January 16, 2013

የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ዘገባ


7 comments:

Anonymous said...

የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተገቢ ነው። ምክንያቱም የዚህ ሁሉ ችግር ፈጣሪ አባ ኃብተ ማርያም (አባ መልከ ጼዴቅ) ናቸው። ይህንን የሚያውቁ ካህናት እዚሁ አሜሪካ በብዛት ይገኛሉ። ይህንን የሚቃውም አንድም የአንድ አካባቢ ሰው መሆን አለበት ወይም ወያኔን የሚቃወም ወይም ስለነገሩ ያልገባው ነው። ለምሳሌ ያህል የአሜሪካና የአካባቢው ሊቀ ጳጳስን አቡነ ይስሕቅ ነፍሳቸውን ይማረውና በሳቸው ጥረት ወደ አሜሪካ ከመጡ በኋላ በህገር ልጅነት በመሰባሰብ ቡድን በመፍጠር ስደተኛ ሲኖዶስ አቋቁመው ታሪክን ጥላሸት ቀብተዋል። እኝህም አባት ሲኖዶስ ማቋቋሙ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት የማይጠቅምና ትክክልም አለመሆኑን አጥብቀው በማሳሰባቸው ከመሃላቸው እንዲወጡ ተድርጉዋል። ይህ ሲሆን ታሪኩ እነሱ እንደተበደሉ ሲናገሩ ግን ለኅሊናቸውም አልከበዳቸውም። እስቲ ስብስባቸውን እንመልከተው በካህናቱ ማለቴ ነው አንድም የተቀላቀለ ሌላ ጎሣ እንኳን የለም ከመነኮሳት ከመምህራኑ ጀምሮ እስከ ሊቀ ጳጳሳቱ ስለዚህ የተያዘው የጎሣና የፓለቲካ አካሄድ በመሆኑ እዚሁ ይቀመጡ። ከልብ ያልሆነ እርቅ ድሮውን ከእግዚአብሔር ስላልሆነ ውጤትም እንደሌለው የታወቀ ነበር። ኢትዮጵያ በነበሩ ጊዜ ለምናውቃቸው ሁሉ ለሚያደርጉት ነገር አዲስ አይደለም። ልቡና ይስጣቸው እላለሁ።

Anonymous said...

የተከፋፈሉት የቤተ ክርስቲያኗ አባቶች እስካሁን ባደረጉት ሙከራ በመካከላቸው ዕርቀ ሰላም ለማውረድ አልታደሉም። ሌላው ቢቀር በስሜት ተነሳስተውና በየምክንያቱ ወገን ለይተው የፈጸሙትን እጅግ አሳዛኝ የእርስ በእርስ ውግዘት እንኳ ለፍቅና ለሰላም ሲሉ እስከ ዛሬ ማንሳት አልቻሉም።

ልዑል እግዚአብሔር ያልተለመነን የጎደለ ነገር ቢኖር ነው ። ይህም በኢትዮጵያም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖሩትን ከአርባ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ምእመናን የሃያ ዓመት ስቃይ ወደ ባሰው አደጋ ታማኝ የሆነ ምድራዊ እረኛ ወደ ማጣቱና ወደ መበታተኑ አፋፍ አድርሷቸዋል። አደጋውም አውሬ እጅግ በበዛበት ዘመን መከሠቱ ለአባቶችም ሆነ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ፈጽሞ እንደማይበጅ እሙን ነው።

ስለዚህ ቀኑ ፈጽሞ ሳይጨልም በውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩት አባቶች ባለችው የተስፋ ጭላንጭል ተጠቅመው ``የቄሣርን ለቄሣር፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር`` ብለው በመነሳት፣ መሥዋዕት በመክፈል ዕርቀ ሰላሙን ፈጥነው ከዳር እንዲያወጡ ምእመናን በሙሉ የተማጸኑበት እጅግ አሳሳቢ ኃላፊነት ነው። ይልቁንም ፍቅር፣ ሰላምና ዕርቅ በተግባር ሊታዩ የሚገባቸው አባቶች ዘወትር የሚሰብኳቸው ሊጣሱ የማይገባ የልዑል እግዚአብሔር ትእዛዛት ናቸው።

በኢትዮጵያና በውጭው ዓለም የሚኖሩ ምእመናን እግዚአብሔርን ምርኩዝ አድርገው ቤተ ክርስቲያናቸውን ከአደጋ ለመከላከልና አንድነቷን ላለማስነካት ዝግጁ ናቸው። ዛሬ በታላቅ ጉጉት የሚጠብቁት ዕርቀ ሰላም መሥርተው በጋራ የሚያሰልፏቸው አባቶችና ለቤተ ክርስቲያኗ ደኅንነትና አንድነት ሲል ያልተቆጠበ መሥዋዕት ለመክፈል የተዘጋጀ መሪ አባት ብቻ ነው።

Anonymous said...

በጣም ያሳዝናል ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉት ጳጳሳት ትግራይ የራሱዋን ሲኖዶስ ታቁዋቁማለች አሉ፡ ከአንድ ጳጳስ የማይጠበቅ ንግግር ነዉ፡ የመንግስት ካድሬወች እያሉ እንዴት ብሎ አንድነቱ ይምጣ? ከፓለቲካ ነጻ መሆን አለባችዩ መጀመሪያ። የመንግስት ደጋፊ ካድሬወችም ብዙወቹ የዉጩን ጳጳሳት ላይቀበሉ ይችላሉ ምክንያቱም የሀይማኖት ነገር ሳይሆን የሆድ እና አድር ባይነት ስለበዛ፡ አቡነ መርቆሪወስ እማ በጸሎት እና በአርምሞ 21 አመት ሙሉ የአላዉያንን ፈተና ተቁዋቁመዉ አሉ፡ መጪዉንም አምላክ ያዉቃል። ህዝቡ እርስ በራሱ ከመወነጃጀል፡ አንድ ሁኑ ብሎ ድምፁን ቢያሰማ ጥሩ ነገር ነዉ፤ ከሙስሊሞቹ እንኩዋን ብዙ መማር ይቻላል።

Anonymous said...

I ageer with you. we Ethiopiaweyn just come down.why we always be very emotional? we have to solve the problem and talling them we are not follwing any of them unless they are pace.I remember ten years ago the bleme each other so now what? they don't care abuot US. I am rellay sorry what happen to US.ESPECIALLY ABUN ABRAHAM!!!!WHAT HAPPEN TO HIM.I SURPRISED.

Anonymous said...

pleas click the link

Anonymous said...

Pleas click the link.....

http://2.bp.blogspot.com/-HF83Q8fPse4/TltOR_fGS7I/AAAAAAAAAO8/EAkAlosXdvQ/s1600/11.JPG

Hailu said...

This is the act of the devil not that of spiritual fathers.

As you have darkened our hope for a united orhtodox church, let God vanish from your sight the government power you fear and choose to serve.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)