February 2, 2013

“አንድ ክርስቶስ!” “አንድ ሲኖዶስ!” “አንድ መንጋ!


(ወልደ  አረጋዊ፤ በተለይ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት/ PDF)፦ ሕት ጣፋጭም መራራም ዋዋን ደጋግማ ትግታለች፡፡ ዛሬ ረቡዕ ሰው፣ ብሎም ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ በመሆኔ ብቻ እጅግ መራራውን የሕይወት መርዶ ተጎንጭቻለሁ፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያኔና በምዕመኑ ላይ በግፍና በማን አለብኝነት ስለተዘጋብን “የሰላም በር” መርዶ ሬት ሬት እያለኝ ሰምቸዋለሁ፡፡


አባቶቻችን ፈረዱብን! እንዲያ ከአናፍ እስከ አናፍ ያስተጋባውን የመንጋው የተማኅጽኖ ጥሪ አልገደዳቸውም ነበር እና “ቅድሚያ ለምርጫ” ማለትን ወደዱ፡፡ እጅግ መራራ ነው፡፡ ይህን መስማትም ሆነ ማሰብ እጅግ ይመራል፡፡ በመለያየት ውስጥም መኖር ከሁሉም በላይ አብዝቶ ይመራል፡፡ አባቶቻችን ግን በእኛ በክርስቶስ የአደራ ልጆቻቸው በምንሆን ላይ እጅግ አብዝቶ በሚመረው “የመለያየት ክርስትና” ውስጥ እንድንኖር ዛሬ በድጋሚ ፈረዱብን፡፡ አባቶቻችን አንድ እንዳንሆን በድጋሚ ፈረዱብን!

ዘማሪው እንዳለው “ሰች ፈረዱብኝ አንተ ግን አዳንከኝ” ነውና ታሪካችን ከዛሬ ፳ ዓመታት በፊት የተገነባው የመለያየት ግድግዳ ዛሬም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሰዎች ቢፈርዱብንም እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አባትና የእኛ የልጆቹ መቅበዝበዝና ለክፉው ተላልፈን መሰጠታችን በእውነት የሚገደው እረኛችን ነውና በእውነት ዝም አይልም፡፡ መንጋውን ከመቅበዝበዝ ያድናል ይሰበስበናልም፡፡ ጽሐፍ እንዳለው እርሱ እውነተኛ የበጎች ጠባቂ ነው!

“ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም!” ይላል ያገሬ ሰው፡፡ እነሆ እኛም ኢትዮጵያዊ ክርስቲያኖች ነን እና መቼም ቢሆን በክርስቶስ ተስፋ አንቆርጥም፡፡ እንግዲህ ለአለስት መታት በተለየም ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ  እረፍት በላ በመላው ዓለም የምንገኝ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች “ቅድሚያ ለርቅ” በሚል ዐቢላማ ር ተሰባስበን አባቶቻችን ስንማፀንና ስናግባባ ከርመናል፡፡ ይህ መንገድ ዛሬ ረቡዕ ጥር ፰ ፳፼፭ በይ እንደተዘጋና “ቅድሚያ ለምርጫ” የሚለው ሳብ እንዳሸነፈ መርዶው ደርሶናል፡፡ ስለዚህ በአባቶቻችን የተዘጋውን የአንድነት በር ተስፋ በመቁረጥ እንቀበል ወይስ እኛም እንደቀደሙት ክርስቲያኖች “ክርስቲያን ተስ አይቆርጥም!” እንበል?

እኔ “ክርስቲያን ተስ አይቆርጥም!” ከሚሉት ወገን ነኝ ምክንያቱም በክርስቶስ የማይቻል ነገር እንደሌለ በተረዳ ነገር አውቄለሁና፡፡ ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች መቼም ቢሆን ስለ ሰላም፣ ስለ ፍቅርና፣ ስለ አንድነታችን ተስፋ አንቆርጥምና ምን እናድርግ? ወደሚለው መረታዊና አግባብነት ያለው ጥያቄ መሻገር ያለብን ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ በእኔ በኩል ለመነሻ ይሆን ዘንድ የሚከተሉትን ሳቦች እነሆ

፩ኛ.  የሰላምና የአንድነት ግብረ-ይል!
የአባቶቻች መለያየት በተለይም “ውግዘቱ” እግ ሸክሙ የከበደውና ለያይቶን የሚገኘው በስደት ላይ ምንገኝው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ላይ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ምክንያቱም የተወጋገዙቱ በጋራ የሚገኙት ሀገር ቤት ሳይሆን እዚህ በውጭው ዓለም ነውና፡፡ ስለዚህ የችግሩ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሾች የሆን እኛ በምንኖርባቸው ከተሞች /ስቴቶች/ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየቤተ ክርስቲያኑ አንዳንድ ምዕመን በመወከል የጋራ የሰላም ኮሚቴ በማቋቋም ምዕመኑ በአንድነት ግዚአብሔርን የሚያመልክበት፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጠብቅበት፣ወደፊትም ሊሰሩ ስለሚገባቸው በይት ተግባራት የሚመክርበትና ከሁሉም በላይ አንድነቱንና ብረቱን የሚያፀናበት መድረክ መፍጠር አለበት።

፪ኛ. “አንድ ክርስቶስ!”“አንድ ሲኖዶስ!”“አንድ መንጋ!”
በዚህ የሰላም ኮሚቴ አማካኝነት እዚህ በስደት ያለው ምዕመን የአንድነትና የሰላም መንፈስ ወደ ገር ቤት የሚደርስበትንና እዛም ያለው ምዕመን ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና ለአንድነቱ ተግቶ የሚታገልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል፡፡ ምክንያቱም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየሰማን ያለነው የሌላውን 45 ሚሊዮን ምእመን መፈክሮች ነው፡፡ ይህ ደግሞ በስደት የምንገኘውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች እንደ ውጭው ሲኖዶስ አባቶች ከገር ቤቱ ክርስትና ለመለየት የተጠነሰሰልን የእብደት መንገድ ነው፡፡  ስለዚህ ጥሪያችንም ሆነ መዝሙራችን አንድ ነው፡፡ይውም “አንድ ክርስቶስ!” “አንድ ሲኖዶስ!”“አንድ መንጋ!”

እናንተም አክሉበት!!!

ቸር ወሬ ያሰማን ብያለኹ!!! አሜን
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)