January 3, 2013

አባቶች ሆይ አብነታችሁን አሳዩን

(መ/ር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ/ PDF):- በቀድሞ ዘመን ማዶ ለማዶ በመንደር ተለያይተው በቅርብ ርቀት ላይ  የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንደነበሩ ይነገራል፡፡ እነዚህ ህዝቦች ታዲያ ባልታወቀ ምክንያት ቅሬታ ፈጥረው በሆነው ባልሆነው ምክንያት እስከ መካሰስ ደርሰው ነበር፡፡ ልዩነታቸውም እየሰፋ ሲመጣ አንዱ ለሌላው መጥፎ ስም መስጠት ጀመረ፡፡ ከአሉባልታዎቹም መካከል፡- የታችኛው መንደር የላይኛዎቹን፤እዚያ ማዶ ያሉት ቡዳ ናቸው ሲሉ፡- በላይኛው መንደር ያሉትም በተራቸው፤ታች መንደር ያሉት ቡዳ ናቸው  እየተባባሉ እርስ በርሳቸው ይተማሙ ነበር፡፡ በሌላ መንደር የሚኖረው ሕዝብም ሁለቱን በቡዳነት ፈርጆ የሚቀርባቸው እስኪያጡ ድረስ ራሳቸው ባመጡት ጣጣ ገለልተኞች ሆነው ብዙ ዘመን ኖሩ፡፡


ከቀኖች በአንደኛው ቀን ከታችኛው መንደር አንድ የመሸበት መንገደኛ ወላጆቹ ቡዳ እንደሆኑ ከነገሩበት ላይኛው መንደር ደረሰ፤ እንዳይገባ ፈራ፤ አልፎ ከሄደ ደግሞ መሽቷልና የጅብ እራት ሊሆን ነው፡፡ ስለዚህም ጥቂት ካመነታ በኋላ፣ ጅብ ከሚበላኝ ቡዳ ቢበላኝ አይሻልምን? ቡዳውንስ በጸበል እድናለሁ፤ ጅብ ከበላኝ መሞቴም አይደል? ደግሞስ ቡዳ ይሁኑ፣ አይሁኑ፣ ሰማሁ እንጂ የበሉት የለ? እንዲያውም በዚሁ አጋጣሚ ጉዱን ልወቅ በማለት አማራጭ ያጣለትን ማደር እውነቱን ማረጋገጫ አድርጎ ሊጠቀምበት በማሰብ ፍርሃቱን አስወግዶ ወደ መንደሩ ገባ ይልና፤ የእግዚአብሔር እንግዳ፣ የመሸበት መንገደኛ ነኝ፤ አሳድሩኝይላል፡፡ በተሰጣቸው መጥፎ ስም ምክንያት እንግዳ የናፈቁት የመንደሩ ሰዎች እጅግ ደስ ብሏቸው ልብን በሚነካ ሁኔታ ተቀብለው፣ እግሩን አጥበው፣ ጥሩ እራት አዘጋጅተው በክብር አስተናገዱት፡፡ በመስተንግዷቸው ውስጡ በጣም የተነካው እንግዳም ለጊዜውም ቢሆን ቡዳ ናቸው የሚለውን ነገር ዘንግቶ ነበር፡፡

ኋላ ላይ ግን የቀረበለትን የማር ጠጅ እየተጎነጨ ሞቅታ ቢጤ ስለተሰማው፣ እናንተዬ እዚያ ላይኛው መንደር ያሉት ሰዎች ቡዳ ናቸው ይባላልሳ! እውነት ነው እንዴ?”  ሲል ወደራሱ መንደር እየጠቆመ ጠየቀ፤ በድንገትም የቤቱ ደስታ በዝምታ ተዋጠ፤ በመካከል ግን አንድ ሸምገል ያሉ አባት፣ እኛ እነሱን ቡዳ ናቸው እንላለን፤ እነሱም እኛን ቡዳ ናቸው ይሉናል፤ የእነሱን እንግዲህ እግዜር ይወቀው፤ እኛም አናውቀውም፤ የእኛን ግን አንተ ዛሬ መጥተሃልና አዳርህን አይተህ ነገ ትመሰክራለህ በማለት መለሱለት፡፡ ያም እንግዳ ሌሊቱን ሙሉአውጣኝ፣ አውጣኝ እያለ ሲጸልይ አደረ፡፡

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አሁን እየታየ ያለው የሁለት ሲኖዶስ ውዝግብም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ከደርግ መውደቅ ጋር ተያይዞ በአገራችን የተከሰተው ሁኔታ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንንም እንግዳ ነገር እንድታስተናግድ አደረጋት፡፡ እርሱም የደርግ መንግሥት አልፎ የኢአዴግ መንግሥት ሥልጣን ሲይዝ በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ አሜሪካ ተሰደዱ፡፡ ቤተ ክርስቲያንም 5 ፓትርያርክ መረጠች፤ በዚህ መካከል ከፍተኛ ውዝግብና ሁለት ሲኖዶስ ተፈጠረ፡፡ አንደኛው ሌላኛውን ወጥ እያለ መጥራትም ጀመረ፡፡ ነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባዔ ዘሐዋርያትየሐዋርያት ጉባዔ በሆነች በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን  የሚለውን መርህ የምታውጀዋን ቤተ ክርስቲያንም አዋጇን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነገር ገጠማት፡፡ ሐዋርያት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ያደረጉት አንድ ጉባኤ (ሲኖዶስ) እንደሆነ ብዙዎቻችን እናውቃለን፡፡ የእኛዎቹ ግን አንድ ቤተ ክርስቲያን ሆነው ሁለት ሲኖዶስ ሆኑ፡፡ አንደኛው የሀገር ቤቱ፣ ሁለተኛው ደግሞ ስደተኛው፡፡

ወንጌሉ፤ ቅዳሴው፤ ስብከቱ፤ ሌቱ፤ ሰዓታቱ አንድ ነው፡፡ በሁሉም አገልግሎት አንድ ናቸው፡፡ ሁለት ሲኖዶስ ሆነው ግን ተከፈሉ፡፡ በእነርሱ መከፋፈል ምክንያት ዝበ ክርስቲያኑም ተከፋፈለ፤ የሁለቱን መለያየት የጠላ ደግሞ የተሻለ የሠራ መስሎት በሌላ መልኩ ተገነለጠ፡- ገለልተኛ በሚል፡፡ ይህ ሁኔታ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት  ለማይፈልጉና መከፋፈሏን ለሚመኙ ደስታ ሆነላቸው፡፡ የተገነጠሉ ሁሉ፣ እንደነ እገሌ ነው የሆንነው በማለት ለተሳሳተ መንገዳቸው ቀድመው የተሳሳቱትን ምሳሌ በማድረግ ቤተ ክርስቲያንን ይገነጣጥሏት ጀመሩ፡፡

ቤተ ክርስቲያን እየደረሰባት ካለው ፈተና አንጻር አሁን ያለችበትን መልካም ደረጃ ስንመለከት፤ የሲዖል ደጆች አይችሏትም የሚል ቃል ኪዳን ያላት መሆኗን ያሳያል፡፡ በዚህ ደስ ቢለንም በየጊዜው በሚከሰተው ፈተና ግን ማዘናችን አልቀረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶች አንድ አለመሆን ነጥቆ በረር ለሆኑት ደፋሮች እና በውድቀቷ መክበር ለሚሹ ምቹ ሁኔታን ፈጠረላቸው፡፡ እነርሱም ወሬ በማራገብ ልዩነቱን አሰፉት፡፡ ልዩነታቸውም በሃይማኖት፣ በሥርዓት ባስ ሲልም በፖለቲካ ሳይቀር እየተወነጃጀሉ የቤተ ክርስቲያንን ፈተና አበዙት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው፣ እለ ከርሶሙ አምላኮሙሆዳቸው አምላካቸውየሆነባቸው በሥጋ ብቻ የሚያስቡና ለጥቅም የሚሮጡ ግለሰቦችም ከአንዱ ሲያኮርፉ ወደ ሌላው ሄዶ ወሬ በማቀበል ክፍተቱን አሰፉት፡፡ አንደኛው ሲኖዶስ ሌላኛውን ሲያጎድፍ ልዩነቱ በዝቶ በአደባባይ እስከ መወጋገዝ ደረሱ፡፡ በዚህ ሁኔታ አንድነቱ ቢኖር ኖሮ ብዙ ሊሰሩባቸው የሚገቡ ሃያ የሚያስቆጩ ዓመታት አለፉ፡፡

የብዙኃኑ ምኞት የነበረውን የልዩነትን ጉዳይ በዕርቅ የመፍታት ሙከራ ተጀምሮ ሳለ በመካከሉ የእግዚአብሔር ጥሪ ሆነና፣ ቀድመው የተሾሙት በሕይወት እያሉ ኋላ ላይ የተሾሙት ተጠሩ፡ዘቦቱ ኲሉ ኮነ ወዘእንበሌሁሰ አልቦ ዘኮነ ወኢምንትኒ”  ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነውም ሁሉ ያለ እርሱ የሆነ አንድስ እንኳን የሆነ የለምተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔር የፈቀደው ሆነ፡፡ አሁን ችግሩ ትንሽ ቀለል ያለ መስሎ ታየ፤ ምክንያቱም የሁለት ፓትርያርክ በሕይወት መኖር ለእርቁ እንቅፋት ይሆናል ተብሎ ይታሰብ ስለነበረ ነው፡፡

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ በብዙዎች ዘንድ የነበረው ግምት፣ አስቀድሞ የተጀመረው ርቀ ሰላም በፍጥነት ይከናወናል የሚል ቢሆንም እንደታሰበው አልተጓዘም፡፡ የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ 5 ብለን ወደ 4 አንመለስም በሚል ሰበብ ዕርቀ ሰላሙን ወደጎን በመተው አዲስ የፓትርያርክ ምርጫ በጥር ወር ለማካሔድ ዝግጅቱን አጠናቀቀ፡፡ የተከፈለችው ቤተ ክርስቲያን አንድ እንድትሆን የሁላችንም ናፍቆት ስለሆነ፣ አሁን ያለው ሁኔታ የሚያስጨንቅ እና ምጥ ውስጥ የሚከት ሆኗል፡፡ አንድነትን የሚያመጣውም በፍቅርና በይቅርታ የተመላ የአባቶቻችን ልብ በመሆኑ በቀደሙት አባቶች ተተክተው የእረኝነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ኃላፊነትን የተቀበሉ አባቶች ምሳሌነታቸውን እንዲያሳዩ ይጠበቃል፡፡ ለፍቅር ሲባል ማንኛውንም ዋዕትነት መክፈል እንደሚገባ የሚያስተምሩ አባቶች ትምህርታቸውን በተግባር እንዲያሳዩ ያስፈልጋል፡፡ በቀጣዩ ዘመንም በአባቶቻቸው የሚተማመኑ ልጆች እንዲፈጠሩ፣ በሃይማኖት ጠንካሮች በአገልግሎትም ደስተኞች እንዲሆኑ በዚህ ጊዜ ከማንኛውም ነገር በፊት ለዕርቀ ላም ቅድሚያ በመስጠት ሁሉም የሚመኘውን እና እግዚአብሔርም የሚወደውን አንድነት ያሳዩ ዘንድ ያሻል፡፡

ስለዚህም አባቶች የቁጥር ጉዳይ ከአንድነት አይበልጥምና ለዕርቀ ሠላሙ ሊከፈል የሚገባውን ዋጋ ሁሉ በመክፈል ምሳሌነታቸውን ሊያሳዩ ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ቤተ ክርስቲያን እስከዛሬ ከደረሰው ለከፋ አደጋ ልትጋለጥ ትችላለች፡፡ ለምሳሌ፡- የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ስድስተኛ ፓትርያርክ ከመረጠ በኋላ በምን ሁኔታ ነው ርቁ የሚቀጥለው? ይህ ራሱ ክፍተቱን የሚያሰፋ እንጂ አንድነቱን የሚያመጣ አይደለም፡፡ ስድስተኛ ፓትርያርክ ከተመረጠ በኋላ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የደረሰው ጥሪ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስም መድረሱ አይቀርምና እሳቸው ሲያልፉ፤ ስደተኛውም ሲኖዶስ የራሱን ፓትርያርክ መምረጡ አይቀርም፡፡ ያኔ ለመሰብሰብ የሚያስቸግር የመበተን ፈተና ሊመጣ ነው፡፡ ስለዚህሳይቃጠል በቅጠልእንዲሉ ፁዓ አባቶች ችግሩን ከወዲሁ በዕርቀ ሰላም እልባት ቢሰጡት አማራጭ የሌለው መፍትሄ ይሆናል፡፡ በተጨማሪ ዕርቀ ሰላሙ የሚጠቅመው ከምእመናኑ ይልቅ ለአባቶች መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ይህ ዕርቅ የመንፈሳዊ ደረጃቸውን የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ የአባትነት አርአያነታቸውንና መንፈሳዊ ብቃታቸውን እንዲሁም ለመንፈሳዊ አንድነትና ለመነኮሱለት የአብነት ዓላማ የቆሙ መሆናቸውን ያመለክታል፤ ይህም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ የመልካም ታሪክ ባለቤት ያደርጋቸዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ደግሞ ዝቡም ሳብ አንድ መሆኑን አባቶች ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ከዚህ በፊት ሁለቱም ሲኖዶሶች አንዱ ሌላውን መናፍቅ ነው እያሉ በአደባባይ ተወጋገዙ፡፡ የዕርቀ ሰላም ድርድሩ ሲጀመር ልዩነቱ የሥልጣን መሆኑ እና የሃይማኖት አለመሆኑ ታየ፡፡ ለዚህ ደግሞ መፍትሔው መንፈሳዊነት ብቻ ነው፡፡ መንፈሳዊነት ሲኖር እኔነት ይቀራል፤ ግትርነት እና አልሸነፍ ባይነትም ይወገዳል፤ ቁጥር ዋጋ ቢስ ይሆናል፤ ያን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን አንድ ትሆናለች፤ አባቶችም ቡራኬያቸው የሚናፈቅ፣ መስቀላቸውንም ለመሳለም ሁሉም የሚሻማው ይሆናሉ፡፡

በስደተኛውም ሆነ በሀገር ውስጥ ባለው ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ድርድር በመልካም ሁኔታ እንዲፈጸም የተወሰነ የጾም አዋጅ ቢታወጅ መልካም ነው፡፡ ምክንያቱም ዕርቀ ሰላሙ በኮሚቴ ሳይሆን በእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ ንባና ጸሎት ቢታገዝ ሁኔታው ይፋጠናል፡፡ አስታራቂ ኮሚቴ የተባሉትም ለማስታረቅ የሚበቃ መንፈሳዊ ሰብ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ ሁሉም ባይሆኑ የተወሰኑት ይታወቃሉ፡፡ የማይታወቁትንም ቢሆን በዚህ ዘመን ማንነታቸውን ለማወቅ በቅርበት ማየት አይጠበቅም፡፡ ሆኖም እነዚህን አባቶች ወደ አንድነት ለማምጣት እርስ በርሳቸው የተቧደኑ ሰዎች ብቻ በቂ ናቸው ማለት ይቸግራል፡፡ ቢያንስ ቢያንስ፡-
1. ይወታቸው አብነት(ምሳሌ) ሊሆኑ የሚችሉ፤
2. በሃይማኖታቸው ነውርና እንከን የሌለባቸው (ከመናፍቅነትና ከተሐድሶ ሐሜት የጸዱ)    
3. ጥቅመኛነት የማያታልላቸውና ለገንዘብ የማያጎበድዱ፤
4. ለመታወቅና ራሳቸውን ለመካብ የማያስቡ፤ ማለትም ከራሳቸው ጥቅም ይልቅ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስቀድሙ ቢሆኑ፡፡
 በአጠቃላይ ከየትኛውም ጎራ ያልሆኑና ምግባራቸው የተመሰከረላቸው መሆን ይኖርባቸዋል እንጂ የታራቂዎች ዘመድና ወዳጅ ስለሆኑ ብቻ አስታራቂዎች መባላቸው ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም የለውም፡፡ ሸምጋዮችን ለመሸምገል (አስታራቂ የሆኑ አባቶችን ለማስታረቅ) ራሱን የቻለ ሽምግልና ይጠይቃል፡፡ የሲኖዶሱን መከፋፈል እንጀራቸው ያደረጉና አገልግሎታቸውን ከጥቅም ጋር ያዛመዱ፣ ሀገር ቤት ሲመጡ የዚህ፣ ባህር ማዶ ሲሄዱ የዚያብቻ ደህና ለተከፈለበት ሰልፍ አሳማሪዎች፤ ሲላቸው ደግሞ በተመቻቸው ሚዲያ እየቀረቡ ራሳቸውን ለማሳወቅ የሚሮጡ፣ አንድ ጥግ ይዘው በቆሙበት ውደ ረት ሞቅታ በተሰማቸው ቁጥር ሌላኛውን እየነቆሩ ልዩነቱ እንዲሰፋ ሚና የሚጫወቱ ሰዎች ዛሬ አስታራቂ ሆነው ማዕከላዊ (ገለልተኛ) ነን ቢሉ የማይታመንና የሚያሳፍር ነው፡፡

የሦስት ሺህ ዓመት ታሪክ ያላትን ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለመፍታት የተሰበሰቡ ሽማግሌዎች ቢያንስ ንጹሓን ባይሆኑ እንኳን አዳፋ መሆን የለባቸውም፡፡ እንደሚታወቀው ዛሬ ራሳቸውን ሽማግሌ አድርገው የቀረቡት አደራዳሪዎች ትናንት የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ አስተማራቸውና፤ ሰርተፍኬት ሰጣቸው፤ ዛሬ ባሉበት ሀገር ስደተኛው ቀጠራቸው፤ ውደ ረት ላይ ሲወጡ ገር ቤቱን እየኮነኑ የመንግሥትን (የሰማዩን መንግሥት እንደሆነ ይታወቅልኝ) ወንጌል የሥጋ ጥቅማቸው ማጋበሻ አደረጉት፡፡ ምዕመናኑ አንድ፤ ቤተ ክርስቲያንዋም አንዲት ሆና ሳለ፤ ያገለግሉት የነበረው ትውልድ እንኳ ሳያልፍ ዛሬ ደግሞ ይናቸውን በጨው ታጥበው አስታራቂ ነን ብለው ተነሱ፡፡ ታዲያ እነዚህ አደራዳሪ ናቸው ወይስ ተደራዳሪ?
                                                                                              

አባቶችን እናውቃቸዋለን፡፡ የዋሆች ናቸው፡፡ ሁሉም ነገር ለአደባባይ የበቃውም በየዋህነታቸው ነው፤ ግትር የሆኑትም በክፋት ሳይሆን የዋህነታቸው በዝቶ ነው፡፡ የዋሆች ባይሆኑ ኖሮ ትናንት አንድ ጥግ ይዘው ሲተቿቸው እና ሲያንጓጥጧቸው የነበሩ ዛሬ ራሳቸውን ሽማግሌ አድርገው ፊታቸው ላይ በሽንገላ ከንፈርአባታችንእያሉ ሲጥመለመሉ ባልተቀበሏቸው ነበር፡፡ እነሱም የአባቶችን የዋህነት ተጠቅመው በጉዳዩ ትከሻ ላይ ተንጠልጥለው የራሳቸውን ስም ለማስጠራት መነሳታቸው አሳዛኝ የታሪክ ተወቃሽነት የሚያስከትል መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ይህ ማለት ግን ሁሉንም አያካትትም፡፡ በስነምግባራቸውና በሃይማኖታዊ አቋማቸው የተመሰከረላቸው መልካም አባቶች በመካከላቸው መኖራቸው እርግጥ ነው፡፡ ሆኖም ቅን አሳቢዎቹ የተሰለፉት ከቅጥረኞ ጎን ስለሆነ ራሳቸውን ከተኵላዎቹ መለየት አለባቸው፤ ባጭሩ ክርዳዱ ከስንዴው ይለይ፡፡ ቀድሞውንም ዝቡ ሳያውቃቸው ቀርቶ ሳይሆን ትኩረቱ ዕርቀ ሰላሙ ላይ ስለሆነ እስከ መከር ይቆይ ብሎ ነው፡፡ አሁን መከሩ ደርሷል፤ ስለዚህ እርቁን እንዳያጨናግፉ ይታጨዱ፡፡ ውስጥ ያሉት መልካሞቹ የቀበሮ ባህታውያንን ያስወግዱና ለአንድ ወገን ያላደላ ሚዛናዊ ጉዞ ያድርጉ፤ የገዳም አባቶችንና የዋሃን ምዕመናንን ይዘውም መንፈሳዊ ጉዞ ያድርጉ፡፡

አጭር መልዕክት ለሀገር ቤቶቹም ለስደተኞቹም

ለሀገር ቤት አባቶች

·         በቤተ ክርስቲያኒቱ በጀት ከአዲስ አበባ ወደ ሀገረ አሜሪካ ልዑካንን በመመደብ ያለመሰልቸት ለዕርቅ መመላለሳችሁ ለአንድነቱ ያላችሁን ሙሉ ፈቃደኝነትና ጉጉት ያሳያል፡፡ የለፋችሁበት እንዲሳካ ከዚህ በታች ያሉት ነገሮች ተግባራዊ ቢሆኑ መልካም ነው፡፡
1.      የፓትርያርክ ምርጫውን ከእርቁ ባታስቀድሙ፤
2.     ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት በየገዳማቱ ለሚገኙ አበውና፤ ለሕዝበ ክርስቲያኑ የተወሰነ የጾም አዋጅ ብታውጁ፤
3.     ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን፤ በረ ካህናትን፤ ሰባክያነ ወንጌል አገልጋዮችንና ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን ምሁራንን በየደረጃ በማሰባሰብ በጉዳዩ ዙሪያ ብታወያዩ የተሻለ ይሆናል፡፡

ባህር ማዶ ላላችሁት   
·         የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ርቅ ጥረት ማድረግ የጀመረው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሉስ እረፍት በፊት መሆኑ እሙን ነው፡፡ እርሳቸው ይወት እያሉ እርቁ ቢሳካ ኖሮ 20 ዓመታት የቆዩበትን መንበር ይልቀቁልን እንደማትሉ ይታመናል፡፡ መቼም አንተ ተዋርደህ እኔ ከብሬ እንታረቅ ብሎ ድርድር የሚጀምር በታሪክ ውስጥ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ ስለዚህ የተጀመረው ዕርቀ ሰላም በመልካም ሁኔታ እንዲፈጸም፡-
1.      የቅዱስነታቸውን የአቡነ መርቆርዮስን ወደ መንበራቸው መመለስን ርቅ ድርድር ውስጥ ባታስገቡ፡፡ የምትታረቁት ለሹመት አይደለምና፡፡ የሀገር ቤቱ ሲኖዶስም በተደጋጋሚ አሜሪካ ድረስ በመመላለስ ለዕርቀ ሰላሙ እና ለአንድነቱ ያለውን ፈቃደኝነት ሲያሳይ የቅዱስነታቸው አቡነ መርቆርዮስን አባትነት አምኖ መሆኑን መዘንጋት የለባችሁም፡፡ ርቁና ሹመቱ  ተለያይተው ቢታዩ መልካም ነው፡፡ ቅዱስነታቸው አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው ቢመለሱ የሚጠላ የለም፤ ለዚህ ግን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተፈጠረ ቅሬታ ካለ ቅድሚያ እሱን መፍታት ይኖርባችኋል፡፡ ደግሞ ራሱን የቻለ ጊዜ ይፈልጋልና ይህንን በመሳሰሉት ምክንያት ልጣንን ጉዳይ ሳይሆን በቅድሚያ እናንተ ብትስማሙና  የሹመቱን ጉዳይ ለመንፈስ ቅዱስ ብትሰጡ መልካም ነው፡፡
2.     የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ከላይ እንደተጠቀሰው አሜሪካን ድረስ ልዑካን መድቦ ለበርካታ ጊዜያት ሲመላለስ ገንዘብ፣ ጊዜና የሕይወት ዋጋ መክፈሉ የታወቀ ነው፡፡ ምሳሌ፡- ላሙ ጉዳይ ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስተው አዲስ አበባ ሲደርሱ በአየር ግጭት (መዛባት) ምክንያት ወዲያውኑ ሕይወታቸውን ያጡት ታላቁ ሊቅ መጋቤ ብሉይ ይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የማይረሱ አባት ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህንን በማሰብ በተለሳለሰ ሁኔታ የልባችሁን በር ርቁ ብትከፍቱና ሁኔታዎች በፍጥነት እንዲስተካከሉ ብትተባበሩ መልካም ነው፡፡ ደግሞስ ሁሌ ከዚህ ብቻ መኬዱ ለምንድን ነውለምን እናንተስ ኢትዮጵያ በመምጣት ርቁ ያላችሁን ፍላጎት አታሳዩም? ምን አልባት ከመንግሥት ጋር ያለውን መቃቃር እንደ ምክንያት ትጠቅሱት ይሆናል፡፡ መቼም ሁላችሁም ከመንግስት ጋር እንዳልተቃረናችሁ ግልጽ ነው፡፡ እጃቸውን ፖለቲካ ውስጥ ያላስገቡ አዳዲስ ፁዓ ኤጲስ ቆጶሳት እንዳሉ ይታወቃል፤ ነገር ግን እስካሁን ከእናንተ ወደዚህ የመጣ ልዑክ የለም፡፡ ከዚህ አንጻር ርቁ ከፍተኛ ፍላጎት የሚታይበት የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ነው ቢባል ማጋነንም ማድላትም አይሆንም፤ ምክንያቱም ገንዘብ፣ ጊዜና ሕይወት ከፍሏልና፡፡ ዝበ ክርስቲያኑ ከእናንተ ከባህር ማዶዎቹ አባቶች የአባትነት መዓዛ ይፈልጋል፡፡ እንደ ሀገር ቤቶቹ እናንተም ርቁ ጉዳይ ዋጋ የሚያስከፍል ከሆነ ዋጋ ክፈሉ፡፡ ሀገራቸው መግባት የሚችሉ ልዑካን ከዚያም ይምጡ፡፡
3.     በተደጋጋሚ እንደሚጠየቀው የቅዱስነታቸው የአቡነ መርቆርዮስ ሳብ ምን እንደሆነ ከአንደበታቸው  ቢሰማ  የተሻለ ነው፡፡ በዙሪያቸው ያሉት ሰዎች እሳቸውን ደብቀው የሚደራደሩባቸው ጉዳይ ግልጽ አይደለም፡፡ እናንተም በሩን ዘግታችሁ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ጋር ርቁ የመጡ አባቶችን አለማገናኘት ራሱ ሌላ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ፓትርያርኩን  ከአዲስ አበባ አሜሪካ ድረስ ያለ መሰልቸት ከሚመላለሱት ፁዓ አበው ጋር እንዲገናኙ አድርጉ፤ የእሳቸውም ስሜት እና ፍላጎት ከአንደበታቸው ይሰማ፡፡
4.     በመጨረሻ  በአገር ቤትም ሆነ በባህር ማዶ ያላችሁ አበው፡- ዕርቅን የማይፈልግ ከእግዚአብሔር አይደለምና ለእርቁ ከምንም በፊት ቅድሚያ ቢሰጥ የተሻለ ነው፡፡ እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ አቡነ መርቆርዮስ ቢመጡ እሰየው ነው፤ ካልሆነ ግን ዕርቅ አይሆንም አይባልም፡፡ በአደባባይ የተወጋገዛችሁትን በአደባባይ ፍቱት፤ ውግዘቱ ይነሳ፡፡ እዚህ ያሉት ባህር ማዶ ሲሄዱ የፈለጉበት ቤተ ክርስቲያን ያገልግሉ፣ ያስቀድሱ፣ ወዘተ... የአጵሎስ፣ የኬፋ ማለት ይብቃ፡፡ እዚያም የውጭዎቹ ጋር የሚያስቀድሱትና የሚቀድሱት ተሳትፎዋቸው ሀገር ቤት ሲመጡ አይቋረጥ፡፡ የተሰደዱት ሀገር ቤት የሚገቡበት አማራጭ ቢታጣ እንኳን ቢያንስ ቢያንስ መተቻቸቱና መነቃቀፉ ቀርቶ እንደ ሁለት ሀገረ ስብከትም ሆነው ቢሆን በጸሎት በመተሳሰብ ያገልግሉ፡፡ ህዝቡን ከንትርክ ያሳርፉት፡፡ ዕርቅ፣ ዕርቅ የሚባልበትም ዓላማ አንዲት ቤተ ክርስቲያን በፍቅር ስትገለገል ለማየት ነው፡፡ ለዚህም የእናንተ አብነታችሁ ያሻል፡፡

ለአንባቢዎች -
ጸልዩ በእንተ ላመ ቤተ ክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባዔ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኀበ እግዚአብሔር”“በእግዚአብሔር ዘንድ የቀናችና ርትዕት ስለምትሆን  አንዲት ቅድስት የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ቤተ ክርስቲያን ሰላምን ለምኑ 

እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ያጽናልን!!!

45 comments:

Anonymous said...

kale heyewet yasemalen!!! i wish this article posted on every blog and read by everyone specially the part what they should do the last page i could not agree any more .
bless him .
chere yaseman
Amena

Anonymous said...

ጸሐፊው የአገር ቤቱን ሲኖዶስ ደግፎ የውጭዎቹን እያወገዘ ይህ አቀራረብ እንዴት ዕርቅን የሚደግፍ ሊሆን ይችላል ? ደግሞስ እግዚአብሔር ማንን ለሞት እንደሚጠራ እርግጠኛ መሆን ይቻላል ? ጸሐፊው ለብፁዕ አቡነ መርቆሪዎስ የተመኘውን ሞት እኮ ቀደም ብሎ አቡነ ጳውሎስ ከዚያም እርሣቸውን ተክተው ፓትርያርክ እንዲሆኑ ታስበው የነበሩትን የመቀሌውን ሊቀጳጳስ አቡነ ዮሐንስን ወስዷል :: ስለዚህ አገር ቤት ያሉትና በወያኔ የሚታዘዙት አንዳንድ ጳጳሶች ዳግም ቀኖና ሽረው ፓትርያርክ ቢሾሙ እግዚአብሔር ያንንም ጳጳስ በሞት ላለመንጠቁ ምን ማስተማመኛ ይኖራል ? ምክንያቱም 'እግረ -ቀጭን ይሞታል ሲባል እግረ -ወፍራም ተጠራ ' ይባላልና ::

Haileyesus said...

This is what one can call SHIMGILINNA! May we pass this message to each one of Our 60-65(48/50+13/15) Liquane Papapasat?! (through kahinat, diakonat & all ye bete kihinet kerabi sewoch) who are set to determine the fate of this One, Apostlic Church, then Judged by their Individual role in this historic opportunity they are provided by YE FIKIR ABAT JESUS CHRIST!!! HISTORY WILL TELL!!! Who else other than Abatoch themselves that can form NEKEFA YELELEBACHEW SHIMAGILEWOCH to help them reach an agreement. May we all spell out and assist who shall be replace by who to Abatoch Again??? Any more constructive articles from YE KURT KEN LIJOCH please!!!

Anonymous said...

Enaneta ande hono mameheran kala heiwate yasamalen

Anonymous said...

LaAbatochachen ande yamearage Haile yesetelene
Yaena K.Marekoriose Amelaka eredane

Anonymous said...

Yakedosane Amelaka eredane

Anonymous said...

ማነህ ደግሞ አንተ ፕሮፌሰር መስፍን በአንድ ጽሁፋቸው ላይ እንደጠቀሱት በኢትዮጵያ ውስጥ በሰፈነው ህገ-አራዊት ማን ሊዳኝ ነው ግቡ የምትለው? ለመሆኑ አንተም እዛው ነህ ከሆንክስ እነዚህ አራዊቶች ህዝቡን እንዴት እያስተዳደሩት እንደሆነ ንገሩኝ ማለትህ ከሆነ መጀመሪያ አይንህንም ልብህንም ክፈት።

Anonymous said...

Very interesting and true message!!! God bless you!

Anonymous said...

It is good article. But I don't agree that asking the "sedetegnaw sinodose " to go back to Addis Ababa and have a meeting.are you kidding? The writer didin't understand what TPLF is doing for the last 21 years. Don't forget TPLF Is above the law. They can do what ever they want. So please don't advice the meeting to be held in Ethiopia where TPLF is above the law of the country.

Hailu said...

It is perplexing!

‘Sint teblo teblo memhir Paulose wodehuala hido wuha chelesbet’.

I hate to repeat this but have to do so for the sake of such an uninformed or cleverly confusing memhir.

It is abundantly clear for all of us that the 4th Patriarch His Holiness Abune Merkorios was unjustly removed from his 'menber' with utter disregard to the church's age old canon law. Even worse was that His Holiness was removed by the government just to replace him with their ethnic man. This is confirmed unambiguously (eg. letter written by the 4th Patriarch, testimony of the then PM Tamirat, recent interview by President Girma on VOA, etc). This violation of the church’s law is the one that lead to the division in our church. It is perplexing to see the likes of 'Memhir Paulos Melakesilassie' attempting to make it sound otherwise.

The issue is not about a personal matter when we say that the 4th Patriarch should return to his 'menber'. IT IS ALL ABOUT RESTORING RULE OF LAW, i.e., the canon law.

There is no a personal quarrel between any of the bishops in exile and those in Ethiopia. The negotiation is only to resolve the division that resulted when the canon law was violated and Aba Paulos was assigned as a '5th Patriarch' some 20 years ago. It is unholy when ‘memhir Paulose’ tries to make it sound like the Bishops in the Synod in exile are interested only in 'siltan'. He must know that His Holiness Abune Merkorios is still the Patriarch. He does not have earthly 'siltan' that anyone can take away. It is a spiritual leadership that he has and he will have it for his life. SO, WHEN WE SAY THAT THE 4TH PATRIARCH SHOULD RETURN TO HIS 'MENBER,' IT IS NOT ASKING FOR SILTAN FOR HIM. IT IS ALL ABOUT CORRECTING THE MISTAKE COMITTED 20 YEARS AGO FOR THE SAKE OF RESTORING UNITY IN OUR CHURCH. It is, therefore, absurd for Memhir Paulos to write “ የቅዱስነታቸውን የአቡነ መርቆርዮስን ወደ መንበራቸው መመለስን የዕርቅ ድርድር ውስጥ ባታስገቡ፡፡ የምትታረቁት ለሹመት አይደለምና፡፡”
The other accusation the 'memhir' labeled against those who are working hard to mediate between the synods is disheartening at best and malicious at worst. What is their sin if they work hard to get agreement between the fathers in order to restore unity in our church? What has the ‘memhir’ done to end the division in our church before he whipped his mud sling?


In all memhir Paulos Melkea Silassie's article appears to be either an opinion of the uninformed or a sinister act in disguise. If he indeed cares about unity in our church, he should not accuse the peace makers but do his part.

May God give us the wisdom to end the division in our church. Amen.

Anonymous said...

መ/ር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ
በጽሑፍህ ስለ አባቶች የዋሕነት ጠቅሰሃል፡፡ « የአገር ቤቱን መልእክተኞች ደከማችሁ ዋተታችሁ በገንዘቡ ተጫወታችሁበት፤ ከእንግዲህ በዕርቅ እያሳበባችሁ ውጭ ውጭ ማለት በቃችሁ ብለህ አስጠንቅቀሃል፡፡ በስደት የሚኖሩትንም እናንተም በተራችሁ ኑና ወያኔ ጉያ ሥር ሰላምና እርቅ ውለዱ ብለሃል፡፡ ለመሆኑ ስደት ምን ማለት እንደሆነ ይገባሃል? ድሮውኑ ባይቸግራቸው ባይገፉ ለእንደ አንተ ያለ ወጠጤ አገራቸውን ትተው ይወጡ ይመስልሃል? ከመሰልህ አንተም የዋሕነቱን እጅግ አንዛዛኸው፡፡ ካድሬነት ከሆነ ግን ይህችን የወያኔ ብልጣብልጥነትህን ምናምንቴህ ውስጥ ወሽቀህ ብትደብቃት ይሻልሃል፡፡

Anonymous said...

Kale Heiwot Yasemalen!

Please also include the ROLES AND RESPONSIBILITIES of us (Ethiopian Orthodox church followers) IS JUST TO PRAY FOR OUR CHURCH UNITY - NOT TO TAKE SIDE AND MAKE THINGS WORSE.

Amen Chere Yaseman!

Unknown said...

የጸሓፊው ሀባብ በሀተታው ውስጥ ያሉት ቁምነገሮች ብዙም ክፋት የላቸውም። ችግሩ ከማሰሪያ አንቀጹ/መደምደሚያው ላይ ነው። ይኸውም የችግሩ ምክንያት የሆነው የቀኖናውን ጥሰት እንደ ዋናው የችግሩ ምንጭ መሆኑንና እንዲስተካከል አለመገለጡ ነው። ይህ ደግሞ የኒህ ፀሓፊ ብቻም ሳይሆን የብዙዎችም ሁኖ እያየን ነው። ለመሆኑ ስለቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጣስ ምን ያህል ነው የሚያሳስባቸው? የሚል ጥያቄ መጠየቁ የግድ ነው። የተጣሰው ቀኖና ሊስተካከል የሚችለው ደግሞ በመንግሥት ጣልቃ ገብነትና በቤተ ክህነት ወስጥ በነበሩት ተባባሪዎቹ ከመንበራቸው እንዲነሱ የተገደዱት አባት ተመልሰው በጉልበት ከተነሱበት መንበር ላይ ሲቀመጡ ብቻ ነው። ይህ ሲሆን ብቻ ነው ችግሩ ሊፈታ የሚችለው። ምክንያቱም የችግሩ ብቸኛ ፈጣሪ ይኸው ስለሆነ። በሽታውን እያወቅን መዳኅኒቱን ለመውሰድ እስካልተስማማን ድረስ በሺታውን ከሰውነታችን ማስወገድ አንችልም። ይህ ሳይሆን ምን አይነት አንድነት ነው ሕጋውያኑ ከሕገ-ወጦቹ ጋር ሊመሠርቱ የሚችሉት? ለይስሙላ ስለ ቤተ ክርስቲያን እንቆረቆራለን እያልን ስለ ቀኖናዋ ደግም ''እንደ ሁኔታው'' የሚል አቋም ይዘን መከራከራችን የሚያሳየው ነገር ቢኖር አድርባይነትንና መንግሥተ እግዚአብሔርን ሳይሆን መንግሥተ ዓለምን በመፍራት ነው። አዎ ለዚህ እኮ ነው ''ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም'' ያለው እራሱ ጌታ !ስለዚህ እኔ ለኒህ ወንድሜና እርሳቸውን ለመሰሉት የምለው ተቃራኒ ጥቅም ላላቸው ለሁለት ጌቶች ለመገዛት አትሞክሩ ነው ። አድርባይነት ከመንፈሳዊነት ጋር አብሮ አይሄድም ። ዝምድናም የለውም !

Anonymous said...

@ Hailu ... 'who said it is perplexing...' and others who share the same idea:
Let me ask you....
Is it fair to take such a position while going to a discussion for the purpose of the churchs unity?... to be a blind fan of one side instead of praying to God to give our fathers the wisdom to solve the problem?
We all know that H.H Abune Merkorios was dethroned for unfair reasons, and information is revealed that there was only one bishop or few who disagree with this on the then Synod. So How can you say His Holiness is still a patriarch while he was dethroned, though not fair? Are you saying a Patriarch is superior over a synod?
And, after all, who are you to correct or restore the cannon law of the church? And to decide how it should be corrected? Have you assigned your self as a synod? Please be advised!
Besides, I agree that this is the problem to be addressed! But not me, you or anybody! We shouldn't take a position.
Let's Pray and work hard so that our fathers (from both sides) would seat together in peace and with the Holy spirit to discuss and decide how to correct past mistakes and restore the churches unity! And then we will accept what ever they decide: Bringing back the fourth Patriarch to the throne, going together to the selection of 6th Patriarch(in unity) or what ever our fathers decide with Holy-spirit!
"Hawariat besebesebuat be Andit Kidist Betekirsitian Enamilan!!!"

Anonymous said...

Chear yasamane

Anonymous said...

Enamenalane yesakalenale basalote enebareta
Kaga Gare yalawe yebaletale

Anonymous said...

በሃይማኖታቸው ነውርና እንከን የሌለባቸው (ከመናፍቅነትና ከተሐድሶ ሐሜት የጸዱ)፤
3. ጥቅመኛነት የማያታልላቸውና ለገንዘብ የማያጎበድዱ፤
4. ለመታወቅና ራሳቸውን ለመካብ የማያስቡ፤ ማለትም ከራሳቸው ጥቅም ይልቅ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስቀድሙ ቢሆኑ፡፡
በአጠቃላይ ከየትኛውም ጎራ ያልሆኑና በሥነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው መሆን ይኖርባቸዋል እንጂ የታራቂዎች ዘመድና ወዳጅ ስለሆኑ ብቻ አስታራቂዎች መባላቸው ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም የለውም፡፡ ሸምጋዮችን ለመሸምገል (አስታራቂ የሆኑ አባቶችን ለማስታረቅ) ራሱን የቻለ ሽምግልና ይጠይቃል፡፡ የሲኖዶሱን መከፋፈል እንጀራቸው ያደረጉና አገልግሎታቸውን ከጥቅም ጋር ያዛመዱ፣ ሀገር ቤት ሲመጡ የዚህ፣ ባህር ማዶ ሲሄዱ የዚያ… ብቻ ደህና ለተከፈለበት ሰልፍ አሳማሪዎች፤ ሲላቸው ደግሞ በተመቻቸው ሚዲያ እየቀረቡ ራሳቸውን ለማሳወቅ የሚሮጡ፣ አንድ ጥግ ይዘው በቆሙበት ዐውደ ምሕረት ሞቅታ በተሰማቸው ቁጥር ሌላኛውን እየነቆሩ ልዩነቱ እንዲሰፋ ሚና የሚጫወቱ ሰዎች ዛሬ አስታራቂ ሆነው ማዕከላዊ (ገለልተኛ) ነን ቢሉ የማይታመንና የሚያሳፍር ነው፡ waw yehe malet keteta yemimeleketew keastarakiwoch west diakon andualem dagmawin new.thank you merewa

Anonymous said...

memhir ewenaten makeble yakatwot yemeslalu. knonawen yanbebu!

Anonymous said...

ለመሆኑ አሜሪካ ያላችሁ በፖለቲካና በዘር ያበዳችሁ የትኛው መነኩሴ ነው ከኢትዩጵያ የተባረረው ምንድነው ክፋት የምታወሩት ለምን መርቆርዮስ አይናገሩም »ተገፍተው መገፋት ምንድነው?መቸ ነው አባታዊ ቡራኪ ሰጥተው የሚያውቁት ለምን ትሽፋፍናላችሁ»ምድረ ወሮ በላ ሁሉ አቡነ መርቆርዮሰ ለምን አይናገሩም ተገፍተዋል ከ ተገፉ አሁንም በ ስልጣን ላይ ያለው ወያኔ ነው ምን አዲስ ነገር መጣ እዚህ ያሉት አርብ እና እሮብ የረሳ ሁሉ እናውቅችኋለን ዝም ብትሉ ይሻላል »‹»«?

Anonymous said...

Dear Kebede Bogale,

You said ለመሆኑ ስለቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጣስ ምን ያህል ነው የሚያሳስባቸው? Are you really serious? Do you wana discuss who neglected church law's? Why you guys talk about ስለቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጣስ just to push your interest? Don't you think removing your shoes inside the church part of ቀኖና ቤተ ክርስቲያን? Who neglect it? I tell you Church(es) under the administration of H.H Abune Merkorios. If want me add more የተጣሰ ቀኖና by your end, I will. However, I prefer church fathers to find a solution.

I know wayane has done a great damage on our church, but please don't blame Wayane for everything.

Anonymous said...

በመጀመርያ መ/ር ጳዉሎስን ቃለ ሒወት ያሰማልን በትክክል ነዉ ያስቀመጥከዉ ? ግን ኣንዳንዶች ኣላቹሁ ወያኔ የምትሉ ይሔ እኮ የቤተክርስትያን ጉዳይ ነዉ ኣትቀላቅሉ እሺ በእዉነት ፓትርያሪኩ ኣቡነ መርቆርዮስ ለመን ኣይናገሩም ምንድነዉ ሰለሳቸዉ እየተነገረ ሌላዉ የሚቀላቅለዉ ራስቸዉ ይናገሩ መፍትሔዉ ያለዉ እሳቸዉ እጅ ነዉ ለምን ኣይናገሩም ለምን ትሕትና ኣያሳዩም በሳቸዉ ግዜ ነዉ እኮ ቤተክርስትያን የተከፈለችዉ ለምን ሁሉን ጥለዉ ገዳም ኣይገቡም መንድነዉ ሰልጣን ወደ መንበራቸዉ ባይመለሱስ መን ይቀርባቸዋል ? እሳቸዉ እኮ ቢናገሩ ወይ ሁሉን ጥልዉ ገዳም ቢገቡ ሁሉ ነገር ያከትማል ነገር ግን እሳቸዉ ቢመለሱ ኣንዳንዶች ስላላቹሁ የቤተክርስትያን ሰላም የማትፈልጉ ወያኔ እያልችሁ ጊዚያችሁን የምጨርሱ ? እግዛኣብሔር ለቤተክርስትያን ሰላም ይስጥ ኣባቶች ደግሞ ኣርኣያ የሁኑልን

TESFAYE ZESHUMARA MARIAM said...

Tsegawun yabzalih.........

Hailu said...

To sim aytere (anonymous) who wrote January 3, 2013 10:50 PM in opposition to what Hailu wrote,

You said,
"Let me ask you....Is it fair to take such a position while going to a discussion for the purpose of the churchs unity?... to be a blind fan of one side instead of praying to God to give our fathers the wisdom to solve the problem?
We all know that H.H Abune Merkorios was dethroned for unfair reasons, and information is revealed that there was only one bishop or few who disagree with this on the then Synod. So How can you say His Holiness is still a patriarch while he was dethroned, though not fair? Are you saying a Patriarch is superior over a synod?"

I agree with you that there is no need to be a blind fan of any group. However, as you have confirmed it in the same paragraph, His Holiness Abune Merkorios was unjustly removed from his position in Addis against the age-old canon law of the church. By your own admission you don't dispute this fact. Then, how is it being 'blind supporter' to state and advocate for the truth?

Then, I would like to test your Orthodox faith. Is it an earthly power to be a Patriarch that any powerful group can take it away at any time?

I say to you, if you see things from a spiritual perspective only, His Holiness Abune Merkorios was and still is a spiritual leader and the legitimate Patriarch of EOTC. Period.

“ይህች ሹመት (ፓትርያርክነት) በአንድ ዘመን በአንድ ሀገር ለሁለት ሰዎች ልትሆን አይገባም። ይህ በአንድ ሀገር ከተደረገ ግን አስቀድሞ ለተሾመው ትጽና።”

"ፓትርያርክ በህይወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ ሊሾም ስለማይገባውና ያንን ስርአት ደግሞ እረኛ ተደርጎ የተሾመው ጳጳስ ከማናችንም በላይ ሊያስጠብቅ ስለሚገባው ለአንድ ጳጳስ እንኳን እራሱ ፓትርያርክ መሆንን መፈለግ ያንን ስርአት የሚያፈርሱትን ዝም ማለትም ትልቅ ጥፋት ነው::"

Therefore, my brother/sister, telling the truth is one thing and being a blind supporter is something else.

If you really care about your church, be truthful and don't be afraid of earthly powers in telling the truth. Our complacency has seriously damaged our church for the past 20 years.
May God of the truth help unite our church. Amen.

Anonymous said...

መምህር ቃለ ሕይወት ያሰማልን!
..
እኔ መቼስ እርቅ ሲባል እንደማንኛውም ክርስቲያን ወንደሞቼና እህቶቼ እርቅ፤ ሰላም፤ አንድነት ለተባለ ሁሉ ብደግፍም ከሁሉ ግን ምን አይነት የሚለውና መፍትሄ ተገኘለት ቢባልም እንኳ ከዚያ በኋላ ለሚመጣ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትና ስራት ሁሌም ያሳስበኛል።
አንዲት እህቴ ባለሁበት ከተማ መጥታ ያጫወተችኝን በአጭሩ ላውጋቹህ። ላለሁበት ቤት-ክርስቲያን ማጠናከሪያ እንዲሆን ምእመናን ያላቸውን ትርፍ ልብሶች እያወጡ ሲሸጡ አይታ፤ "ለምንድን ነው ዘፋኝ አስመጥታቹህ ገንዘብ በቀላሉ ማትሰበስቡት? እኛ በሎስ አንጅለስ (ቤት-ክርስቲያን ስሙን አልጥቅስም)በየጊዜው የምናደርገውና ጥሩ ብር የምንሰበስበው በሱ ነው። ማንም ከኃጢአት የጸዳ ደግሞ የለም። ልብስ ተሸጠ፤ ዘፋኝ አስመጣ፤ ሌላ ስራ ተሰርቶ ብር መጣ .."
ሌላው ደግሞ ዛሬ በአንዳንድ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይዮች (በተለይ ዘማሪያን) የጠዋት ቁርስ ሳይቀር እየበሉ ማገልገል እንደሚችሉ በአንዳንድ አባቶች (እንደ ሀገሩ መሆን ነው ብለው) እንድተነገራቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው።
ጫማ አጫሞ ቤተ ክርስቲያን መግባት የአደባባይ ሚስጥር ነው።
አዝማሪዎች በቅድስት ቆመው 'መዘመር የአደባባይ ሚስጥር ነው።
የማርያም ቅዳሴ በአንዳንድ ቤተ ክርስቲያን እንደማይቀድስ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
በጾም አሣን መብላት በተውንበት ዘመን የለም አሳማንም ብትበሉ ትችላላችሁ ተብለው ቅርጥፍ አድርገው እየበሉ ስለ አሳማ መበላት የሚከራከሩ ጥቂቶች አይደሉም። በአደባባይ።
ቆብ ደፍተው ሰልፍ የሚወጡ አባቶች ጥቂቶች አይደሉም።
ደጀ ሰላሞቻቸውን ለፖለቲካ መድረክ ጭምር የሰጡ አብያተ-ክርስቲያኖች ጥቂት አይደሉም። እንዲያወም "ቤተ ክርስቲያናችን የስደተኞች ቤተ-ክርሲያን ነው"ብለው በጠራራ ፀሐይ በአደባባይ የሚናገሩ አሉ። ፎርም ሞልቶና ከገንዘብ ጋር ለቤተ-ክርስቲያን አባልነት የሚጠይቅ አዲስ አባል፤ የቦርድ የመጨረሻ ውሳኔ ካልተጨመረበት አባል መሆን የማይቻልበት ቤተ-ክርስቲያን እንደዚሁ አለ። ሌላም ሌሎች በሀገራችን ላሉ አባቶች፤ ምዕመናንና በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያናችን ጆሮ ያልደረሰ ግን ለእኛ ለውጮቹ የተለመዱ ሆነዋል (ብዙዎች ከዚያ የራቅን ብንሆንም)።
...መጪው አደጋ አሁን'ከምንሳሳለት እርቅ'በእጅጉ የከፋ እንዳይሆን ስጋቴ ነው።
..
ግድ የለም ሁላችንም 'ወደየ በኣታችን'።
..ከዚያም የዚህ ወይም የዚያ ሲኖዶስ ወይም ገለልተኛ ሳይል/ባል ካህናት ከካህናት፤ መዘምራን ከመዘምራን፤ ሰበካ ጉባኤያት ከሰበካ ጉባኤና ከቦርድ አባላት፤ ምዕመናንም ከመእመናን ጋር በየአካባቢው ሲመችም በስቴት ደረጃ ግንኙነቱን በአገልግሎት ብሎም ተቀምጦ በመወያየት ይጀምር፤ ያጠናክር።

ለሁሉም እግዚአብሔር ይጨመርበት

ቴክሳስ

Tekle said...

To those who say we should accept whatever decision the synod in Addis makes, please address the following historic facts about the synod members.
When His Holiness Abune Tewoflos, the 2nd Patriarch of EOTC, was murdered by the derg, there were bishops who signed their names in support of his removal from the Patriarchate.

When His Holiness Abune Merkorios was unjustly removed from his ‘menber’ and exiled by the government, there were bishops who signed their names as well. Even worse was that these bishops told lies saying the His Holiness relinquished his 'menber' because of ill health. Now we know this is an absolute lie.

Now, in both cases of the 2nd and 4th Patriarch there were bishops in the synod who colluded with the earthly powers and removed their brothers.

Should any true Orthodox Christian accept such decisions just because the synod members signed their names under whatever circumstance?

In my view, the position taken by some of the commentators above is an absolute recklessness to blindly accept such decisions just because it is claimed as decision of the synod. We should accept and follow only the truth.

Anonymous said...

@ Hailu... and Tekle...
First let me apologize for being a bit 'simetawi'. I really appreciate the way Hailu responded to my comment; But that doesn't mean I agree.
you can test my orthodox faith in any way you want. The canon of my Orthodox faith have never said a Patriarch cannot be dethroned. Yes, being a Patriarch is a life time authority, but with few condition of dethronement. Eg: Nistrius was a patriarch of Constantinople, and he got dethroned. So there are conditions to dethrone a patriarch, though they are few. The main issue regarding Abune Merkorios is: was the process( of dethronement) done according to the conditions of canon law? That is why most of us feel it is not fair... But,for any reason, if the synod done it, it is valid, and don't forget that time the synod was in full unity! And It is the synod,that has the authority to enthrone or dethrone a patriarch, no other earthly power. The Synod, the patriarch, and all 'kahnat' should not be said earthly power as their authority is not earthly!
@ Teklu....
You are right that their were some Bishops who show agreement with derg for prosecution of H.H Abune Tewofilos. But, be advised, it is not the Holy synod who do this! Those Bishops done it individualy. The case with the 4th patriarch is completely different, b/c it is the Holy synod who decide in this case. We should not confuse the position taken by some Bishops with the decision of Holy synod.
In the Orthodox faith the decision of the Holy synod is above all decisions in the church. It is the synod who should correct past mistakes and bring solution for the current problems.
We need to pray and work hard to help our fathers from both sides to seat together and discuss.
Let our GOD give our fathers the wisdom, peace, and unity!

Anonymous said...

God bless you, Tekle.

Anonymous said...

I appreciate Hailu's comments on the canon law of EOTC. We may say it whatever we like unless we deeply know the law. If we are follower of this Holly Church, we have to ruled by this law whether we like or not. The one who respond for Hailu is in an ambiguous situation about the difference between the two leaderships - the earth and spiritual. In addition,I'm not satisfied with the writer's conclusion even if he begun with truth. If he is talking about peace and unity, how can we believe that with the violation of the canon law. Where is our Christianity?

Hailu said...

To sim aytere (anonymous) who responded above to Hailu and Tekle,

You are absolutely correct about the unjust and non-canonical nature of the removal of the 4th Patriarch from his ‘menber’ in Addis (mind that because it was done for unjust reason it does not have any bearing on the spiritual authority of the Patriarchate). However, I really don’t understand why you choose to contradict yourself.

1. You say that His Holiness Abune Merkorios was removed unjustly but then you seem to suggest such decision by the synod should be accepted.

2. You seem to suggest the synod members made the horrible mistake of removing their brother on their own goodwill. If you are honest, you cannot miss the proven fact the drama was orchestrated by the government.

When I said "by powerful group" in my statement "Is it an earthly power to be a Patriarch that any powerful group can take it away at any time?", I meant the government. I don’t have that contempt to our fathers to call their spiritual leadership an earthly power. However, the unspiritual decisions some have made can force anyone to question their spiritual maturity.
It is sad for you to say "... But,for any reason, if the synod done it, it is valid." How could it be valid if it was done based on LIES?

Anonymous said...

ወንድማችን መ/ር ጳውሎስ ሥጋዊ ሥልጣንን ከመንፈሳዊ የክህነት አገልግሎት ጋር አነጸሮ መመልከቱ በቤተ ክርስቲያን መምህራን የሚባሉ ሰዎች ስለ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ትውፊትና መንፈሳዊነት የዘመናችን መምህራን ያለቻውን የአስተሳሰብ ደረጃ ያመለክታል። እንደኔ እንደኔ አራተኛው ፓትርያርክ ይመለሱ የምላው የቤ/ክንን ልዩነት ከማክሰሙ ባሻገር ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጠበቅም ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብዬ ስለማምን ነው። እንደ ወንድማችን አስተያየት አቡነ መርቆሬዎስን በሥላጣናቸው ሥጋዊ እርባና እንዲያገኙበት የሚደረግ ድርድር ተደርጎ ከታዬ ትክክል አይመሥለኝም ምክንያት በእውነት ለእርሳቸውም ሆነ አበረዋቸው ላሉት ውጩ ዓለም የሚሻላቸው ይመስለኛል። በሀገራችን ያለውን መከራ እያዩ ከመኖርi ያሉበት ዓለም እንደሚሻል የታወቀነው።
ሌላው ለቤ/ክ መለያየት በአንድ ዘመን ሁለት አባቶች መኖራቸው እንደሆነ መምህሩ ከተረዳ እንዴት ሌላ አባት በአዲስ አበባ ሲሾም ልዩነቱን እንዲቀጥል እንደሚያደርገው አልታየውም? ዋናው ቁም ነገር አንድ አባት አንድ መንበር አንድ ሲኖዶስ እንዲኖር ከተፈለገ ሥልጣን የሚባለው የአስተዳደር ሥራ ለባለዘመኖቹ ሰጥቶ ፓትርይርኩን መመለስ ለቤ/ክ አንድነትና ሰላም ታልቅ መፍትሔ ነው። መንግስት ቅዱስ ፈቃዱ ከሆነ!

Unknown said...

ከላይ ስምህን ደብቀህ ለ2ቱ ወገኖች በባዕዳን ቋንቋ መልስ እየሠጠህ ያለኸው ወገን፡"And It is the synod,that has the authority to enthrone or dethrone a patriarch" ሲኖዶስ አንዴ የሾመውን ፓትርያርክ እንደገና መልሶ በሚሽርበት መስፈርት ነበር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ከሥልጣናቸው ''የሻራቸው''? የሃይማኖት ሕጸጽ ተገኝቶባቸው ነው ? አእምሮዋቸውን ስተው ነው ? በደዌ ዳኛ ባልጋ ቁራኛ ተይዘው መዳን የማችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰው ነው ? በነዚህ ምክንያቶች ካልሆነ አንዴ ''ብፁዕ ወቅዱስ ወርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት '' ብሎ የሾመ ሲኖዶስ ''የዐይንህ ቀለም አላማረንም'' ብሎ እንደተራ ሙያተኛ ወግድ ከዚህ ጥፋ ብሎ ማባረር እንደሚችል እኮ ነው እየነገርከን ያለኸው። የተ ያገኘኸው መረጃ ነው ? እስቲ በድጋሚ ሃሳቡን የቀዳህበትን ምንጩን አመላክተንና እንመልከተው። ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰን ሲኖዶስስ እንዴት ነው ቅዱስና ሕጋዊ/ቀኖናዊ ብልን አመራሩን እንድንቀበል የምንገደድበት ምክንያት? የምንገደድበት ሕግ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የትኛው አንቀጽ ላይ ተጥቅሷል? ፍትሐ ነገሥት ? በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዓለማዊ መንግሥት የራሱን ሕገ መንግሥት ስለሚጥስ ሲኖዶሱም ያን ነው አርዓያው አድርጎ መከተል ያለበት ከተባለ በግልጽ ይነገረን። ለማንኛውም ብትችል የፊደላችን ባለቤት ስለሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ስለሆነ እየተነጋገርን ያለነው በራሳችን ፊደል ብትጽፈው ይመረጣል። ከትሕትና ጋር ፤ ከበደ ቦጋለ ዘውእቱ ሰማዕተ ጽድቅ ።

Anonymous said...

ይድረስ ለደጀ ሰላም
ከጥቂት ቀናት ወዲህ ደጀ ሰላም የሚያካሂደው ውይይት ዕርቀ ሰላም ለማውረድ ከሚደረገው ጥረት እየራቀ በመሄድ አንዱን ወይም ሌላውን ወገን በመደገፍ ወደ ሙግትና ወደ አሰልቺ ንትርክ ያደላ ይመስላል። ይህ ደግሞ ሃያ ዓመት በከንቱ የባከነበት ፍሬ አልባ ድርጊት ስለሆነ ውይይቱ ዕርቀ ሰላሙ እውን እንዲሆን ወደሚረዱት ገንቢና አግባቢ ሀሳቦች ቢያቀና ይበጃል።

Zetewahido said...

May God bless my brother/sister who wrote.

"እንደኔ እንደኔ አራተኛው ፓትርያርክ ይመለሱ የምላው የቤ/ክንን ልዩነት ከማክሰሙ ባሻገር ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጠበቅም ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብዬ ስለማምን ነው። እንደ ወንድማችን አስተያየት አቡነ መርቆሬዎስን በሥላጣናቸው ሥጋዊ እርባና እንዲያገኙበት የሚደረግ ድርድር ተደርጎ ከታዬ ትክክል አይመሥለኝም ምክንያት በእውነት ለእርሳቸውም ሆነ አበረዋቸው ላሉት ውጩ ዓለም የሚሻላቸው ይመስለኛል። በሀገራችን ያለውን መከራ እያዩ ከመኖር! ያሉበት ዓለም እንደሚሻል የታወቀ ነው።"

I may add, if we fail to correct the mistake now, it will remain as precedence for any earthly power or powerful group to remove the Patriarch of EOTC any time in the future.

May God help us take the right course of action to unit our beloved Church, EOTC.

Anonymous said...

@ Kebede Bogale:
"ሲኖዶስ አንዴ የሾመውን ፓትርያርክ እንደገና መልሶ በሚሽርበት መስፈርት ነበር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ከሥልጣናቸው ''የሻራቸው''?"
የነ መልስ፡_ ነው ብዬ አላምንም!
አላማዬ ፓትርያርክ "ፈጽሞ የማይሻር" አለመሆኑን ለማመልከት እንጅ አቡነ መርቆርዮስ የተሻሩት በቀኖናችን መሠረት አንተ ከዘረዘርካቸው ምክንያቶች በአንዱ ነው ለማለት አይደለም። እኒ በወቅቱ ህጻን ነበርኩ፤ በክርስትናም ገና አልተወለድኩም ነበር። ታድያ አሁን ላይ ሆኜ ከ 2 አሥርት አመታት በፊት የሆነን እና በአግባቡ ያልተገለጠን ነገር እንድህ ነው ማለት አልችልም። ባለኝ መረጃ ልክ የራሴን አስተሳሰብ ይዛለው እንጅ!
እርግጥ ነው፤ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ሲኖዶስ ሊሳሳት ይችላል። ለምሳሌ፦ የከልቄዶን አለም አቀፍ ሲኖዶስ ተሳስቶ ነበር።
የኔ አሳብ ግን ሲኖዶስ ከተሳሳተ ስህተቱን በራሱ እንዲያርም እንወተውተዋለን ወይስ አናውቅህም ብለን እራሳችንን ሲኖዶስ እናረጋለን?፣ ወይስ ሌላ ሲኖዶስ እንመሰርታለን? ይህን ካደረግን የማን ስህተት ይብሳል?
ዋኖቻችንን ተሳስታችኋል ብለን ካፈነገጥን እኛስ ትክክል ስለመሆናችን ምን ዋስትና ይኖረናል? ሃይማኖታችን ቅዱስ ሲኖዶስ ትክክል የመሰለንን ሲወስን እንድንቀበለው፤ ትክክል ያልመሰለንን ሲወስን ደግሞ አናቅህም/አንቀበልህም፤ ውሳኔውንም የትቅት አባቶች ውሳኔ እንድንል ያዛል። እንድህ አይነት ሥርአት ካለ እስቲ አስረዱኝ።
አስለዚህ እኒ እያልኩ ያለሁት እራሳችንን "ከሲኖዶስነት" እናውርድ እና ምዕመን እንሁን፤ አባቶችንም እባካችሁ ቁጭ ብላችሁ ምከሩ ባለፉት ስህተቶች ለታመመችም ቤተ ክርስቲአን መድህኒት የሚሆን ውሳኔ ወስኑ እያልን እንወትውት፤ ለዚህም እንጸልይ፤ የሚያስፈልገውንም ለማድረግ እንትጋ ነው።

Anonymous said...

ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ - ይበጣጠስ!


ለቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ያልሆነ
ጳጳስ - ይበጣጠስ!


ለቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ያልሆነ
የሰንበት ት/ቤት - ይበጣጠስ!


ለቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ያልሆነ
መንፈሳዊ ማኅበር - ይበጣጠስ!


ለቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ያልሆነ
ሰባኪ - ይበጣጠስ!


ለቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ያልሆነ
ዘማሪ - ይበጣጠስ!


ለቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ያልሆነ
የቤተክርስቲያን አገልጋይ - ይበጣጠስ!


ለቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ያልሆነ
ምእመን - ይበጣጠስ!

Anonymous said...

አባቶችን እናውቃቸዋለን፡፡ የዋሆች ናቸው፡፡ ሁሉም ነገር ለአደባባይ የበቃውም በየዋህነታቸው ነው፤ ግትር የሆኑትም በክፋት ሳይሆን የዋህነታቸው በዝቶ ነው፡፡ የዋሆች ባይሆኑ ኖሮ ትናንት አንድ ጥግ ይዘው ሲተቿቸው እና ሲያንጓጥጧቸው የነበሩ ዛሬ ራሳቸውን ሽማግሌ አድርገው ፊታቸው ላይ በሽንገላ ከንፈር “አባታችን” እያሉ ሲጥመለመሉ ባልተቀበሏቸው ነበር፡፡ እነሱም የአባቶችን የዋህነት ተጠቅመው በጉዳዩ ትከሻ ላይ ተንጠልጥለው የራሳቸውን ስም ለማስጠራት መነሳታቸው አሳዛኝ የታሪክ ተወቃሽነት የሚያስከትል መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡

danf said...

BETAM ASTEMARI INA HULUM KIRSTIAN LISEMAW YEMIGEBA GUDAY NAW. DEJESELAMOCH BETECHALE METEN YIHEN TSUF HULUM LISEMAW SILEMIGEBA IBAKACHU BEMEGENAGNIYA BUZUHAN YITELALEF ZEND YEBEKULACHUN ADIRGU.

Anonymous said...

ባህር ማዶ ላላችሁት
· የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ለዕርቅ ጥረት ማድረግ የጀመረው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሉስ እረፍት በፊት መሆኑ እሙን ነው፡፡ እርሳቸው በሕይወት እያሉ እርቁ ቢሳካ ኖሮ 20 ዓመታት የቆዩበትን መንበር ይልቀቁልን እንደማትሉ ይታመናል፡፡ መቼም አንተ ተዋርደህ እኔ ከብሬ እንታረቅ ብሎ ድርድር የሚጀምር በታሪክ ውስጥ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ ስለዚህ የተጀመረው ዕርቀ ሰላም በመልካም ሁኔታ እንዲፈጸም፡-
1. የቅዱስነታቸውን የአቡነ መርቆርዮስን ወደ መንበራቸው መመለስን የዕርቅ ድርድር ውስጥ ባታስገቡ፡፡ የምትታረቁት ለሹመት አይደለምና፡፡ የሀገር ቤቱ ሲኖዶስም በተደጋጋሚ አሜሪካ ድረስ በመመላለስ ለዕርቀ ሰላሙ እና ለአንድነቱ ያለውን ፈቃደኝነት ሲያሳይ የቅዱስነታቸው አቡነ መርቆርዮስን አባትነት አምኖ መሆኑን መዘንጋት የለባችሁም፡፡ ዕርቁና ሹመቱ ተለያይተው ቢታዩ መልካም ነው፡፡ ቅዱስነታቸው አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው ቢመለሱ የሚጠላ የለም፤ ለዚህ ግን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተፈጠረ ቅሬታ ካለ ቅድሚያ እሱን መፍታት ይኖርባችኋል፡፡ What is the main cause of this disunity? The only thing that divided the fathers is this issue. How on earth you say this? Yor are not Paulos, but Sauol! Yemewugeawun biret bitkawem lante yibisibhal!

Anonymous said...

የመጨረሻው ዘመን ላይ ስለሆንን በቤተክርስትያን ላይ መከራ ችግር ፈተና እንዲሁም በረቀቀ ሁኔታ ሰይጣን በድካማችንና በፍላጎታችን ውስጥ በመግባት ይገኛል። ወገኖቼ ከዛሬ ነገ የፈተናው አይነት እየበዛ እንጂ እቀነሰ አይመጣም። ስለዚህ በፀሎትና በፆም አብዝተን አምላክን መጠየቅ አለብን። ልብ ያለው ልብ ይበል።

Anonymous said...


ጠላት ዲያብሎስ ቤተክርስቲያናችንን ለመበታተን፣ ይህም ባይሳካለት ምእመናንን ማስኮብለሉን ሊቀጥል ማለት ነው?

የአፍቃሪ ወያኔው ፓትርያርክ አባ ጳውሎስ ከመነሻው ሹመታቸው ሕገ-ቤተክርስቲያንን የጣሰ ስለነበር ነው ተቃውሞ የገጠመው። በኋላም ግብራቸውም እንዳስመሰከረው በ5ኛው የፓትርያርክነት ዘመናቸው ቤተክርስቲያናት ተዘርፈዋል፣ ንዋዬ ቅድሳት ተመዝብረዋል፣ ምእመናን ተሰይፈዋል፣ አባቶች ተሰድደዋል፣ ገዳማት ተቃጥለዋል፣ አሁንም የዋልድባ ገዳም እየታረሰ ይገኛል፣ የተሃድሶ መናፍቃንን በማስፈልፈልና በመሾም እምነታችንን ሲያስበርዙ ምእመናንን ሲያስኮበልሉ ቆይተዋል። 20 ዓመት ሙሉ ቤተክርስቲያናችን ያሳለፈችበትን ዘመን "የጨለማው ዘመን" እንዲባልም አስገድዷል። ይህ በቤተክርስቲያን ላይ የደረሰው ጥፋት ሁሉ ምንጩ የመንግሥትን ፈርጣማ ክንድ ተንተርሶ ሕገ-ቤተክርስቲያንን በመጣስ በተደረገ የፕትርክና ሹመት መሆኑ ግልጽ ነው።

አንዲት አገር እንደ አገር ሕዝቧን በሰላም አንድ አድርጋ ለማስተዳደር በሕግ ትመራለች። አንድ መንግሥትም እንደ መንግሥት አገርን ለመምራትና መንበረ መንግሥቱን ለማስቀጠል የሕጎች የበላይ የሆነውን ሕገ መንግሥት አክብሮ እና አስከብሮ ይኖራል። የወያኔ መንግሥትም "በነፃነት፣ በዴሞክራሲ፣ በእኩልነት፣ በፍትሐዊነት ጥያቄ ስም ሕገ-መንግሥቴን በሃይል ለመናድ የሚታገሉ አሸባሪዎች ናቸው" እያለ ዘብጥያ የሚያወርዳቸው ስንቶቹን ነው? ወያኔም "ሕገ-መንግሥቴ ከሌለ እኔም የለሁም!" በማለት ሌሎቹ ተቀበሉት አልተቀበሉት ሳይሆን፣ የመሠረተውን መንግሥት በመንግሥትነቱ ለማስቀጠልና ጅምር ዓላማዎቹን ለማሳካት ሲል ሕገ-መንግሥቱን አጽንቶ መያዝ፣ ይህንንም እውን ለማድረግ ደግሞ የማይመዝዘው ሰይፍ፣ የማይቀብረው ፈንጅ እንደሌለ አይተናል።


ታዲያ ወያኔ ለዓለማዊ መንግሥቱ "ሕገ-መንግሥት ወይም ሞት!" እንዳለ ሁሉ የቤተክርስቲያንም ሕገ-መንግሥቷ ቀኖናዋ ነው። ከላይ "የጎንደር ምንቸት ውጣ የትግሬ ምንቸት ግባ" ብለው ጎሳና ዘር ቆጥረው የፃፉትም ጸሐፊ አማራጭ ሃሳባቸውን ባያካፍሉንም "መጀመሪያ ቀኖናው ይከበር" በሚለው ሃሳብ በተለይም በቤተክርስቲያን መፃኢ ሰላም ላይ የዘር መርዛቸውን በመርጨት የቱባ ወያኔዎቹን ባለስልጣናት አባባል አንፀባርቀውታል። ይህም ቀደም ሲል በአቶ ተፈራ ዋልዋ፣ በቅርቡም በአቦይ ስብሃት በአደባባይ ሲለፈፍ ቆይቷል፣ ዛቻቸውንም ወደ እውነት እየተረጎሙት አይተናል።

ታዲያ አገራችን የብሔር-ብሔረሰቦች አገር እንደመሆኗ መጠን፣ የሚሾመውም አንድ ፓትርያርክ ብቻ እስከሆነ ድረስ፣ ፓትርያርክ ሊሆን የሚችለው ካሉት ብሔር ብሔረሰቦች ውስጥ የአንደኛው ብሔር ሊሆን ግድ ይሆናል። ጉዳዩ ከብሔሩ ወይም ከጎሳው ሳይሆን ሕገ ቤተክርስቲያንን "አክብሮ በማስከበር" እና "በአለማክበር" ወይም "በእምነት ጸንቶ ከመኖር እና ካለመኖር" ላይ ነው የሚሆነው።

በዚህ የዘረኝነት ልክፍት ከቀጠልንም የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅድስት አርሴማ ሰማዕትነትን፣ እንዲሁም እነ ቅዱስ ኤፍሬም እና አባ ህርያቆስ የደረሷቸውን ጸሎቶች፣ ወዘተ ኢትዮጵያውያን ያውም ከእኛ ብሔር ስላልሆኑ አንቀበልም ልንል ነውን? ይህንንማ እኮ መናፍቃን በግልጽ እየሰበኩን ይገኛሉ። የግድ የበግ ለምድ መልበሱ አስፈላጊ አይደለም። ብቻ ቆይታችሁም ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጎሳ ስላልሆነ አናመልከውም እንዳትሉ እንሰጋለን።


ታዲያ ይህ የዘረኝነት ችግር ካልሆነ የእርቁ ነገር ለምን አስፈራን? "ወንድሜ ሆይ በመጀመሪያ ሂድና ከወንድምህ ጋር ታረቅ" የተባለውን የጌታ ትዕዛዝ ማስታወሱ ይበጃል፤ "የኋለኛይቱ ስህተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለች"ና (ማቴ 27-64) "ከ5ኛ ወደ 6ኛ ፓትርያርክ እንጅ እንዴት ወደ 4ኛ ወደ ኋላ እንመለሳለን" የሚለው አባባል ቁጥር ነው የሚያስጨንቀን ወይንስ ሕገ-ቤተክርስቲያን? ወደ ኋላ ተመልሶ በፊት የተጣመመውን ማስተካከልና መመለስ ካልተቻለ፣ በሃጢያት ውስጥ ያለ ሰው ንስሃ ከገባ ሃጢያቱ ይሰረይለታል። ተመልሶ ሃጢያት እንዳልሠራ ይሆናል። የሚባለውን አስተምህሮት እንዴት እናየዋለን? ንስሃ መግባት ሃጢያትን መልሶ ካነፃ የተጣመመውን ሕገ-ቤተክርስቲያን በንስሃ እንዴት ማስተካከል አይገባም?

ቤተክርስቲያን ሄደን ለፈጣሪያችን በህብረት ጸሎት "እግዚኦ ማህረነ ክርስቶስ" በማለት የምህላ ፀሎት ማድረግና የጌታን መልካም ፈቃድ መጠየቅ እንዳይቻል፤ ቤተክርስቲያኒቷን ተቆጣጥሮ ያለው የጨለማው ቡድን በመሆኑ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ "እልል በሉ! አጨብጭቡ! ነው የሚባለው። እንዲያ ሲልም ሙስናው ሥር በሰደደ መጠን አስተዳዳሪውና የሰበካ ጉባኤው ተጣሉ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ወይም ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው እንዲህ የሚያስደርጉን ሲባል መስማት ነው!

አንዳንዴም ከቤተክርስቲያን ወጣ ስንል ቀን ዘማሪ የነበረው ማታ ጨፋሪ ሆነው በሚገኙት የተሃድሶ ወገናት የቤተክርስቲያንን ክብርና ቅድስና ሲያስረክሱት ማየት ነው። ከዚያም ወጣ ሲባል ማንነቱን የዘነጋ፣ ለአገሩም ሆነ ለሃይማኖቱ ደንታ የሌለው፣ ፀጉሩን ያንጨበረረ፣ ሱሪውን ዝቅ አድርጎ ቂጥኝ እንደያዘውና ሞያሌ እግሩን እንደበላው ሰው ፎቀቅ ፎቀቅ የሚል ትውልድ ነው የምናገኜው። ይህ ሁሉ ዝብርቅርቅ ሕገ-ቤተክርስቲያን በየደረጃው በመጣሱ እና በመናቁ የተነሳ አይደለምን?

በስደት ላላችሁትና እርቀሰላሙን ለምትደግፉ በሙሉ፤ "እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ፤ ከምኩራባቸው ያወጡአችኋል። ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድሏችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። (ዮሐ ም16 ቁ1-2)። "ከሰው ይልቅ፤ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል" (የሐዋ ም5 ቁ29) ይላልና በአቋማችሁ እንድትጸኑ።

አንድ ቅዱስ አባት "ቤተክርስቲያንን ለፈተና አጋልጠን ወደ ገዳም አንገባም" ያሉትን ቃል ሳስብ የተስፋ ብርሃን ይፈነጥቅብኛል። እኛንም እረኛ እንደሌለው በግ ከመበተን የሚጠብቁን ጥቂት ሆነው በእግዚአብሔር እርዳታ ድል የሚያደርጉ አባቶች አይጠፉም በማለት።

አሁን እኛ ባለንበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን የጎደለውን ሞልተን፣ የተጣመመውን አስተካክለን፣ የጎበጠውን አቅንተን፣ ቤተክርስቲያናችንን በአንድነትና በሰላም፣ በሕገ-ቤተክርስቲያን መምራት ሲገባን፤ አሁንም የዘመነ-መሣፍንትን ታሪክ እያነሳን፣ ስለአንድነት ሳይሆን ስለመለያየት፣ ስለሰላም ሳይሆን ስለ ዘር ጥላቻ የምንሰብክና የምንታገል ከሆነ፣ ባለፉት 20 የጨለማ ዓመታት ለደረሱት ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ካልተፈለገለት፤ በሌላው ጎራ ደግሞ ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ - ይበጣጠስ! ለቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላምም ያልሆነ ጳጳስ፣ የሰንበት ት/ቤት፣ መንፈሳዊ ማኅበር፣ ሰባኪ፣ ዘማሪ፣ የቤተክርስቲያን አገልጋይ፣ ምእመን - ይበጣጠሱ! በማለት የተሰጠው አስተያዬት እውን ሆኖ ወደ ተባባሰ ሁኔታ ካመራ ሊደርስ የሚችለው ጥፋት በቃላት የማይገለጽ፣ በቀላሉ የማይገመት ይሆናል።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
እግዚአብሔር ቤቱን ይጠብቅ

TEKILEYE said...

dont juge. i think you better stop reading bible and you are in the rong road please read your friends blog. they never juge and they try to get the old orthodox in ethiopia. who are you to tell to the pop that cant be in the power again. you dont know how hard to prctice realigion out of your country antema min hasa alebihe

Sinner said...

To "Anonymous" who is responding to "Haile" and "Tekle" and all.

Adam sinned and even though he was repentant he still suffered the concequece. Even to this day we Christians are forgiven from our original sin; however, we are not completely free from transgressing God’s law until we leave this earth. The lesson is sin exists, no excuse or opinion will undo it, Adam could not get his grace back while living on earth, Abel was not revived from death, we need to bare the consequence, and hope for the grace of God to help us repent daily.

If the opinion is true concerning the unrighteous removal of Abune Merkorios, then, the correct way to proceed to correcting situation where God’s law was broken is REPENTANCE. That is to mean, there needs to be recognition of the sin/trangression of God's law/Church cannon committed by the individuals then a return to righteous action. This can only be done by the every people who are in need to repent, "we did this ___ and it was wrong, now we are on the correct path.” Whether done privately (between all our fathers) or announced to the whole church this is the step needed.

The reason for all confusion and division is because there is no repentance. What will happen if this continues? The transgression will continue and get worse (just like in Noah’s time). Ethiopian Orthodox followers are we as a church following all the church cannon laws universally and even within our individual churches? We are in difficult times. My main point is we cannot undo the concequence of sin caused by our selves or others, what has happened has happened, at this point we need to cry for our selves and the whole church like Adam, and hold fast to God’s Law like Noah and Lot until God’s judgment comes, just because God is quite does not mean He is not observing. This is what I have learned from my fathers.

Anonymous said...

ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባቶች እንዲሁም ልጆች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አድረሳችሁ። የተላለፉትን አሰተያየቶች እንደተመለከትኩት የተለያዩ አመለካከቶች ተስተናግደዋል መልካም ነው የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በመሆኑ ተገቢም ነው። አሁን እንደምመለከተው በአስተያየቶቹ ላይ ያለው ሁኔታ አንዱ የአንዱን በመደግፍና በመቃወም ላይ እንጅ ብዙው ነገር ለቤተ ክርስቲያኗ የሚጠቅማት ሆኖ አይታይም። ይህንም ለማለት የምደፍርበት ዋናው ምክንያት የእግዚአብሔር ሳይሆን የሰው እጅ ስለበዛት ነው ይህም ማለት ከመጀመሪያው የፓትሪያርክ ሹመት ጀምሮ የሰው እጅ አለበት። ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ሥልጣን ነበራችው የሳቸውን ለየት የሚያደርገው የእምነቱ ተከታይ መሆናችው ነው። ከዛ በኋላ ወደ ሥልጣንየመጡት ኮሎኔል መንግሥቱና አቶ መለሰ የርእዮተ ዓለም አራማጅ ስለነብሩ የሁለቱም ጡንቻ በቤተ ክርስቲያን ጠንከር ብሎ ታይቶአል። የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ለምን ይታያል ቢባል ቀላል መልስ የሚሆነው ከፍራቻ የሚመጭ ነው ም ክንያቱም ብዙ የሕዝብ ቁጥር ስለሚታይበት አደገኛ ነው ብሎ በማሰብ ነው። ይህንን ከተገነዘብን የአሁኑ የቤተ