January 28, 2013

ቤተ ክህነት የአዲሱን ፓትርያርክ ምርጫ የሚቃወሙትን እንደምትከስ አስፈራራች


(ደጀ ሰላም፤ ጥር 20/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 28/2013/ PDF)፦ ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ ሰላማዊ የሽግግር ጊዜውን ለማደናቀፍ የሚገኙ ቡድኖችን፣ የመገናኛ ብዙኅንና ግለሰቦችን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ማስጠንቀቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል የስድስተኛውን ፓትርያርክ አሿሿም በሚመለከት ሕገ ደንብ ወጥቶ ምርጫውን ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ውስጥ መሆኑን የሚያውቁ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኅን፣ ከውስጥ አፍራሽ ኃይሎች የሚቀበሉትን ፀረ ሰላምና ከእውነት የራቀ አሉባልታ ከድረ ገጽ ያገኙ በማስመሰልና ምንጮቻችን እያሉ በውጭና በአገር ውስጥ ያለውን ምዕመናን እያወናበዱ በሚገኙት ላይ ቤተ ክህነት ክስ መመሥረቷን የዘገበው ጋዜጣው መግለጫውን የሰጡት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሳይሆኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ መሆናቸውን አብራርቷል።


የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የተጠቀሙባቸው ቃላት በርግጥ ጉዳዩ የቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ሌላ አስመስሎታል። “ፀረ ሰላም፣ ማደናቀፍ፣ አፍራሽ ኃይሎች” የሚሉትን ቃላት በቤተ ክህነት ሳይሆን በቤተ መንግሥት አደባባይ ሲነገር ስለምናውቃቸው አሁንም ማስጠንቀቂያው የማን ነው የሚለውን እንድንጠይቅ ያደርገናል። ማስፈራራት ግን መልስ አይደለም። ግዴላችሁም ልብ መግዛት ይሻላል። ለማንኛውም የዚህን ዜና ዝርዝር ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል።       

ቸር ወሬ ያሰማን አሜን

ቤተ ክህነት የፓትርያርክ ምርጫን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱትን አስጠነቀቀች

-   በአንዳንዶቹ ላይ ክስ መሥርታለች፤

(ሪፖርተር ጋዜጣ)፦ የቀድሞውን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን ሕልፈት ተከትሎ፣ ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ ሰላማዊ የሽግግር ጊዜውን ለማደናቀፍ የሚገኙ ቡድኖችን፣ የመገናኛ ብዙኅንና ግለሰቦችን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስጠነቀቀ፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔን በማሟላት የቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና በሚያዘው መሠረት፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን በመምራት በሕጉ መሠረት መንበሩን የሚጠብቁ አባት በመሰየም ቀጣይ ጉዞ ሰላማዊ ለማድረግ እየተሠራ ባለበት በአሀኑ ጊዜ፣ ከውስጥና ከውጭ ያሉ በጐ አመለካከት የሌላቸው ግለሰቦች አፍራሽ ተግባር እየፈጸሙ እንደሚገኙ ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡ 

የስድስተኛውን ፓትርያርክ አሿሿም በሚመለከት ሕገ ደንብ ወጥቶ ምርጫውን ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ውስጥ መሆኑን የሚያውቁ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኅን፣ ከውስጥ አፍራሽ ኃይሎች የሚቀበሉትን ፀረ ሰላምና ከእውነት የራቀ አሉባልታ ከድረ ገጽ ያገኙ በማስመሰልና ‹‹ምንጮቻችን›› እያሉ በውጭና በአገር ውስጥ ያለውን ምዕመናን እያወናበዱ በሚገኙት ላይ፣ ቤተ ክህነት ክስ መመሥረቷን ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል፡፡

በአንድነትና በመደማመጥ መንፈስ እየሠራ የሚገኘውን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ አሉባልታ በመንዛት ትርምስ እንዲፈጠር ለማድረግ የሚንቀሳቀሱት ቡድኖችም ሆኑ ግለሰቦች ከቃላት ያለፈ ተግባር መፈጸም የማይችሉ ቢሆንም፣ ዝም ብሎ መመልከቱ ድርጊታቸውን እንደመደገፍ ስለሚቆጠር፣ በቀጣይም በመገናኛ ብዙኅኑም ላይ ሆነ በግለሰቦቹ ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ቤተ ክህነት በዝግጅት ላይ መሆኗን፣ የቤተ ክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ አስታውቀዋል፡፡

ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ወይም የሚመለከታቸው ኃላፊዎች ማብራሪያና መግለጫ ሳይሰጡ፣ ምስላቸውንና እነሱ እንደተናገሩ በማስመሰል በአንዳንድ ድረ ገጾችና የመገናኛ ብዙኅን እየተገለጸና እየተጻፈ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ሕዝቡ ወደ ትርምስና አላስፈላጊ ሁኔታ ውስጥ እንዳይገባ የሚያደርጉትን አመስግነዋል፡፡ ቤተ ክህነት ትክክለኛ መረጃ ለሕዝብ እንዲደርስ የምትፈልግና የምትደግፍ መሆኑን አክለው፣ ያልተባለን ተብሏል ብሎ ፎቶን በማስደገፍ ባገኙት ቦታ መለጠፍ የሚያስጠይቅ ከመሆኑም ባሻገር ተገቢ አለመሆኑንም አስረድተዋል፡፡

18 comments:

Anonymous said...

እኔ እቃወማለሁ ፣ አጥብቄ እቃወማለሁ ፣ በሙሉ ጉልበቴ እቃወማለሁ ። የቤተ ክህነት ክስ ከቤተክርስቲያን ሠላም አይበልጥም !!!
ድሮስ ከ ሴ ረኛ መንግስትና ካድሬ የሚጠበቀው ይህ አይደለ እንዴ !!!
እኛም እኮ ከ ተኩላ ወተት ጠበቅን :አሁንስ ጫካ ግቡ ይመስላል


ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርክ !!!!

ደመቀ said...

እሸቴ ደመቀ
እስቲ ከልባችሁ ከሆነ እዚህ ህግ ካለበት ከምእራቡ አለም ላይ ሆናችሁ ለማስፈራራት ሞክሩ።መሳቂያ ነበር የምትሆኑት! ሃሎ! በቤተ-ክርስቲያን መቀለዱን የጀመራችሁት ዛሬ ሳይሆን ህገ-ወጥ ፓትርያርክ ከሃያ አመት በፊት ስታስቀምጡ ነው።ዋልድባ ሁለቱን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቷል ገና ይቀጥላል።

Unknown said...

Folks: it is getting dirtier and dirtier. To keep quiet dumbly or even to remain at the level of mere talk amounts now to betraying those in danger, and ultimately, to a denial of God. We have deliberated enough, let us act now. ACT!

Anonymous said...

"አዲሱን ፓትርያርክ ምርጫ የሚቃወሙትን እንደምትከስ አስፈራራች"

ይገርማል ያሳዝናል

ከመንግስት ጋር ሆነው አባ ሳሙኤልን ወይም መሰል ለመምረጥ ታጥቀው ተነስተዋል
ምእመናን ቢቀበሉ ባይቀበሉ ግድ የላቸውም መንፈሳዊነትም የላቸው
ወጣቱም ትቶ ወደሌላ ቢሄድ እነሱ በድሎትና በቅምጥልና የሚያኖራቸው ገንዘብ
የደሀው ወዝ ለመኪና ለወርቅ በቂ አለን በለው ተነስተዋል
ወንጌልን ለማስተማር አልተሰማሩም

Anonymous said...

this is a reality shows "gun and bullets" Ato Eskender gbre seytan weyane,you will pay the price a person like you don't belong holly church area. the time will come!!!

Anonymous said...

ke zinb maar Endemayitebek ke WEYANE ***SELAM*** ayitebekim.yezare 20 amet bemadenager yetederegew zare begehad.EGZIABHER bizegeyim yasayal Eskeziyaw atibiken Enkawemalen!!!!

Anonymous said...

ቤተክርስቲያንን ለሚሰቅሏት እና ለሚያሰቅሏት ወዮላቸው!
Read the whole article opening this link:-
http://gudayachn.blogspot.no/2013/01/blog-post_16.html

Anonymous said...

እግዚኦ ማህረነ ክርስቶስ!
የነዚህን የተረገሙ ሰዎች ያለቦታቸው ገብተው የሚዘባርቁ ምን ይሻላል?
አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ ብሎ የቤተ ክህነት ሰው ሲሳይ መረሳ ብሎ አስተዳዳሪ እግዚኦ የሰው ያለህ ነው መቸም ኧረ ስንቱን ተሸከምን ስንቱን አየን የማይገባቸውን በድፍረት የጵጵስና ቆብ የጫኑትን ጥቁር ለበስ ወንደ ላጤዎችንና እነሱንም አይዞችሁ መንበሯን ብቻ ያዙ የሚሉትንም ክፉ መካሪ “ዲያቆናት” “ሰባኪያነ ወንጌል” የሰላም አምባሳደር “አውተር” ጆከር ሁሉም ቀለዱ ቤትህን ተዳፈሩ ተቀራመቱ በክርስቲያኑንም ላይ ተማከሩ በምድራዊ ፍርድ ቤት እናስፈርድብሀለን ብለው ዛቱ ጌታ ሆይ አንተ አምላካችን ክንድህን አንሳ አሁንም አሳያቸው ፍረድባቸው አሁንም ህልውናህን ዘንግተዋልና ልባቸውም በጥቅምና በዘር ተሰውሮባቸዋልና ለጥፍትም የተመደቡ ናቸውና አምላክ ሆይ በነዚህ ሰወች ላይ ፍረድ።
አሁንም ገዳማትን ያፈረሰ ይፍረስ!
አባቶችን ያሰረ ያሳደደ ያዋረደ በታላቅ ጉባኤ ላይ ይዋረድ አንገቱን ይድፋ ከዛም ወደ እንጦሮጦስ ይዳፋ!
ቤተክርስቲያናችንን ለማጥፋት የተነሳ እርሱ ይጥፋ! በሀይማኖታችን እጁን ያስረዘመ ወያኔ ይውደም!! ይደምሰስ !!!
እድሜው ይጠር ይጥፋ!!
ይህም እርግማን “ከቃላት ያለፈ ተግባር” መሆኑን ባለቆቻቸው ላይ ደርሶ ስላልተረዱት በራሳቸው ላይ ይውረድ!!!

Ben said...

እኔስ፡የአስተያየት፡ናዳ፡ማንበን፡ሰለቸኝ፡፡ከዚህ፡በፊት፡በአስተያየቴ፡ለመግለጽ፡እንደሞከርኩት፡አስተያየት፡ብቻውን፡እንደ-ከንፈር፡መምጠጥ፡ይቆጠራልና፡ለሃይማኖት፡ለእውነት፡የቆማችሁ፡ሁሉ፡በቁርጠኝነት፡በጸሎት፡በመታገዝ፡እንነሳ፡፡

መርሆዓችንም፡-

" ታቢታ፡ቁሚ" ይሁን፡፡

አዎን፡ሃይማኖታችንን፡እንጠብቅ፡ተኩላዎችን፡አጥብቀን፡እንቃወም፡አለበለዚያ፡የሚደርሰው፡አደጋ፡ከምንገምተው፡በላይ፡ዋጋ፡ያስከፍለናል፡፡

Anonymous said...

Thanks to Almighty after 21 years people get to understand what Weyans are . believe me as long as we keep silent and say the usual I don't care music " God will punish them" over and over we will jeopardize our church. I do believe God will pay them in full to what they did and keep doing . How about us do you guys think keeping quiet will lead us to reward? I don't think so. We all are responsible

Anonymous said...

ቤተክርስቲያን minim aladeregechim አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ new meglecha yesetew so, ቤተክርስቲያን አስፈራራች banil yimeretal!!!!

ቤተክርስቲያንን ለሚሰቅሏት እና ለሚያሰቅሏት ወዮላቸው!

Anonymous said...

http://mesfinwoldemariam.wordpress.com

አቶ ዳንኤል ለመናገርና ለመጻፍ ያለው ፍጥነት በሚናገርባቸው ጉዳዮች ላይ ካለው እውቀት ጋር አይመጣጠንም፤ እንዲያውም ያውቃል እንዲባል የሚጽፍ አንጂ አውቆ የሚጽፍ አይመስልም፤ አቶ ዳንኤል ሳላውቀው በጻፈው ላይ አስተያየት ስሰጥ ይህ ሁለተኛዬ ነው፤ ከዚህ በፊት በአንድ ጋዜጣ ላይ በጣም የታወቀውን የአየርላንድ ችጋር በ150 ዓመታት ያህል አቅርቦት በማየቴ አስተያየት ሰጥቼበት ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ስለመክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ በጻፈው ላይ አጭር አስተያየት ልስጥ፤ እንዲያው እንትንን እንትን ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል የሚባለውን በመከተል እንጂ ትርፍ ይኖረዋል ብዬ አልገምትም፤ ከደርግ ዘመን ጀምሮ የተለያዩ ካድሬዎች ደብተራዎችም ጭምር ማነብነብን እንደተናጋሪነት ሠልጥነውበታል፤ ስለዚህም ሰውም ማነብነባቸውን እንደእውቀት እየወሰደው ይወናበዳልና በጊዜው መልስ መስጠት ግዴታ ይመስለኛል፤ የሰው ልጅ በምን ይታፈራል? በወንበር፤ በወንበር አይደለም በከንፈር፤ ይባላል፡፡

ነገር ሳላበዛ ጥቂት ነጥቦችን በማንሣት የአቶ ዳንኤልን የማንበብ ችሎታና የተንኮል ክህነት ብቻ ለአንባቢዎች ላሳይ፤ ስለአስተያየቱ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ አይደለም፡፡

አንደኛ፣ ደጋግሜ እንብቤዋለሁ ይላል፤ ይህንን ባይነግረን ጥሩ ነበር፤ በመናገሩ ብቻ እንዳናምነው ማስረጃ ይሰጠናል፤ ያላነበበውን ደጋግሜ አንብቤዋለሁ ማለት ያስፈለገበት አስገዳጅ ምክንያት ምንድን ነው? አውቃለሁ ብሎ በመነሣት ለማሞኘት ወይም ለማታለል ካልሆነ በቀር ሌላ ምክንያት ያለ አይመስለኝም፤ እንደአቶ ዳንኤል ያለውን ለማስጠንቀቅ ደጋግሜ አነበብሁት በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ‹‹የዩኒቨርሲቲን ዓለም የማያውቁ ሰዎች ሌላ ትርጉም በመስጠት እንዳይሳሳቱ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ በአካል በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሆነው ልባቸው ከደብተራ ተንኮል ላልጸዳም ቀናውን የእውነት መንገድ እንዲያመለክታቸው እመኛለሁ፤›› የሚል ተጽፎ ነበር፤ ይህንን አቶ ዳንኤል አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም፡፡

ሁለተኛ፤ ‹‹ለመሆኑ ታሪክ ይከሽፋል? የክሽፈት ታሪክ ሊኖር ይችላል እንጂ የከሸፈ ታሪክ ሊኖር ይችላል? የስኬት ታሪክ ይኖራል እንጂ የተሳካ ታሪክ ይኖራል? አንድን ታሪክ ከሽፏል ወይም ተሳክቷል የሚያሰኘው ምን ምን ሲሆን ነው? … በመጽሐፉ የምናጣው ታላቁ ነገር ይሄ ነው፤›› በዚህ ትርጉም የማይሰጥ የቃላት ድርደራ ላይ ምንም አስተያየት መስጠት አይጠበቅብኝም፤ ይቀጥልና ‹‹.. የታሪክን ክሽፈትና ስኬት መበየኛ ነገሮችን አስቀድመው በማሳየት አንድ ታሪክ ከሸፈ ወይም ተሳካ የሚያሰኙትን መመዘኛዎች …›› ይላል አቶ ዳንኤል፤ ካላነበበው ‹ደጋግሜ አንብቤዋለሁ› በማለት ብቻ ጭንቅላቱ ውስጥ አይታተምለትም፤ የሚከተለው እንደሚነበብ ሆኖ የተጻፈ ነበር፤ ‹‹መክሸፍ የምለው አንድ የተጀመረ ነገር ሳይጠናቀቅ ወይም ሳይሳካ እንቅፋት ገጥሞት መቀጠል ሳይችል ዓላማው ሲደናቀፍና በፊት ከነበረበት ምንም ያህል ወደፊት ሳይራመድ መቅረቱን ነው፤›› ይህ ተጽፎአል! አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም፡፡

ሦስተኛ፤ ‹‹ታሪክ ጸሐፊዎቹን ከታሪኩ ጋር አብሮ መውቀጥ ከተልባ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ ዓይነት ይሆናል››! ይላል፤ ይህ ሰው አንብቤአለሁ፤ አውቃለሁ፤ ሲል በመሃይም ድፍረት ነው፤ የሚከተለው ተጽፎአል፤ ‹‹አንድ ሰው በአገርና በሕዝብ ጉዳይ ላይ ከጻፈ ‹‹ማንም ዜጋ በጉዳዩ ላይ የመሳተፍና ሀሰቡን በሙሉ ነጻነት የመስጠት መብት አለው፤ አለዚያ በየጓዳችን በሐሜት ብቻ እየተዘላዘልን እውነትን አንጥሮ በአደባባይ የማውጣቱን ዘዴ ሳንማር ሌላ ሦስት ሺህ ዓመታት እንቀጥላለን፤›› ይህንን አላነበበውም፤ ካነበበውም አልገባውም፡፡

አራተኛ፤ በራሱ ላይ ሲፈርድ ቶሎ ሳይጽፍ መቆየቱን ለማስረዳት ምናልባት ከእሱ የተሻለ ሰው ቢጽፍ፣ ምናልባት ፕሮፌሰር ባሕሩ ቢጽፍ፣ ምናልባት የታሪክ ሊቃውንትቱ ተማሪዎች ቢጽፉ፣ ምናልባት የታሪክ ክፍሉ ቢጽፍ በማለት ጠብቆ እንደነበረ ይገልጻል፤ እነዚህ ሁሉ የሱን ምኞት እሱ በፈለገው ፍጥነት ሳያሙዋሉለት ቀሩና እነፕሮፌሰር ባሕሩን ላጨበት ሥራ ራሱን አቀረበ፤ የሱ ድፍረት የሌሎቹን እውቀት የሚበልጥ ለማስመሰል ጻፈ፤ ድፍረቱን ልናደንቅለት ይገባል፤ በማያውቁት ጉዳይ ደረትን ገልብጦ በሙሉ እምነት ማነብነብ የካድሬዎች ባሕርይ ሆኖ በቤተ እግዚአብሔርም ገብቶአል፡፡አምስተኛ፤ አቶ ዳንኤል ከአዋቂነት ወደመንፈሳዊነት ይሸጋገርና ‹‹አንድን አካል መልስ ለመስጠት በማይችልበት ጊዜና ሁኔታ መሄስና መውቀስ ከሞራል አንጻር ፍትሐዊ አይሆንም፤ የሀገሬ ሰው ‹ሙት ወቃሽ አትሁን››› እዚህ ደግሞ ጭራሽ ሊወጣበት ከማይችለው የአለማወቅ ማጥ ውስጥ በድፍረት ገባ! ‹‹ሞራል›› ስለሚለው ነገር ምንም እንደማያውቅ ሳያውቅ አወጀ፤ ድፍረት ብቻውን በምንም መንገድ እውቀት አይሆንም፤ ለመራቀቅ ፈልጎ ራሱን በአለማወቅ አዘቅት ውስጥ ከተተ፡፡

ስድስተኛ፤ በጽሑፉ መደምደሚያ ላይ የደብተራ ተንኮል አፈትልኮ ይወጣል፤ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ያነሣና በደብተራ ተንኮል አንዱን ‹‹ዶክተር›› የሚለውን መልክ የሌለውና ስም የሌለው የደብተራ ምሥጢር ያደርግና፤ ‹‹እኒህ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ዶክተር ወደመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ዘንድ በማን በኩል እንደሄዱ ፕሮፌሰር መስፍን ያውቃሉ፤›› ብሎ ይለጥፍብኛል፤ እግዚአብሔር ያሳያችሁ ስሙን ያልጠቀሰውንና የማላውቀውን ሰው የእኔን ስም ጠርቶ እንደማውቀው አድርጎ ሌላ ስሙን ያልጠቀሰውንና እኔ የማላውቀው ‹‹ዶክተር›› ወደመንግሥቱ ያቀረበ እያለ ውሸት ሲያጠነጥንና ሲፈትል ጊዜ ያጠፋበት ምክንያት አልገባኝም፤ ተንኮሉ እዚህ ላይ አያበቃም፤ ታደሰ ታምራትን ‹‹መንግሥቱ ከመሸኘቱ በፊት ግን ‹ከዶክተር እገሌ ጋር ቅሬታ አላችሁ መሰል፤ አንዳንድ ነገር ነግሮኝ ነበር፤ እዚያው ተነጋግራችሁ ፍቱት፤ አላቸው፤›› ይልና የመጨረሻዋን የደብተራ ተንኮል ጣል አድርጎ ይደመድማል፤ ‹‹አሁን እዚህ መጽሐፍ ላይ ቤተ መንግሥቱን አየሁት፡፡›› ምን እንዳየ፣ የት እንዳየ፣ ምንና ምን እንደተገናኘ የደብተራ ምስጢር ነው፤ ያቀረበውን ሁሉ የማን ባለሙዋል ሆኖ ያገኘው እንደሆነም አይናገርም፤ እንዲህ ያለ ሞላጫነት! ስለእውቀት ከተጻፈ መጽሐፍ ተነሥቶ ወደመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ጓዳ ገብቶ፣ ስሙ የማይጠራ ዶክተርን መነሻ አድርጎ፣ ይህን ሁሉ እኔ እንደማውቅ ተናግሮ በድንቁርና ምርጊት ይደፍነዋል! እንዲህ ያለ ሰው ስለእውቀት ለማውራት ለምን ይነሣል? ከበሽታ በቀር ምን ሌላ ይገፋፋዋል?

hailu said...

Judging by the content of the threat spat out by Eskindir, it sounds as if Reporter is quoting 'bete seytan' rather than what we know as 'bete kihnet'. What hurts the most is the damage such people inflict on our church, and the many folks who may abandon their mother church because of such figures as is Eskindir.

Those who ridicule and scoff at God's house will soon pay a price. Eskindir and his likes will have no excuses for such shameful political threats against children of Orthodox Tewahido Church.

You may assign your 6th cadre but you will not succeed threatening us to follow your flawed political appointment. We will denounce and fight against their illegal move disregarding our yearning for the unity of our Church.


For we now clearly know who our Patriarch is, we won’t be fooled by the cadre’s brouhaha.

Anonymous said...

አይ ቤተ ትክነት

Anonymous said...

ጳጳሶች በ፮ኛው ፓትርያርክ ምርጫ አንድ እንዳልሆኑ ከእነሱ መግለጫ ምእመን ተረድቷል፤ ታድያ እርስ በርሳቸው ሊተሳሰሩ ነው? ጉድ ነው ዘመኑ። ጎበዝ ቢሆኑና ለእምነታቸው ቢገዙ የመንግስትን ጫና ለመቋቋም ማድረግ የሚገባቸው ሁሉም ላልተወሰነ ጊዜ ገዳም መግባት ነበር። ታድያ ምን ያደርጓል ሁሉም ለቄሳሩ ሃብት ባለቤት ሆነዋል፤ ቪላቸው፣ መኪናቸውና የባንክ ብራቸው ይወረስባቸዋል። ገዳምና ብርቅ ድንቅ ቤተ ክርቲያናት እየነደዱ እነሱ ለሹመት ይናኮራሉ።

Anonymous said...

እውነት ቤተ ክህነት ከፓትርያርክ ምርጫ በፊት ዕርቀ ሰላም ይቅደም የሚሉትን ሰዎች በምድራዊ ፍርድ ቤት ለመክሰስ አሰበች?!! በሪፖርተር ጋዜጣ አማካይነት ዓለም እንዲያወቀው የተሰራጨውን ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያዋርድ ወሬ በእርግጥ ብፁዓን ጳጳሳቱ ሁሉ አውቀውት የወጣ ነው? ከሆነ የት ድረስ ይወረዳል?!! ጳጳሳቱ እንዴት የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር፣ የቄሣርን ለቄሣር መሆኑን ሳቱት? ወሬው የተሰራጫው ጳጳሳቱ ሁሉ አውቀውትና ተስማምተውበት ነው ብሎ ማመን ያዳግታል!! ከሆነ የጉድ ጉድ ነው። ስለዚህ ደጀ ሰላም ትክክሉን ከጳጳሳቱና ከአቃቤ መንበሩ አጣርታችሁ ትክክሉን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በአስቸኳይ የመግለጽ ታላቅ አደራ አለባችሁ። በተለይ በአሁኑ ሰዓት ቤተ ክርስቲያኒቱን ከአደጋና ከውርደት የመጠበቁ ኃላፊነት ወደ ምእመናን እያዘነበለ ሄዷልና።

Anonymous said...


I think it is good to focus on the substance not the form. The message is clear. Professor is a true man, I believe. So he starts and finishes in the stronger tone and terms possible which I believe describes his straightforwardness. Diplomacy may not be appropriate in this instance, but civility is always wise. I also believe a somehow softer tone could convey the same message in a civilized manner.
More important here will be the lesson for Daniel and others like him who with their arrogance tend to criticize everything without the requisite information or knowledge. That cannot be constructive. it doesn’t yield good fruit except to please those who are led by their emotion than facts.
Anyone has a right to comment on anything. That is human freedom. Feedbacks should be clear wether that is based on knowledge or emotion or attitude or arrogance. We should take care for our followers on the seeds we are sowing.
Daniel will have some good skills, but he cannot be everywhere. he can’t be in politics, in religion, in history, in research, in sport, in social studies, in anthropology, in economics, in finance in law. At least we can be good in few things. Daniel doesn’t like to learn , but he always pretends as though he knew everything-that is called hypocrisy. That is a big thing which leads to untimely failure. Daniel beware. Professor, take time to maintaining your civility. Professor, may I say you are role model for many Ethiopians, and your wording is below the standard and the expectation of many Ethiopians ( i feel so). The content is much more to be appreciated. I believe that there is a lot of truth in it.
http://mesfinwoldemariam.wordpress.com/2013/01/27/%e1%8b%a8%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%8a%a4%e1%88%8d-%e1%8a%ad%e1%89%a5%e1%88%a8%e1%89%b5-%e1%8a%ad%e1%88%bd%e1%8d%88%e1%89%b5/#comment-185

Anonymous said...

እስከ መቼ ድረስ አለማወቃችንን እየሸፋፈንንና እያደነቅን እንደምንኖር አልገባኝም። ዳኔል ክብረት በድፍረት በደንብ ያልተረዳውንና የማያውቀውን ነገር ጻፈ፤የነገሩ መነሻ የሆኑትና ነገሩን በደንብ የሚያውቁት ፕ/ር መስፍን ደግሞ አለማወቁን እንዲያውቅ ፊት ለፊት ነገሩት፤ ስለዚህ ዳኔል ከዚህ ትምህርት ይውሰድ….በዙሪያችን የተኮለኮሉት ሰዎች ስላጨበጨቡልን ብቻ ሁሉንም ማወቅ አይቻልም። ፕሮፌሰሩ የጻፉበት ነገር ደግሞ ሲሬየስ (serious)የሆነ የሀገር ጉዳይ ነው። እንዲያው ዝም ተብሎ “ማንበብና መጻፍ ስለተቻለ” ብቻ ማንም ዘው ብሎ የሚጽፍበት አይደለም። ምንአልባት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስበር ያገኘኋት ልጅ….ኬንያ ውስጥ ያየሁት በንደር ጣራው…..ከ ቦስተን ወደ ዲሲ ስበር ያጋጠመኝ ….ምናምን እያሉ እራስን በተመራማሪነት ማዕረግ ላይ አስቀምጦ የሚዘላብዱበት አይደለም። ስለዚህ እንደሰሞኑ የቢሄራዊ ቡድኑን ሽንፈት ከማወደስ አባዜ እንውጣና ሽንፈትንና አላዋቂነትን እንጋፈጥ። በርግጥ አገሩ የደፋር አገር ሆኗል፤ ሳያወቁ አዋቂ ነን ባይ፤ ሳይችሉ እንችላለን የሚሉ ብዙ ደንቆሮዎች ሞልተዋል፤ እንዲህ አይነቶቹን ሰወች አትችሉም ፤አታውቁም ልንላቸው ይገባል። የፕሮፌሰሩ ጽሁፍ ጥሩ ማሳያ ነው፤ “እንትንን እንትን” ማለት ያስፈልጋል። ስለዚህ ሽንፈታችንና አላዋቂነታችንን ፊለፊት እንጋፈጣቸው። እድሜና ጤና ለፕ/ር

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)