February 28, 2013

ደጀ ሰላም ከወራት በፊት አቡነ ማትያስ እንደሚሾሙ ያሳወቀችው እውን ሆኗል፤


አዎን፤ አቡነ ማትያስ 6ኛ ፓትርያርክ ሆነዋል

  •      ደጀ ሰላም እያካሄደች ባለችው መደበኛ ያልሆነ “የድረገጽ” ድምጽ አሰጣጥ አቡነ ማቴዎስ ብዙ መራጭ አግኝተዋል፤
  •     ምርጫውን ለሚቃወሙትም፣ ለሚደግፉትም ቀጣዩ ጉዞ እንዴት ይሆናል? እንዴትስ መሆን አለበት?
  •      በውጪ አገራት ካሉ ምእመናን፣ ካህናትና አብያተ ክርስቲያናት የሰከነና የጋራ የሆነ ዘላቂ መፍትሔ ይጠበቃል፤
  •      ውጪ አገር ካለው ሲኖዶስ የበሰለና ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ህልውና የሚበጅ አቅጣጫ ይጠበቃል፤
  •      ድራማው ተጠናቋል፣ ውይይቱ ይቀጥላል።

Not Breaking News: Abune Mathias Has won


የ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫው ወደ መጠናቀቁ ነው


  •     ደጀ ሰላም እያካሄደች ባለችው “የድረገጽ” ድምጽ አሰጣጥ አቡነ ማቴዎስ ቅድሚያውን ይዘዋል፤
(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 21/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 28/2013/ PDF)፦ አምስቱን እጩ ፓትርያርኮች ያካተተው የ6ኛው ፓትርያርክ መርጫ ይህንን ዜና በሠራንበት ወቅት እየተካሄደ ሲሆን ከመራጮች አብዛኛዎቹ ድምጻቸውን ከኮሮጆው ውስጥ እንደጨመሩና የቀረው የመራጭ ቁጥር ከ100 እንደማይበልጥ ታውቋል። የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮችን ጨምሮ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጀምሮ በየደረጃው ድምጽ መስጠት የሚችሉት መራጮች ያለ ምንም ግርግርና ወከባ ድምጻቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ከዚህ አስቀድሞ ዛሬ ጠዋት በተደረገላቸው ገለጻ “ምርጫው ነጻ እና መራጮችም ያለ ምንም ችግር የራሳቸውን እጩ ብቻ እንዲመርጡ” ምክር ተለግሷቸዋል። በቀሩት ሰዓታት ቀሪ መራጮች ካርዳቸውን ከኮሮጆው ከጨመሩ በኋላ  አሸናፊውን መለየት ወደሚያስችለው ሥርዓት ይሸጋገራሉ።

February 26, 2013

የ5ቱ እጩ ፓትርያርኮች አጭር የሕይወት ታሪክ


(MK Website/ PDF http://bit.ly/YwKqd1):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ አስመራጭ ኮሚቴ በመሠየም እጩ ፓትርያርኮችን ለመምረጥ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ ከካህናት፤ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች፤ ከማኅበረ ቅዱሳን፤ እንዲሁም ከምእመናን ጥቆማ እንዲያካሔዱ ተደርጓል፡፡ በተካሔደው ጥቆማ መሠረት አስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማውን በግብአትነት በመጠቀም አምስት ሊቃነ ጳጳሳትን በእጩነት በማቅረብ የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርቧል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም ከየካቲት 16 – 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ውይይት በማካሔድ አምስቱም ሊቃነ ጳጳሳት በእጩነት እንዲቀርቡ አጽድቋል፡፡

February 25, 2013

ሽማግሌዎች ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን አነጋገሩ፤ አስመራጩ መግለጫ ሰጠ


(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 18/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 25/2013/ PDF)፦ ቅዳሜ የካቲት 16/2005 ዓ.ም ቀርበው በአብዛኛው የቅ/ሲኖዶስ አባላት ይሁንታ አግኝተዋል የተባሉት አስምት ሊቃነ ጳጳሳት በመጪው ሐሙስ ለሚካሄደው የፓትርያርክ ምርጫ ያለፉ መሆናቸውን አስመራጭ ኮሚቴው ዛሬ በጋዜጣዊ መግለጫው ገልጿል።

February 24, 2013

የዕጩዎች ምርጫው እንደፈለጉት ያልሆነላቸው ጳጳሳት ሙግት ገጥመዋል

(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 16/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 23/2013/ PDF)የስድስተኛው  ፓትርያርክ  አስመራጭ   ኮሚቴ  በዛሬው   ዕለት  የዕጩዎቹን  ዝርዝር  ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባቀረበበት ወቅት ምርጫው በፈቀዱት መልክ አልሔደላቸውም የተባሉ ጳጳሳት ሙግት ገጥመው መዋላቸውን የደጀ ሰላም ምንጮች ገለፁ።

“ፓትርያሪክ እንድሆን የመንግስት ባለሥልጣን አላግባባሁም” (ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)


  • ‹ካህናትና ምእመናን ለቤተ ክርስቲያንና ለቤተ ክርስቲያን ብለው ብቻ ማሰብ፣ ይገባቸዋል›› - (ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)

(አዲስአድማስ ጋዜጣ፤ የካቲት 17/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 24/2013/ PDF)የምርጫው ሂደት በይፋ ከተጀመረ አንሥቶና ከዚያም በፊት ቀጣዩ ፓትርያሪክ እንደሚኾኑ ብዙ ከተነገረላቸው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል አንዱ ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በፓትርያሪክነት ምርጫው ከሚሳተፉ ከ800 በላይ መራጮች የምርጫ ድጋፍ ለማሰባሰብ በሥልጠና ስም በርካታ ገንዘብ ማውጣታቸውን፤ በሕንፃ ኪራይ፣ በሥራ ምደባ፣ በውጭ ተልእኮና በሹመት አሰጣጥ ለብዙዎች ቃል መግባታቸውን፤ ከዚህም አልፎ ቀጣዩ ፓትርያሪክ እርሳቸው እንደሚኾኑ ራሳቸውን ለመንግሥት አካላት ስለ ማስተዋወቀቸው በአንዳንድ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡

February 20, 2013

የውጪውን ጠላት ለመመከት በቅድሚያ የውስጥ ችግሮቻችንን ማስወገድ ይኖርብናል


ቤተ ክርስቲያን አልተከፈለችምበሚለው መጣጥፍ መነሻነት የተዘጋጀ ….
(ከመልዐከ ብሥራት፣ ቨርጂኒያ/PDF)፦ ጌታቸው ኃይሌ ናቸው ለዚህ ጽሑፌ መነሻ የሆኑኝ። በቅድሚያ ልባዊ ምሥጋናዬና አክብሮቴ ይድረሳቸው፡፡ በዚህ ጽሑፌ የምናገረው በእውነት ለቤተ ክርስቲያን ለሚጨነቁ ምዕመናንና አገልጋዮች ብቻ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ላለፉት ሃያ አንድ ዓመታት በታላቅ ፈተና ውስጥ አልፋለች፡፡ አሁንም እያለፈች ነው፡፡ እግዚአብሔር አይበለውና ምናልባት የከፋው ፈተና ያለው ከፊት ለፊታችን ሳይሆን አይቀርም፡፡ የዚህም ሰበቡ ችግሮቻችንን በቅጡ ካለመረዳታችንና ከቸልተኝነታችን የመጣ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ለመሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ችግሮች በተለይ በውጪው ዓለም ምንና ምን ናቸው?

አስታራቂ ጉባኤው መግለጫ አወጣ

(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 13/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 20/2013/ PDF)፦ በአባቶች መካከል የተፈጠረውን መለያየት ላማራቅና ዕርቅ ለማውረድ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የቆየው የሰላምና አንድነት ጉባኤ ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ አወጣ። የመግለጫው ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ላለፉት ሦስት ዓመታት በአገር ቤትና በውጭው ዓለም የሚገኙ አባቶችን በማስማማት ቤተ ክርስቲያንን አንድ ለማድረግ ያደረገውን ከፍተኛ ጥረት በዝርዝር ለመግለጽና የዕርቁ ሒደት ምን ይመስል እንደነበር በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም ለሚኖሩ መላው ኦርቶዶክሳውያን ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምርን እንዲያውቁት ለመግለጽ ነው” ያለው መግለጫ ዝርዝር ሐሳቦችን አካቷል። ሙሉ ቃሉን ከዚህ በታች ተመልከቱ።

February 9, 2013

ሁሉንም ጊዜ ይፍታው


(ገብሩ ለክርስቶስ በተለይ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት/PDF)፦ “ወሰብአ ኢትዮጵያ ኢይሢሙ ላዕሌሆሙ ሊቀ ጳጳሳት እማእምራኒሄሙ  ወኢበሥምረተ ርእሶሙ፡፡ እስመ ጳጳሶሙ ይከውን እምታእተ እዴሁ  ለበዓለ  እስክንድርያ   ዘይደልዎ  ይሢም ላዕሌሆሙ ሊቀ  እምኀቤሁ  ዘውእቱ  መትሕተ ሊቀ  ጳጳሳት”፤ ትርጉም የኢትዮጵያ  ሰዎች ከዐዋቂዎቻቸው ወገን በራሳቸውም ፈቃድ ሊቀ ጳጳሳትን ለራሳቸው አይሹሙ፡፡ ጳጳሳቸው ከእስክንድርያ በዓለ መንበር ሥልጣን በታች ነውና፡፡ ከሊቀ ጳጳሳት በታች የሆነውን ሊቀ ጳጳስ  ከእነርሱ ወገን ሊሾምላቸው የሚገባው እርሱ ነው፡፡” (ፍትሐ .ነገ አንቀጽ 2 ቁ 50)::

February 5, 2013

“ሢመት”

(ከመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው የጡመራ መድረክ የተገኘ/ PDF):- ሢመት፦ ሹመት፥ ሥልጣን፥ ማዕርግ ማለት ነው። የሚሾም፥ የሚሸልም፥ የሚያሠለጥን፥ የሚቀድስ፥ የሚያከብር ደግሞ እግዚአብሔር ነው። የይሁዳ ገዢ ጲላጦስ፦ ጌታችንን፦ “ልሰቅልህ ሥልጣን እንደ አለኝ፥ ወይም ልፈታህ ሥልጣን እንደ አለኝ አታውቅምን?” ባለው ጊዜ፥ “ከሰማይ ካልተሰጠህ በቀር በእኔ ላይ አንዳች ሥልጣን የለህም፤” ያለው ለዚህ ነው። ዮሐ ፲፱፥፲-፲፩።

February 2, 2013

በኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመን አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ካህናት፣ ዲያቆናትና ምእመናን የተማኅጽኖ ደብዳቤ

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለዉ "ከሁሉም ግን ፍቅር ይበልጣል።"
(READ THIS ARTICLE IN PDF)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በውስጧ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ቤተ እምነቶች ጋር እንኳ ፍቅርን በማስቀደም በመፈቃቀርና በመከባበር በክርስቶስ ራስነት፣ በሐዋርያት አስተምህሮና እምነት መሠረት ላይ ሐዋርያዊ ተልእኮዋን ስታፋጥን ዘመናትን አስቆጥራ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እኛ ካለንበት ዘመን ደርሳለች። የቤተ ክርስቲያኗ ሐዋርያዊ ጉዞ በርግጥ ጥንትም ቀላል አልነበረም።

“አንድ ክርስቶስ!” “አንድ ሲኖዶስ!” “አንድ መንጋ!


(ወልደ  አረጋዊ፤ በተለይ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት/ PDF)፦ ሕት ጣፋጭም መራራም ዋዋን ደጋግማ ትግታለች፡፡ ዛሬ ረቡዕ ሰው፣ ብሎም ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ በመሆኔ ብቻ እጅግ መራራውን የሕይወት መርዶ ተጎንጭቻለሁ፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያኔና በምዕመኑ ላይ በግፍና በማን አለብኝነት ስለተዘጋብን “የሰላም በር” መርዶ ሬት ሬት እያለኝ ሰምቸዋለሁ፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)