February 20, 2013

የውጪውን ጠላት ለመመከት በቅድሚያ የውስጥ ችግሮቻችንን ማስወገድ ይኖርብናል


ቤተ ክርስቲያን አልተከፈለችምበሚለው መጣጥፍ መነሻነት የተዘጋጀ ….
(ከመልዐከ ብሥራት፣ ቨርጂኒያ/PDF)፦ ጌታቸው ኃይሌ ናቸው ለዚህ ጽሑፌ መነሻ የሆኑኝ። በቅድሚያ ልባዊ ምሥጋናዬና አክብሮቴ ይድረሳቸው፡፡ በዚህ ጽሑፌ የምናገረው በእውነት ለቤተ ክርስቲያን ለሚጨነቁ ምዕመናንና አገልጋዮች ብቻ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ላለፉት ሃያ አንድ ዓመታት በታላቅ ፈተና ውስጥ አልፋለች፡፡ አሁንም እያለፈች ነው፡፡ እግዚአብሔር አይበለውና ምናልባት የከፋው ፈተና ያለው ከፊት ለፊታችን ሳይሆን አይቀርም፡፡ የዚህም ሰበቡ ችግሮቻችንን በቅጡ ካለመረዳታችንና ከቸልተኝነታችን የመጣ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ለመሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ችግሮች በተለይ በውጪው ዓለም ምንና ምን ናቸው?


ችግሮቹ አንድ በአንድ ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ ስለዚህ ነገሮችን በጥሞናና በሰከነ ሁኔታ እንድንመረመር ወቅቱ ያስገድደናል፡፡ በአገራችን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ መክፋት በቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጠረው መከራ እንዳለ ማንም ይረዳዋል፡፡ ይሁንና ግርግር ለሌባ ይመቻልና የፖለቲካው መክፋት መልካም ሁኔታ የፈጠረላቸውና ችግራችን እንዲወሳሰብ ያደረጉ ክፍሎች ካሉም ችግሮቻችንን ከመንስዔው ጀምሮ በጥንቃቄ መመርመር የብልህ አካሄድ ይሆናል፡፡ የጦር መሣሪያ የሚፈበርኩ አገሮች በዓለም ላይ ጦርነት ባይኖር ኖሮ ከስረው ይዘጉ ነበር፡፡ የዓለማችን ፖለቲካ አካሄድ እንደሚያስተምረን ከሆነ ደግሞ መሣሪያ ሻጮቹ ገበያውን ሆነ ብለው እንደሚፈጥሩት ማስረጃ መጥቀስ አያሻም፡፡ አቶ ስዬ አብርሃ በአንድ ወቅትኢህአዴግ ጦርነትን መሥራትም ይችላል ሲሉ እንደተናገሩት የውስጥ ችግሮቻችንን ሆነ ብለው የሚሠሩ ብሎም የሚያባብሱ፣ ግርግሩ ገበያ ያደራላቸው አካላት መኖራውን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

በአጭሩ ለመናገር ዋናውና ልናስወግደው የሚገባን ችግር አለ። ሁላችንም እንስማማበታለን፡፡ ነገር ግን ዋናውን ችግር በሕብረት ሆነን እንዳንመክት ጎዳናውን የሚያወሳስቡ ሌሎች በቅድሚያ ልናስወግዳቸው የሚገቡንን ተጨማሪ ችግሮችም አሉን፡፡ነዚያን በቅድሚያ ማስወገድ ያስፈልገናል፡፡ ከውጪ ያለብንን ጠላት ከውስጥ አንድ ሳንሆን እንጋፈጠው ብንል ውጤቱ የታወቀ ስለሆነ በፊት የውስጡን ችግር እናስወግድ፡፡ የውጪውን ለመቋቋም የተሻለ ዝግጅት የሚኖረን ያን ጊዜ ነው፡፡

በዚህ ከተስማማን ወደፊት እንቀጥልና የቤተ ክርስቲያናችንን ችግሮች በቅድሚያ እንደ/ር ጌታቸው ኃይሌ በድፍረት እንጠቁማቸው፡፡ ከዚያም በግልጽ እንወያይባቸው፡፡ ያለዚያ ለውስጥ ደዌአችን ማርከሻ መድኃኒት ሳንወስድ በሥልጣን ላይ ያለውን አስከፊ አገዛዝ ለመቃወምና እርሱን ለማጥቃት ብቻ ብለን የወያኔን ኃጢአቶች ብቻ መላልሰን ብንናገራቸውውሃን እንቦጭከማድረግ የዘለለ የምናገኘው ጥቅም አይኖርም፡፡ ስለዚህ ወደ ውስጣችንም የመመልከት ድፍረቱ እንዲኖረን እውነታው ያሳስበናል፡፡ በቅድሚያ ራሳችንን እንመርምር!!! በተጨማሪም ዛሬ ያልተዳሰሰው ችግራችን ነገ ያልተጠበቀ ክፉ ችግር (ካንሠር) ማስከተሉ አይቀርም፡፡ ወደድንም ጠላንም በእስከዛሬው ቸልተኝነታችን የተነሣም አንዳንድ የካንሠሩ ምልክቶችም ችግራችን በተንሠራፋባቸው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች መታየት ጀምረዋል፡፡ እርሱን እመለስበታለሁ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ጎልተው ለሚታዩት የቤተ ክርስቲያናችን ችግሮች ምንጩ ወያኔ ብቻ ነው ብሎ ማመን ፍፁም የዋህነት ነው፡፡ ጌታቸው ኃይሌ ነካክተውታል፡፡ ይሁን እንጂ ታሪካዊ ስሕተት የፈጸሙት ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ የውጪ ሲኖዶስ አቋቋመናል ያሉት አምስቱ ጳጳሳት ጭምር ናቸው፡፡ የስደት ሲኖዶስ ማቋቋም ትክክልና ሕጋዊነት እንደሌለው እያወቁ  “ውሻ በቀደደው ዥብ ይገባልእንዲሉ ነገ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ እንዳያስተውሉ የሥልጣን ጉጉት ዓይናቸውን ጋርዶት ወያኔ በቤተ ክርስቲያን ላይ ካደረሰባት በደል የሚከፋውን በደል የፈጸሙት እነሱ ናቸው፡፡ 

እነዚህ ሰዎች ብልሆችና ለቤተ ክርስቲያንና ለቀጣዩ ቅውልድ አርቆ አሳቢዎች ቢሆኑ ኖሮ የጀመሩት ጉዞ ለማንም እንደማይበጅ ተገንዝበውወንበሩ ለኛ ይገባልየሚል መንቻካ ግትርነታቸውን ትተውየከፋፍለህ ግዛአጀንዳን አንግቦ የመጣውን ወያኔን ሕዝቡን አንድ በማድረግ በልጠውት በተገኙ ነበር፡፡ ነገር ግን እልህ የተሞላው የሞኝ ጉዞአቸውና ገታራነታቸው ሳያውቁት የራሱ የወያኔ ዓላማ ተባባሪ አድርጓቸው አረፈ፡፡ አንድ ጥላ ሥር መሰብሰብ የነበረበትን የአንድ ቤተ ክርስቲያን ምዕመን ለሥልጣን ጥማቸው ሲሉ ከፋፈሉት፡፡ የታደለ ወያኔ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መሥራት የነበረበትን የመከፋፈልና የመበጥበጥ አጀንዳውን በብዙ ፐርሰንት አቀለሉለት፤ እናም ደጋግመው ሳያስቡበት፣ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል እንዳለችው እንስሳ በራስ ወዳድነት ያቋቋሙትሲኖዶስምዕመኑን ከመከፋፈልና ከማወናበድ እንዲሁም ለግለሰቦች መጠቀሚያ ከመሆን የዘለለ ሃያ አንድ ዓመት ባስቆጠረው ዕድሜው ለቤተ ክርስቲያንና ለበጎቿ ያስገኘው አንዳችም ፋይዳ የለም::

ሰዎች ብዙ ጊዜ፣ አሁን/ር ጌታቸው በጽሑፋቸው እንደጠቀሱት ስለጎሰኝነት የሚያነሱት ነገር አለ፡፡ ስለ ጎሰኝነት ሲወሳ አንድ ነገር በድፍረት ልናነሣ የግድ ነው፡፡ ጣትን ወደ ወያኔ አቅጣጫ ብቻ መጠቆም አግባብም ሞራላዊም አይደለም፡፡ ሌባንሌባ!!” ብለን በድፍረት ስንሰድብ እኛ ሌቦች መሆን የለብንም፡፡ ያለበለዚያ ሌባው እየሳቀአመድ በዱቄት ይስቃልበማለት በራሳችን ላይ ማላገጡ የማይቀር ነው፡፡ እና ሁል ጊዜ በጎሰኝነት የምንከሰው ወያኔን ብቻ ነው፡፡ ምክንያታችንም ወያኔ ከአንድ ጎሣ (ከትግራይ) የወጣ፣ በደደቢት የተጠነሰሰ ጠባብ የጎጠኞች ቡድን በመሆኑ ነው፡፡ ሲጠነሰስም በስምንት ሰዎች ነበር፡፡ እነዚህስ አምስቱ ሲኖዶስ አቋቋሚዎች፤ ነፍሳቸውን ይማረውና አቡነ ዜና ማርቆስ፣ አቡነ መልከፀዴቅ፣ አቡነ ኤልያስ፣ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ (አቡነ ይሥሐቅ በፊት ተሳስተው አብረዋቸው የነበሩ ቢሆንም ኋላ ግን ነገሩ ሲገባቸው ተለይተዋል) እንዲሁም የቀድሞው ፓትርያርክ ራሳቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፤ የነርሱ ሁኔታስ በምን መነጽር ነው የሚታየው? እነዚህምኮ የመጡት ከአንድ ክፍለ ሐገር ነው፡፡ እንዲያውም ምንጫቸው ከአንድ አውራጃ  ነው፡፡ ጎሰኝነት በኛ ላይ ሲሆን ጌጥ፣ በወያኔ ላይ ሲሆን ግን የሚያስጠላ፣ የሚዘገንን ቁስል የሚሆነው እስከመቼ ነው? ያለው ሰው ትዝ አይለኝም፡፡ ስለዚህ እነዚህም ያው ጎሰኞች ናቸው፡፡ አሁንም ቢሆን ስደተኛ በሚሉት ሲኖዶስ ውስጥ በቅርቡ ከተሾሙት 13 ጳጳሳት ውስጥ ለመልክ ከተቀየጡት የሌላ ጎሣ አባላት በስተቀር ሁሉም ለማለት ይቻላል ያው የአንድ አካባቢ ሰዎች ናቸው፡፡ ዝርዝራቸውን ማውጣት ይቻላል፡፡

ወያኔ የጎሰኝነት መልኩን ለመቀየር (ለማጭበርበር) ራሱ ጠፍጥፎ በሠራው ኢሕአዴግ በተሰኘ ጭምብሉ፤ እነዚህም ሕጋዊው ሲኖዶስ እያሉ በሚጠሩት ጭምብላቸው ውስጥ እየተሸሸጉ ነው የግል ፕሮግራሞቻቸውን የሚያከናውኑት፡፡ ቢዋጥልንም ባይዋጥልንም ሐቁ ይኸው ነው፡፡ ይህን ችግር ዛሬ በለጋነቱ አፍረጥርጠን እንዲስተካከል ካላደረግነው ነገ ከማይስተካከልበት ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ሌላ ችግር ሲፈጥር ሁላችንም ቢያንስ በሕሊና ዳኝነት ተጠያቂ መሆናችን አይቀርም፡፡አይ ሠላም፣ በስምሽ ስንት ግፍ ተሠራእንደተባለው በዳያስፖራው ማኅበረሰብ ውስጥ በኢትዮጵያና (በጋራ ጠላታችን በወያኔ) ስም በቤተ ክርስቲያን ላይ ስንት ዓይነት ጥፋት ደረሰ!!! እና ትግሬም ይሁን አማራ፣ ኦሮሞም ይሁን ጉራጌ ጠባብ አስተሳሰብ አራማጅ ከሆነ ጎሰናና ጎጠኛ ነው፡፡

ስለዚህ በወያኔ የተኮነነ ጣልቃ ገብነት ላይ ተቃውሞዬ እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን የነዚህ ሊቃነ ጳጳሳት በስማችን እየነገዱ አላስፈላጊ የሆነ ሲኖዶስ ማቋቋማቸው ከኩነኔም ኩነኔ እርሱ ነው፡፡ ይህ ድርጊታቸው በወያኔ ተነጠቅን በሚሉት ሥልጣን በኩርፊያ ተነሳስተው በግል ደረጃ ያደረጉት የሞት ሽረት ትንንቅ እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ሕልውና አስፈላጊ ስለሆነ የወሰዱት ርምጃ አለመሆኑ በሁላችንም ዘንድ በደንብ መታወቅ አለበት፡፡ ይህም እውነታ ባለፉት የሃያ አንድ የመከራ ዓመታት ውስጥ ሲኖዶሱ አንድም ጥቅም አለመስጠቱን በሚገባ አረጋግጦልናል፡፡ ከነሱ ጦሰኛ ሲኖዶስ መመሥረት ለቤተ ክርስቲያን የተረፋት ነገር ቢኖር ዋናውን የጋራ ጠላት አስቀምጦ እርስ በርስ መከፋፈል፣ የወንድማማቾች ጠብና ክርክር፣ ስድድብና መወጋገዝ ብቻ ነው፡፡ አጋጣሚው በከፈተላቸው ዕድልም የሃይማኖት ተቃማዊዎቻችን በጥሩ ሁኔታ እንደተጠቀሙብን ሌላው የማንክደው ሐቅ ነው፡፡

ጌታቸው ኃይሌ ከተናገሩት ውስጥበሀገሪቱ ላይ የዘሩትን ጎሰኝነት ዘረኝነት ከማታውቀው ቤተ ክርስቲያን አስገቡትሲሉ ያስቀመጡት አባባል ሐቀኝነቱ እንዳለ ሆኖ ነገር ግን ለዚህ ችግርም መከሰት ተጠያቂው ጎሰኛው የወያኔ መንግሥት ብቻ አለመሆኑን በቅጡ መመልከት ያስፈልጋል፡፡ ይህን ለመመልከት እስቲ ከወያኔ መምጣት በፊት የነበረውን የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለአንድ አፍታ ወደ ኋላ ተመልሰን እንዳስሰው፡፡ የቀድሞው ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሥልጣን ላይ የቆዩበትን ጊዜ ማለቴ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ወያኔ ያደረገውን የቤተ ክርስቲያን ጣልቃ ገብነት ደርግም ሲፈጽመው የቆየ ባሕል መሆኑን ልብ ማለትስፈልጋል፡፡ ብዙ ሰዎች ይህ ዓይነቱ ተግባር የወያኔ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ በቀጥታ፣ ደርግ ደግሞ እንደ ወያኔ በሥውር በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ጣልቃ ይገቡ ነበር፡፡

ወያኔዎች ልክ አቡነ ጳውሎስን በመንበሩ ላይ በጉልበት እንደሰየሙ ሁሉ አቡነ መርቆሬዎስንም በሥልጣን እንዲቀመጡ ያደረጉት ደርጎች ነበሩ፡፡ እንዲያውም ለሹመት ያቀረባቸው (ኢንዶርስ ያደረጋቸው) በወቅቱ የጎንደር ፈላጭ ቆራጭ የነበረው የመንግሥቱ ቀኝ እጅ መላኩ ተፈራ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ከአቡነ መርቆሬዎስ በፊት የነበሩት ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ /ሃይማኖት ባረፉ ጊዜ ይነገር የነበረ አንድ ቀልድ ነበር፡፡ ደርጎቹ መንበረ ሥላጣኑን የሚሰጡት ታማኝ መነኩሴ (ጳጳስ) ሲያፈላልጉ በነበረ ጊዜ መንግሥቱ /ማርያም ተናገረ የተባለው ቀልድ ነው ቀልዱ፡፡እገሌ አይሆንም ጠማማ ነው” “እገሌ መሐይም ነው እገሌም እንዲህ ነው”  ወዘተ.. እየተባለ ከጳጳስ ጳጳስ ሲመረጥ በነበረ ጊዜታማኝጳጳስ ፍለጋው ጊዜ ስለወሰደ ነው አሉ፤ አጅሬበቃ እንግዲህ እንደፈረደብኝ እኔው ደርቤ እሰራዋለሁአለ ይባላል ፓትሪያርክነቱን…..። 

ወደ ርዕሰ ጉዳዩ እንመለስና በየወቅቱ የነበሩ የኢትዮጵያ መንግሥታት ቤተ ክርስቲያንን መቆጣጠራቸው የታወቀ ልምምድ ሲሆን እንኳን ወያኔ በጉልበቱ (በአፈ ሙዝ) በሥልጣን ኮርቻ ላይ የተወዘፈው መንግሥት ይቅርና ሌላውም ቢሆን ቤተ ክርስቲያንን መቆጣጠር ግድ የሚሆንበት ምክንያት ቤተ ክርስቲያንን እንደ ልቧ ለቅቆ እንደ መንግሥት መቆም  እንደማይችል ስለሚታወቅ ነው፡፡

ስለዚህ በአገራችን የመንግሥት በቤተ ክርስቲያንን ጣልቃ መግባት ወያኔ የጀመረው አዲስ ፈሊጥ አይደለም ለማለት ነው፡፡ ይህን ደግሞ ከኛ ከምዕመናን የበለጠ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች አሳምረው የሚያውቁት ሕያው ታሪካችን ሲሆን ይህንን ዓይነቱን ግዙፍ ሐቅ ወደጎን ትቶ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና ውጪ ሌላ ሲኖዶስ ማቋቋማቸው ጊዜ በሰጠው ጉልበተኛ የተነጠቁትን ሥልጣናቸውን በግላቸው መልሶ በእጅ ለማድረግ በዳረጉት መፍጨርጨር እንጂ እውነት መንበሩ ከኢትዮጵያ ለመሰደድ የሚያበቃው ችግር ስለደረሰ አይደለም፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ነገር ግን ለዚህ የሥልጣን ትግላቸው (ሽኩቻቸው) ፍጆታ ያደረጉት ቤተ ክርስቲያኒቱንና እኛኑ ምዕመናንን መሆኑ ነው፡፡
 
የጳጳሳቱ አንደበት ለምዕመናን ጆሮ በጣም ቅርብ ስለሆነፓትሪያርክ እያለ ፓትሪያርክ ተሾመሕግ ፈረሰ!!” ስላሉ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ውስጡን (ሐቁን) ያላወቁ ምዕመናን እውነት ነው ብለው ተቀበሏቸው፡፡ የአይሁድ ጳጳሳትም ክርስቶስን በሰቀሉት ጊዜ የምዕመናንን ቀልብ የሳቡትኢየሱስ የሙሴን ሕግ ሽሯልበማለት ነበር፡፡ ከዚህ ሌላ ደግሞ መታወስ ያለበት ሌላ አንኳር ጉዳይ አለ፡፡ ጌታቸው ኃይሌ  “ጎሰኝነትን ከማታውቀው ቤተ ክርስቲያን ዘረኝነትን ያስገቡወያኔዎች ናቸው ይላሉ፡፡ እኔ ደግሞ ልክ ነዎት ወያኔዎች የተባለውን ፈጽመዋል። ነገር ግን ይህን ዓይነት አስነዋሪ ሥራ የሠሩ እነርሱ ብቻ አይደሉም እላቸዋለሁ፡፡ ምንም እንኳን ወያኔ በቤተ ክርስቲያን ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ ከመጠን ያለፈ ቢሆንና የብፁዕ አቡነ ጳውሎስ አስተዳደር በጎሠኝነትና በሙስና የተጨመላለቀ ቢሆንም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ሰፍኖ የነበረው ቅጥ ያጣ የጎሰኝነት አስተዳደር፤  ታሪክ ፈጽሞ ሊረሣው የማይችል የታሪካችን መጥፎ ጠባሳ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ መጥፎና የተበላሸ አስተዳደር በብዙዎች ዘንድ እጅግ ከፍ ያለ ብሶትና ቁጭት አከማችቶ የነበረና አሁን ያለፈ ታሪክ ስለሆነ ብቻ ቸል ተብሎ ሊታይ የማይችል ሥቃዩ አሁን ድረስ ያልሻረ ችግር እንደሆነም መረዳት ይገባል፡፡ አሁን ድረስ ቤተ ክርስቲያኒቱን እየለበለባት ያለው የዚያን ጊዜው የኮመጠጠ እርሾ ነው፡፡ እነዚያው ሰዎች ናቸው ይኸው ዛሬም መንበሩ ተሰድዷል እያሉ የበደል በደል የሚሠሩት፡፡

አቡነ ጳውሎስ ሲከሰሱባቸው ከነበሩ ችግሮች ዋነኛው ጎሰኝነትን በቤተ ክህነት ውስጥ አስፋፍተዋል፣ ከርሳቸው ጀምሮ እስከ ዘበኛ ድረስ ትግሬ ብቻ እንዲሰገሰግ አድርገዋል፡፡ በየአድባራቱና በዋና ዋና መንፈሣዊ የሥራ ኃላፊነት ቦታዎች የሚያስቀምጡት እነዚያኑ ያገር ተወላጆቻቸውን ብቻ ነው የሚል ነው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ መንግሥት የንፁሐን ዜጎችን ደም ሲያፈስ በዝምታ ተመልክተዋል፣ በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በመሣሪያ ሰው ገድለዋል/አስገድለዋል፣ ታጣቂ ናቸው፣ በቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሙጢኝ ብለው የተጠለሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለፀጥታ ወታደሮች አሳልፈው ሰጥተዋልወዘተየሚሉት ከብዙዎቹ  ከሚሠነዘሩባቸው ክሶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

የቅርብ ጊዜ ታሪካችን እንደሚያስረዳው ከሆነም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስም ፍፁም ተመሳሳይ የሆነ ክስ ይሠነዘርባቸው ነበር፡፡ በዘመናቸው ከራሳቸው ከፓትሪያርኩ ጀምሮ እስከ ታች ድረስ በቤተ ክህነት ዙሪያና በሌሎችም የኃላፊነት ቦታዎች የመቀጠር ዕድል የነበረው ጎንደሬ ብቻ ነበር፡፡ እንዲያውም የርሳቸው የበለጠ የጠበበ ሲሆን ከመላው ጎንደር እንኳ ቅድሚያ የሚሰጠው ፋርጣ ለሚመጣው ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እንደ አቡነ ጳውሎስ ሁሉ በርሳቸውም ላይ ይሰነዘሩባቸው ከነበሩት ክሶች ውስጥ ደግሞ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን እንይ፡፡

ፓትሪያርኩ ኢሕዲሪሸንጎ ላይ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ባሉ ቁጥርኢሠፓው መጣ!” ይባሉ ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምዕመናንን ለማሳለም መስቀል አወጣሁ ብለው ኮልቱን መዘዙት ይባሉ ነበር፡፡ መላኩ ተፈራ ያን ሁሉ ወጣት ሲጨፈጭፍ (እርሳቸው በወቅቱ የጎንደር ሊቀ ጳጳስ ነበሩ) ያገር ሽማግሌዎች ተሰብስበውአባታችን ምነው ይህ ሁሉ ደም ሲፈስ ዝም ብለው ይመለከታሉ?” ተብለው ተጠይቀው ጭራሹን  “የሊቀ መላኩ ሠይፍ እንዳይበላችሁ አርፋችሁ ብትቀመጡ ይሻላል!!” ብለው  ሽማግሌዎቹን አስፈራርተዋል ተብሎ ይታሙ ነበር፡፡ ሊቀ መልዐክ የተባለው መላኩ ተፈራ መሆኑ ነው፡፡

እንግዲህ ይህ ሁኔታ ወለል አድርጎ የሚያሳየን ነገር  በአቡነ መርቆሪዎስም አስተዳደር ዘመን ጎሰኝነቱና የሙስናው ደረጃ በሕብረተ ሰቡ መካከል በተለይም በቤተ ክህነት አካባቢ ፈጥሮት የነበረው እጅግ የመረረ ብሶት ልክ አሁን በአቡነ ጳውሎስ ዘመን እንደነበረው ተመሳሳይ እንደነበረ ነው፡፡ ስለዚህ ወያኔ አቡነ ጳውሎስን በሥልጣን ማስቀመጡ የማይታበል ሐቅ ቢሆንም ደርግ ተወግዶ ሕዝቡ የመናገርና የመሰብሰብ ነፃነት ባገኘ ጊዜ በቤተ ክህነት ውስጥ ተቀስቅሶ የነበረው አመፅ ከዚያ ታምቆ ከነበረው ቁጭትና ብሶት የተወለደ እንጂ ወያኔ ወገቡን አስሮ ያስተባበረው የለውጥ እንቅስቃሴ አልነበረም፡፡ ሁኔታው ራሱ በስሎ ጊዜውን ሲጠብቅ የነበረ ስለነበር ነገሩ እግዚአብሔር በፈቀደ ጊዜ ሲፈነዳ በአቡነ መርቆሬዎስና በአስተዳደራቸው ላይ የተቀሰቀሰው ከፍተኛ አመጽ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው እንዲለቁ አስገድዷቸዋል፡፡ ማስረጃም አለ፡፡

በነገራችን ላይከአቡነ መርቆሬዎስ ጋር ለመሥራት እንቸገራለንብሎ እግሩ እንደገባ ለቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ የፃፈና በጫካ ሲያፈስ የነበረው ደምና ያገኘውየጦርነት ድልያሰከረው፣ የአገሪቱን ሥልጣን በአፈሙዝ ተቆጣጥሮ የመጣው የሽፍታ ቡድን በፊት ለፊት (በደረቅ አማርኛ) “ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል አይደለችም!! በኃይል፣ በቅኝ የተያዘች ሉዐላዊት አገር ናትእያለ በከፍተኛ እብሪት ሲደነፋ የነበረው ወያኔ አቡነ መርቆሬዎስን ከሥልጣን ለማባረር ሲል በቤተ ክህነት ውስጥ በካህናት አማካኝነት አመጽ አስተባብሮ በድብቅ ቲያትር የሚሠራበት ምክንያቱም በዚያ ሰዓት ደግሞ ጊዜውም አልነበረውም፡፡ በዚያ ሰዓት የወያኔ ቋንቋ ሁሉዘራፍ!” “ውረድ እንውረድ!”መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ!” “ነፍጠኛ አማራ፤ በመሳሰሉት የዕብሪት አነጋገሮች የተሞላ እንደነበር የሚያስታውስ ሁሉ አቡነ መርቆሬዎስን ከሥልጣን ለማውረድ ከዚህ የተለየ መንገድ (ለምሣሌ ሥውር ቲያትር ምናምን) ይጠቀማል ብሎ አያምንም፡፡ ወደድንም ጠላንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለፈነዳው አብዮት እርሾውም መርዙም በወቅቱ የነበረው የተበላሸው የአቡነ መርቆሬዎስ አስተዳደር ያስቀሰቀሰው አመጽ ነበር፡፡ ሕዝቡ፣ በተለይም ካህናቱ ታፍነው ስለነበር በአገሪቱ ነፍሶ የነበረው የለውጥ አየር በውስጣቸው የታመቀውን የቁጭትና የብሶት ስሜት አገነፈለው፡፡ በቃ እውነተኛ ታሪኩ ይኸው ብቻ ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያናችን እውነተኛ መፍትሔ የምንፈልግ ከሆነ ሳንፈራ ልንነጋገርባቸው ከሚገቡን ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ይህ የታሪካችን ክፍል ነው፡፡ የወያኔን ኃጢአት ብቻውን መዘርዘር ፋይዳ የለውም፡፡ በአጠቃላይ አቡነ መርቆሬዎስን ከሥልጣን ለማባረር ከአጀንዳዎቹ አንዱ ቢሆንም ወያኔ ግን አዲስ አበባ ገብቶ ይህን በተግባር ለማዋል ከመንቀሳቀሱ በፊት አብዮቱ ራሱን በራሱ አቀጣጥሎት ነበር፡፡ እነ መለስ ዜናዊ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ጥይት አላባከኑም፡፡

አቡነ መርቆሬዎስም ይህን የሕዝቡን ስሜት በሚገባ ከተረዱት በኋላ የርሳቸው ነገር ያበቃለት መሆኑን ከልባቸው ስላመኑበት ቀሪ ዘመናቸውን በንስሐ፣ በአታቸውን ዘግተው ለመኖር በመወሰን በጤና መታወክ የተሳበበ መልቀቂያቸውን ጽፈው ለሲኖዶሱ አቀረቡ፡፡ እርግጥ ነው፤ እርሳቸው ሲወገዱ ወንበራቸውን እናገኛለን ብለው ለቅዱስ ሲኖዶሱ መልቀቂያ እንዲያቀርቡ ያግባቡአቸው የነበሩ የራሳቸው የቅርብ ሰዎች እነ አቡነ ዜና ማርቆስ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ እርሳቸውና ሌሎች ከታች ሆነው ወንበራቸውን ሲጎመጁ የነበሩት ሊቃነ ጳጳሳት መልቀቂያቸውን (በጤና ምክንያት ለመሰናበት የቤተ ክርስቲያን ቀኖና እንደሚፈቅድ ስለሚያውቁ በመከሩአቸው መሠረት ያጻፉአቸውን መልቀቂያ) ከመቅጽበት ተቀብለው  ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው አሰናበቷቸው፡፡ ድርጊቱ ግን በኋላ በወያኔ ተሳበበ፡፡ ሌላው በጣም የሚገርመው ነገር እነ አቡነ ዜና ማርቆስ ወንበሩን እንረከባለን ብለው እርግጠኞች ስለነበሩ ለአሥር ወራት ያህል መንበር ጠባቂ ሁነው ሲሠሩ ፓትሪያርኩ በጉልበት፣ በሕገ ወጥ መንገድ ተነሱብለው አንዲት ተቃውሞ አለማንሳታቸው ነው፡፡ ነገር ግን ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ጠብቀው በምርጫው ተሣትፈው ሲያበቁ ውጤቱ ያልጠበቁት ሲሆን ጊዜ አቡነ ጳውሎስንይደልዎ! (ሹመት ያዳብር) ብለው መርቀውከአገር ከወጡ በኋላ (አቡነ መርቆሬዎስ ሥልጣን ከለቀቁ ከአንድ ዓመት በኋላ መሆኑ ነው) የሕግ ጥያቄ አነሱ፡፡ፓትሪያርክ እለ ፓትሪያርክ ተሾመ!!” አሉ፡፡

የስደት ሲኖዶስ አቋቋሚዎቹ ሊቃነ ጳጳሳት ከዚህ በኋላ ፓትሪያርኩ የሌሉበትሲኖዶስ ተሰዷልለማለት ስላልቻሉ በዚህም በዚያም ብለው በተንኮል የፈነቀሏቸውን ፓትሪያርክ እንደምንም ብለው በኬንያ በኩል እንዲወጡና እንዲቀላቀሏቸው አደረጉ፡፡ ይሁን እንጂ ፓትሪያርኩን ከአገር ማስወጣት የተከፈለው መሥዋዕትነት ቀላል አልነበረም፤ ፕሮጄክቱ ከአንድ ዓመት በላይ ወስዶባቸዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ወደ ገዳማቸው ሊገቡና በንስሐ ሊታጠቡ ቆርጠው የነበሩት የቀድሞው ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ታሪክ ይቅር የማይላቸውን ታላቁን ስሕተት ፈጸሙ፡፡ ሁሌ በሰው እንደሚመሩ ይታሙ የነበሩት ሰው ይኸውና እስከዛሬ ድረስ የነ አባ ሀብተማርያም መጫወቻ ሆነው ቀሩ፡፡  ታዲያ እነ አባ ሀብተ ማርያም (አቡነ መልከ ዴቅ) አሁን  ድረስጳጳሱ ሕይወታቸውን ለማትረፍ ብለው በድብቅ ከአገር ተሰደዱሲሉ ይተርካሉ፡፡ ባይንቁን ኖሮ ግን ኮብራቸውን እያስነዱ ከአጃቢዎቻቸው ጋር የጠረፍ ወታደሮችን የይለፍ ሠላምታ እየተቀበሉ በሰላም የወጡትን ፓትሪያርክ እንደ አይጥ ሰው ሳያያቸው ወጡ እያሉ ለማውራት ባልደፈሩ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ኃጢአታቸውን ለመሸፈን የተጠቀሙበት ዘዴ እንደሆነ ግን ማንም በቀላሉ ያስተውለዋል፡፡ ከድሮ ጀምሮ አሁን ድረስ የዚህ ሁሉ ኢንጂነር አቡነ መልከ ዴቅና አቡነ ዜና ማርቆስ አንድም ቀን ነገሩን በሠላም ለመፍታትና የተሻለ ነገር ለመፍጠር ፍላጎት አሳይተው አያውቁም፡፡ ከዚህ ጋር አባሪ የተደረጉትን ለጊዜው ይጠቅማሉ ያልኩአቸው ሰነዶች እውነቱን ለመገንዘብ ስለሚረዱ ትመለከቱአቸው ዘንድ እጋብዛለሁ፡፡
 
እነዚህ ሊቃነ ጳጳሳት ይህን ሁሉ ያደረጉትና እደረጉ ያሉት ቀድሞውንም ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመታደግ ሳይሆን ተቀማን ያሉትን ሥልጣን የሚያስመልሱ ስለመሰላቸው ነበር፡፡ ታዲያ ለነሱ የሥልጣል ሽሚያ ምዕመኑን ያስከፈሉት ዋጋ እጅግ በጣም ውድ ሆነ፡፡ እነሆ አነርሱ በቀደዱት ቀዳዳ በመሹለክ በሆነ አገር የሚገኝ አንድ ቤተ ክርስቲያን ምናልባት ወያኔ የወደቀ እንደሆን ተብሎ ወደፊት የሚቋቋመው የትግሬ አፈንጋጭ ሲኖዶስ አካል ለማድረግ ካሁኑ ዝግጅቱን አጠናቋል ይባላል፡፡ በዚህ የተነሣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከቅዱስ ሲኖዶስ የአስተዳደር መዋቅር ነጥሎየትግራይ ኮሚኒቲተብሎ የሚታወቅ የትግሬዎች ማኅበር የግል ንብረት አድርጎአታል፡፡ እንግዲህ ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል ማለት እንደዚህ ነው፡፡ 

ስለዚህ እነዚህ አምስት ሰዎች ራሳቸው የከፈቷትን ቀዳዳ ራሳቸው የሚደፍኑበትን ሥራ ቀኑ ሳይመሽ የማፈላለግና የመጠገን ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ይህን እንዲያደርጉ የሚያስገድዳቸው ደግሞ የኛ የምዕመናን ግፊት ብቻ ነው፡፡  ያለበለዚያ ዕድሜ ልካቸውን ከታሪክና ከሕዝብ ለመታረቅ ያስቸግራቸዋል፡፡ ከሁሉም በፊት ግን ኃላፊነቱ የምዕመናን ነው፡፡ በስሕተት ጎዳና መመራታችንን ተረድተንየሕጻናትን ልብ ለዐዋቂዎች፣ የዐዋቂዎችን ልብ ለሕፃናት እሰጣለሁተብሎ በመጻፉ እነርሱ ሊያደርጉ የሚገባቸውን ካላደረጉ ሊደረግ የሚገባውን ነገር ለማድረግ መነሣት አለብን፡፡ በዜሮ ውጤት የተደመረው ያለፈው ዘመን ታሪካችን ከዚህ በላይ ጥፋት ሳያደርስ ይብቃ! እነርሱ እንደሆነ መንበሩ ለነሱ ካልተመለሰ በስተቀር አንድም ጊዜ የዕርቅ ፍላጎት አሳይተው አያውቁም፡፡ አሁንም የላቸውም፡፡ የዋኆች ምዕመናን ግን እርቅ ይመጣል ብለው ተስፋ ሲያደርጉ ኖሩ፡፡ እኛ ካልገፋናቸው እርቁ በራሳቸው አነሳሽነት ይመጣል ብለን እንደ ኅብስተ መና ብናንጋጥጥ እግዚአብሔርም ታሪክም ልጆቻችንም ይወቅሱናልና ሁሉም የተዋሕዶ ልጅ ከልቡ ያስብበት ዘንድ አደራ እያልኩ ለጊዜው እሰናበታለሁ፡፡ 

እግዚአብሔር ይታረቀን። አሜን።

ማሳሰቢያ ስለ አባሪ ሰነዶች

ሦስት የተለያዩ ሰነዶች አባሪ ሆነዋል፡፡ ከነዚህ ግን ሦስተኛው አባሪ (ቃለ ጉባዔ አሥራ አንድ ገጾች ሲኖሩት ከገጽ 2 – 8 ድረስ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት የሌላቸው ሲኖዶሱ በሌሎች ርዕሶች ላይ የተነጋገረባቸው ስለሆኑ ሁሉንም ማያያዝ አላስፈለገም፡፡ ስለዚህ ገጽ 1 እና 9 -1 1 ያሉት አራት ገጾች ብቻ መያያዛቸው አንባቢ ይረዳልኝ ዘንድ ምኞቴ ነው።
53 comments:

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይስጣችሁ ይህ ታሪክ ከሁለት ቀን በፊት ቋጠሮ ላይ ወጥቶ አንብቤው ለአንድ ጓደኛዬ ነግሬው እርሱ ሊያነብ ሲገባ ጽሁፉ ተነስቶአል በታም ገረመኝ ሰዎች ለምን እውነትን ይፈራሉ ጽሁፉ እውነተኛ ታሪክ ነው እንደውም የሚቀረው አለ በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ሰው ተገደለ ተብሎ እንደመጀመሪያ ይነገራል ነገር ግን በመጀመሪያ በአቡነ መርቆሪዎስ ጊዜ ነው ቤተክህነት ጊቢ ውስጥ ሰው የተገደለው እና ታሪኩ ትክክለኛ ስለሆነ ብዙ ሰዎችን ሊጎራብጣቸው ይችላል ጸሃፊው ግን ቃለ ህይወት ያሰማልን እያልኩ የቋጠሮ ዌብ ሳይት አዘጋጆች ግን እውነትን አትሸሽጉ ለግለሰብ ሳይሆን ለህዝብ ስሩ ዋዋዋዋዋ

Anonymous said...

ይህ ጽሁፍ ለእኔ እስከ ዛሬ በወሬ ደረጃ ብቻ ሲባሉና መረጃ ያልደገፋቸው ከነበሩ ሁሉ በጣም ጠቃሚና በታሪካዊ ጠቃአሚነቱም በጣም ከፍ ያለ ነው። ለጸሐፈው እግዚአብሔር ዕድሜ ይስጥልን መማለትን ወደድኩ።
አንድ ነገር ግን እዚህ ላይ ማለትን እወዳለ፤ 1ኛ - ለምን ይህንን ለመጻፍ 21 ዓመት ፈጀ?
2ኛ - መረጃዎቹም ለምእመናን አይን እስኪበቁ ለምን ይህን ያህል ዘመን አስፈለጋቸው?

ለምን ተዘገየ? ለምን? ለምን? ለምን አሁን?

Anonymous said...

መልዐከ ብሥራት ጥሩ እይታ ነው።
ሁላችንም እንዲህ ዓይናችን ከፍተን የምናየው መቼ ይሆን።
ይህ ችግር በመላው ዓለም ያለን ምዕመናን ልናውቀው የሚገባ ነው።
ደጀ ሰላሞች ኢትዮ ሚድያ ላይ ወጥቶ ብዙ ሰው ሳያነበው ነበር ያነሱት። እንኳንም አስነበባችሁን። ተባረኩ።

Anonymous said...

Melekam tsehafi mesleh yebaetekresiteyan lijochin lemawonabed silehone tasazihaleh. Ante erasin eko zeregneteh kulechi belo betsehufeh yitayal. Yesewen gudef yemitelekem ante maneh?

Anonymous said...

Melekam tsehafi mesleh yebaetekresiteyan lijochin lemawonabed silehone tasazihaleh. Ante erasin eko zeregneteh kulechi belo betsehufeh yitayal. Yesewen gudef yemitelekem ante maneh?

Anonymous said...

ስራፈት ቤክ በጭንቅ ውስጥ ሆና ወዳጄ ያሌለን ጠላት ላጥቃ ዪላሉ፥፥ ይህንን ሁሉ መነባንብ ሰው ለመውቀስ ከሚያባክኑት ዋናውን ጉዳይ ቢያብራሩበት ይሻል ነበር፥፥

Anonymous said...

I have read this on Ethiomedia and then it was removed. That is the kind of censorship that the "free" media is fighting against. Anyways, it is good to get both sides of the story and to let the facts speak for themselves. Please post more documents regarding what hapenned in the early 90s.

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች ይህ ምን ይጠቅማል ብላችሁ እዳወጣችሁት እግዜር ያውቃል። በጣም የሚያሳዝነው ግን ደጀሰላምም ሳታውቀው ይሁን አውቃ በውጭ ላሉትን አባቶች ለማደከም ያታለመ ጽሑፍ ነው። የኢትዮጵያውያውን አፍራሽ ኃይል መሸነፍ ስለመንችል ስደተኞቹን እንምታ በማለት የታቀደ ነው። ገና ብዙ ይጠበቃል፤ ደጀ ሰላምም የሰላምና አንድነት ክህነቷን መደብተር መጀመሯን በዚህ ጽሁፍ መስተንግዶ መረዳት ይቻላል።
የመጀመርያው አስተያየት ሰጭ ቤተ ክህነት ውስጥ የሞተውን ሰው ታሪክ በአባ መርቆርዮስ ጊዜ ነው የሞተው በመለት በቤተ ክርስቲያን መድረክ አባ ጳውሎስን በመቃወም ከሞተው ሰማዕት ጋር ለማነጻጸር በመሞከሩ ተገርሜአለሁ።
ምናለ የሚመሳሰል ነገር ብንናገር እጆቻችም ነገ በሞት ይታሰራሉa ለምን በሚገባ የማናውቀውን ታሪክ እንናገራለን።
ነአኩቶ ለአብ
ከላስታ ላሊበላ፤

Anonymous said...

ኢትዮ :ሚዲያዎች: በጣም: ታሳፍራላችሁ:: በመጀመሪያ :እንደዚህ: ከፈራችሁ: ጽሁፍ: መርጣችሁ :ተቀበሉ:: በራስ: አለመተማመን: ለምን: አስፈለጋችሁ? የጻፋችሁትን: ጽሁፍ: በፍጥነት: ማንሳታችሁ: ትዝብት: ላይ: ጥሏችኋል:: እድሜ: ለደጀ: ሰላም: በተረፈ: ይህ :ሁሉ: ጥፋት: ሲጠፋ: ለምን: ዝም: እንዳሉ: ጸሃፊው: አልገባኝም:: ይህንን: ጉዳጉድ: ይዘው: ነው:: አካኪ: ዘራፍ :አገር: ይያዝ :ቀኖና: ፈረሰ:: ቀኖና: ተጣሰ:: የሚሉት: ጅብ: በሰው: ሀገር: ሄዶ: ቁርበት: አንጥፉልኝ: ይላል: ማለት: ይህንን: ነው:: ወይ: ስደተኛ :ሲኖዶስ: ሃሰተኛው: ሲኖዶስ: ቢባል: ይሻላል:: ወይ :ግሩም: አያሰኝም??????????????????????????

john said...

This could be true. But that doesn't mean it will give legitimacy for the spiritual fathers in Addis to do the same or worse right now and also for the government to create a turmoil inside the church . We should n't accept it as a norm.

Honestly as a human being, who is absolutely pure from making sin every second of his/her life? Especially when someone is in a higher position and challenged by internal interest and external influences. Just think of the prophet Moses for a second, how he was challenged when he was asked by the people to give them water.Therefore I would say this could be true.I see three points/claims/ on the 4th Pope in this article. 1.He kept quite during the time of massacre in the region of Gonder
2. He permitted(started)the spread of ethnic activities in the church during his leadership as a pope. 3. He established(involved himself) in the formation of an exile Synod.

Now the most important question is what is the solution?
I think the solutions are,
1. assume he did all those things and it is true, what will be wrong if he could acknowledge it and ask excuse.Nothing. I think he would get the blessing in the face of God, he would be able to see the unity of the church while he is alive and will be remembered for the generation as the father of confession/humbleness/.Or, assume he didn't do any of the above claims and he is clean, but still acknowledges and asks excuse.What would be wrong? Again nothing! But this time he would get even more blessing from God and would push forward the unity of the church for ever.
2.What would be wrong if all other fathers of the church in exile Synod do the same spiritual activity as mentioned in number 1. I would say they would get the same blessings from God and put a united and strong church that can defend itself for the generations to come .
3.What would be wrong if the spiritual fathers in Addis put aside their personal interest,defend the truth and resist the influence of the government with passion and spiritual commitment,give priority to the unity of the church, protect the church (instead of destroying).
Again they would benefit themselves and the christian people at large.
4. Finally,I think it is the responsibility of the christian people to protect as well as unit the church, as that is what God would like to see from us.
To protect the church we all have to win ourselves fist.

Anonymous said...

God Bless you brother,
thank you dejeselam for posting.

Anonymous said...

ዝንጀሮ የመቀመጫዋን ጠባሣ በመስታወት ዐይታ "ይህቺ ደግሞ አስቀያሚ ፍጡር ማናት!" ብላ ሣቀች ይባላል። እናም የዚህ በማር የተለወሠ ጽሑፍ አቅራቢ ልክ እንደዚያች በራሷ መቀመጫ ጠባሣ እንደተዘባበተችው ፍጡር ሆኖ ታየኝ። እንዲያው አንዳንድ ሰው በተለያዩ ምክንያቶች ʻየቤተክርስቲያኒቱ ምሥጢራዊ ሠነዶች በእጄ ገቡʼ ብሎ የማይሆን ነገር መጻፍ ትርፉ ቅሌት ብቻ ነው።

Kebede Bogale said...

በጣም የሚያሳዝንና የሚያብሳጭ አፍራሽ ጽሑፍ ነው። በሐሰትም የተሞላ ነው። ብፁዕ ወቅድዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሻለቃ መላኩ ጎንደር ከተማ ወጣቱን ሲጨፈጭፍ በነበረበት ጊዜ የጎንደር ሀገረ ስብከት ጳጳስ አልነበሩም። ጳጳስ ሁነው የተሾሙት ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም ነው። የመጀመርያ ሀገረ ስብከታቸው ጎዴ ነበር። በ1972 ዓ.ም ነበር ሀገረ ስብከታቸው ጎንደር የሆነው። ቀይ ሽብር የቆመው ደግሞ በ1971 ነው። ኢሠፓኮ ከተቋቋመ በሁዋላ ቀይ ሽብር ቁም ነበር። እውነቱ ይህ ነው። ከሁሉም የሚገርመው ጎንደሬዎችን 'ጎሠኞች' ማለታቸው ነው። ጎንደር እንደ ክፍለ ሀገር እንጅ እንዴት እንደ ጎሣ ይፈረጃል ? ለመጀመሪያ ጊዜ መስማቴ ነው። እስካሁን የምሰማው ጎንደር የዐምሐራ ነገድ እንደሆነ እንጅ ጎንደር የሚባል የነገድ ስም አላውቅም ነበር። ግን በስም ኢትዮጵያውያን ነን እያሉ በመንደርተኝነት በሺታ የተለከፉ ሰዎች ስላሉ ገና ብዙ እንሰማለን። ፀሐፊው ፀረ ወያኔ መስሎ ነው የቀረበው እንጅ ሥራው የወያኔ መሆኑን ነው የጽሑፉ ይዘት የሚያሳየው። በኛ የህይወት ዘመን የተፈፀመውን ነገር ከጸሓፊው ሌላ ማንም እንደማያውቅ አድርጎ ማቅረቡ እድሜው ከ35 ዓመት በታች ያለውን አዲስ ትውልድ የተሳሳተ መረጃ ለመስጠትና ወያኔ እየሠራው ያለው ነገር ካሁን በፊትም በጎንደር ''ጎሥሳዎች'' እንደተሠራና የተለመደ ነገር እንደሆን ለማሳምን ተብሎ ነው ። ደጀሰላምም የራስዋን የርማት ነጥቦችን በጽሑፉ ሕዳግ ላይ ማስቀመጥ ይገባት ነበር። ማለት ፤ ቀይ ሽብር መቸ ተጀምሮ መቸ እንዳቆመ ፥ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ መቸ ጳጳስ እንደሆኑ ፥ መጀመሪያ የተሾሙበት ሀገር ስብከት የት እንደሆነ ፥ ጎንደር ሀገረ ስብከታቸው መቸ እንደሆነ ወዘተ..የመሳሰሉትን እርማቶች መስጠት ይገባ ነበር። ያም ሆነ ይህ በመቶ ሺህ የምንቆጠር ምዕመናን በቅዱስ አባታችን የሚመራውን ሕጋዊ ሲኖዶስ እንቀበላለን። የወያኔን የካድሬ ስብስብ እንደ ሲኖዶስ ቆጥራችሁ በዚያ መገዝትን የመረጣችሁ ወገኖች ደግሞ መብታችሁ ነው። ''ያም የኛ አይደለም ፥ ይህም የኛ አይደለም'' ብላችሁ ራሳችሁን በነዶክተር እንትና ሲኖዶስ ስር ለመመራት የፈልጋችሁም እንዲሁ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ባይፈቅድላችሁም አሜሪካዊና አውሮፓዊ መብታችሁ ነው። ''this is America''በሚለው መርህ መሠረት መጓዝ ነው።

Anonymous said...

ጸሀፊው እንደሚለው እውነት መደበቅ የለበትም በሚለው መሰራታዊ ሃሳብ እስማማለሁ ነግር ስለእውነት ጠበቃ የቆመ ሰው ሊዋሽ አይገባውም።፡ ሰሓፊው በጻፈው ውስጥ ብዙ ውሸት ተካቶበታል ይህም የሚያስረዳን እውነትን ለምገለጥ ሳይሆን በእውነት ሰበብ ሌሎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ዓላም ያደረገ ጽሁፍ ኘው። ለምሳሌ አንዱ ከገረመኝ ትልቁ ውሸት ብጹእ አቡነ ዜና ማርቆስ አቃቢ መንበር እንደነበሩ ያትትና መልሶ ደግሞ ፓትርያርክ መሆን ስላልቻሉ አኩርፈው ወጡ ይላል። እዚህ ላይ ጸሀፊው የምጠይቀው ነገር ለመሆኑ አቃቢ መንበር ፓትርያርክ ምርጫ ውስጥ ለምግባት ቀኖና ቤተክርስቲያን ይፍቀዳል እንዴ? ይኸ በራሱ ያለዎትን የቤተክርስቲያን እውቀት አጠያይያቂ ያደርገዋል። በተጨማሪ የአደባብይ ሚስጥር የሆነውን የብጹእ ፓትርያርክ አቡኑ መርቆርዮስን የስልጣን መልቀቅ እንደ ትልቅ ያልተገለጠ ምስጢርና አሁን እርስዎ የደረሱበት ምስጢር አስመስለው እዚህ ግባ በማይባል ማስረጃ አስደግፈው ሲያቀርቡ ሲጀምርም የጹፉ ዓላም ምን እንደሆነ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። ስለጸሃፊው ያለኝን አስተያየት እዚህ ላይ ላብቃና ደጀ ሰላም እንደዚህ አይነት አፍራሽና በውሸት የተጨመላለቀ ጽሁፍ ለማስተናገድ ለምን እንደፈለጋችሁ ካላችሁ የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪነት አንጻር ሳየው በጣም ግራ የሚያጋባ ነው።

Anonymous said...

actually it makes sense i just want to say thank you for the post.

Anonymous said...

I am very surprised of Deje selam blog. I saw an article written by Getachew Haile but you take it off. Why don't you need to know the reallity. You always try to hide the truth. Wow please don't fear the truth.

Anonymous said...

Ye Ahunu Yibas!
Whoever wrote and gave us this detail information, I've one message to him/her. It is too late too little. I still (hope many more) do not understand why these documents were invisible from the public? Had these documents been public nearly 20-years ago (at the time when they form the so called "migrated synod"), our mother church would not have been in the situation where it is now. "Sayikatel beketel endilu". I'm sorry to say it, knowingly or unknowingly those of you, who knew the truth from the beginning, have been cooperative for all these messes by hiding the truth from those innocent pilgrims, and you'll be equally accountable for everything. You do not have to wait until someone cross the red line to reveal the truth. BTW, I highly appreciate Prof Getachew for his honesty and came forward and crossed the true red line that had never been crossed for the last 20+ years, of course with admitting his mistake (confession) publicly. Such self motivated public correction of mistakes (confession) should be very much encouraged, b/c it is very unusual for our community. Many members of the church are seeking to know the truth about their mother church. Let's separate the church issue from the political differences; "ye Egziabhern Le Egziabher Ye kesarn Le Kesar" newna kalu. Thus, those of who knew the truth (with evidence like the one we just read), please come forward and tell the truth for those of us who had no idea what happened 20+ years ago, and thus supper duperly confused and still are on the crossed road.

Anonymous said...

መልዐከ ብሥራት እግዚአብሔር ይስትዎ።
በወሬና በተባራሪ፡ጽሁፍ፡የምናነባቸውን፡እውነታዎች፡በሚጋባ ነው፡ያስቀመጡት።፡ይበል፡ብለናል።

ኦክላሆማ፡፡አሜሪካ

ቅዱስ ሃብት በላቸው said...

..... “እንዲያውም ለሹመት ያቀረባቸው (ኢንዶርስ ያደረጋቸው) በወቅቱ የጎንደር ፈላጭ ቆራጭ የነበረው የመንግሥቱ ቀኝ እጅ መላኩ ተፈራ እንደነበር ይታወቃል፡፡” ..... በዘመነ ሕወሃት ብዙዎች ከወያኔ ጋር የሚሞዳሞዱ ሰዎች ይህንን ቃል ሲያስተጋቡት ሰምቻለሁ። ነገር ግን አንዳቸውም ለዚህ የሚጠቅሱት ማስረጃ የለም። ወያኔዎቹ ቅዱስ ፓትርያርኩን ከመንበራቸው አንስተው ራሳቸው የቀቡትን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ እንዲያመቻቸው ሲሉ ይነዟቸው ከነበሩት የስም ማጥፋት ዘመቻዎች አንዷ ይቺ ነበረች። አስፈላጊ ከሆነ ሌልፕቹንም መጥቀስ ይቻላል። እንኳን ፓትርያርኩን አይደለም አሁን በስደት የሚገኙት አባ ገ/ስላሴ በቅርቡ በኢሳት ቴሌቭዥን ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ እንደተናገሩት ከአቡነ ጳውሎስ ጋር በተገናኙበት ወቅት አባ ጳውሎስ የሻለቃ መላኩ ተፈራን ስም አንስተው እንደዘለፏቸው ተናግረዋል። http://www.youtube.com/watch?v=w7L9bGBPPx8 በዘመነ ወያኔ አንድን የጎንደር ክፍለ ሃገር ተወላጅ ለማጥቃትና ለማጥላላት “የመላኩ ተፈራ ምንትስ ነው...!” ማለት የተለመደ ብሂል ነው።
እድሜ ልኩን ለሰራው ታሪክ ይቅር ለማይለው ጥፋት ወደ ፈጣሪው አጎንብሶ መጾም መፀለይ በሚገባው ጊዜ ከአፉ ጭቃ የሚተፋው የአዛውንቱ ቀላል ስብሃት ነጋ፤ እንዲሁም መሰል የህወሃት አጋንንቶች ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ለመቆጣጠር ካድሬዎቻቸውን ቆብ አስለብሰው ገዳም ውስጥ ሁሉ አስርገው ያስገቡ እንደነበር የቀድሞው የማሕበሩ ሊቀመንበር አቶ አረጋዊ በርሄ በመፅሃፋቸው በሚገባ ማስረጃ እየጠቀሱ ተንትነውልናል። እንዲያውም አሁን ከዋነኞቹ እጩ ፓትርያርኮች አንዱ እንደሆኑ እየተነገረላቸው ያሉት አቡነ ሳሙዔል (የቀድሞው አባ ተከስተ ብርሃን) ለዚሁ ተልዕኮ ታጭተው ዋልድባ ውስጥ ቆብ ደፍተው ኑረው ወያኔ አዲስ አበባ ሲዘልቅ አብረው የመጡ ታጋይ መሆናቸው ይነገራል። ለዚህም ነው “ስር ዓተ ምንኩስና ፈጽሜበታለሁ” የሚሉት ታሪካዊው የዋልድባን ገዳም፣ ወያኔ ወደ ስኳር እርሻነት ለመቀየር እያደረገ ያለውን ጥፋት ለመቃወም እንኳን ያልፈለጉት። እንኳን ዓለምን ንቀውና ጠልተው የኖሩበት ለዘመናት የብዙዎች መጠጊያና መጠለያ የሆነ አምላክን ለማመስገን የተመሰረተ ገዳም አይደለም በአንድ ጀምበር የተሰራ የጨረቃ ቤትም ሲፈርስ ያሳዝናል።
ለመሆኑ አንተ ቅዱስ ፓትርያርኩን ለሹመት ያቀረባቸው መላኩ ተፈራ ነው በማለት በርግጠኝነት ለመመስከር የደፈርከው ከምን ተነስተህ ነው? ... የቤተክርስቲያናችንን ሶስተኛውን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖትም የተሾሙት በደርግ ዘመነ መንግስት መሆኑ ይታወሳል። ብጹእ አቡነ ተክለሃይማኖት (አባ መላኩ) ለፓትርያርክነት የተመረጡት የጵጵስና ማዕረግ እንኳን የሌላቸው ተራ መነኩሴ ሳሉ ነበር። እርሳቸውንስ ለሹመት ያቀረባቸው የትኛው ባለስልጣን ይሆን?
“ .... የቀድሞው ፓትርያርክ ራሳቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፤ የነርሱ ሁኔታስ በምን መነጽር ነው የሚታየው?” ..... ባጠቃላይ ጽሁፍህ ከሚዛናዊነት ያልፀዳና ወደ አንድ ወገን ያዘነበለ ለመሆኑ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ የሚያስፈልግ አይመስለኝም። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የቀድሞው ሳይሆን አሁንም በህይወት የሚገኙ በመንፈስ ቅዱስ የተሾሙ ትክክለኛው የቤተክርስቲያናችን ፓትርያርክ መሆናቸውን የሚመሰክሩ በሚልዪን የሚቆጠሩ ምዕመናንንና ካህናትን ድምጽ ለማድመድ፣ አድምጠህም ለመመስከር የተከፈተ ሕሊናና ጆሮ እንደሌለህ ያሳብቅብሃል።
“ ... ወያኔ አቡነ ጳውሎስን በሥልጣን ማስቀመጡ የማይታበል ሐቅ ቢሆንም ደርግ ተወግዶ ሕዝቡ የመናገርና የመሰብሰብ ነፃነት ባገኘ ጊዜ በቤተ ክህነት ውስጥ ተቀስቅሶ የነበረው አመፅ ከዚያ ታምቆ ከነበረው ቁጭትና ብሶት የተወለደ እንጂ ወያኔ ወገቡን አስሮ ያስተባበረው የለውጥ እንቅስቃሴ አልነበረም፡፡ ሁኔታው ራሱ በስሎ ጊዜውን ሲጠብቅ የነበረ ስለነበር ነገሩ እግዚአብሔር በፈቀደ ጊዜ ሲፈነዳ በአቡነ መርቆሬዎስና በአስተዳደራቸው ላይ የተቀሰቀሰው ከፍተኛ አመጽ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው እንዲለቁ አስገድዷቸዋል፡፡ ማስረጃም አለ፡፡”
በጽሁፍህ ላይ መልሰህ መላልሰህ ፀሃይ የሞቀውን ሃቅ ለማለባበስ በመሞከር ወያኔ ፓትርያርኩን ለማውረድ ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንዳልነበረው ለማሳመን ትሞክራለህ። ማስረጃ ብለህ ከጽሁፍህ ጋር ያያዝካቸው ፋይሎችም በተለይም ሁለቱ ከጽሁፍህ ጋር የሚዛመድ አንዳችም ጭብጥ የሌለባቸው ናቸው። ሶስተኛውና የአስር ሊቃነ ጳጳሳት ስም የተዘረዘረበትም ቢሆን አቡነ ጳውሎስን ለማስቀመጥ እንዲያመች መንገድ ለመጥረግ አሁንም ቤተክርስቲያኗን በማመስ ላይ የሚገኙ ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው አባቶች ተጽዕኖ ተርቅቆ የወጣ መሆኑ ያስታውቃል። ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ አባቶች ቤተክርስቲያናችን በወቅቱ ከነበሯት ሊቃነ ጳጳሳት መካከል አስሩ ብቻ መሆናቸውም ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል።
ይህ ሁሉ ኩነኔና ውርጅብኝ መደምደሚያ ላይ ቢያንስ ቢያንስ ለቤተክርስቲያችን ችግር የመፍትሄ ሃሳብ አለመሰንዘሩ ደግሞ ፀሃፊው ለሃሜትና ለአሉባልታና ለወቀሳ ብቻ ያለፈውን እያነሳ የሚኮንን ሰው ቢያንስ ቢያንስ የራሱ አዕምሮ ያፈለቀውን የመፍትሄ ሃሳብ ጣል ማድረግ ይጠበቅበት ነበር። እንደሚታወቀው የተከፈተውን የሰላም በር ዘግቶ 6ኛውን ፓትርያርክ ለመሾም የሚደረገው ርብርብ በበርካታ የቤተክርስቲያኗ ምዕመናንና ካህናት ዘንድ ተቀባይነት ያላገኘ ነገር ነው። የአዲስ አበባው ቅዱስ ሲኖዶስ በመቶ ሺህ ብሮች የሚቆጠር ገንዘብ ፈሰስ በማድረግ በተለይ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስና በስደት የሚገኘውን ቅዱስ ሲኖዶስ አስመልክቶ በኢቲቪ የሚተላለፍ ዶክመንተሪ ፊልም እንደተዘጋጀም ሰምተናል። ምናልባት እስካሁን ሳይቀርብ የዘገየው “ጅሃዳዊ ሃረካት” የተሰኘው መሰል የኢቲቪ ድራማ ያስከተለውን ኪሳራ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይመስለኛል። ይህንን ፅሁፍ ሳነብ ዓላማው ተመሳሳይ ስለሆነብኝ አገር ቤት እየተሰራ ያለውን ለማዘናጋት ተሰልቶ የቀረበ ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አድሮብኛል። ፀሃፊው የሰሞኑ አነጋጋሪ ጉዳይ ስለሆነው 6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ዙሪያ እየተደረገ ስላለው ሽኩቻ ትንፍሽም አለማለቱ ደግሞ ይህንኑ ግምቴን ወደ እውነት ያስጠጋዋል።
እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያናችንን በቸርነቱ ይጠብቅልን እንጂ ከቀድሞው የባሰ እጅግ አደገኛ ነገር እየመጣ ነው።

Anonymous said...

Dear Deje selam,

I advice you to post my comment from yesterday this is your second time to refuse not to post my comment. You are going to push me to write an article, the church issue on non-church related websites. Whether you are doing good or bad, you are almost the only blog to address our voice. Don't select what you feel comfortable to your idea. If you do so better you close your blog as Deje Selam and get courage your own idea openly with your name. Write what you feel not what you think accepted by the public. We can't go an inch with a double personality.

Anonymous said...

I'm very surprised to read some of the comments directly attacked both the writer and Dejeselam. Its unfair and unjust! Those attacking seems to me supporter of of the either woyane or the previous patriarch!

The reality is the writer, who every the person, described the truth and I know its facts! We know what had happend during Aba Merkorewos's time.

Yes Aba Paulos was tribalist and destroyed the entire EOC and became a member of woyane circle. So also Aba Merkorewos! He was a member of Mengistu's shengo and narrow tribalist! If you are not Gondere you have no place in his time. Who was in power during Aba Merkorewo's time. Remember this Kene during his time: "Lezeemesta Fanta Weenda-bet Eboa Weste Betekihenet" (translated as if he didn't come from Farta and Endabet he will never allow to get in Bete Kihnet).

Furthermore lets look at any diaspora churchs...Gondere prists don't like others to be around. Their problems seems to me the same as woyanes (Woyane's also don't feel comfortable to be with other Ethiopians).

I congratulate the writer to write the facts we know during the time Aba Merkores was removed from the Church.

For me there is no much choice between the two groups!

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች ይህ ምን ይጠቅማል ብላችሁ እዳወጣችሁት እግዜር ያውቃል። በጣም የሚያሳዝነው ግን ደጀሰላምም ሳታውቀው ይሁን አውቃ በውጭ ላሉትን አባቶች ለማደከም ያታለመ ጽሑፍ ነው።

minwaga alew selaefew wengele mezerezere ye wedefitune mastekakele new yikire tebabalo ande mehone new.....

betekirstianachine ena ega memenane bechenke lay honene yehine alubalta POST mareg aytekmeme.BE EWENETU BE DEJE SELAMOCHE AZEGALEWE............KAHUNE BEWALA LEMAMEN YIKEBDEGALE POSTOCHACHEWENE

Anonymous said...

በጣም የሚያሳዝንና የሚያብሳጭ አፍራሽ ጽሑፍ ነው።
በጣም የሚያሳዝንና የሚያብሳጭ አፍራሽ ጽሑፍ ነው።
በጣም የሚያሳዝንና የሚያብሳጭ አፍራሽ ጽሑፍ ነው።
እንኴን አንድነት ሊፈጥር ይቅርና ለእርቅ እንኳን የሚያደራድር አይደለም ማንም ጠላት የተባለ እንደዚህ አይነት የዳንኤል የክብሪት /ክስረት አይነት አካሄድ በጣም የሚያሳዝንና የውሸት ድሪቶ ነው::
“ፓትሪያርክ እለ ፓትሪያርክ ተሾመ!!” ብለው ለመጀመሪያ የተቃወሙት አቡነ ጳውሎ ስ በተሾሙ በዛው እለት ከአሜሪካ አቡነ ይስሀቅ ነበሩ voa ላይ መጠየቅ ይቻላል። አቡነ ይሳቅም እንደማንኛውም የሲኖዶስ አባል አድስ አበባ ሄደው ሁኔታውን ካዩ በኌላ ከምርጫው ሳይሳተፉ ስብሰባውን እረግጠው እንደተመለሱና በአሜሪካ ላለነው አጥቢያወች ሁሉ ትክክለኛ የኢትዮጵያ ፓትሪያሪክ በህይወት ያሉት አቡነ መርቆሬዎስ እንደሆኑ መመሪያ የሰጡን ይህ የምናውቀውና ያሳለፍነውን ታሪክ ሌላ መልክ ከማስያዝ በስደት ካሉት አባቶች ያለህን ችግር እዛው ብትፍታ ይሻልህ ነበር::
አቡነ መርቆሬዎስም ሁኔታወች ሲረጋጉ ከምርጫ በፊት እንደገና ተሺሎኛል ብለው እንደነበርም ይነገራል ሌላው የዘለልካቸው የታምራት ላይኔን ኑዛዜ ዊኪሊክስ ያወጣውን እና በኢሳት እንደሰማነው የካናዳው ሊቀ ካህናት ስለታምራት ላይኔ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ነው ::
አሁን ይህን ታሪክ ማጣመም ለምን አስፈለገ አላማውስ ምንድን? ስንል አንድነት ሳይሆን አላማው ግልጽ ነው መድከም አያስፈልግም "በገለልተኝነት " ለመቀጠል ከማሰብ የመነጨ አባዜ ነው::
ሌላውን ለምን ገለልተኛ መሆን አስፈለገ የሚለው ምክንያቱ ስለሚያስጠላኝ ወደዛ አልገባም ::
መሆን ያለበት
የመጀመሪያው አማራጭ፦ በስደት ካሉት አባቶች ጋር ያላቸውን የተለያዩ ችግሮች በሂደት መቅረፍ እንደሚቻ በማመን አብሮ በአንድነት እናት ቤተክርስቲያንን መታደግ ::
ሁለተኛው:- ወያኔን ወግኖ መቀጠል::
ገለልተኝነት ለኔ በፖለቲካው አለም እንዳሉት ተቃዋሚነን ብለው ተቃዋሚወችን የሚሰልሉ እና የሚቃወሙ የልደቱ እና በቤተክርስቲያናችን ደግሞ የዳንኤል ክብረት አካሄዶችን ይማሰላሉ ።
በስደት ያሉ አባቶች የዛሬዋን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን አሁን ላለችበት ያደረሷት እነሱ ናቸው ክፉም ሆነ በጎ ስራ ሰርተው ተሰደዋል አሁን እነሱን እንደ ሌላ ፍጡር ያልሆነ መልክ ማላበስ ጥሩ አይደለም በእንደዚህ የተጣመመም ሀሳብ ይዞ አንድነትን አይሰበክም ሁሉ ነገር በፍቅርና በመከባበር እንጂ በጉልበትና በአድማ ውይም እኔ ያልኩት ካልሆነ በሚል ግትርነት አንድነት አይመጣ::
ሌላው ደጀ ሰላም የተለያዩ ሀሳቦችን ማንሸራሸር መልካም ነው ብዥታን የሚፈጥሩ አደገኛ ጽሁፎች ላይ ግን ጥንቃቂ ማድረግ ያስፈልጋል ለምሳሌ ይህ ጽሁፍ የአቡነ መርቀሪዮስ ፕትርክና ላይ ጥያቄ ያለው ይመስላል ነገር ግን የኢትዮጵያው ሲኖዶስ እሳቸው የሸሟቸውን ጳጳሳት ተቀብለዋል ታዲያ እኛ ከዚህ የምንረዳውን ተረድተናል ሌላ ብዥታ መፍጠር አላስፈላጊ ነው እና በውጭ ያለነውን ወደ አንድነት የሚያመጣ ነገር ብንወያይ ደስ ይለኛል።
ዘሚካኤል ከቦስተን

Anonymous said...

ደጀሰላመ ንገሩ ሁሉ ክሞላጎደል እውነት ነው. አነዚሀ 5 አባቶች they created their own senodos bay their method the other geleltegna formed . this 2 non organization came because of this people, this all church problem because of this people . this all our weakens because of this people .this people destroyed our kenone and everything i don't know how we can solve. really i am expecting only from god

yo said...

አለመታደል ሆነ እና በቤተክርስትያናችን ርካሽ ፖለቲካ እና ጉድ እየሰማን ነዉ፡ በደርግ ጊዜ እኮ አቡነ መርቆሪወስ የክፍለ ሀገር ጳጳስ ነዉ የነበሩ በሁዋላ የቀደሙት ፓትርያሪክ ሲሞቱ ለ3አመት እንደተሾሙ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን መጣ፡ ይታያችሁ እንግዲህ ይህ አተላ ጸሀፊ ነዉ እንግዲህ ዘረኛ ነበሩ እያለ የሚዘባርቀዉ፡ በዛን ጊዜ እኮ ኤርትራዊያንም ነበሩ፡ ዘረኝነቱስ የነገሰዉ አሁን ነዉ ምክንያቱም ዘረኛዉ ኢህአዴግ ሁሉንም ለመቆጣጠር በአንድ ዘር ስልጣኑን አስያዘ፡ የጸሀፊዉም ማንነት ሳታዉቁ ደጀሰላሞች ባታቀርቡ ጥሩ ነዉ።ለቤተክርስትያኑዋ መዳከም ተጠያቂዉ በሃገር ዉስጥም በዉጭም ያለዉ ሲኖዶስ ሆኖ እያለ እዚህ ላይ ያለዉ ጽሁፍ ግን እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ የሚል ይመስላል። ጸሀፊዉ ተሀድሶ እና ከዉስጥ ገብቶ ለማወናበድ የሚሰራ ይመስላል፡ ምንም ፍሬ ነገር ሳይጽፍ ወይም የመፍተhae hasab saiset ዘረኝነትን እና ክፍፍልን የሚያስፋፋ ይመስላል፡ አሁንም ሀገር ዉስጥ ያሉት አባቶቸሀ ከኢህአዴግ መንግስት ጋር እጅና ጉዋንት ሆናችሁ እየሰራችሁ ነዉ ያላችሁት፡ ገዳማቱ ሲፈርሱ፡ ቤተክርስትያን ስትከፋፈል ዝም ብላችሁ፡ መነቃቀፉ እኮ በእሳት ላይ ቤንዚን እንደመጨመር ነዉ የሆነዉ፡ መጽሀፍ ቅዱስ እኮ ይቅር ተባባሉ ነዉ የሚለዉ፡አህያ በቀደደዉ ጅብ ይገባል እንዲሉ፡ ቤተክርስትያኑዋን ለበለጠ ችግር እያጋለጣችሁዋት ነዉ፡በሁላችንም ይቅር ይበለን፡፡

Anonymous said...

በጣም የሚያሳፍር ተግባር። ለመሆኑ ዶ/ር ጌታቸው በዋቢነት የተጠቀሱበትን ድርስት ይደግፉታል ማለት ነው?

ውድ ደጀሰላሞች ይህን የፕሮፖጋንዳ መጣጥፍ ለንባብ ማብቃታችሁ፤ ለዘረኞችና ሐይማኖታችንን ለማጥፋት ተግተው ለሚሰሩ ድግ ስራ አበርክታችኋል። በተረፈ አማራ መጥፋት አለበት፡ አገራችንን ከአማራና ከኦርቶዶክስ ተጽእኖ ነጻ አደረግናት ላለው ስብሀት ነጋ መልካም አስተዋጽኦ መልካም ስራ ሰርታችኋል። ለነገሩ ይህችን አገርና ይህችን ቤተክርስቲያን ለማጥፋት ለተጀመረው ተግባር ደግ ስራ እየሰራችሁ ነው። ለዋጋችሁ የአዲስ አበባው መንግስት መልካም ምስጋና ማናልባትም.....

ወድ ደጀ ሰላሞች በጣም አዘንን ይህን ቆሻሻ የፕሮፖጋንዳ መግለጫ በማውጣታችሁ። ይህን ተቀብሎ ደጅ ለመጥናት ከሆነ ደግ ነው። ትናንት ሐይለስላሴ ጉግሳም፤ ሰርቶታል። አቡነ ቄርሎስም ደግመውታል። አቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ሚካኤል ሰማእትነትን ሲከፍሉ ቄርሎስ ጀኔራል ቦዶሊዮን ተቀበሉ። ባረኩትም። በዚያ አላቆሙም። የካቲት 12/1929 የአዲስ አበባን ፍጅት ያስከተለውን የማርሻል ግራዚያኒ መንበር ሲባርኩ ቆሰሉ። ይህ ታሪክ ዛሬ ኢትዮጵያና አማራ ከኦርቶዶክስ ጋር ስለተያያዙ መጥፋት አለባቸው። ለዚህ አባሪና ተባባሪ ደግሞ ይኸው የናንተም ድህረገጽ አንዱ ሆነ ማለት ነው።

Anonymous said...

ለዚህ ከንቱ ጽሁፍ የሚያስጠላ ካካ ልብወለድ ድርቶ ድርሰት ብለው ትስማማላችሁ? የሸዋና የጎንደር ከተት አንድ የሚያደርግ አጣን እንጂ የሚያዋጋ የሚለያይ የሚያናቁር መቸ ጠፋ
እባካችሁ ከደጀ ሰላም ብሎግ ላይ ይነሳልን
ደጀ ሰላም የተዋህዶ ልጆች እንጂ የነገረኞችና የጎጠኞ መነሀሪያ አይደለችም!!!

Anonymous said...

ደጀሰላማውያን ይህንን ፅሁፍ ማውጣታችሁ በጣም ደስ ብሎኛል። ይህ ፅሁፍ ኢትዮሚዲያ ላይ እንዳነበው አንድ ወንድም በስልክ ነግሮኝ ድረገጡን ብከፍተው ላገኘው አልቻልኩም። ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ፤በዚሁ ድረገጥ አዘጋጅ Editor's Note - When we published Prof. Getachew Haile's church-related article recently, we had no clue that we were opening Pandora's box. We tried to publish one after the other. But the flood continued to this day. Due to our limited capacity, we regret to inform the public that we can no longer publish articles around the same issue anymore. Thank you for your understanding. እምትል ማስታወቂያ ቢጤ ተለጥፋ አየሁኝ። ቆየት ብሎ ግን የቀሲስ አስተርአዬ ጦማር ወጣ። በሃገራችን ሃሳብ በነፃ እንዲንሸራሸር እሚታገሉ ሰዎች ባገር ቤት እሚደረገውን እዚህ ሲደግሙት በማዬቴ አዘንኩኝ።።ለማንኛውም የመላከ ብሥራት ፅሁፍ በነጋታው በሌላ የመረብ ሰሌዳ ተሰቅሎ አየሁት። አነበብሁትም። በቤተ ክርስትያን ያለን አገልጋዮች፤ በተለይም እድሜአችን ገፋ ያለ ፤ይህ ነገር እንደ አምስት ጣታችን አሳምረን እምናውቀው ስለሆነ ብዙ ላይገርመን ይችላል። “ኢየሃድጋ ለሃገር ዘእንበለ አሃዱ ሄር” እንዲል መጻፉ ሆነና ፕሮ. ጌታቸው ሃይሌን የመሰለ፤ ቆም ብለን እንድናስብ እውነቱን እሚፈነጥቅ መምህር አገኘን። መላከ ብስራትም ይህንን ችግር ክስሩ እንድንመረምረው እሚጋብዝ ፅሁፍ ከነማስረጃው ማቅረባቸው ልናመሰግናቸው ይገባል። በመሰረቱ አንድ ሰው በሽታውን ለሃኪም ከደበቀ መዳን አይችልም። አንድ ሰው የበፊተኛ ሃጢአቱን በንስሃ ካላፀዳው የእግዚአብሔርን መንግስት አያያትም። እኛም የቤተ ክርስቲያናችንን ችግር ከስር መርምረን፤ ደፍረን ለመናገር ካልቻልን መፍትሄ ማግኘት አንችልም። የስደተኛ አባቶቻችን መሰደድ በራሱ ችግር አልነበረውም ነገር ግን ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ፤ ቤተክርስቲያንም እንደ ተቋም በህይወት እያሉ “እኛ ካልመራነው” ተብሎ እዚህ ሲኖዶስ ማቋቋም በውነቱ የጥፋት ሁሉ ቁንጮ ለመሆኑ ጥያቄ የለውም። ህገ-ወጥ ተኹኖ ህገወጦችን ተዉ ለማለት ከባድ ነው። መላከ ብሥራት ‘መጀመሪያ ውስጣችንን” ማለታቸው እውነት አላቸው።በርግጥ ተሸፋፍኖ መኖር የለመዱ እንዲህ ደፍሮ እሚናገር ሲመጣ ቢደናበሩ ያለ ነው፤እንዲህ አይነት ፅሁፎች በነከበደ ቦጋለ ቤት የራስ ምታት መቀስቀሳቸውም አለምክንያት አይደለም። የጋሽ ከቤ የወያኔን የካድሬ ስብስብ እንደ ሲኖዶስ ቆጥራችሁ…ወዘተ” አፍ እላፊ ሌላ ሳይሆን “ገለልተኞች ተንጋግተው ወደኛ ይመጣሉ” ተብሎ የተጠበቀው ህልም ሆኖ በመቅረቱ የተፈጠረ ንዴት እንደሆነ ጉዳዩን እምንከታተል ሰዎች እንረዳዋለን። እኛ የጨንቀን የ40 ሚልዮን ምእመናን ቤተ/ክ የህልውና ችግር እንጂ የተወሰነ ክፋዩ የመንበር ጉዳይ አይደለም። የምናውቀው አንድ አገር ነው፤ አንድ ቤተ/ክ ነው፤ አንድ ሲኖዶስ ነው። የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀርም የተበላሸውን የሃገርም ሆነ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በውጭም በውስጥም ያለ ህዝብ ተባብሮ አንድ ቀን እንደሚያክመው መተማመን ይገባል። በሌላ በኩል መላከ ብሥራት በጽሁፋቸው
“ትግሬም ይሁን አማራ፣ ኦሮሞም ይሁንጉራጌ ጠባብ አስተሳሰብ አራማጅ ከሆነ ጎሰኛና ጎጠኛ ነው፡፡” ያሉት ልብ ልንለው ይገባል። ጎጠኝነቱ የተወሰነ ክፍል በሽታ ብቻ አይደለም። በሽታው ብዙዎችን እሚነካ ነው በዛ መጠን ታዲያ ታካሚው መድሃኒቱን መውሰድ እንጂ አካሚ ሆኖ መቅረቡ ለራሱም ለሌላውም አይበጅም።

Anonymous said...

WOW!!! DEJESELAM AREN'T YOU PRO ORTHODOX CHURCH?.....YOU POST THIS TRUSH... AS TRUSH AS GETACHEW HAILE'S ARTICLE?...THOSE RASIST INDIVIDUALS FROM SHEWA ARE "HYINA WITH OUT A TOOTH"...YOU CAN BARCK!!

Anonymous said...

“እኛ ካልመራነው” ያሉት እኮ ገለልተኛ ነን ያሉት የሸዋወቹ ናቸው ጎንደሬም ትግሬም አይመራንም የሚለው የሸዋውን ቡድን ባንድ ወቅት ዲሲ ላይ እነ ዶ/ር ማሪያሞችንና አባ መላኩን ጨምሮ ገለልተኛ የሚባል ነገር አትጀምሩ ተብለው ቢመከሩ ጎንደሬም ትግሬም አይመራንም ብለው የሸዋ ፓትሪያሪክ እየጠበቁ እነሆ አንዱ አልፎ ሌላው ሊተካ ነው::ታዲያ እኔ ደግሞ በተራየ ዘመኑ የኛ ነው /የወሎ/ልበል? ነገሩ እኮ ሀያላን እኛ ብቻ ነን ባዮ ገገሙ :: ነገሩን ቀለል አድርጋችሁ ተመልከቱት የሚመለከው እና አንድ የሚያደርገንን እንመልከት በእውነቱ ከሆነ በሁሉም ወገን ያሉት አባቶች ቤተክርስቲያንን በውጭው አለም በማስፋፋት በስደት የምንገኝን ኢትዮጵያውያንን እየባረኩና እያጽናኑ የማይካድ ታላቅ አገልግሎት እየፈጸሙ ነው ስለዚህ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው የምንገኝ ፍቅርን እናስቀድም ሁሉም ከንቱ ነውና::

Anonymous said...
ከጎንደርም ወነ ከትግርራይ ነን የሚትሉ ጠባቦች (ምዕመንም ወንክ ጳጳስ) ጠባብነታችውን ኣውልቁና የሰውን ዘር ሁሉ በደሙ - የወደደውን ክርስቶስን ልበሱት። በእናንተ የስልጣን የዘር እና የፖለቲካ ትግል ቤተክርስቲያንን አዳክማቹ ለጠላት መንገድ አትክፈቱ። ሃዋሪያው ቅ. ጳውሎስ በአንድ ወቅት እንዲ አለ... በጠላቶች ፈተና...በሃሰተኛ ወንድሞች ፈተና፤ እናም ቤተክርስቲያናችን አትፈትናት።

ጊዜው፦ የቤተክርስቲያን ልጆች ተባብረው በፍቅር ከመቼውም ይልቅ የሚሰሩበት እንጂ አንድ አባት ያሁም ኣልፍልግም ታምሜአለው ብለው በፈቃዳቸው ያስረከቡትን ለምን መንበር ላይ አልተቀመጡም ብሎ የቤተክርስቲያ ሃይል የሚባክነበት አይደለም።

እስቲ ከግብጽ ቤተክርስቲያን እንማር እንሱ ከአፍሪካ እስከ ላቲን አሜሪካ ለሰው ዘር ሁሉ መዳን ብለው ይሰራሉ ። እኛ ግን በሰሜን አሜሪካ ጠቅምጠን ከቀዬአንችን ያለውን ሰው እየፈለግን እንቆጥራለን፤ እንሾማለን ። መቼ ነው የኬንያ፤ የሱዳን፤የዛየር፤የጋና፤የጀማይካ... ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት እንዲቋቋሙ የምንረዳውና ሃዋርዊ ተለኮ የምናደርገውስ? ጌታ ያለን እኮ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በስሜ እያስተማራቹ ..እያሳመናቹ...እያጠመቃቹ ደቀምዛሙርቴ አድርጉ ነው። አንድ አባት ለምን መንበር ላይ አልተቀመጡም እያልን ዋናውን የክርስትና አላማ እየረሳን እንዳይሆን እንጠንቀቅ።

እስቲ ኢትዬጵያ ስትሄዱየ አህዛብ የአምልኮት ስፍራዎችን እንዴት አዳዲስ እንደወኑ ተመልከቱ፤ መርካቶም ሂዱና ማን ንግዱን እንደትቆጣተረው፤ ስንትም ክርስቶስንና ወገኖቹን የሚሰድብም መጻፍት ገበያ ላይ እንዳለ አስተውሉ። ከአዋሳ እስከ ላንጋኖ(ሶደሬ) ፤ ለምን ቤተክርስቲያን እንደሌለ ግን በሳውዳረቢያ ቋንቋ ብቻ ደጃቸው ላይ የተጻፈባቸው ብዙ ህንጻዎች መንገድ ዳር እዳቆጠቆጡ እዩ። ባህርዳርም እንደገባቹ ቅ.ጊዮርጊስ ቤ/ክ እስከምትደርሱ ስንት አዳዲስ የአህዛብ ህንጻዎች እንዳሉ ተመልከቱ። ለምንስ ባላፉት አመታት የቤተክርስቲያ አባላት ቁጥር(በመቶኛ) ቀነሰ ብላቹ እራሳቹን ጠይቁ? ከነዚ ሁኔታዎች የምንረዳው የጎንደርና የትግራይ ትግል ቤተክርስቲያን ተልኮዋን አንዳትወጣ አንቅፋት አንደወነባት ነው። በነገራችን ላይ ፅሑፉን የፃፍክ 95% ልትመሰገን ይግባሃል፥፥

የተኛ ንቃ! said...አንድ አባት ያሁም ኣልፍልግም ታምሜአለው ብለው በፈቃዳቸው ይሁን በታምራት ዕውሬም ሆነ ላይኔ ተፅዕኖ ያስረከቡትን መንበር ተመልሰው ካልተቀመጡበት ብሎ የቤተክርስቲያን ሃይል የሚባክነበት አይደለም።

ጊዜው፦ የቤተክርስቲያን ልጆች ተባብረው በፍቅር ከመቼውም ይልቅ የሚሰሩበት ነው:: ክርስቲያኖች ኣራት ዓይናማ ሆነው በኣካባቢያቸው በኣፍርካ ቀንድና በዓለም በጠላት ምን እየተሴረ እንዳለ ተገንዝበው በሕብረት የሚንቀሳቀሱበት ነው አንጂ፤ ከጎንደርም ወነ ከትግራይ የወጡ ጠባቦች የክርስቲያኖች ጊዜ እና ሃይል የሚያባክኑበት ኣይደለም፥፥

Anonymous said...

ፀሃፊውም ሆነ ደጀ ሰላማውያንን እያመሰገንኩ፤

መቼስ ይህን ጽሁፍ ከፖለቲከኛ - ባለ አንድ ዓይናና ባለ አንድ ጆሮ፤ ከዜጋም ባልጌ፤ 'ከሃይማኖተኛም' ዘረኛ ካልሆነ በስተቀር ማንም የሚቃወም ያለ አይመስለኝም።
አረ ብዙ የምንለው አለን፤ አረ በዕውነት ሐቁ መቼስ ወጣና

ዳላስ-ቲክሳስ

Anonymous said...

እነዚህ ሰዎች ብልሆችና ለቤተ ክርስቲያንና ለቀጣዩ ቅውልድ አርቆ አሳቢዎች ቢሆኑ ኖሮ የጀመሩት ጉዞ ለማንም እንደማይበጅ ተገንዝበው “ወንበሩ ለኛ ይገባል” የሚል መንቻካ ግትርነታቸውን ትተው “የከፋፍለህ ግዛ” አጀንዳን አንግቦ የመጣውን ወያኔን ሕዝቡን አንድ በማድረግ በልጠውት በተገኙ ነበር፡፡ ነገር ግን እልህ የተሞላው የሞኝ ጉዞአቸውና ገታራነታቸው ሳያውቁት የራሱ የወያኔ ዓላማ ተባባሪ አድርጓቸው አረፈ፡፡ አንድ ጥላ ሥር መሰብሰብ የነበረበትን የአንድ ቤተ ክርስቲያን ምዕመን ለሥልጣን ጥማቸው ሲሉ ከፋፈሉት፡፡ የታደለ ወያኔ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መሥራት የነበረበትን የመከፋፈልና የመበጥበጥ አጀንዳውን በብዙ ፐርሰንት አቀለሉለት፤ እናም ደጋግመው ሳያስቡበት፣ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል እንዳለችው እንስሳ በራስ ወዳድነት ያቋቋሙት “ሲኖዶስ” ምዕመኑን ከመከፋፈልና ከማወናበድ እንዲሁም ለግለሰቦች መጠቀሚያ ከመሆን የዘለለ ሃያ አንድ ዓመት ባስቆጠረው ዕድሜው ለቤተ ክርስቲያንና ለበጎቿ ያስገኘው አንዳችም ፋይዳ የለም::

Belihu AkakiZeraf said...

Why stabbing many of on the back! if not, this is very foolish commentary. There is no moral equivalence between an idiology that created Tigray above Ethiopia and TPLF before EOC and then some kind of Gonder regionalim. Give me a break. This is an attempt to appear smart/analytical by using false equivalence. People have been sustaining wounds from stabs in the back constantly but please stop dusting off salts on our gashed fleshes.

Anonymous said...

Here go again Deje huket entertaining fear, smear and division one another. Weyane is laughing because of this blog and propaganda.

Anonymous said...

እውነት ሲነገር እንዲህ ያንጣጣል መቸም ይገርማል ፡ ንጉሡ አፄ ዮሐንስ (ደጉ ዮሐንስ )እውነቱ ቢነገር ይህ አሣ ቆሞ ይሄድ ነበር
አሉ ይባላል፡፡ ታዲያ እስከመቸ ህዝብ ሲታለል ይኖራል ፡፡እንደኔ በወቅቱ ያልነበሩ ሰዎች ማወቅ ያለባቸውን እውነት እንዲያውቁ፡ መደረጉ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ፀሐፊውን ቃለ ሕይወት ያሰማልን እላለሁ

Anonymous said...

አራቱ ያንድ መንደር ተወላጅ ጳጳሳት አቡነ መርቆሬዎስ ሳይታመሙ ታምሜአለሁኝ ብለው ሲወርዱ ዋና ተባባሪዎች ነበሩ። ለምን? ስልጣኑ ከእጃቸው እንደማይወጣ እርግጠኞች ነበሩና። ዶኩሜንቱ እንደሚያሳየውና በፊትም በብዙዎች ዘንድ እንደሚታወቀው ረዳታቸው አቡነ ዜናማርቆስ ነበሩ የዚህ ድርጊት ዋና ተዋናይ። ፓትሪያርኩ በተሎ ጓዛቸውን ጠቅለው ከመኖሪያቸው ጭምር አጣድፈው እንዲወጡ ያረጓቸው ዜና ራሳቸው ናቸው። አባ ጳውሎስ በትንሽ ድምጽ ብልጫ ፓትሪያርክ ሆነው ሲመረጡ ህልማቸው ውሃ በላው። ያኔ አንድ በአንድ ወደ ወንዝ ልጆቻቸው ሰሜን አሜሪካ በመምጣት “ፓትሪያርክ በህይወት እያለ…” የምትል ነጠላ ዜማ ለቀቁ።
ፓትሪያርክ በህይወት እያለ ሌላ ሊሾም አይገባም ብለው በወቅቱ የሞገቱ አንድ አባት አቡነ ይስሐቅ ብቻ ነበሩ። የኋለኛው የአራቱ ያንድ መንደር ተወላጅ ጳጳሳት ጉዳይ ግን ከስልጣን እንጂ ከቀኖና ጋ የተያያዘ ነገር የለውም።የነ አባ ሃብቴን ጉድ ለማወቅ የፈለገ ሟቹ አቡነ ይስሐቅ በ2003 አመተ ምህረት ያወጡትን "በሀገረ ስብከቱ ለተፈጠረው ችግር የመፍትሄ ጥሪ" የምትል መፅሄት መመልከት ይችላል። ለብዙዎቻችን ሲያንቀን የነበረው ይሄ ሃቅ አደባባይ መውጣቱ መልካም ነው። ሃቅ ያድናል እንጂ አይጎዳምና ያለፈውን ስህተት አርመን ወደፊት ለመሄድ እንድንችል እንደ ክርስቲያኑ ከያኒ ቴዎድሮስ ካሳሁን “የሄድንበት መንገድ ያሳዝናል” ማለት ያስፈልጋል።

Anonymous said...

I find this article very interesting. It discloses all the reality. That is it! Thank you!!

Anonymous said...

Dear MElake Besrat

Kale Hiywot yasemalin

This is the Absolute true history of the "Papas who called themselves exile SYNOD". You exposed them this what they are . Most of their followers now knows the reality, start leaving their groups, specially in Australia, New zealand also in USA and Europe, This is a powerful message for those people who are no information about those fIVE 5, people.

This is a great article with including the documents.
May GOD bless u Melake Besrat

Anonymous said...

This is veeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeery
trrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrruuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuueeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeee

እውነት ሲነገር እንዲህ ያንጣጣል መቸም ይገርማል ፡ ንጉሡ አፄ ዮሐንስ (ደጉ ዮሐንስ )እውነቱ ቢነገር ይህ አሣ ቆሞ ይሄድ ነበር
አሉ ይባላል፡፡ ታዲያ እስከመቸ ህዝብ ሲታለል ይኖራል ፡፡እንደኔ በወቅቱ ያልነበሩ ሰዎች ማወቅ ያለባቸውን እውነት እንዲያውቁ፡ መደረጉ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ፀሐፊውን ቃለ ሕይወት ያሰማልን እላለሁ

Anonymous said...

በጣም የሚያስደንቅ ነው። ለዘኢመጻ ፋርጣ ወአንዳቤት ኢቦኣ ውስተ ቤተክህነት። ወያኔ ዘረኛ ኣባ ጳውሎስ ዘረኛ ኣባ መርቆሬዎስ ዘረኛ ናቸው። በጥቅሉ ሁሉም ጎነደሬ ሁሉም ተግሬ ዘረኛ ኣየደሉም። ብዙ የምናውቃቸው ከዚህ ካንሰር በሽታ የጸዱ ወዳጆች ኣሉን ። ለዘረኝነት መስፋፋትና ለበክርስቲያን መከፋፈል የኣባ ጳውሎስና የኣባ መርቆርዎስ ከፍተኛ ኣስተዋጽዎ ኣለው። ሁለቱም የቤተክርስቲያን ካንሰሮች ናቸው። ደጀ ሰላሞች አግዚኣብህር ጸጋውን ያብዛላችሁ። አውነትን ለገለጽከው ወንድም አድሜና ጤና ይስጥልን። አንደ ኣበደ ውሻ አናንተን ለመንከስ የሚቾሁት ሁሉ ሚስጥሩ ስለታወቀባቸው ነው። ወንዱ ከኣውስትራሊያ

Anonymous said...

Dear Meleake Bistrat

Kalehiwot yasemalin!

You explicitly told us the real story and problem surrounding us. It is a great article and a great contribution towards finding defining where we are, and where we should go. We have to face the truth!! It is not because we are from this camp or from the other camp.

Muluken Abera said...

it's not worth,completely wrong!.

Anonymous said...

First, I thank DS for hosting opposing ideas.

As to the writer, in this piece of writing he or she seems very angry,emotional rather than being logical and resonable. I just feel it's propoganda of TPLF. The mean-spirit speaks volumes that this writer is against unity,facts,freedom you name it any good things. I want facts not trash emotions, feelings and others.Let me give you just one fact supported by evidence out of the tonnes of weyane's plan and excution to destroy our church.

Please read the excerpt below from late TPLF leader himself.
“የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር በ1979 አመተ ምህረት አስተሳሰብ ለዋጭ የፕሮፓጋንዳ መርሀ ግብር ለሚመለምላቸው ቀሳውስት ዘረጋ። የማሰልጠኑ ዓላማ ቤተ ክርስቲያኗን ከህዝብ ለይቶ በመምታት ስፋቷን ማጥበብና በትግሬአዊነት ላይ ብቻ የተመሰረተ ስሜት በትግራይ ተወላጆች ጭንቅላት መክተት ነው። ቤተ ክርስቲያኗ ለረዥም ዘመናት በህዝቡ አዕምሮ ላይ ስትተቀርጸው የኖረችውን ብሄራዊ የኢትዮጵያነትን ስሜት ከትግራይ ህዝብ አዕምሮ ጠራርጎ በጠባቡ ትግሬአዊነት ስሜት በመተካት የቤተ ክርስቲያኒቱን ይዘት እያጠበቡ ራሷን ቤተ ክርስቲያኒቱን መምታት ነው።...መነኮሳት በመምሰል ደብረ ዳሞ ወደ መሳሰሉት ገዳማት ሰርጎ በመግባት የድርጅቱን እቅድ በማስተጋባት የሚያዳክም አጥኝ ኃይል በስብሀት ነጋ መሪነት ተመሰረተ። "
source:ከቀድሞው የሕ.ወ.ሓ.ት. ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ መጽሐፍ

I just feel this junk is like "Feyel wedhi kizemzem wedia"
Please first educate yourself to be better citizen before some kind of junk and trash come out of your mouth.

Gebre Ke Etissa T/Haymanot

Anonymous said...

አዬ የጎጠኛ ነገር፣
አንዱ የዋህ ጎንደር ብሎ ብሔር የለም ብሎ ሊሞግተን ፈለገ
ትግሬ ብሎ ግን ብሔር አለ፡፡ ጎንደር ብሎ ብሔር አለመኖሩ የሚታወቅ ቢሆንም ነገር ግን ጎነደሬ ብሎ ጎጠኛ መኖሩ ሐቅ ነው፡፡
አንተ የሰው ምላስ ተውሰህ የመጣህ ሰው‹ ለመሆኑ ልትለን የፈለግከው ጎንደር የሚባለው ስም መላ ኢትዮጵያዊ በጥቅሉ የሚታወቅበት ስም ነው ማለትህ ከሆነም ተናገረውና እንስማህ፡፡

ብራዘር ችግር የለም ከሃያ አንድ ዓመት በኋላ ቢሆንም ችግሩ መኖሩን፣ የተወሰኑ የጎንደሬን ስም የሚያጠፉ ባለጌዎች በሠሩት አፀያፊ ሥራ ቤተ ክርስቲያን ተዋርዳበታለች፣ በጎቿ ደግሞ ከእግዚአብሔር መንገድ ወጥተው በአንድነትና በፍቅር ከመቆም ፈንታ በጠብና በክርክር ብሎም በጥላቻ እንዲተያዩ ሆኗል ብለህ በአይን በሚታየው እውነት እመንና በመፍትሔ ማፈላለጉ ላይ ተራዳን፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ጊዜ ያለፈበትን የጠባብ ጎንደሬዎችን (ሁሉንም ጎንደሬን ማለቴ አይደለም) ነጠላ ዜማ አታዚም፡፡ ማንም አይሰማህም፡፡ ምክር የምትሰማ ከሆንክ አገርህንና ቤተ ክርስቲያንህንም የምትወድ ከሆነ ከነዚህ ሰዎች ራስህን ለይተህ ውቀሳቸው፡፡ ከጥፋት መንገዳቸው ተመልሰውም ሕዝቡን በንስሐ ወደ ነበረበት የአንድነት ማዕድ እንዲመልሱት ምከራቸው፡፡ የእስካሁኑ ጉዞ እኛን አልጠቀመንም ነገር ግን ጠላቶቻችንን (ወያኔን ጨምሮ) አብቸንችኖአል፡፡ ይህን እንደምታውቅ እረዳለሁ፡፡
መቼም ከሃያ አንድ ዓመት በኋላ አንተ ገና ሳትነቃ ስለቀረህ አይመስለኝም ጎጠኝነት የተጠናወታቸው አንዳንድ ጎንደሬ ካህናት በአውደ ምሕረት ላይ እንኳ ሳይቀር በድፍረት ቆመው ሲደሰኩሩ እንደነበረው ጎንደር ብሎ ብሔር የለም የሚሉትን የምትደግምልን፡፡
ብራዘር! ያ ዘመን አልፎ እነሆ አሁን ደግሞ በዳያስፖራው መካከል ሁለተኛ አብዮት ቤተ ክርስቲያንን በበደሉ ጳጳሳት ላይ ተቀስቅሷል!! መቆሚያ ያለው እንዳይመስልህ፡፡ ምክንያቱም የነሱ ነገር የዛሬ 21 ዓመት እንደነበረው አሁን ደግሞ በውጪ አገር ሲያደርጉ በነበረው የአመጽ ሥራቸው ማሠሮው ሞልቶ መፍሰስ ስለጀመረ ነው፡፡ ገነፈለ ማለት ይህ ነው፡፡ ስለዚህ መላከ ብሥራት እንዳሉት ይብቃ!! ወደ አንድነት በሚወስደን ነገር ላይ እናተኩር፡፡ አንተ ልትሸፍንላቸው ብትሞክርም መላከ ብሥራትና እርሳቸውን የመሳሰሉ ሰዎች እንግዲህ በማስረጃ እያጋለጡአቸው ነው፡፡ ምን አለ በለኝ ገና ብዙ ሚሥጥር ይጎለጎላል፡፡
ሌሎቻችሁም ጎጠኞች የሆናችሁና ፀሐፊውንና ደጀ ሰላምን የምትጎነታትሉ በሙሉ፣ እስቲ አደብ ግዙ፡፡
እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ፡፡
በነገራችን ላይ መልአከ ብሥራት ( ኢትዮጵያዊው ዊኪ ሊክስ) መቼ ነው በደጀ ሰላም ላይ ዳግም ብቅ ብለው የምናይዎ? ካሁኑ እጅዎ ከምን!! ብያለሁ
ቃለ ሕይወት ያሰማልን
እኛንም ቸር ያሰማን

Anonymous said...

Medre forem hula.

Anonymous said...

It's Look like ETV.

Anonymous said...

Anonymous said...
First, I thank DS for hosting opposing ideas.

As to the writer, in this piece of writing he or she seems very angry,emotional rather than being logical and resonable. I just feel it's propoganda of TPLF. The mean-spirit speaks volumes that this writer is against unity,facts,freedom you name it any good things. I want facts not trash emotions, feelings and others.Let me give you just one fact supported by evidence out of the tonnes of weyane's plan and excution to destroy our church.

Please read the excerpt below from late TPLF leader himself.
“የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር በ1979 አመተ ምህረት አስተሳሰብ ለዋጭ የፕሮፓጋንዳ መርሀ ግብር ለሚመለምላቸው ቀሳውስት ዘረጋ። የማሰልጠኑ ዓላማ ቤተ ክርስቲያኗን ከህዝብ ለይቶ በመምታት ስፋቷን ማጥበብና በትግሬአዊነት ላይ ብቻ የተመሰረተ ስሜት በትግራይ ተወላጆች ጭንቅላት መክተት ነው። ቤተ ክርስቲያኗ ለረዥም ዘመናት በህዝቡ አዕምሮ ላይ ስትተቀርጸው የኖረችውን ብሄራዊ የኢትዮጵያነትን ስሜት ከትግራይ ህዝብ አዕምሮ ጠራርጎ በጠባቡ ትግሬአዊነት ስሜት በመተካት የቤተ ክርስቲያኒቱን ይዘት እያጠበቡ ራሷን ቤተ ክርስቲያኒቱን መምታት ነው።...መነኮሳት በመምሰል ደብረ ዳሞ ወደ መሳሰሉት ገዳማት ሰርጎ በመግባት የድርጅቱን እቅድ በማስተጋባት የሚያዳክም አጥኝ ኃይል በስብሀት ነጋ መሪነት ተመሰረተ። "
source:ከቀድሞው የሕ.ወ.ሓ.ት. ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ መጽሐፍ

I just feel this junk is like "Feyel wedhi kizemzem wedia"
Please first educate yourself to be better citizen before some kind of junk and trash come out of your mouth.

Gebre Ke Etissa T/Haymanot

ውድ ገብሬ
የምታወራው የጠፋብህ ይመስላል፡፡ ፀሐፊው በኢሞሽን ውስጥ ሆነው መፃፋቸውን፣ ጽሑፉን በንዴት ውስጥ ሆነው እንደፃፉት ተናግረሃል፡፡

ዋናው የጽሑፉ ጭብጥኮ አምስቱ ጳጳሳት ፣፣ስደተኛ›› የተባለ ሲኖዶስ ማቋቋማቸውና የዚህ ድርጊታቸው ሕገወጥነት ነው፡፡ በዚህ ሳቢያም ቤተ ክርስቲያኒቱና ልጆችዋ የማያስፈልግ ዋጋ ከፈሉ ነው፡፡ ለዚያውም በጣት ለሚቆጠሩ ራስ ወዳዶች ፍላጎት!!
እንጂ ፀሐፊው ሲጽፉ የነበራቸውን ስሜት ለማወቅ የጓጓም፣ የጠየቀህም የለም፡፡ ባንተው ብሶ ደግሞ ፍየል ወዲህ ቅምዝምዝ ወዲያ እያልክ ልታምታታን ትፈልጋለህ፡፡ ስሜትህን ተቆጣጠረው እንጂ ጎበዝ!፡፡
ልብ ካለህ ይልቁንስ በነአቡነ ዜና ማርቆስና በነ አቡነ መልከ ፀዴቅ አማካኝነት ስለተቀነባበረውና ማስረጃ ስለቀረበበት መፈንቅለ ፓትሪያርክ ጉዳይ ላይ አነጣጥረህ የምትለውን ካለህ በል እንስማህ፡፡ እኛ የምንፈልገው የሚሳደብ ሳይሆን ገንቢ ሃሳብ የሚሰነዝር ሰው ነው፡፡ ዋናውን ጉዳይ ትተህ ፀሐፊውን መስደብህን ተው፡፡ በወያኔ ስም መነገድ ከእንግዲህ ስለማይቻል ወያኔ ምናምን የሚለውን ነገር ከንግዲህ እዚህ መድረክ ላይ ባታመጣ ይሻልሃል፡፡
ስለ መናደድ ካነሳህማ አንተና መሰሎችህ የተናደዳችሁት ጎጠኞችና ጎሰኞች ስለተባላችሁ፣ እቅጩ ስለተነገራችሁ ነው፡፡ እውነቱ ሲነገረው ብዙ ሰው ይበሳጫል፡፡ ፀሐፊው ቢናደዱ ደግሞ እናንተ በቤተ ክርስቲያናችንና በኛ ላይ 21 ዓመት ሙሉ በሠራችሁብን ቁጭ በሉ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ያልተናደደ ሰው አታገኝም እረፈው!!! በቁጭ በሉ ሞሳ ተሠርቶ እየሳቀ ወደ ቤቱ የሚገባ ሰው ቢኖር እብድ ብቻ ነው፡፡

Anonymous said...

I would like history to be a witness. who is racist ? Who is the most courapted ? Who is the most divisive ? TPLF ,as its name stands for, it's for "stupid Tegree" not for loving,caring,and good people of Ethiopia. You can post as many articles as you wish ,the fact is the church is colonized by TPLF for the last two decades. Now,you want play a blaming game for what you did.It doesn't work this time.No more division on race,gender,religion,and etc. To overcome and destroy this divisive cancer "TPLF",we must stand united.

God bless mother. Ethiopia!!!

Anonymous said...

wow, now I know the problem began centuries ago;when king hailesilassie,menilik were using the church to suppress the people of Ethiopia. God bless you, an honest writer. Dejeselam, thank you for posting it. Now I know the truth. Why do we say all the problems we have in our church happened in the last 21 years; when it really began hundreds years ago.

Anonymous said...

መልዐከ ብሥራት ያሉት ትክክለኛና የተረጋገጠ ማስረጃ ነው። ደጀ ሰላም አንዳንዴ ጽሁፎችን ስለሚደብቅ እንጂ እኔም እዚህ ስለአሉት ስለ አብ ሃብተ ማርያም (አባ መልከ ጼዴቅ) የማውቀውን ብዬ ነበረ ነገር ግን ታፍኖ ቀርቶአል። እዚህ በውጨ ያለው የመነኮሳት ስብስብ ከፓትሪያርኩ ጀምሮ ከጥንቱም የሚመሩት በእኚሁ ከላይ ስማቸውን በጠቀስኳቸው ሰው ስለሆነ ቤተ ክርስቲያንኗን ለመክፈል ለተደረገው ለውደፊትም ለሚሆነው ሁሉ ተጠያቂው እሳቸው እንጂ ሌሎቹ አይደሉም ይህንን በሚገባ አውቀዋለሁ። እኚህ ሰው ለእድሜ እንደታደሉት ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ችግር ለመፍጠር ምንም ጊዜም እንደ መልካም ነገር ታድለውታል። ይህን እድል ግን ለንስሐ ቢሆን እንዴት መልካም ነበረ። ጎጠኛ ናቸው ፖለቲከኛ ናቸው ይህ ትክክለኛ መለያቸው ነው አልተጋነነም። እርቁም የሽፋን መንገድ ነው እንጂ እሳቸው በሕይወት እያሉ ይሆናል ማለት አይደለም። እሳቸው እርቅን ፈልገውት ሳይሆን የተኛውን ፖለቲካ ቀስቅሶ ጉዙውን ለመቀጠል እንጅ እስከ እማውቃቸው ድረስ እልህኛና ትዕቢተኛ መሆናቸውን ነው ነገር ግን እዚህ በውጪ ያለውን ትውልደ ኢትዮጵያ አብዛኛው ማለት ይቻላል ብዙ የነገሩ ግንዛቤ ስለሌለው ፖለቲካውን በማንተራስ ከወዲያ ወዲህ ያተራምሱታል እነሱም እነውቱን አጥተውት ሳይሆን መኖር የሚቻለው በዚሁ አካሄድ በመሆኑ ነው። የአባ ጳውሎስ ችግር ራሱን የቻለ ስለሆነ ከነሱ ሁኔታ ጋር የሚያገናኘው አይደለም። ችግሩን ብቻም ማውራት መፍትሄ ስለማይሆን ክርስቲያኑ ህብረተሰብ ነገሮችን በጥንቃቄ መመርመርና እውነቱ የት እንዳለ ለማወቅ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አለበት። በሆነው ባልሆነው መከፋፈል ግን የሚበጀው ለጠላት ነውና እውነትን በመነጋገር መተራረም ከሌለ የባሰ ሁኔታ ውስጥ መዘፈቅ እንጅ ምንም የሚያመጣው አንድም ነገር ስለሌለ ከልብ እናስብበት። እነሱንም እንዲታረሙና ቤተ ክርስቲያን በትክክል እንዲመሯት ካስፈለገ በእውነት ላይ ተመሥርተን በመወያየት አንድነትን ማምጣት ከቻልን ብቻ ነው። በእውነት ላይ የተመሠረተ አንድነት ቤተ ክርስቲያንንም ሆነ ሀገርን ከጥፋት ያድናልና እንበርታ እንወያይ። እግዚአብሔርም በቸርነቱ ይርዳን። ደጀ ሰላሞችም ላባችሁን ሰፋ አድርጋችሁ ለማወያየት በርቱ እላለሁ፡

Anonymous said...

ይድረስ ለደጀ ሰላም፦ ምን ጉድ እየሰማንና እያየን ነው? እስካሁን ይፋ የወጣው አሰቃቂና አሳፋሪ በደል አልበቃ ብሎ፣ በሁለቱም ወገን ያሉት አባቶች ገና ምኑ ታይቶ ብዙ የምንጎለጉለው ጉድ አለ እያሉ በመዛት ውዝፉን ሁሉ በመገናኛ ብዙሐን ጭምር ለመንዛት እየፎከሩ ነው። ኧረ ስለ ቤተ ክርስቲያኗ ስትሉ ተዉ በሏቸው!! ይልቁንስ እገሌ ከእገሌ ሳይባል ሁሉም ተጸጸተውና በመካከላቸው ዕርቀ ሰላም መሥርተው በጋራ ሱባኤ ልዑል እግዚዝብሔርን ይቅርታና ምህረት ይለምኑት። ይምራቸዋል። እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኗን ከመከፋፈል፣ ምእመናኑን ግራ ከማጋባትና ከመበታተን ያድናቸዋል። የሃያ ዓመት ሽፍንፍን በደል፣ ግፍና ስቃይ ይበቃዋል። ስለ እውነት፣ ስለ እርቅ፣ ስለ ሰላምና ስለ አንድነት አዘውትረው የሚሰብኩትን ትምህርት እነርሱም ዛሬ ደፍረው በተግባር ላይ ካዋሉት ሕዝቡ አምኖ አባቶቼ ብሎ ይቀበላቸዋል። የቤተ ክርስቲያኗን ሕግ ማስከበርና አንድነቷን መጥበቅ የሚቻለውም በዚህ በተቀደሰ መንገድ ብቻ ነው።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)