክ ነው)
አባት ናፈቃት ኢትዮጵያ አባ አቡነ የምትለው
ልጀ ብሎ ሚሞትላት አባ ብላ የምትጠራው

Anonymous said...

ልቡ የሞተ ወረኛ መንጋ በተሰባሰበበት ሁኔታ አንዳንድ ካህናት ነን የሚሉ ሰዎች የወጣላቸው ተዋንያን ቢሆኑ አያስገርምም እነዚህ ሰዎች ሲያስፈልግ እየተለሳለሱ (ቅን ተብሎ ለመጠቀስና ባአቋራጭ ወደፊት ለመምጣት)፤ ተቃዋሚ እየመሰሉ (የወደቀ ስማቸውን ለማንሳትና ስለላውን ለማደራጀት)፤ ሲፈለጉም ተጃጅለው እያጃጃሉ ከቤተመንግስት የተደረሰውን ድራማ ባለ ቆቦቹ ጥሩ እየተጫወቱት ነው ..ይቀጥላሉም… ደራሲውም ይቀጥላል፡፡ ድራማው ይቀጥላል!!!!!

Anonymous said...

ልቡ የሞተ ወረኛ መንጋ በተሰባሰበበት ሁኔታ አንዳንድ ካህናት ነን የሚሉ ሰዎች የወጣላቸው ተዋንያን ቢሆኑ አያስገርምም እነዚህ ሰዎች ሲያስፈልግ እየተለሳለሱ (ቅን ተብሎ ለመጠቀስና ባአቋራጭ ወደፊት ለመምጣት)፤ ተቃዋሚ እየመሰሉ (የወደቀ ስማቸውን ለማንሳትና ስለላውን ለማደራጀት)፤ ሲፈለጉም ተጃጅለው እያጃጃሉ ከቤተመንግስት የተደረሰውን ድራማ ባለ ቆቦቹ ጥሩ እየተጫወቱት ነው ..ይቀጥላሉም… ደራሲውም ይቀጥላል፡፡

Hailu said...

For God's sake, is this really a spiritual thing what these people are doing?

Oh my beloved Orthodox! I bitterly feel sorry for we have made you a prey to these unholy people in long robes. I deeply feel sorry for we have left you at the mercy of a government led by atheists and menafikans.

No matter how they conduct this so called election, it remains a shame and illegal one. The dirty drama they orchestrate only makes it worse and affirms its ungodliness.
Regarding the top actor that will come out of this drama, they can give it whatever name they want but he will not be a father to us, the Orthodox Tewahido believers. Not even for a second. We rather say “ወለእመ ተራድአ በመኳንንተ ዝንቱ ዓለም፡ወተሠይመ ለቤተ ክርስቲያን እምሃቤሆሙ ይትመተር ወይሰደድ ውእቱኒ ወኩሎሙ እለ ተሳተፍዎ”(ፍ.ነ. ፻፸፭) ማለትም፦ “በመንግስት ድጋፍ የተሰየመ ግለሰብ ጭንጋፍ ነው”። በቦታው እንዲቀመጥ የተባበሩት ሰዎችም ህይወት የሌለውን ህይወት ያለው በማስመሰል የተባበሩ ናቸውና ጭንጋፎች (ምቱራን) ናቸው።

Regardless of this madness, the only legitimate Patriarch of the EOTC remains the 4th Patriarch, His Holiness Abune Merkorios.


Anonymous said...

Dear dejeselam!!!!!
i am confused. no body confused me, only dejeselam. i hope you will post this. i visit dejeselam almost every day for the last 3-4 years. when there was disagreement between the holly synod and when som of the papasat was beaten by some gangsters in their living houses abune samuel was one of the fore runners who was fighting for the best interst of the church and DEJESELAM WAS PRIZING HIM FOR HIS STRONG STAND and dedication, but dejeselam stands againt him. whats wrong? someting smells fishy in here. and dejeselam was prizing abune abraham for his dedication in DC and his stron stand against abune paulos, but know what happen? is this two people stand against the church or some one stand against them? why dejeselam has contradiction in its reports. IF WE ALL ARE SEEKING THE TRUTH, PLEASE POST MY COMMENTS. i love dejeselam, but some of the reports are against each other. ARE WE ALL STANDING FOR THE CHURCH OR ARE CREATING DISAGREMENTS WITH IN THE CHURCH.
GOD WILL DEFEND THE CHURCH NO MATTER WHAT. FORGIVE ME GOD.

Anonymous said...

Hulum kentu new dejeselamin chemro . . . Manin enamin zend gra geban?!

Anonymous said...

ወይኔ ቤተ ክርስቲያን! ወይኔ እናቴ!ወይኔ ማረፊያዬ ዛሬ አነባሁልሽ፡ ከወትሮው ይልቅ ዛሬ ለአንቺም ለራሴም አለቀስኩ። ልጄ ብለሽ ተቀብለሽኝ በጥምቀት ሰማያዊ ሃብትን ሰጥተሽኝ፣ የቃልን ወተት እየመገብሽ አሳድገሽኝ፣ ህብስት ስጋና ደሙን መግበሽኝ ዛሬ የሚሸጡሽኝ እጄን አጣምሬ ተመለከትኩ። እኔም ከሞቱልሽ ቅዱሳን እኩል በፍርድ ፊት እቆማለሁ? ምን እናገር ይሆን? ወዮ ለራሴ...

Anonymous said...

I just want to say that the intention by those who are nominated including Aba Mathias to decline is just nothing,but just part of a very fake and cynical way of doing things. The drama does not make any sense. In other words ,those mominees and members of the Synod ( I am sorry I do not think it is fair to use an adjective of"Holy") playing a highly mischvieous/disgracful/cheap tactic to present themselves as if they are self-less and not power mongers. There is no doubt that they have borrowed this dirty drama from their sister palace of Arta Kilo and the headquartes of the ruling party. No matter they try to pretend and intrigue , things are too late to salvage unless they confess and clean themselves from a very dirty mix betweeen religion and politics!! That is what it is !!

Unknown said...

''ነገር ግን ሰው ሁሉ በተኛበት ጊዜ ጠላት መጣና በስንዴው ውስጥ እንክርዳድ ዘርቶ ሄደ። ስንዴው በቅሎ ባፈራ ጊዜ እንክርዳዱም በዚኣው ወቅት ታየ። ስለዚህ የእርሻው ባለቤት አገልጋዮች ወደ እርሱ ቀርበው'ጌታ ሆይ! በእርሻህ መልካም ዘር ዘርተህ አልነበረምን? ታዲያ እንክርዳዱ ከወዴት መጣ ? አሉት።'እርሱም 'ይህን ያደረገ ጠላት ነው 'አላቸው። አገልጋዮቹም ' ታዲያ ሂደን እንክርዳዱን እንድንነቅለው ትፈልጋለህን?' ኣሉት። እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው ፥ 'አይሆንም ፤ ምክንያቱም እንክርዳዱን ስትነቅሉ ስንዴውን አብራችሁ ትነቅላላችሁ ። ስለዚህ ተዉአቸው እስከ መከር ጊዜ ድረስ ስንዴውም እንክርዳዱም አብረው ይደጉ ፤ በመከር ጊዜ ዐጫጆችን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ንቀሉ፤ በእሳት እንዲቃጠልም በየነዶው እሰሩ ፥ ስንዴውን ግን ሰብስቡና በጎተራ ክተቱ' እላቸዋለሁ።" ማቴ. 13 ፤ 25-30። ይህ የጌታ ቃል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በኛ ዘመን እየተፈፀመ አይደለንም? እንክርዳዱም ስንዴውም አብሮ ተዘርቶ ስለበቀለ ለብዙዎች ስንዴውን ከእንክርዳዱ ለመለየት የተቸገሩበት ጊዜ ነው። የጠመጠመው ሁሉ ቄስ ነውን ? ቆብና አስኬማ ለባሹ ሁሉ ጳጳስ ነውን ? ስንዴውን ከእንክርዳዱ ለይተን የምናውቅበትን ጥበብ እራሱ መንፈስ ቅዱስ እንዲገልጽልን በማኅበርም ባይን በየግላችን እንጠይቀው። አንድ ሃሳብና አንድ ልብ ሳንሆን ''ማኅበረነ ባርክ ወእቀብ በሰላም''ብንል ሊሰማን ስለማይችል በየግላችን እንንገረው። ስንዴውን ከእንክርዳዱ ለይተን ያወቅን ካለን ደግሞ ስንዴያችንን በማኅበር እንጠብቅ !

Anonymous said...

ቴክሳስ፡ ይበል ብለናል !!
አቶ ቦግ-አለ ይበልጥ እንዳይቃጥሉ ፈራሁ።

መ.ዘ./ዲሲ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)