February 2, 2013

“አንድ ክርስቶስ!” “አንድ ሲኖዶስ!” “አንድ መንጋ!


(ወልደ  አረጋዊ፤ በተለይ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት/ PDF)፦ ሕት ጣፋጭም መራራም ዋዋን ደጋግማ ትግታለች፡፡ ዛሬ ረቡዕ ሰው፣ ብሎም ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ በመሆኔ ብቻ እጅግ መራራውን የሕይወት መርዶ ተጎንጭቻለሁ፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያኔና በምዕመኑ ላይ በግፍና በማን አለብኝነት ስለተዘጋብን “የሰላም በር” መርዶ ሬት ሬት እያለኝ ሰምቸዋለሁ፡፡


አባቶቻችን ፈረዱብን! እንዲያ ከአናፍ እስከ አናፍ ያስተጋባውን የመንጋው የተማኅጽኖ ጥሪ አልገደዳቸውም ነበር እና “ቅድሚያ ለምርጫ” ማለትን ወደዱ፡፡ እጅግ መራራ ነው፡፡ ይህን መስማትም ሆነ ማሰብ እጅግ ይመራል፡፡ በመለያየት ውስጥም መኖር ከሁሉም በላይ አብዝቶ ይመራል፡፡ አባቶቻችን ግን በእኛ በክርስቶስ የአደራ ልጆቻቸው በምንሆን ላይ እጅግ አብዝቶ በሚመረው “የመለያየት ክርስትና” ውስጥ እንድንኖር ዛሬ በድጋሚ ፈረዱብን፡፡ አባቶቻችን አንድ እንዳንሆን በድጋሚ ፈረዱብን!

ዘማሪው እንዳለው “ሰች ፈረዱብኝ አንተ ግን አዳንከኝ” ነውና ታሪካችን ከዛሬ ፳ ዓመታት በፊት የተገነባው የመለያየት ግድግዳ ዛሬም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሰዎች ቢፈርዱብንም እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አባትና የእኛ የልጆቹ መቅበዝበዝና ለክፉው ተላልፈን መሰጠታችን በእውነት የሚገደው እረኛችን ነውና በእውነት ዝም አይልም፡፡ መንጋውን ከመቅበዝበዝ ያድናል ይሰበስበናልም፡፡ ጽሐፍ እንዳለው እርሱ እውነተኛ የበጎች ጠባቂ ነው!

“ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም!” ይላል ያገሬ ሰው፡፡ እነሆ እኛም ኢትዮጵያዊ ክርስቲያኖች ነን እና መቼም ቢሆን በክርስቶስ ተስፋ አንቆርጥም፡፡ እንግዲህ ለአለስት መታት በተለየም ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ  እረፍት በላ በመላው ዓለም የምንገኝ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች “ቅድሚያ ለርቅ” በሚል ዐቢላማ ር ተሰባስበን አባቶቻችን ስንማፀንና ስናግባባ ከርመናል፡፡ ይህ መንገድ ዛሬ ረቡዕ ጥር ፰ ፳፼፭ በይ እንደተዘጋና “ቅድሚያ ለምርጫ” የሚለው ሳብ እንዳሸነፈ መርዶው ደርሶናል፡፡ ስለዚህ በአባቶቻችን የተዘጋውን የአንድነት በር ተስፋ በመቁረጥ እንቀበል ወይስ እኛም እንደቀደሙት ክርስቲያኖች “ክርስቲያን ተስ አይቆርጥም!” እንበል?

እኔ “ክርስቲያን ተስ አይቆርጥም!” ከሚሉት ወገን ነኝ ምክንያቱም በክርስቶስ የማይቻል ነገር እንደሌለ በተረዳ ነገር አውቄለሁና፡፡ ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች መቼም ቢሆን ስለ ሰላም፣ ስለ ፍቅርና፣ ስለ አንድነታችን ተስፋ አንቆርጥምና ምን እናድርግ? ወደሚለው መረታዊና አግባብነት ያለው ጥያቄ መሻገር ያለብን ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ በእኔ በኩል ለመነሻ ይሆን ዘንድ የሚከተሉትን ሳቦች እነሆ

፩ኛ.  የሰላምና የአንድነት ግብረ-ይል!
የአባቶቻች መለያየት በተለይም “ውግዘቱ” እግ ሸክሙ የከበደውና ለያይቶን የሚገኘው በስደት ላይ ምንገኝው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ላይ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ምክንያቱም የተወጋገዙቱ በጋራ የሚገኙት ሀገር ቤት ሳይሆን እዚህ በውጭው ዓለም ነውና፡፡ ስለዚህ የችግሩ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሾች የሆን እኛ በምንኖርባቸው ከተሞች /ስቴቶች/ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየቤተ ክርስቲያኑ አንዳንድ ምዕመን በመወከል የጋራ የሰላም ኮሚቴ በማቋቋም ምዕመኑ በአንድነት ግዚአብሔርን የሚያመልክበት፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጠብቅበት፣ወደፊትም ሊሰሩ ስለሚገባቸው በይት ተግባራት የሚመክርበትና ከሁሉም በላይ አንድነቱንና ብረቱን የሚያፀናበት መድረክ መፍጠር አለበት።

፪ኛ. “አንድ ክርስቶስ!”“አንድ ሲኖዶስ!”“አንድ መንጋ!”
በዚህ የሰላም ኮሚቴ አማካኝነት እዚህ በስደት ያለው ምዕመን የአንድነትና የሰላም መንፈስ ወደ ገር ቤት የሚደርስበትንና እዛም ያለው ምዕመን ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና ለአንድነቱ ተግቶ የሚታገልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል፡፡ ምክንያቱም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየሰማን ያለነው የሌላውን 45 ሚሊዮን ምእመን መፈክሮች ነው፡፡ ይህ ደግሞ በስደት የምንገኘውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች እንደ ውጭው ሲኖዶስ አባቶች ከገር ቤቱ ክርስትና ለመለየት የተጠነሰሰልን የእብደት መንገድ ነው፡፡  ስለዚህ ጥሪያችንም ሆነ መዝሙራችን አንድ ነው፡፡ይውም “አንድ ክርስቶስ!” “አንድ ሲኖዶስ!”“አንድ መንጋ!”

እናንተም አክሉበት!!!

ቸር ወሬ ያሰማን ብያለኹ!!! አሜን

27 comments:

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይፈርዳል! ለሁሉም እንደ ስራው እና የልቦናው ሃሳብ ይከፍለዋል መንሹ በእጁ ነውና:: አሁንም ወደፊትም "አንድ ክርስቶስ!" "አንድ ሲኖዶስ!" "አንድ መንጋ!"

Anonymous said...

ግን አሁን ጥፋተኛው ማነው? የሀገር ውስጥ ወይስ የዉጪው?? እኔ እስከሚገባኝ ከወያኔ እኩል አሜሪካ ያሉት ትልቁን የጥፋተኝነት ደረጃ ይወስዳሉ፡፡ ለህዝቡ የማይጨነቁ ለስልጣን ግን የሚንገበገቡ ናቸው፡፡ ግን ሁላቸውም የእጃቸውን ማገኘታቸው ያተኛሉ የህዝቡም እንባ የትም ፈሶ አይቀርም፡፡ ሰው እኮ ስለሰላም ሰለፍቅር ብሎ ብዙ ነረር ያደርጋል፡፡ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እኮ ማየት አለባቸው፡፡ ሁል ግዜም የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ እንዴት አንድ እረኛ አባት ለህዝቡ የሚያስብ ከሆነ ገና ያኔ ወያኔ ሲያባራቸው ለምን እንቢ ተገፍቼ ነው የወረድኩት አላሉም? ከብዙ አመት በኋላ ተገፍቼ ነው የወረድኩት ማለትስ አግባብ ነው??

Anonymous said...

Hmmmm .. a person who gave commen anonymous like me is completely wrong. Pls try to understand before you give your final sayings.

Anonymous said...

This is very wrong comments

Solomon said...

በበኩሌ በአቡነ መርቆሪዎስ ላይ አንዳንድ የሀይማኖት ነቀፋ ያለባቸውን ሰዎች ሁሉ መደበቂያ እንዲያገኙ በማድረጋቸው ቤተክርስቲያኗን ጎድተዋል የሚል ቅሬታ ቢኖረኝም በርሳቸው በኩል ግን በዚህ ባሳለፍነው ረጅም ጊዜ አስችሏቸው ዝምታን መምረጣቸው ከሚያስደምማቸው አንዱ ነኝ። በዛሬ ጊዜ በየጥቅሙና በየዘሩ ተከፋፍሎ 'እኔ ልሰማ' የሚለው ጳጳስ በበዛበት ጊዜ አቡነ መርቆሪዎስ ሁሉን አስችሏቸው ዝምታን መምረጣቸው የእግዚአብሔር ጸጋ ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? እርሳቸው በዚህ አይነት ትእግስት፣ አርምሞና ዝምታ ለዓመታት ተቀምጠው እያለ የ"አዲስ አበባው ሲኖዶስ" መግለጫ ዛሬ የርሳቸውን ስም በማብጠልጠል የጻፈውን ስመለከት እርሳቸውን ይበልጥ እንዳከብራቸው አድርጎኛል። ሐዋርያ መሆን ማለት ከዚህ የተለየ አይመስለኝም። ይህ በዚህ እንዳለ መንግሥትና በቤተክርስቲያን ውስጥ የተሰገሰጉ የመንግስት ካድሬዎች በየመድረኩ እየተመሳሰሉ እየገቡ አቡነ መርቆሪዎስን እንዲናገሩ መገፋፋታቸው ያስገርመኛል። የሰይጣን የተንኮል ወጥመድ አድርጌም እወስደዋለሁ። ሁሉን ነገር የሚያመጣው ከዚያም የሚመልሰው ያው መንግሥትና ካድሬዎቹ በሆኑበት ሁኔታ እርሳቸው ምን እንዲሉ ነው የሚፈለገው? አንድ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደርሳቸው ፓትሪያርክ ለመሆን የበቃ ሰውስ በራሱ ፈቃድ 'እግዚአብሔርም ሕዝብም ቢፈልገኝ የፓትሪያርክነቱን ወንበር አልወስድም' የማለት መብትስ አለው ወይ? አልፈልግም ቢሉም አሁን እየሆነ ካለው ሁኔታ ጋራ የሚቀበላቸውም የለም። 'መንግሥት ጠንቸኛ ሆኖብን የእግዚአብሔርን ሳይሆን የስጋን ሥራ እንድንሠራ ስላደረገን እርስዎ ያን ተቀብለው ስልጣኑን አልፈልገውም ይበሉ' ማለትስ ተገቢ ነው? ይህን ቢቀበሉ እርሳቸውንስ የኀጢያቱ ተባባሪ አያደርጋቸውም? ይህ የክርስቲያን ጥያቄ ሳይሆን ክርስትና ዞሮበት የማያውቅ ሰው ጥያቄ መሆኑ በዚህ ይታወቃል። የርሳቸውን ጸሎትና ዝምታ፣ የምእመናንን ለቅሶና ዋይታ፣ የገዳማውያንን ስደትና መንከራተት አይቶ ጆሮን ጭው በሚያሰኘው በራሱ መንገድ እግዚአብሔር መልስ እንደሚሰጠን ቅንጣት መጠራጠር አያስፈልግም።

Anonymous said...

የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ እንደተፈራውም ዕርቀ ሰላሙን አሽቀንጥሮ ወርውሮ ።እግዚአብሔር ይፈርዳል! ለሁሉም እንደ ስራው እና የልቦናው ሃሳብ ይከፍለዋል መንሹ በእጁ ነውና:: አሁንም ወደፊትም "አንድ ክርስቶስ!" "አንድ ሲኖዶስ!" "አንድ መንጋ!"

Anonymous said...

ahehehehe!! 1 kirstos eshi 1 synodos meche honena 2 adrgew sichawetu eyayenew fukerawn entewna 1 enadergew not for us for the coming generation Geta yirdan!!

Anonymous said...

መዝ 50፡3-5 ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል። አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፤ እሳት በፊት ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ።

Anonymous said...

በእውነት አእምሮአችንን ካላጣን በቀር በውጭ ሀገር ባሉ አባቶች ለመፍረግ አንችልም፤ ባላንስ ላማድረግ በሚል እኩል መፍረድ የለብንም። ሥልጣኑንም ቢሆን እኮ እኔ እደሰማሁት ከሆነ ከወያኔ ጋር የሚሰራ ጳጳስ እንደ ራሴ ይሁንና በሙሉ ኃላፊነት ይስራ፤ ነገርግን አራተኛው ፓትርያሪክ ወደመንበራቸው ተመልሰው በጸሎትና በቡራኬ የሚካሂደውን መንፈሳዊ ሥራ ብቻ እያስፈጸሙ ይኑሩ፤ ይህም ለህገ ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ ይጠቅማል በሚል በሰላም ጉባኤው አጋባቢነት ተቀብለው ነበር አሉ። እንደ እውነቱ አሁን ሁላችንም በውጭ ካሉት አባቶች ላይ ያለንን ጥላቻ አስወግደን እንዲያሰባስቡንና ስለቤተ ክርስቲያን አንድነት አብረን እንድንሰራ እንዲያደርጉ ልንጠይቅ ያገባል፤ ሲሆን እንሱ ይህን ጥሪ ባቀረቡልን። በአዲስ አበባ በተጨባጭ የሰማሁት ደግሞ ንቡረ እድ ኤልያስና አባ ሳሙኤል በቀጥታ ለፓሊስ እየደወሉ ሰው እስካማሰሳር ሙሉ መብት አግኝተው የሲኖዶሱ ክብር አዋርደውታል። ለመንጋው ጩኸት ቅዱስ ሲኖዶስ መልስ ለመስጠት ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ስለዚህ በውጭ ሀገር ያሉ አባቶች ልበሰፊ ሁነው ሁሉንም ቢያሰባስቡን፤ ለቤተ ክርስቲያን ነጻነት አብረናቸው ብንሰራ፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዲጠበቅ የሊቃውንት ጉባኤ ቢቋቋም መልካም ነው ብየ አስባለሁ። ምክንያቱም ወደድንም ጠላንም በውጭ ሀገር ያለቸው ቤተ ክርስቲያን እየሰፈች ነው የምትሔደው።
ዘ አባ ኢየሱስ ሞዓ
ከደሴ

Anonymous said...

እረኛ ያጣ መንጋ
በእዉነት ለእዉነት ኖሮ ቃሉን በግብር የገለጠ
ነብሱን ከሥጋዉ አብልጦ ራሱን ለአምላክ የሰጠ
መንጋዉን ከዱር በትኖ እልፊኝ ገብቶ ያለመሸገ
ሙሽራዪቱን ሊጠብቅ ህቱም ቃልኪዳን ያረገ
ለእምነት ለጽድቅ የቆመ የመስቀሉን ጉጥ የማይሸሽ
የመለኮትን ማደሪያ መቅደሱን የማያቆሽሽ
የክርስቶስ ርስት አቃቢ የእምነት አርበኛ ጠፋ
ምንደኞች ቤቱን ወረሩት ጊዜዉ ከክፋት ከፋ።
ርስቷን እያስነጠቁ ጥሪታቸዉን ያበዙ
ላዕካነ መኳንንት አበዉ ሊቃዉንት በዙ።
የዓለምን ጓዝ አራግፈዉ ወደ ቅድስቷ የገቡ
አስኬማ አንገላፕዮን ሹመት ክብሯን የደረቡ
የሰማዩን አክሊል ናቁ ኪዳናቸዉን ዘነጉ
ሹመኞችን እጅ ነሱ ለምድራዊ ክብር ተጉ።
ዕቀቦሙን እየወረብን ይባርኩን ይፍቱን ያልናቸዉ
ከጫማቸዉ ትቢያ ልሰን ቡራኬ የለመንናቸዉ
ብርቱ ቀንበር ሊጭኑብን ከወደቀበት አነሱ
የጳዉሎስ የኬፋ ሊሉን መሃላቸዉን አደሱ።
የህግ የሥርዓት መምህራን በቅኖናዋ ቆመሩ
በመናፍቃን ታዘዙ ከአረማዊያን መከሩ።
ለሰማያት ክብር ታጭተዉ እረኝነት የተሾሙ
እንደ አሕዛብ ሆኑብን የተስፋ ቃል እንዳልሰሙ።
ጴጥሮስ!!!!
የሊቀ ጳጳስ መለኪያ የእምነት የአገር አርበኛ
በጸሎት በምልጃህ አጽናን እረኛ አጥተናል እኛ።
ጉልበትህ ብርክ ሳይይዘዉ ከፋሽስቶች ሸንጎ ቆሞ
ያንተ አንደበት ዝም ሳይል በሞት ጦማር ተለጉሞ
አቻዎችህ አንገት ደፉ በሰላም ቀን እጅ ሰጡ
ለመኳንንት ተንበርክከዉ ይናገሩበት አፍ አጡ።
በአዉደ ምህረት የጀገኑ መጽሐፍ ገልጠዉ ያስተማሩ
ሰማዕትነትን ሸሹ የሥጋን ገዳዮች ፈሩ።
እመ ብርሃን እናታችን ትንፋሿን እፍ ያለችብህ
ሞትን ንቀህ እንድትፀና ኃይል ብርታት የሰጠችህ
ጴጥሮስ!!! በጸሎትህ እርዳን
‘ምነዉ እመ ብርሃን?’ በልልን
ምነዉ ቀኝሽን ረሳሻት
የስምሽን መታሰቢያ የአስራት ቤትሽን ተዉሻት?

W/Medhin

Anonymous said...

ይህን ጸሐፊው ያቀረቡትን ገንቢ የሆነ መሠረተ ሀሳብ እኛ ወደ ሃምሳ ሚሊዮን የምንጠጋ በኢትዮጵያና በውጭው ዓለም የምንኖር የቤተ ክርስቲያኗ ካህናትና ምእመናን ስለ ፍቅር፣ ስለ ሰላምና ስለ አንድነት ከልዑል እግዚአብሔር በታዘዝነው መሠረት በፍጥነት ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት አለብን። አርማችንም “አንዲት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ አንድ የኢየሱስ ክርስቶስ መንጋ፣ አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ” ነው።

ሃያ ዓመት ሙሉ የውስጥ ሲኖዶስ የውጭ ሲኖዶስ በመባባል ተወጋግዞ መኖር ያተረፈው ነገር ቢኖር ቤተ ክርስቲያኗን ክፉኛ መጉዳትና ሃምሳ ሚሊዮን ልጆቿን ሰብሳቢና ታማኝ እረኛ አሳጥቶ ለአውሬ መዳረግ ነው። ይህ ሁኔታ ከአሁን በኋላ ቢቀጥል ውጤቱ የባሰ መበታተን፣ መጎዳትና መሰቃየት ይሆናል።

ስለዚህ ሰላምና ፀጥታ ባለበት በውጭው ዓለም የሚኖሩ በሚሊዮን ሳይሆን በሺዎች ብቻ የሚቆጠሩ አባቶች፣ ካህናትና ምእመናን አድማሳቸውን አስፍተው ለራሳቸው ከሚያደርጉት ባላነሰ ሁኔታ ኢትዮጵያም ውስጥ ታፍነው በየገዳሙ፣ በየአድባሩ፣ በየገጠሩና በየከተማው በስቃይ ላይ ላሉት ካህናትና ምእመናን አበክረው ሊያስቡ ይገባል። እንዲሁም በመካከላቸው ያለውን መቃቃርና መለያየት በፍጥነት አስወግደውና ኢትዮጵያ ከሚኖሩት ዝግጁ ሆነው መሪ ብቻ በመጠበቅ ላይ ካሉት አያሌ ቆራጥ አባቶችና ምእመናን ጋር አብሮ በመሰለፍ የቤተ ክርስቲያኗን ደኅንነትና አንድነት ተግተው እንዲጠብቁ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስጠይቅ የሃምሳ ሚሊዮን ሕዝበ ክርስቲያን ከባድ አደራ አለባቸው።

Kebede Bogale said...

ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ሃበ ዮሐንስ ከመ ያጥምቆ በፈለገ ዮርዳኖስ፥ ወውጺኦ እማይ ተርኅዎ ሰማይ መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ፥ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ። እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ መታሰቢያ ዕለት በሰላም አደረሳችሁ። 2005-33=1972 ዛሬ የምናስበው 1,972ኛውን የጥምቀት በዓል ነው። ባገራችን በኢትዮጵያ ዛሬ የሚከበረው እርግጠኛ ነይ በደስታና በሐሴት ይሆናል ብየ አላስብም። ምክንያቱም ባገር ውስጥ ያሉት ''የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች'' በውጭም ሆነ በውስጥ ለምንኖረው ምዕመናን ጠብቀነው የነበረውን እርቅና ሰላም እንደማይሆንና የዛሬውን የጥምቀት በዓል በመሪር ሐዘን እንድናስበው አድርገውታልና ። ኣወ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች የሀገሪቱ ከተማዎች ለቱርስት መስሕብ (tourist attractions ) ተብሎ በድራማ/ትእይንት መልክ ታስቦ ይውላል። ጳጳሳቱ ሳይሆኑ ግን ባለባበሳቸው ለድራማው ማድመቂያ በልብሰ ግርማ መስለው፥ አጊጠውና ደምቀው የሚታዩበት ቀን ነው። አድርባይ ዘማሪዎችና ባለቅኔዎችም ከጥምቀቱ ባለቤት ከራሱ ከኢየሱስ ክርስቶስ ይልቅ ለነዚህ በልብሰ ግርማ ላጌጡ ፥ ጳጳሳት መስለው ለሚታዩ የፖለቲካ ካድሬዎች፥ ከፍተኛ እንክብካቤና ውድሴ ከንቱ እያጎረፉላቸው የሚውሉበት ዕለት ይሆናል። ይህ ነው እውነታው ! የእምነቱ ጠላቶች የእምነት መሪዎች መስለው እምነቱን እያጠፉበት ያለውን ዘመን አምላክ እንዲያሳጥርልን ወደርሱ ብቻ እንጽልይ።

Anonymous said...

Ene yemaygebagn neger lemindin nuw chigirun hulu addis Abeba yalew sinodos nuw yefeterew yeminlew? America yalew ye kehadi "abatoch" sibsib aydel ende yezih hulu chigir menesha. Addis Ababa yalew sinodosima tikililegna wusane nuw yasalewfew. Ke wenbedewoch gar dirdir kezih belay le asar...bilual.

Hailu said...

"ጠንቸኛ ሆኖብን የእግዚአብሔርን ሳይሆን የስጋን ሥራ እንድንሠራ ስላደረገን እርስዎ ያን ተቀብለው ስልጣኑን አልፈልገውም ይበሉ' ማለትስ ተገቢ ነው? ይህን ቢቀበሉ እርሳቸውንስ የኀጢያቱ ተባባሪ አያደርጋቸውም? ይህ የክርስቲያን ጥያቄ ሳይሆን ክርስትና ዞሮበት የማያውቅ ሰው ጥያቄ መሆኑ በዚህ ይታወቃል። የርሳቸውን ጸሎትና ዝምታ፣ የምእመናንን ለቅሶና ዋይታ፣ የገዳማውያንን ስደትና መንከራተት አይቶ ጆሮን ጭው በሚያሰኘው በራሱ መንገድ እግዚአብሔር መልስ እንደሚሰጠን ቅንጣት መጠራጠር አያስፈልግም። "

For me, it has never been much clearer than this as to who I should follow as the Patriarch of our Orthodox Church.
We have witnessed the unholy and non-spiritual decision these cadre bishops have passed. So, we will not accept them as fathers of the my beloved Church. Even more so, we will reject our right the the 6th cadre they may assign.

Now more than ever, the 4th Patriarch, His Holiness Abune Merkorios is indeed the legitimate Patriarch.

Tekle said...

I share the pain and anguish the writer expressed over the shameful decision these so called fathers passed. It is an unfortunate error of epic proportion in the history of our Church.

My question for the writer and my fellow Orthodox Christians is that,
Why should we care about the 'wugzet' from these people which was done without reason and out of malice? Is it not what we call "wofe gezit"?

On one side we say these bishops are government operatives. On the other hand we worry about their 'wofe gezit'. We should not care about any of the curses that came out of these so called bishops.

For me the right kind of 'wugzet' is the one that was passed by Aleka Ayalew, bless his soul, becaus it was done for right reason, i.e., the illegal assignment of the late Aba Paulos, etc.


Therefore, ignore the irrelevant 'gizit'. Let’s unite around the 4th Patriarch and strengthen the Orthodox Church in the Diaspora then in Ethiopia. We know some good bishops in Ethiopia are suppressed by the cadres. The government is run by atheists and ‘menafkans’. They don’t care if the Orthodox Church disappears. They in fact work to weaken it because they have wrongly labeled it clearly that it is the 'church of neftegnas'.

Therefore, if those of us in the Diaspora unite our Church, then we can be a voice for the voiceless fathers and fellow Christians in Ethiopia. If we unite, we can do wonders to save our monasteries and assist the monks who are persecuted by the government operatives.

Anonymous said...

"አንድ ክርስቶስ፤ አንድ ሲኖዶስ፤ አንድ መንጋ!" ጥሩ አባባል ነው። ዘመናት ተሻግሮ እኛጋ የደረሰውም ይኸው ነው። እንግዲህ የጠመመውን ማቃናት ካስፈለገ ሲኖዶስን በርበሬና ሚጥሚጣ ይመስል "ወደ አሜሪካ ይዠው መጥቻለሁ" ያለውና ሁለት ሲኖዶስ እንዲኖረን ምክንያት የሆነውን አካል መጠየቅ ያስፈልጋል። በኢትዮጵያ ያለው ሲኖዶስ "ቀኖና አፍርሶ ፓትሪያርክ በህይወት እያለ ፓትሪያርክ ሾሞአል" ብለን እንኳ ብናምን ለስደተኛ አባቶች ሁለተኛ ሲኖዶስ ለመመስረት ምክንያት አይሆንም። ይልቁንም ስደተኞቹ ጳጳሳት ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚያስችላቸውን ሥራ መሥራት ነበረባቸው። አላደረጉትም። ተደላድለው ነው የተቀመጡት። ሲጀመር ሊቃነ ጳጳሳቱ ዜና ማርቆስ፤ መልክፄዴቅ፤ ኤልያስ መሰደድም አልነበረባቸውም። ሃገረ ስብከት ነበራቸው በጎቻቸውን በትነው፤ "ትዳራቸውን" አፍርሰው ነው የመጡት። ጵጵስና ትዳር ነው። ሃገረ ስብከትህ የትዳር አጋርህ ማለት ነች። ታመመች፤ አጣች፤ ነጣች ብለህ አትተዋትም። እነዚህ አባቶች ትዳራቸውን ማፍረሳቸው ብቻ አይደለም ችግሩ የሰው ምሽት ማማገጣቸውም ጭምር እንጂ። ለምን ቢሉ አሁን ተደላድለው የተቀመጡበት የሐዋርያው የአቡነ ይስሐቅ ሃገረ ስብከት ነው። እነዚህ አባቶች ቦታውን የያዙት በወረራ፤ የሰው ምሽት ቀምተው ነው። ለመሆኑ የወረዱት ፓትሪያርክ መርቆሬዎስ ናቸው፤ እነሱ ሃገረ ስብከታቸውን የቀማቸው የለም። ምን ሆን ብለው ነው የተሰደዱት? ፓትሪያርክ መርቆሪዎስ ስለወረዱ? ማን ሆነና ያወረዳቸው! ቀኖና ስለፈረሰ? ማን ሆነና ያፈረሰው! ቢሆንስ ቀኖና ለመጠገን አሜሪካ ድረስ ምድከም ለምን አስፈለገ? መሰደዳቸውስ ምን ፈየደ? ፓትሪያርክ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው የመመለሳቸውን ጉዳይ አፋጠነ?ምንም። ስለዚህ ይህንን ችግር ከስሩ ማየት መቻል አለብን። "አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ" የእነዚህ አባቶች መሰደድና እዚህ መጥቶ ሲኖዶስ ማቋቋም የችግሮቹ ምንጭ ነው። መሪዎች ነን ከተባለ፤ እረኞች ነን ካልነ ፈተና ሲመጣ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት ያሳየውን ጽናት ምሳሌነቱ ለኛ ነው። ካልቻልን እድሉን ለሌሎች እንስጣቸው። አገርም ተንቀሳቃሽ ድንኳን አይደለችምና። ሰሞኑ በአንድ መጦመርያ ያየኋት ያባታችን ያቡነ ቴዎፍሎስ ቃል ምንኛ ወቅታዊ ነች።ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በሃሰተኛው የደርግ “ተሃድሶ ኮሚሽን” ተወንጅለው ለስራት ከመዳረጋቸው በፊት አንዳንድ ወዳጆቻቸው እንዲሸሹ መክረዋቸው ነበር። ቅዱስነታቸው ግን የሚደርስባቸውን ማንኛውንም መከራ ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ቆርጠው ስለነበረ ምክሩን አልተቀበሉትም፤

እኔ አሉ ቅዱስነታቸው “ እኔ ከዚህ ደረጃ የደረስሁት ከትቢያ ተነስቼ ነው። በሰላሙ ጊዜ ስሾም ስሸለም አባ! አባታችን! እየተባልሁ ስከበር ኑሬአለሁ።ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ከንጉሰ ነገስቱ ጀምሮ ያሉ ታላላቅ ሰዎች እየታሰሩ ያለ ፍትህ እየተገደሉ ናቸው እኔም በሃገሬና በቤት ክርስቲያን ስም የሚደርስብኝን ማንኛውንም መከራ መቀበል እንጂ መሸሽ ተግባሬ አይደለም። አባቶቼ ሃዋርያትና ሰማእታት ሰለ ቀናች ሃይማኖታቸው ሲሉ በሰይፍ ተቆርጠው፤ በገመድ ታንቀውና በእሳት ተቃጥለው በሰማእትነት ተሰውተዋል፤ እኔም እንደነሱ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያን ክብር ስል እስከ ሞትም ድረስ ቢሆን መከራና ስቃይ ከመቀበል በቀር ወደ ኋላ የምልበት ምክንያት የለም።

ቀደም ሲል በነአቡነ ጴጥሮስ ላይ የደረሰውን የሰማእትነት ሞት እኔም የነሱን ፅዋ ቆርጨ እንድቀበል እንጂ እንድሸሽ አይገፋፋኝም፤ ለእኔ ህይወት ሲባል በብዙ ድካም የተገኘውን የቤተ ክርስቲያን ክብር አላዋርድም፤ ባንገቴ ላይ ስለት (ሰይፍ) እያንዣበበ እንደሆነ ይታወቀኛል፤ ቢሆንም እዚሁ ሁኜ የሚመጣብኝን መከራ ለመቀበል ዝግጁ ስለሆንኩ በምንም ተአምር አልሸሽም” ነበር ያሉት።

Z Hailemariam said...

Dear All Ethiopians and Orthodox Christians,
I agree with the motto "One people, One Sinodos, under one God".
I would like to suggest a solution that will help us to reveal from this chaotic crisis. We all know that Woysne is trying to tear apart not only the country but the religious groups as well. Woyane is doing this Tirelessly to implement its plan on the devastation of the country and the society as a whole. Therefore, now this fight is clearly between Orthodox Christians and the "Setan". We need to pray together along the line of each nationalities and tribes who want to get ride of "Setan". If a Christian (Orthodox) people can not come together, there will not be a lasting solution.
Suggestion:
1. Starting from this Sunday all Christians across the world should create an ad hoc committee that will lead each church or congregation to meet the other.
2. Abuna Merkorios must call to the Orthodox Christians around the world and tell them that separation is enough, we all should reconcile, love each other, come to the round table, and show unity for one God and one sinod.
3.As there are Woyane intelligence in our churches around the world, we have to convince them to stop spying for woyane and be a humble and true Christian along with other brother and sisters.
4. We have to send one clear message to the current Ethiopian leaders to stop interfering in our church as the consequence is very bad for themselves.
5.As woyane has made it clear that they are not representatives of Ethiopian Orthodox but Tigrian Orthodox, all Tigrians whether in Ethiopia or abroad must identify themselves and openly start to tell the regime to stop playing games on the innocent Tigris Ethiopians.
6. Jesus came to this world because of his love; we have been saved by him and his scarification is now in vain because the so called big fathers of the Church betrayed him. They will pay the price if we all pray together.
May God help us all and bring back our beloved country and church as a powerful and peaceful being in the world, Amen, Amen, Amen.

Egziabher Ethiopian Ena Hizbuan Yibark.
Wosibhat le egziabher.

Z Hailemariam


Unknown said...

በጽድቅ ትመሰረቻለሽ፤
የግፍ አገዛዝ ከአንቺ ይርቃል፤
የሚያስፈራሽ አይኖርም፤
ሽብር ከአንቺ ይርቃል፤
አጠገብሽ አይደርስም።
ማንም ጉዳት ቢያደርስብሽ ከእኔ አይደለም፤
ጉዳት ያደርስብሽ ሁሉ ለአንቺ እጁን ይስጣል።
እነሆ የከሰሉ ፍም እንዲቀጣጠል የሚያራግበውን፤
የጦር መሣሪያ የሚያበጀውን ፤ አንጥርኛውን የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤
ጥፋት እንዲያደርስም የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤
አጥፊውንም የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤
በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀን መሣሪያም ይከሽፋል፤
የሚከስሽንም አንደበት ሁሉ ትረቺያልሽ፤
እንግዲህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፤
ከእኔ የሚያገኙትም ጽድቃቸው ይኽው ነው፤
ይላል እግዚአብሔር ።
ኢሳያስ 54: 14-17

Bertu

Kebede Bogale said...

ከወያኔ የከፋ ወንበዴ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ እንዴ ? ወያኔ ገና በጫካ ሳለ የመንደሩ ልጆች የሆኑትን ካህናትና መነኮሳት የጦር መስሪያ አስታጥቆ ብዙ ሕዝብ እንዲጨፈጭፉ ያደረገ አሸባሪ ወንበዴ እኮ ነው ዛሬ አገራችንና ቤተ ክርስቲያናችንን የወንበዴ ዋሻ አድርጎ እያወከን ያለው ። መርሕአችንም መሆን ያለበት በግልጽ ጨለማውን ከብርሃን ለይተን ''አንድ አምላክ ፥ አንዲት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፥ አንድ ሕጋዊ/ቀኖናዊ ሲኖዶስ '' መሆን አለበት። ይህ በማያሻማ ቋንቋ መቀመጥ አለበት ። ምክንያቱም አሁንም አዲስ አበባ ያለውን በነ ዐባይ ፀሐዬ የሚመራውን በድፍረት ''ቅዱስ ሲኖዶስ'' እያሉ የሚጠሩ ስለማይጠፉ። የመንፈ ቅዱስ ስጦታ የሆኑትን ፤ እርቅን ፥ ሰላምን ፥ አንድነትን እንደማይፈልግ በጥመቀቱ መታሰቢያ በዓለ ሰሞን ለምዕመናን ያስረዳ የፖለቲካ ካድሬዎች ስብስብ ''ቅዱስ ሲኖዶስ '' ብሎ መጥራት መንፈስ ቅዱስን እንደመስደብ እንደሚቆጠር ጠንቅቀን የምናውቅ ምዕመናን በዚህ እግዚአብሔር እራሱ በሚጠራበት ስም አንጠራውም። ይህን አመጸኛ ስብስብ በዚህ ቅዱስ ስም የሚጠሩትንም 'ወኢይትሆለቁ ምስለ አባግዓ መሬቱ ለክርስቶስ'ብለን እናወግዛቸዋለን።

Anonymous said...

I always see your comments and publication on the peace of our church. I never see any thing on the other side of it i.e what is beyond the peace. Do you think that in this type of our church organization we can not loss our believes in near future if we get in to peace? Please, please see what is beyond the peace. do you want peace with Tehadeso...What do you mean why we really push peace and peace where we have peoples who believe in different from our mother church. Are you telling us to have a peace with Tehadeso? You are saying peace peace.... to cry tomorrow....

Anonymous said...

wey Gud....every thing id belamed on Woyana aha.....even dicsion of your parents on their family is blamed......

Tsegaye Meshesha Gugssa said...

Yes, one Christ! one Holy Synod! one Herd! rvatoni

Anonymous said...

ዛሬ በአንድ አድርገን ድረ ገጽ ላይ ያየሁትን ጥሩ ጽሁፍ መሰረት በማድረግ የጻፍኩትን አስተያየት የሚጠቅም ከሆነ ብዬ እዚህም መለጠፍ ወደድኩ።
በዘመናችን ታራቂ የሆኑ አባቶች ማጣታችን በእርግጥ ያሳዝናል። ያሳፍራልም። ምክንያቱም እናንተ በትክክል እንደገለጻችሁት አሁን የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ከዚህ የተሻለ ጊዜና አጋጣሚ ማግኘት ማግኘት አስቸጋሪ ስለሚሆን ነው። ደግሞም “የሚገርመው ግን የተጋፈጠውን ፈተና ይህንን ያህል መስዋዕትነት እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አለመሆኑና ፍቅርን በማሳየት ፤ እልህንና ካፈርኩ አይመልሰኝ በመተው ፤ ከግል ጥቅም በመተው ቤተክርስቲያንን ጥቅም በማስቀደም ፤ ለተቀቡበት ሰማያዊ አገልግሎት ታማኝነትን በማሳየት በቀላሉ የሚፈታ መሆኑ ነው፡፡’’ አሁን ቁምነገሩ ያለውና ልናተኩርበት የሚገባው የተጋረጠውን አደጋ እንዴት እንቀንስ የሚለው ነው። እኔ በተለይ ምእመናን የሚከተሉትን ብናደርግ እላለሁ፤ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ።
1. በአባቶች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት ምንጩ ዓይን ያፈጠጠ የሥልጣን ሽኩቻ እና ዘረኝነት መሆኑ እርግጥ እየሆነ የመጣ በመሆኑ በየትኛውም ወገን የቀደሙት አባቶች የሠሩት የቤተክርስቲያን ቀኖና እና ሥርዓት እየተጠቀሰ የሚነገረንን ሰበብ እየተቀበልን ከመለያየት መቆጠብ። ቤተከርስቲያንን አንድ የሚያደርጉ አባቶች እስከሚነሱ ድረስ በየትኛውም ጎራ የተሰለፉትን አባቶች መንፈሳዊ ስልጣን በማክበር የምንገለገል መሆኑን ነገር ግን አንዱን በማውገዝ ሌላውን በማግነን የማንተባበ መሆኑን በተግባር ማረጋገጥ፤
2. በተለይ ከሀገር ውጭ የምንኖር ምእመናን በፍጹም የዋህነት መንፈስ በያልንበት የቤተክርስቲያን አስተዳደር ጸንተን አገልግሎት በመስጠትና በመቀበል መጽናት። የቤተክርስቲያንን ትምህርትና ሥረዓት ሳይበርዙ በየትኛውም አስተዳደር የሚያገለግሉ ካህናትንና የሚገለገሉ ምእመናን ከመውቀስ/ከመንቀፍ መቆጠብ። ይልቁንም በዓላትን በአንድነትና በፍቅር በጋራ ማክበር። ለቤተክርስቲያን በሚጠቅሙ ሥራዎች ሁሉ አስተዳደራዊውን ድንበር ተሻግረን መተባበር።
3. ቤተክርስቲያናችን የፖለቲከኞች መፈንጫ እንዳትሆን (የወያኔም ሆነ የተቋዋሚዋቹ) በንቃት መጠበቅ። ከፖለቲከኞች ጋር በመተባበር የቤተክርስቲያንን ጥቅም አሳልፈው ከሚሰጡ ካህናትና ሰባኪያን መለየት።
4. ውሉን ማግኘት ከሚያስቸግረውና በቀላሉም መቋጫ ከማይገኝለት የቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ ችግሮች ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ የራሳችንና የመጪውን ትውልድ መንፈሳዊ ሕይወት በሚያንጹ ተግባራት መጠመድ።
5. በማንኛውም ሁኔታ መለያየትን ከሚያስከትሉ ተገባራት በመቆጠብ በማናቸውም ምክንያት ቤተክርስቲያናችን በጥቂት መነኮሳት ጥል እንደማትከፈል ማረጋገጥ፥
6. አስተዳደራዊውን ክፍተት ተጠቅመው የቤተክርስቲያንን ትምህርት ለመቀሰት የሚያደቡትን በንቃት መጠበቅ
7. እውነተኞቹ የወንጌል መምህራንና ካህናት ምእመናን ከዚህ አሳፋሪ የመለያየት መንፈስ ወጥተው በአንድነትና በፍቅር የሚገለገሉበትን መንገድ ማስተማርና መምራት እንጂ አንዳችም የሚለያይና የሚከፋፍል ትምህርት ከማስተማር መቆጠብ፤

Birile said...

I am not clear as to what other options The Synode in Ethiopia could have presented in their negotioation table with the outside synod? As for me, they have presented every posible solution. The return of Abune Merkoriosto his privious position is very contadictory and controvercial ground for the disagrement.Abune Merkorios had abandond his privious position for a political reason according to the outside synod. If so, what is differnt now to go and get this position back given the same political system? Is he willing to claim it? If he wasn't able to withstand the chalenge when he was 20 years yonger, can he stand the challenge now? If not,and if he is not willing, why should they take this as a point of disagreement a turning point to the history of the church? hatread is driving us crazy. Greed has blinded us all. We are simply an instrument of politicians who dont care about the church anyways.The Lord instructed St. Peter to take care of HIs sheeps. This should be the priority of the Prists.nothing else.

Anonymous said...

ከላይ ሃሳብ ለሰጡት ለአቶ ከበደ ቦጋለ

የእነዚያ አካሄድ ትክክል አይለም ማለት እኮ እዚህ ያሉትን ንጹህ አያደርጋቸዉም ቤተክርስቲያንን በመግጉዳት እንዲሁም ዘረኝነቱና ኑፋቄዉን በማስፋት እዚህ ያሉት ቢበልጡ እንጂ አያንሱም ስለዚህ ለእዉነት እንጂ ለግለሰቦች መወገን ማቆም አለብን
ይህን እንዲያደርጉና ከእግዚያብሔር ትዕዛዝ ይልቅ ለሰዉ እንዲገዙ ያደረጋቸዉ የእኛም የምዕመኑም ድክመት አለበት

Anonymous said...

Tesfa...
@ Kebede Bogale...
እንድህም አልክ...
"...በጥመቀቱ መታሰቢያ በዓለ ሰሞን ለምዕመናን ያስረዳ የፖለቲካ ካድሬዎች ስብስብ ''ቅዱስ ሲኖዶስ '' ብሎ መጥራት መንፈስ ቅዱስን እንደመስደብ እንደሚቆጠር ጠንቅቀን የምናውቅ ምዕመናን በዚህ እግዚአብሔር እራሱ በሚጠራበት ስም አንጠራውም። ይህን አመጸኛ ስብስብ በዚህ ቅዱስ ስም የሚጠሩትንም 'ወኢይትሆለቁ ምስለ አባግዓ መሬቱ ለክርስቶስ'ብለን እናወግዛቸዋለን።"
የምታወግዝበትን ሥልጣን ከየት እንዳመጣኀው አላውቅም፣ ስለ ስድብ ቃልህ እንደምትጠየቅ ግን አትዘንጋ!
ደግሞም፣ ችግር በተከሰተ ጊዜ ከጉባኤው ጋር፣ ከዎንድሞቻቸው ጋር ችግሩን መጋፈጥ ሲገባቸው፣ ይህ ካልተቻለም ችግሩ እስኪያልፍ በግላቸው ተሰደው የችግሩን ጊዜ አሳልፈው መመለስ(እንደነ አቡነ ገብርኤል) ሲገባቸው ምዕመኑን ጥለው ከሄዱ በኋላ 4 እና 5 ሆነው የመሰረቱትን ቡድን "ህጋዊ ሲኖዶስ" ብላችሁ ተቀበሉ፣ እነሱ ጥለው የመጡትን ዋናውን ጉባኤ ደግሞ አውግዙ ስትል አለማፈርህ! እንደዎትሮህ ዎያኔ አሳዶአቸው ነው፤ በግፍ ተሰደው ነው ... ምናምን ብትል ያምርብህ ነበር። ይህ ሃሰት የሌለበት እውነት ነው። ነገርግን ዎያኔ ፈተና ሲያመጣባችሁ ተሰደዱና ለአንዲት ቤ/ክ ሌላ ሁለተኛ ሲኖዶስ መሥርቱ የሚል ህግም ሆነ ትውፍት አልነበረንም። የዎያኔ ፈተና በዛ ቢባል ቃሊቲ ነች! የቀድሞ አባቶች እኮ አንገታቸው በሲባጎ እስኪታነቅ ፈተናን ታግሰዋል/ተጋፍጠዋል። አቡነ ቴዎፍሎስ እኮ ከንጉሱ ቤተሰቦች ጋር መሰደድ ይችሉ ነበር፣ እሳቸው ግን እንደሚገደሉ እያወቁ ለወደፊቷ ቤ/ክ ሲሉ እስከ ህይዎታቸው ህቅታ ድረስ ተጋደሉ።
እና ወንድም ቦጋለ፣ እንዲህ ባሉ አባቶች ሰማዕትነት ያሸበረቀ፣ በነ አቡነ ተ/ሃይማኖት(3ኛው) ንጹህ እምነት ያጌጠውን ቅ/ሲኖዶስ አውግዛችሁ በነ አቡነ መልከጼዴቅ "አፈንጋጭነት" የተመሠረተውን ቡድን "ቅ/ሲኖዶስ" ብለን እንቀበል እያልከን እኮ ነው።
እንዴ... ተውን እንጂ፣ ለእርቅ ሲባል ሁሉም ወገን መስዋዕትነት ይክፈል በሚል ብንወያይ እውነታው ማይታወቅ አስመሰላችሁት እኮ!
ጸሃፊውን ግን እግዚአብሔር ይስጥልኝ! ቃለ ህይዎትን ያሰማልን!
"አንድ ክርስቶስ! አንድ ሲኖዶስ! አንድ መንጋ!"

Hailu said...We know for sure the Synod in Ethiopia is under the control of an opressive government and shaken from the inside by cadre 'bishops'.

As such it has kept silent when the age old monastery Waldiba is desecrated. It has violated the church's cannon law and exiled its rightful Patriarch just to put the synod under the control of a TPLF cadre, the late Aba Paulos.
We know for sure the Synod in Ethiopia is under the control of an oppressive government and shaken from the inside by cadre 'bishops'.

As such it has kept silent when the age old monastery Waldiba is desecrated. It has violated the church's cannon law and exiled its rightful Patriarch just to put the synod under the control of a TPLF cadre, the late Aba Paulos.

So, how can we call this 'synod' a holy synod if it once again reaffirms its willingness to commit yet another blander in our church? This is not what a Holy Synod does. If it does unholy things,the we shall NOT call it a Holy Synod.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)