January 14, 2013

Kesis Dr. Mesfin Tegegn on ESAT

5 comments:

Anonymous said...

ሊነጋ ነው መሰለኝ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነት ሲነገር ሰማሁ-ተመስገን አምላኬ። "የተማረ ይግደለኝ!" እሚለው የኛው ሰው እንድህ ያለ ተልቡ ውስጥ እሚገባ ሲያገኝ ነው። ጎበዝ ደነቆርን እኮ! እውነቱ እሚነግርን ማነው? ዋናው የጉዳዩ ባለቤት 4ኛው ፓትሪያርክ ቢለመኑ ፤ቢባሉ ምንም!! ትንፍሽ የለም። እንዲህ ባለ አብይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የተፃፉት መፃህፍት ሁለት ብቻ ናቸው። የአባ መልከፄዴቅ ቋሚ ምስክርነት እና የመምህር ጌታሁን የሐሰት ምስክርነት እና ሶስተኛው በመፅሄት መልክ የወጣው የአቡነ ይስሐቅ ምስክርነት ናቸው። እኤአ በ1993 የወጣው የታላቁ አባት አቡነ ይስሐቅ ጽሁፍ የሚከተለው ይገኝበታል " የትግራይ ነፃ አውጭ ያቋቋመው መንግሥት ፓትሪያርኩን አቡነ መርቆሬዎስን በዘዴ ለማውረድ የሃገሪቱን ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት በመሸንገል፤ በማማባል፤ ሹመት በማጓጓት፤ በማስፈራራት አስተባበራቸው።የካቲት 15/1989 አ/ም የወጣው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በርዕሰ አንቀፁ እንደገለፀው "በራሳቸው ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሥልጣን ፈላጊነት እና ግፊት" ታምሜአለሁ ብለው መንበራቸውን ለቀቁ። "በራሳቸው ረዳት ሊቀ ጳጳስ" የሚለው ዛሬ አሜሪካ በስደት የሚኖሩትን ብፁእ አቡነ ዜና ማርቆስን ነው። ጳጳሳቱና ሊቃነ ጳጳሳቱ የፓትሪያርኩን ከስልጣን መውረድ ተቀብለው የፓትሪያርኩን ሥራ ወር ተራ (የሦስት ወር እብሬት) ገብተው በቡድን ማካሄድ ጀመሩ። የመጀመሪያው ቡድን በብፁእ አቡነ ዜና ማርቆስ ሊቀ መንበርነት እየተመራ የቤተ ክርስቲያኗ ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት ሌላ ፓትሪያርክ ለመምረጥ ዝግጅታቸውንና ቡድን እየፈጠሩ ውይይታቸውን ቀጠሉ። የነ አቡነ ዜና ማርቆስ ወር ተራ ሲያልቅ እነሱን የተካው አዲስ ቡድን በውስጥ ለውስጥ ምክክር አሸንፎ በጩነት ያቀረባቸው አቡነ ጳውሎስ አምስተኛ የኢትዮጵያ ፓትሪያርክ ለመሆን በድምፅ ብልጫ ተመረጡ። ስለምርጫው ውይይት በሚደረግበት ጊዜ ፓትሪያርኩ ሳይታመሙ ታመዋል ተብሎ ከመንበራቸው መውረዳቸው ከተቀበሉት መህል ጥቂቶቹ በተለይም እነ ብፁእ አቡነ መልከጼዴቅ እብሬታቸው አልፎ ምርጫው እነሱ በሚፈልጉት መንገድ እማይሄድ መሆኑ ሲያዩ በውይይቱ ጊዜ አድመውና አኩርፈው በስብሰባው ላይ ሳይገኙ ቀሩ። ጓደኞቻቸው የሲኖዶስ አባላት ወር ተራችንን ለምን አስለቀቁን ብለው ሲኖዶሱን "መፈንቅለ ሲኖዶስ ተፈጠረ" "በኩዴታ የተፈጠረ ማህበር" የሚል ፈሊጥ አመጡበት። እኔም በዚያን ጊዜ ከሁሉም ይልቅ ቅድሚያ ሊሰጠው እሚገባውን"ፓትሪያርክ በህይወት እያለ ሌላ ፓትሪያርክ አይሾምም። የሚለውን የቤተ ክርስቲያን ህግ ይዤ ስጮህ በቂ ድጋፍ በማጣቴ ተሸነፍኩ። አኩርፈው በስብሰባው ሳይገኙ ከቀሩት ማህል ብፁእ አቡነ መልከጼዴቅ በአቡነ ጳውሎስ ሹመት ጊዜ በሥራተ ሲመቱ ተካፍለው፤ "ሹመት ያዳብር" ብለው፤ በአዲሱ ፓትሪያርክ ተባርከው ካገር ከወጡ በኋላ በስደት አሜሪካን አገር ሲደርሱ "ፓትሪያርክ በህይወት እያለ ሌላ ፓትሪያርክ አይሾምም" የሚለውን ቀኖና ይዘን ከምንጮኸው ጋራ አንድ ሆነው የተቃውሞ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ቁጥራችንን አበዙልን። አዎ ብዙ የተደበቁ እውነቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ቀሲስ መስፍን እንዳሉት እውነቱ ይነገረን። ወገንተኝነታችን ለቤተ ክርስቲያንችን ብቻ ይሁን። እግዚአብሔር ሃገራችንና ቤተ ክርስቲያናችንን ይባርክ

Anonymous said...

Thank u Kesis endew min laderghi angeten new yaraskew.lets know the truth for once and for all.
1= what hapen in that meeting?
2= Let Abune merqoryos speak about what hapen in that day? I realy don't want to hear abune melkesedik.
3= If there were any video about that meeting the synodos in ethiopia should realese it and close this case for once and for all.

Finally i just wann say you are a brave tewahedo son kesis,u did ask the real question unlike the rest of fake and celiberty preachers,zemaryan,diaqonati.menokasati,papassati and specailly sunday school members. From denver to minnosota,from dc to losangeles,from vegas to atlanta non of the megilecha ask this question what hapen that day? but it is easy for them to send megilecha to dejeselam... ayeee ye-america cristina....

ye-vegasu

Unknown said...

ኹለት ነገሮች፦

1) ከቤተ ክርስቲያን ምንጻር (perspective) አኳያ በቅጥነተ ልብ ለሚመለከት፦ ርሷን ሊጠብቁ ራሷ ቀብታ ያነገሠቻቸውን "ሥዩማነ እግዚአብሔር" መንግሥት፥ ርሷን ሊያጠፉ በርሷ ጠላቶች ቅባት ከነገሡ "ሥዩማነ ዕልወት" መንግሥት ጋራ በእኩል ዓይን ማየት ይቻላል ወይ? እንደ ቤተ ክርስቲያን እይታ ያፄዎቹ መንግሥት ከደርግ እና ወያኔ መንግሥት ጋር ንባብ ቢያሳብረው ምስጢር አያሳብረውም!

2) ደግሞስ እስከ አቡነ ባስልዮስ ዘመን ድረስ ወደዃላ እየተጓዙ "እንዲያ ነበር፥ እንዲህ ነበር" ማለት "ዓሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል" እንደተባለው አይኾንምን?

ይልቅ ከሰሞኑ መጣጥፎች ክሽን ብሎ የሚያረካ አስትያየት ያገኘኹት "ስምዐ ጽድቅ" ያስነበበችውን ነው። እንዲህ የሚል ያለበትን፦

"አንድ ቦታ ላይ አቁመን የትናንቱን የውዝግብ አጀንዳ እንዝጋው። መቃቃርና መገፋፋት በተጠናወተው መንፈስ ስለትናንት ጥፋት ብቻ መነጋገር አቁመን ስለ ነገም የቤተ ክርስቲያን ዕድገት እንምከር።"

ባካችን ይችን ምክር እንስማ!

beEwunet said...

@Geez Online

እውነት ነው! አሁን ቁም ነገሩ Geez Online እንዳሉት ነው! የፈሰሰ ውሃ አይታፈስ አይደል የሚባለው ያለፈው ታሪክ አልፏል አሁን ቤተ ክርስቲያናችን ያለፈውን የተበላሸውን ታሪኳን የምታስተካክልበት ምቹ ጊዜ ዛሬ እና ዛሬ ብቻ ነው!!!

Anonymous said...

ክፍል 2
አወ "ለቤተክርስቲያኔ ተቆርቋሪ ነኝ፣ እኔም የቤተክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል" የምንል ከሆነ ደግሞ፤ በውስጣችን ያለውን ፍርሃት እና ራስ ወዳድነት አሽቀንጥረን እንጣለውና፤ ለእምነታችን፣ ለቤተክርስቲያናችን ድምፃችንን ከፍ አድርገን በተግባር እናሰማ።

ከሙስሊም ወንድሞቻችን ስለእምነታችን በድፍረት መናገርን እንማር። የይስሙላ እምነት ወይም ሲመቸን አማኝ መሳይ፣ ቤተክርስቲያን ስትበደል ታዛቢ ወይም ከንፈር መጣጭ መሆን ቤተክርስቲያንን ከጥፋት አይታደጋትም።

ስለዚህ ቤተክርስቲያናችንን ለማጥፋት የተጀመረውን ሴራ እኛ አውቀን ካላከሸፍነውና ቤተክርስቲያናችንን ካልተከላከልን፤ ለጥፋቱ የመጀመሪያ ተጠያቂዎች ጥፋት አድራሹ ዓላማውን እያሰካ ያለው ወያኔ ሳይሆን፤ ቤተክርስቲያናችን እንደምትጠፋ እያወቅንና መከላከል እየቻልን ያልተከላከልነው እኛው እናምናለን የምንለው እንሆናለን።

ወያኔ በብልጣብልጥ አካሄዱ ሆድ አደሮችን በመያዝ፣ አንዴ ጠበቅ አንዴ ለቀቅ እያደረገ ምእመኑም ተስፋ ቆርጦ ግዴለሽ እንዲሆን በማድረግ፣ ቤተክርስቲያንን ቢቻለው ማጥፋት፣ ካለዚያም የተሃድሶያውያን የማድረግ ዕቅዱን ደረጃ በደረጃ እያሳካ ነው። አሁንም ቢሆን መጭው የጥምቀት በዓል እስከሚያልፍ ድረስ የከረረ እርምጃ ሳይወስድ ግን ዓላማውን የሚያከሽፉበትን መንገዶች እየተከላከለ ይቆይና የጥምቀት በዓላት ካለፉ በኋላ ጡጫውን ማንሳቱ አይቀሬ ነው።

ስለዚህ አሁን መንግሥትም የተስማማ ወይም ከአቋሙ የረገበ ቢመስል እውነት እንዳይመስላችሁ። የሩቅ የሩቁን ክስተቶች እንተዋቸውና ከዋልድባ ገዳም መታረስ ምን እንማራለን? አንድ አድርገን ብሎግ እንዳስነበበችን "ቦታው የትግራይ ክልላዊ መንግስት አካል እንጂ የአማራ ክልላዊ መንግስት አይደለም ስለዚህ በገዳሙ ላይ ሃሳብ መስጠት የሚችሉት የክልሉ ተወላጅ የሆኑት መነኮሳት እንጂ ማንም አይደለም" ያሉትን እስኪ እናጢነው። መጀመሪያ ወረዳውን ከአማራ ክልል ወደ ትግራይ ወስደው ከለሉ፣ ከዚያ ቦታው የትግራይ እንጅ የአማራ አይደለም በማለት የዘረኝነትን መርዝ በቤተክርስቲያናችን፣ ያውም ዓለም በቃኝ ብለው ባሉት አባቶች መካከል መንዛት ማለት ምን ለማለት ነው? የትግራይ ኦርቶዶክስ አማኞች ገዳሙ እንዲፈርስ ይስማሙበታል ለማለት ነው? ወይስ በዘር ሽፋን ድጋፍ ለማሰባሰብ?

ስለዚህ በምንም ነገር ሳይዘናጉ እና ጊዜ ሳያልፍ በእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ለሚገኘው ምእመን እውነቱ ፍርጥርጥ ተደርጎ ይነገረውና፤ የጥምቀት በዓል ሕዝበ ክርስቲያኑ በአንድነት የሚሰባሰብበት ቀን በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ሰው "የቤተክርስቲያኔ ጉዳይ እኔንም ያገባኛል" "ሕገ-ቤተክርስቲያን ይከበር" "ከፓትርያርክ ምርጫ - እርቅና ሰላም ይቅደም" ብለን ድምፃችንን በአንድነት ከፍ አድርገን ማሰማት ይኖርብናል።

ይህን ማድረግ ካልቻልን ግን ወደዳችሁም ጠላችሁም በትናንትናው ዕለትም “አቡነ መርቆርዮስ ከሚመለሱ፤ ለምን መንግስቱ ኃይለማርያም ይምጣ አትሉም” በማለት አባይ ፀሐዬ አሁንም ወያኔ ከእቅዱ ወደ ኋላ እንደማይል አርድተውናል http://www.zehabesha.com/archives/15936 ይመልከቱ። ቀደም ሲልም አቦይ ስብሃት በቅዠት ሳይሆን በእቅዳቸው ላይ ያለውን "ጳጳሳቱ አይረቡም፣ ቤተክርስቲያኒቷ ትበታተናለች" ብለው በድፍረትና በንቀት እቅጩን እንዳረዱን "እረኞቹ ከተበተኑ መንጋውን ለመበተን ቀላል ይሆናልና፣ለቤተመንግሥት ሕግ የማይጠቀምበትን የእድሜ ገደብ በፓትርያርክ ምርጫ መስፈርት አስገብቶ አባቶችን ከጨዋታ ውጭ አድርጎ ማሰደዱ አይቀሬ ይሆናል።

ያኔ እንወዳታለን የምንላት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የተሃድሶያውያን መፈንጫ ትሆናለች። ወደዳችሁም ጠላችሁም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሚለውን ስም ብቻ ወርሰን እንዳሉትም እኛ ከፈቀድን እንታደሳለን ካልፈቀድንም ተበትነን እንቀራለን።

ስለዚህ ይህ ከመሆኑ በፊት የጥምቀት ዕለት ድምፃችንን ከፍ አድርገን በማሰማት ሃይማኖታዊ ግዴታችንን መወጣት ይኖርብናል። እስከ ጥምቀት ድረስ እያንዳንዱ ሰው ለሚያውቀው ሕዝበ ክርስቲያን ይህንን ሃይማኖታዊ ጥሪ ማስተላለፍ እና በቂ መንፈሳዊ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል።

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኑን የሚጠብቅ አንድ ሙሴን ይልክልን ዘንድ እንለምነው።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)