January 22, 2013

አዳነ ግርማ - የቅ/ገብርኤል ወዳጅ - ግሩም ጎል


(ደጀ ሰላም፤ ጥር 14/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 22/2013/ PDF)፦ ኢትዮጵያ በአንድ እግሯ ቆማ ባመሸችበት በትናንትናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታ ግሩም ድንቅ ጨዋታ፣ ግሩም ድንቅ እግር ኳስ አየን። በዚህ ታሪካዊ ጨዋታ ላይ የማታ ማታ አቻ የምታደርገውን ጎል ያስቆጠረው የቅ/ገብርኤል ወዳጅ አዳነ ግርማ ነበር። እገሌ ሃይማኖቱ ኦርቶዶክስ ነው፤ እገሌ ሌላ ነው የሚል ከፋፋይ ሐሳብ ለማቅረብ ሳይሆን አዳነ የሚለብሰውን 19 ቁጥር ስንመለከት ቅ/ገብአርኤልን እንደሚወድ፣ የሐዋሳ ልጅ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የልጁንም ስም “ገብርኤል” ብሎ መጥራቱን ለማስታወስ ወድደን ነው።


ኢትዮጵያውያን በሰው አገር እንደዚያ ተሰብስበው፣ ባንዲራችንን ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ አይቶ ዕንባና ሳግ የማይመጣበት ኢትዮጵያዊ አይኖርም። እኛ የምንመለከተው እግር ኳስ ብቻ አይደለም። የአገር ክብር ትንሣኤ ሲያገኝ ነው። ብዙዎች ኢትዮጵያውን አትሌቶቻቸውም ሆኑ እግር ኳስ ተጫዋጮቻቸው ሲጫወቱ በልቡናቸው የሚመጣባቸው 22 ሰዎች የሚያንከባልሉት አንድ “ቅሪላ” (ኳስ ለማለት) ሳይሆን አገር፣ ክብር፣ ታሪክ፣ ማንነት፣ ኢትዮጵያዊነት ነው። የኢትዮጵያ ትንሣኤ!!!!!!!

እንኳን ደስ ያላችሁ!! ቸር ወሬ ያሰማን አሜን4 comments:

Anonymous said...

Thank you Deje Selam, be globalization zemen endih aqtacha bizu gin weqtawi hunetan ayayzo maqrebachihu yemiyasmesegnachihu new.Haymanotawi nek media should report any issue which has direct and indirect relation or influence on that particular religion followers.The first commentator (Selamachihu yibza) need to consider that if such issue was found in other abroad media, it will be head of the news.
Thank you Deje Selamoch
from Europe

Anonymous said...

Betam desyelale Ye-Ethiopa Amelak yetemesegene yehun ke-31 Amet behula lezihe laderesen Ye-Ethiopian tensaiwan endihu kerb yargelen ye-kedus Gebriel tradaient ayleyen.

Birile said...

Praise be to The Lord Almighty!
Let the help of The Almighty God be with them. Let them come victorious and safe! Amen!
They have performed great.For me, they are champoion already. We have to remember them in our prayer.
His love to The Archangel Saint Gebreal, would be appreciated by all Christian and Muslims, for Saint Gebreal is loved by all Christian and Muslims. Absariw Kidus Melak Melkamun Yabsiren! Amen!
Congratulations!!!

Anonymous said...

ሁላችኹም ያሰፈራችሁት ጽሑፍ በጣም የሚያስመሰግናችሁ ነው። ከአፍ የሚወጣ መጥፎ ቃል ራስን ያስገምታልና። ለሳላዲንም ገብርኤል አለለት እኮ። እንደእምነቱ ነው። ቁልቢ ገብርኤል የሄደ ሰው ይኸንን በቀላሉ ማወቅ ይችላል። እዚያ የተሳለ ሁሉ ይሄዳል። አገራችን ኢትዮጵያንና ኃይማኖታችንም እንዳትደፈር ተከባብረን መጠበቅና አብሮ የመኖር ጠባያችን እንዳይቀየር እግዚአብሔር ይጠብቅልን/ይጠብቀን። ኳስ ተጫወቶቻንም እግዚአብሔር ብርታቱን ሰጥቷቸው አሸናፊዎች ለመሆን ያብቃቸው። እንኳን ለበዓለ ጥምቀቱ ሁላችችሁም በየአላችሁበት አደረሳችኹ። ደጀሰላምም፡ ሚዛናዊ የሆነ አቀራረብ እንደሚጠበቅባችሁም ግልጽ እንደሆነ ሳትረዱትም አልቀራችኹም። እንደ ኳሱ፤ ካቀረባችሁልን አንዳንድ መልእክቶችም ውጤት ሳንሰማ የቀረንበትም ጊዜ አለ። ከተከታተላችሁ እነዚያ ያላለቁና በውጥን ተይዘው ያሉ ሁኔታዎች ማሰሪያ አንቀጹን ያላወቅን አለን። መልስ ፈልጉልን።
ብርሃን
ከዳላስ፤ ቴክሳስ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)