January 20, 2013

“አንድ ጥምቀት፣ አንድ ሃይማኖት” የሚል ጥቅስ የያዙ ወጣቶች ታሠሩ


(ደጀ ሰላም፤ ጥር 12/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 20/2013/ PDF)፦ ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ ያለውን “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ጥምቀት” የሚል ጥቅስ ያለበት ቆብ ለሰንበት ት/ቤታቸው ገቢ ማስገኛነት በመሸጥ ላይ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ መታሠራቸው ታወቀ።


ጥር 11/2005 ዓ.ም ታቦተ ሕጉን ተከትለው በሞቀና በደመቀ ሃይማኖታዊ መንፈስ በማክበር ላይ እያሉ በፖሊስ የታሠሩት ስድስት ወጣቶች ሲሆኑ ጥቅሱ የተጻፈበትን ቆብ ይሸጡ የነበሩት ደግሞ ለብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ገቢ ለማስገኘት በሚል እንደሆነ ተገልጿል። መንግሥት የሃይማኖት አክራሪነትን እዋጋለኹ በሚለው ዕውቀት የጎደለው ተግባር ‘አንድ ሃይማኖት’ የሚል ቃል የሚናገሩ ክርስቲያኖችን በሙሉ በማሳደድ ላይ ይገኛል። የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይለ ቃል እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረተ እምነት የሆነውን ቃለ እግዚአብሔርን መናገር፣ ማስተማርም ሆነ በጽሑፍ መያዝ ሌሎች እምነቶችን እንደመዋጋት ተደርጎ እንዲቆጠር በመናገር በፖሊስ ጥብቅ ማዋከብና እንግልት የሚፈጽመው መንግሥት እነዚህን ስድስት ልጆች የያዘው በዚሁ ምክንያት መሆኑን በወቅቱ በቦታው የነበሩ እማኞች ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩ ቀደምት መንግሥታት ሁሉ በባሰና በከፋ መንገድ በቤተ ክርስቲያኒቱ የውስጥ ጉዳይ ረዥም እጁን አስገብቶ የሚያምሰው የፖለቲካው መዘውር በቅርቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤያት ላይ ሳይቀር ባለ ሥልጣኖቹን በመላክ የሲኖዶሱ ተሰብሳቢ ለመሆን በመሞከር ላይ መሆኑን ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል።

መንግሥት በአገሪቱ ቀደምት እምነቶች ላይ ያለውን አቋም ለካድሬዎቹ በተከታታይ ሥልጠኛ በመስጠት የሚያስጠናበት ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል። ለዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ድረስ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና በሌሎች ኃላፊዎች ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና እስልምና ላይ ያነጣጠረ ሲሆን በባለሥልጣናት ቁጥር ሰፊ ተሰሚነት ያገኙትን ፖሮቴስታንቶችን ግን ምንም አይነካም። መንግሥት በነባር አገራዊ ቤተ እምነቶች ላይ እያስፋፋ የመጣው ጣልቃ ገብነት ድንበሩን አልፎ የእስልምና መሪዎችን በማሰር፣ የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶስ በመዘወር መገለጡ ይታወቃል።

መንግሥት ለባለሥልጣኖቹ የሚሰጠውን ሥልጠና ለማወቅ ለምትፈልጉ ወደፊት እንዳስፈላጊነቱ ሙሉ ዶኩመንቱን ለማቅረብ እንሞክራለን።

ቸር ወሬ ያሰማን አሜን

12 comments:

Hailu said...

This is what is expected of a government led by athiests and menafkans. They have waged war against our Orthodox faith and Church like it has done to followers of Islam. It seems that the protestants are their favorite as these groups usually don't care about history, country and flag.

Anonymous said...

እኔ እንደሚታየኝ አሁን ነቃ ማለት የሚገባን ጊዜ ነው ኢህአዴግ ለምን ድን ነው እስልምናንና እና ኦርቶዶክስን ማጥቃት የፈለገው ይህ ግልፅ ነው ሁለቱ አብዛኛውን ህዝብ የሚወክሉ በመሆኑ እነዚህን አካላት በማጣላት ረዥም እድሜ እጓዛለው የሚል አመለካከት ስላለው ነው፡፡ በዚህም ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ሳያውቁ መጠቀሚያ እንዲሆኑ እየተደረጉ ነው፡፡ እስቲ ሙስሊሞች ክርስትና ማጥቃት ከፈለጉ ለምን ኦርቶዶክስን ብቻ ያጠቃሉ ወይም ፕሮቴስታንቶች ለምን መልስ አይሰጡም ምክንያቱም ይህንን ዓይነት የሰውን ሃይማኖት የማንቋሸሽና መዳፈር ቤት ለቤት በመሄድ የጀመሩት ፕሮቴስታንቶች ናቸው ግን ፍላጎታቸው ሁለቱን ሃይማኖት አናቁሮ የራሳቸውን መንገድ ማሳመር ስለነበር ድምጣቸውን አጥፍተው ውስጥ ውስጡን ሲሰሩ ይህው ቁጥራቸውን ወደ 20 ፐርሰንት አሳድገዋል፡፡ አሁንም እንደ ምህረተአብ የመሳሰሉ ሰዎች በዚህ ወሳኝ ወቅት ስለቤተክርስቲያን አንድነትና የጋራ ሃገራዊ ትግል እንደማስተባበር አሁንም የህዝብ አስተሳሰብ ለመቀየር የሚያደርጉትን አካሄድ በረጋ ሁኔታ ማሰብ ያስፈልጋል እላለሁ፡፡

Tigestu Bezalen said...

የእግዚአብሔር መከር ሲደርስ።
===================
ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥ ማቴ. 20:26
ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ። አንዱ ምንም ሳይሆን ምንም የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና። ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፤
እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና። ነገር ግን ቃሉን የሚማር ከሚያስተምረው ጋር መልካምን ነገር ሁሉ ይከፋፈል።

አትሳሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት።
እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ።
ገላትያ ሰዎች 6: 2-10

እስኪ እባኵት ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጫኑና ቪዲዮውን በንጹህ ህሌና ሆነው እየተመለከቱ የእግዚአብሔርን ስራ ይመርምሩ።

http://ecadforum.com/ethiopianvideo/2013/01/18/on-ethiopian-orthodox-church-current-situation/

Anonymous said...

እመቤታችንን፣ ተክልዬን፣ አቡነዓረጋዊንና ሌሎች ቅዱሳንን እያላገጠና እያጣጣለ የሚሰብከውን ፓስተር ዳዊትን በኢቲቪ ስለሃይማኖት መከባበር ሊሰብከን ያመጡት ቀን እኮ ግልጽ ሆነ መናፍቃን ምንም እንደማይባሉ። የመለስ ዋና አማካሪስ መናፍቅም አልነበር። 500 የመናፍቃን ቸርች ቤኒሻንጉል ያሰራው ቡድን ዉስጥ እነ ያረጋል አይሸሹምና ሌሎች መናፍቅ ነበሩበት። አሁንም ፈደራል ጉዳዮች ፕሮቴስታንቶች በመንግስት ፖሊሲ አመሃኝተው ያሻቸውን የሚፈጽሙበት ቦታ ነው። ኢሃድግ ድማ ሁለቱን ነባር እምነቶች ማባላትን ሌላው የስልጣን ዘመኑን ማቆያ እንዳሰበው ከድርጊቶቹ ማየት ይቻላል።

Anonymous said...

ወንድሞቸ ዝምታዉ እስከ መቸ ነዉ??????

andnet berhane said...

የተከበራችሁ ውድ እደጀሰላም ድሕረ ገጽ አዘጋጆች እንድምን ከርማችኋል አምላካችን ብርታቱንና ኃይሉን ያድላችሁ ሰላምና መረጋጋት ፍቅርና ተውሃዶ የቤተክርስቲያናችን ይጠብቃት በማለት ያለኝን ታላቅ ክብርና ሃይማኖታዊ ፍቅሬን ስገልጥ ፡ ነገርግን ከዚህ በማያያዝ ሁላችንም ቤርገጠኝነት ተውሃዶ እምነታችን ስትነካና ማእገሯ ሲነቃነቅ አባቶችም የተሰጣቸውን ክርስቶሳዊ ስልጣን ለገቡበት ቃልኪዳን ለመቆምና ጴጥሮሳዊ ተግባር ለማሳየት አለማጫላቸው ታላቅ ሀዘንና ቁጭት በመላው ምእመን እንዳለ በማስገንዘብ እኛ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ስለሀይማኖታችን እስከመሰየፍ መድረስ ሲገባን በችለተኝነት እምነታችንን በማስመሰልና በፍርሃት ተውተን በቤተክርስቲያናችን ሲጫሙባት ማየት ምን ያሕል ያስወቅሰን? አሁንም ወደድን ጠላን እምነታችንንና የእምነት መሪዮቻችን ያለባቸውን ኃላፊነት የተሰጣቸውን ስልጣነ ክሕነት ለመወጣት ባለመቻል በስጋዊና በምድራዊ መንግስት ተማምነው የክርስቶስን ስልጣነ ክህነት አስወግደው ለምድራዊ ተድላና ደስታ ተሸንፈው ቤተክርስቲያንን ሲያምሷት እኛንም ከእምነታችን እንድንዘናጋ በማድረጋቸው ፡ ይህን ከንቱ ዓለም ሊኖሩባት የሚችሉ ለጥቂት መሆኑን በመርሳት ለስልጣን ሽሚያ የሚያደርጉት ጉዞ የሃይማኖት መንገድ ባለመሆኑ መለስ ብለው አማኞንና የተሰጣቸውን ክህነታዊ ስልጣን በመመልከት እኛንም ቤተ ክርስቲያናችንን ለማዳን ተግተው ይጸልዩ እኛም አብረን እንጸልያለን ሱባኤም እንገባለን፡ ነገርግን የይዙትን መንገድ ካልቀየሩ በገዥዎች ተመርተውና ለስጋቸው ተሸንፈው ለጥፋት ከሄዱ አማኙ እምነቱን ለመጠበቅ የሚወስደው እርምጃ እንድጥንቱ በሕበረት ኦርቶዶክስን ለማዳን ሲል ለተወሰነ ወራት በማህበር ሆነው ያለ አባቶች ከቤተክርስትያን ርቆ በጸሎት በሱባኤ ማውገዝ እንድለበት ማሳሰብ እወዳለሁ፡ ያለምእመናን እምነት ቤት የለም ግንቡን ሳይሆን አማኞች መሰብሰቢያና ያምላካቸው መገናኛ የሰላምና የውሕደት ስፍራ ነችና ፡ አምላካችን በምሕረቱ እምነታችንና ሃይማኖታችንን ይጠብቃት፡ ኦርቶዶክስ ተውሃዶ እምነት ለማጠናከር ሁሉም አማኞች በሕብረት እንነሳ የተላያዩ ደብሮች ስም ሳይሆን ውይም አጥቢያ በኦርቶዶክስነታችን እንቁም ፡

Anonymous said...

"ዕውቀት የጎደለው ተግባር", well said Dejeselam, what this government doing is really idiot and we all need to stand on the side of our church.

Gofa Geberal said...

My God, in Ethiopia we reached in this kind of mess. Those police aren't they Christine and Orthodx what is going on. What kind of " Mehaymente is this?" so are we going to change the word of the bible, to satisfy wenyene poltices. Let God give his judgment.

Anonymous said...

+++
አምላከ ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ የከበረ የተመሰገነ ይሁን። ጴጥሮሶችዬ እኔም ያደኩበት ደብር ነው ሰንበት ት/ቤትም እንደዚሁ ግን ለጥቂት በረከት ወጥታችሁ የበለጠ ስለተሰጣችሁ ደስይበላችሁ።
ምነው እናንተን ባደረገን ኖሮ።
መልካም በዓል!
የጴጥሮስ ልጆች ካለንበት !

Anonymous said...

I think this government being foolished himself, they batter watch out what they are doing. this is religion not a politics. I assure them what they are doing is suicide... people will silent in many ways but not in religion...when it comes to heavenly life of Ethiopia their no excuse for us to be silent.. those of you Ethiopian government official don't idiots.. if you continue lead this country make some change on you ideology which most people aware of it... what you have planed before you got in to power lasted u 21 years it is time for you to update in good manner. otherwise don't bring the load to ur innocent people to pay a pric. because in the way we are seeing things just getting worst in many ways. as you may think everythings are in good shape but what you didn't realize is in expected things could happen any moment and time. I hope you don't want any ethics to suffer as result of your failed leadership...

Anonymous said...

Meles Zenawi was one of the pagans leaders on the surface of the earth. thanks God!!! God took him with his father before my country's situation get worst. God has his won purpose. the current archibishops who are working closely with woyane leaders will pay their price soon or later. woyane didn't violate the constitution, the archbishops are violated the constiution because they have invited woyane to work with them, they could have said stop and respect our religious right. instead, they have given him green light to work with them. they think they will stay forever. sorry for Abune Abrham who has two tongues. history will judge him.

Anonymous said...

this is what meles said about last year temket for the damn parliament 'have u guys notice some terrorist hang one religion one country?' he even had blam our lovely maheber ,mahebere kedusan. That's why this damn his employs doing sheet

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)