January 15, 2013

እርስዎስ ምን መፍትሄ አልዎት!?

7 comments:

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች ጥረታችሁን አደንቃለሁ። ነገር ግን ምነው ሕያውን አባት ከሞቱት አባት ጋር ጎን ለጎን አስቀመጣችኋቸው? ያለፉትን አልፈዋል ተዋቸው፤ እረፍት ላይ ናቸውና። በሕይዎት ያሉትን ደግሞ ከሙታን ለይተን በሕያውነት እንያቸው። አሁን አንድ አባት ነው ያለን፤ እባካችው ሌላ ፎቶ ተጠቀሙ።

Unknown said...

http://www.zehabesha.com/archives/15936 ይህን ዜና አያችሁት ?

Anonymous said...

በአባቶችና በምእመናን መካከል ያለው ግንኙነት በእኛና በፖለቲከኞቻችን ካለው ግኑኝነት መለየት ያስፈልገናል። አባቶችን “እንዲህስ ቢሆን ምን ይመስላችኋል?” ማለት ያባት ነው፤ “4ኛው ፓትሪያርክ ቢመለሱ ደስ ይለናል” ማለት መልካም ነው። መማጸን፤ መለመን፤ ማሳሰብ ተገቢ ነው። ካልሆነ ባልተገራ አንደበት እንደወረደ መልቀቅ መቆም አለበት ። ምእመናን የመጨረሻ ውሳኔ ለአባቶች ትተን በፀሎት ማገዝ ነው ያለብን። ሲጀመር ነገር ሲኖዶሱን ማመን ያስፈልጋል። አባቶቻችን ለመንግስት፤ ለዚህም ለዛም ቡዱን ተፅእኖ የሚገዙ፤ የራሳቸው አቋም የሌላቸው ተደርገው እንዲሳሉ ባንዳንድ ወገኖች የሚደረገው ስም ማጥፋት መቆም አለበት። አባቶቻችን መታመን ፤መከበር አለባቸው። ከነምሳሌው “ባለቤቱ ያቀለለው አሞሌ…” ነውና። የአባቶችን እርቅ በሚመለከት በመጀመሪያ ግንዛቤ ለወሰድባቸው የሚገቡ ነገሮች ያሉ ይመስለኛል። ቤተ ክርስቲያን ለሁለት አልተከፈለችም። አሁንም ቤተ ክርስቲያን አንድ ነች። አርባ ሚልዮን የሚሆን ምእመን ካላት ቤተ/ክ የተወሰኑ፤ በጥቂት ሺዎች የሚቆጠሩ ልጆችዋ ባስተዳደር ለጊዜው በመለየታቸው ምክንያት ቤተ/ክ ለሁለት ተከፍላለች ልንል አያስኬድም። አለማዊ ንፅፅርም ከወሰድን ኤርትራ ከኢትዮጵያ ቤተሰብነት ተለየች ነው እምንለው እንጂ ኢትዮጵያ ለሁለት ተከፈለች አንልም። ይህ ልዩነት ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ ቆይቶ ወይም በቤተ ክርስቲያኒቱ ዶግማ ሊቃውንቱ መስማማት አቅቶአቸው የመጣ መለያየትም የለም። ፖለቲካና ወንዘኝነት የፈጠሩት ችግር ነው። በመሰረቱ የተለያዩት አባቶች እንጂ ምእመኑም አይደለም። በውጭ ያለው ምእመን በሦስቱም እንዳመቸው ሲገለገል ነው እሚገኘው ። አብዛኛው ካህንም እንዲሁ። እንዲያውም የሚሳለመው ቤተ/ክ ገለልተኛ ይሁን ስደተኛ የማያቅ አሊያም ግድ እማይሰጠው ምእመን ቁጥሩ የትዬለሌ ነው። ዋናው የእርቁ አላማና መንፈስ መሆን ያንድ አዛውንት አባት ወደ መንበሩ መመለሳቸው ሳይሆን ከግንዱ የተለዩትን ወደ ቀደመ ቦታቸው መመለስ ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ ያገር ቤት አባቶች በተደጋጋሚ እዚህ ድረስ በመምጣት ለእርቅና ለቤተ/ክ አንድነት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።ለዚህም ሊመሰገኑ ይገባቸዋል። ያገር ቤት አባቶች ፤የውጭ አባቶች ከኢትዮጵያ የተለየ ሲኖዶስ ማቋቋማቸው፤ ጳጳሳት መሾማቸው በጽኑ ሲቃወሙት ነበር፤ ተወጋግዘዋልም። ነገር ግን ለሰላም ዋጋ መክፈል አስፈላጊ ስለሆነ ይሄን ችላ ብለው የውጭ አባቶችን “ኑ ሁሉን ነገር ለግዜር ይቅር ብለን አብረን አንድ ሲኖዶስ ሆነን ፓትሪያርክ እንምረጥ” እያሉ ነው። ታዲያ የውጭ አባቶችም በበኩላቸው “4ኛው ፓትሪያርክ ወደ መንበራቸው ይመለሱ” የሚለውን አቋም በመተው ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆን ይኖርባቸዋል። የአቋም ሽግሽግ በሌለበት ሁናቴ እርቅ የሚታሰብ አይሆንም። የጎጡን ሳይሆን የአገሩንና የቤተ ክርስቲያኑን ጥቅም እሚያስቀድም ሁሉ በዚህ የቬኦኤ እንተርቪው በድምጣቸው የለየኋቸው ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ ያሉትን ልብ ብሎ ማስተዋል አለበት። አገራችን ውስጥ ያለውን የተበላሸውን ሁሉ ለመለወጥ ለማሻሻል ጠንክረን መታገል አለብን እንጂ ቤተ/ክ ለትርፍ የተቋቋመች ካምፓኒ ትመስል እዚህ እማታሰሩን ከሆነ ውጭ ወስደን እንተክላታለን ሊባል አይገባም። ቤተ/ክ outsourcing አይመለከታትም። ምእመናን በበኩላችን ለቤተ ክርስቲያኑ የሚበጀው ምንድን ነው ብለን ማጤንና ለኢትዮጵያዊ ባህላችን በሚመጥን ቋንቋ ሃሳባችን ማቅረብ እንችላለን ። በርግጥ የማንኛውም ወገን የመፍትሄ ሃሳብ ከፖለቲካዊና የወንዜ ልጅነት እድፍ የፀዳ መሆን ይኖርበታል። ነገር ግን የመጨረሻው ውሳኔ የሲኖዶሱ መሆኑ መቀበል ያስፈልጋል። ሲኖዶስ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበሩ እንዲመለሱ በስደተኛ አባቶች የቀረበውን ሃሳብ ቢስማማበት እሰየው ነበር። ነገር ግን የለም "ለቤተ ክርስቲያኑ የሚበጀው የሁለቱ ሲኖዶስ መዋሃድና በጋር ሆኖ ምርጫ ማካሄድ ነው” ካለ- ሁሉም ወገን ያስደስት አያስደስት ሌላ ጉዳይ ሆኖ እንደ ቤት ከርስቲያን ልጅነታችን ያንኑ መቀበል ተገቢ ነው። ካልሆነ ያገር ቤቱ ሲኖዶስ የሚወስነው ውሳኔ የእኛን አመለካከት የሚደግፍ ሆኖ ሲገኝ ልናሞግሰው ሳይሆን ሲቀር ደግሞ “የመንግስት እጅ አለበት” የምትል ካርድ ልንመዝባቸው አይገባም። የውጭም አባቶች እኮ በዚሁ መንገድ ከሄድን ከወቀሳ ነፃ አይደሉም። የአገር ቤቱ ሲኖዶስ ከመተቸት የሚያሳልፋቸውን ውሳኔዎች ካለበት ሁናቴ ጋራ አገናዝቦ መረዳት ያስፈልጋል። የውሳኔው ሚዛናዊነት እንደየአመለካከቱ ሊለያይ ይችላል። ትልቁ ነጥብ በውጭ ላለው ሲኖዶስ እውቅና መስጠት ነው። ይህ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ሲባል ያገር ቢቱ ሲኖዶስ የዘረጋው የሰላም እጅ እንደ ዋዛ ማየት የለብንም። የፓትሪያርኩ ወደ መንበሩ መመለስ “ቢሆን ጥሩ” ከማለት ውጭ የእርቁ የማእዝን ድንጋይ ሊሆን አይገባውም። እርቅ በመሰረቱ ያንድ ወገን ፍላጎት ማስፈፀሚያ አይደለም-የጋራ አካፋይ ፍለጋ እንጂ። የጋራ አካፋዩም የሁለቱ ሲኖዶሶች ውህደት ነው። የፓትሪያርክ ወደ መንበሩ መመለስ ያለፈውን ስህተት የማረም ጉዳይ ነው ከተባለም ያለፈውን ምእራፍ መዝጋት ያለብን አንዱን ወገን ጥፋተኛ ሌላው ትክክል በማድረግ ሳይሆን እንደ ትላንቱ አባቶቻችን “የሞትንም እኛ የገደልንም እኛ” በሚል መንፈስ ሊሆን ይገባዋል። ፓትሪያርኩን በመመለስ ብቻ ነው ያለፈውን ስህተት ማረም የሚቻለው ማለት ለቤተ/ክ አለማሰብ ነው። ይህ ስህተትን በማረም ላይ ሳይሆን በድል አድራጊነት አሸንፎ የመውጣት ስሜትን ያሳያል። በሁሉም አባቶች ለተፈፀሙ ስህተቶች የተወሰነውን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አይሆንም። ለማጠቃለል አሁን ቤተ ክርስቲያናችን ከተጋረጠባት ፈተና አንጻር ትልቁ ነገር የአባታችን ያቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበሩ የመመለስ ጉዳይ ሳይሆን፤ በውስጥና በውጭ፤ በቆላና በደጋ ያለው ህዝበ ከርስቲያን አንድ የመሆንና ባጠቃላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከገባችበት ቀውስ የሚያወጣት፤ ለማንኛውም አይነት የፖለቲካ ተፅእኖ እማይንበረከክና፤ ታላቅ መንፈሳዊ ጉልበት( Charismatic power) ያለው አንድ ኢትዮጵያዊ ሺኖዳ እማግኘትዋ ላይ ነው። ልብ እንበል! የመንግስት ተፅኖ ለምን ይኖራል ከማለት ለምን ለተፅእኖ እማይንበረከክ እረኛ አባት አጣን ብለን እንጠይቅ። ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ።

Anonymous said...

ክፍል 1

ግን እኛ ስንት ጊዜ ሞኞች፣ ስንት ጊዜ የዋሆች፣ ስንት ጊዜስ ደደቦችስ እንሆናለን?
ከእባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላልን?

መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት "ቂማችንን አንፈታም ዓላማችንንም አንረሳም" ያለውን ንግግር በቤተክርስቲያናችን ላይ ላለፉት 21 የጨለማ ዓመታት ሲያደርስባት የቆየውን መከራ ሁሉ ብናስታውሰው እውነትም ቂማቸውን (ከጣሊያን የወረሱትን) እየተወጡ እንደሆነ ያስመሰክራል።

ባለፉት 21 የጨለማ ዓመታት በቤተክርስቲያናችን ስንቱ መከራ ሲደርስ ቆይቷል፤
- ስንቶቹ ንጹሃን፣ ብጹኣን አባቶች ተሰደዱ? ስንቶቹስ በረቀቀ ሴራ ተገደሉ? ስንቶቹስ ከቤተክርስቲያን ተገለሉ?
- ስንቶቹ ቤተክርስቲያናትና ገዳማት ተቃጠሉ? ስንቱስ ምእመን ተሰየፈ?
- ስንቱ ንዋዬ ቅድሳት ተዘረፈ?
- ስንቱ ሕገ-ቤተክርስቲያን ተሻረ?
- ስንቱ የአብነት ትምህርት ቤት ተዘጋ?
- ስንቱ የተሃድሶ መነኩሴና ሰባኪ ነኝ ባይ ቤተክርስቲያኒቷን ወረረ?
- ስንት ጊዜስ አባ ጳውሎስ ተሃድሶያውያንን ሲሾሙ እና በእነሱ ላይ ሲኖዶስ የሚያስተላልፈውን ውሳኔ አልስማማም እያሉ ድጋፋቸውን ለተሃድሶያውያኑ ሲሰጡ ቆዩ?
- ስንት ጊዜስ የወያኔ ቱባ ባለስልጣኖች የንቀት ስድባቸውን (አቦይ ስብሃትም ጳጳሶቹ አይረቡም መማለትና ቤተክርስቲያኗ ትበታተናለች ብለው ቁርጡን ነግረውናል) እና ቀደም ሲል እነ አቶ ተፈራ ዋልዋ በአደባባይ ዛቻቸውን በቤተክርስቲያናችን ላይ ስንት ጊዜ ነዝተውብናል?

ይህን ሁሉ እያየን፣ እየሰማን፣ እየታዘብን፣ ከንፈራችንን በመምጠጥ ብቻ ኖረናል።

አሁንም በሰላም እርቅ በድርድር (መፍትሄ ከየገኜ እሰየው ግን አይሆንም እንጅ) ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በብሎግ ሳይቶች ወይም በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ ብቻ ወያኔን በማስፈራራት፤ ከወያኔ ምንም ዓይነት በጎ ነገር መጠበቅ የዋህነት ብቻ ሳይሆን ደደብነት ጭምር ነው። ትዕቢተኛ አትበሉኝ እና እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ እንደሚችል ቅንጣት ያክል ጥርጣሬ የለኝም። ነገር ግን በየትኛውም የቅዱሳን ድል እግዚአብሔር ሃይሉን ቢያሳርፍበትም የቅዱሳኑ ተጋድሎ አለበት። እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር ከፍሎ ፈርኦንን ያሰመጠውና እሥራኤላዉያንን ከፈርኦን እጅ ፈልቅቆ እንዲያወጣ ያደረገው በሙሴ አማካይነት ነው። ለእኛም ሕዝባችንን በይፋ ችግሩን አፍረጥርጦ የሚያስረዳ፣ ተነሱ ውጡ ብሎ ከዘመኖቹ ፈርኦኖች ተላቀቁ የሚለን አንድ ሙሴ ያስፈልገናል። ቢያንስ ቢያንስ ምእመኑ እውነቱ ተነግሮት ከልብ የመነጨ እና የመረረ ሐዘን ወይም ጸሎት መደረግ ይኖርበታል።

በአሁኑ ሰዓት የትኛው ቤተክርስቲያን ነው በነፃነት ለቤተክርስቲያናችን አንድነትና ሰላም የምህላ ጸሎት እናድርግ የሚል? ባለፈው ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጀው የምህላ ጸሎት በስነስርዓቱ ተካሂዷል? በየገዳማቱስ ያሉት አባቶች እየተዋከቡና እየታሠሩ ማን ነው ጸሎት አድርሶ ከፈጠሪያችን ምህረትን ሊያሰጠን የሚችል?

ሊያጠፋ የመጣ ምንጊዜም ዓላማው ነውና ያሰበውን ሳያሳካ ለአፍታም ቢሆን አያንቀላፋም።
እኛ ግን፤ በአንዳንድ ብሎጎች ወይም በፌስቡክ ላይ እሮሮ ወይም ተማጽኖ ወይም ዛቻ ስለፃፍን ብቻ ወያኔ ዓላማውን የሚቀይርልን መስሎን ከሆነ፤ አሁንም በድጋሜ ሞኝነት ወይም ደደብነት ነው።

አሁን በየብሎጉ እና በፌስቡክ የሚሰነዘሩት አስተያየቶች አብዛኛው በውጭ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው። በአገር ውስጥ ካለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ ስንቱ ነው የኢንተርኔት አገልግሎት የሚያገኝ? ከዚያ ውስጥ ስንቱ ነው ኦርቶዶክስ? ከዚያ ውስጥ ስንቱ ነው ለእምነቴ ለቤተክርስቲያኔ ያገባኛል ብሎ ለሰማዕትነት የሚበቃ? ይህ ዓይነት ከባድ ፈተና በቤተክርስቲያናችን ላይ ሲጋረጥ በእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ለሚገኘው ምእመን ለምን እውነቱ ፍርጥርጥ ተደርጎ አይነገረውምና ያበጠው አይፈነዳም?

እያንዳንዳችን ለቤተክርስቲያን ፍቅር አለኝ፣ ተቆርቋሪ ነኝ የምንል እስኪ መጀመሪያ እውነት እኔ ለቤተክርስቲያኔ እውነተኛ ፍቅር አለኝ? ወይስ ደንታ ቢስ ነኝ? የእምነቴስ ጽናትስ እስከምን ድረስ ነው? ሰማእት ሆኖ ቤተክርስቲያንን እስከመታደግ ወይስ ከንፈር መጥጦ እስከማለፍ? እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ?

Anonymous said...

Obviously, this is just one sided view! Most of the people who gave comment on VOA are well known Politian, such as Ambassador Imuru Zeleke who is a founder of MORISH AMHARA, Ato Tedla others are of course we know what they will say. VOA needs to be a fair media!!!

Hailu said...

VOA did a good job.

Most agree the only solution is for His Holiness Abune Merkorios to return to his 'menber'.

May God the Almight unite our church.

Anonymous said...

ክፍል - 2

አወ "ለቤተክርስቲያኔ ተቆርቋሪ ነኝ፣ እኔም የቤተክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል" የምንል ከሆነ ደግሞ፤ በውስጣችን ያለውን ፍርሃት እና ራስ ወዳድነት አሽቀንጥረን እንጣለውና፤ ለእምነታችን፣ ለቤተክርስቲያናችን ድምፃችንን ከፍ አድርገን በተግባር እናሰማ። ከሙስሊም ወንድሞቻችን ስለእምነታችን በድፍረት መናገርን እንማር። የይስሙላ እምነት ወይም ሲመቸን አማኝ መሳይ፣ ቤተክርስቲያን ስትበደል ታዛቢ ወይም ከንፈር መጣጭ መሆን ቤተክርስቲያንን ከጥፋት አይታደጋትም።

ስለዚህ ቤተክርስቲያናችንን ለማጥፋት የተጀመረውን ሴራ እኛ አውቀን ካላከሸፍነውና ቤተክርስቲያናችንን ካልተከላከልን፤ ለጥፋቱ የመጀመሪያ ተጠያቂዎች ጥፋት አድራሹ ዓላማውን እያሰካ ያለው ወያኔ ሳይሆን፤ ቤተክርስቲያናችን እንደምትጠፋ እያወቅንና መከላከል እየቻልን ያልተከላከልነው እኛው እናምናለን የምንለው እንሆናለን።

ወያኔ በብልጣብልጥ አካሄዱ ሆድ አደሮችን በመያዝ፣ አንዴ ጠበቅ አንዴ ለቀቅ እያደረገ ምእመኑም ተስፋ ቆርጦ ግዴለሽ እንዲሆን በማድረግ፣ ቤተክርስቲያንን ቢቻለው ማጥፋት፣ ካለዚያም የተሃድሶያውያን የማድረግ ዕቅዱን ደረጃ በደረጃ እያሳካ ነው። አሁንም ቢሆን መጭው የጥምቀት በዓል እስከሚያልፍ ድረስ የከረረ እርምጃ ሳይወስድ ግን ዓላማውን የሚያከሽፉበትን መንገዶች እየተከላከለ ይቆይና የጥምቀት በዓላት ካለፉ በኋላ ጡጫውን ማንሳቱ አይቀሬ ነው።

ስለዚህ አሁን መንግሥትም የተስማማ ወይም ከአቋሙ የረገበ ቢመስል እውነት እንዳይመስላችሁ። የሩቅ የሩቁን ክስተቶች እንተዋቸውና ከዋልድባ ገዳም መታረስ ምን እንማራለን? አንድ አድርገን ብሎግ እንዳስነበበችን "ቦታው የትግራይ ክልላዊ መንግስት አካል እንጂ የአማራ ክልላዊ መንግስት አይደለም ስለዚህ በገዳሙ ላይ ሃሳብ መስጠት የሚችሉት የክልሉ ተወላጅ የሆኑት መነኮሳት እንጂ ማንም አይደለም" ያሉትን እስኪ እናጢነው። መጀመሪያ ወረዳውን ከአማራ ክልል ወደ ትግራይ ወስደው ከለሉ፣ ከዚያ ቦታው የትግራይ እንጅ የአማራ አይደለም በማለት የዘረኝነትን መርዝ በቤተክርስቲያናችን፣ ያውም ዓለም በቃኝ ብለው ባሉት አባቶች መካከል መንዛት ማለት ምን ለማለት ነው? የትግራይ ኦርቶዶክስ አማኞች ገዳሙ እንዲፈርስ ይስማሙበታል ለማለት ነው ወይስ በዘር ሽፋን ድጋፍ ለማሰባሰብ?

ስለዚህ በምንም ነገር ሳይዘናጉ እና ጊዜ ሳያልፍ በእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ለሚገኘው ምእመን እውነቱ ፍርጥርጥ ተደርጎ ይነገረውና፤ የጥምቀት በዓል ሕዝበ ክርስቲያኑ በአንድነት የሚሰባሰብበት ቀን በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ሰው "የቤተክርስቲያኔ ጉዳይ እኔንም ያገባኛል" "ሕገ-ቤተክርስቲያን ይከበር" "ከፓትርያርክ ምርጫ - እርቅና ሰላም ይቅደም" ብለን ድምፃችንን በአንድነት ከፍ አድርገን ማሰማት ይኖርብናል። ይህን ማድረግ ካልቻልን ግን ወደዳችሁም ጠላችሁም በትናንትናው ዕለትም “አቡነ መርቆርዮስ ከሚመለሱ፤ ለምን መንግስቱ ኃይለማርያም ይምጣ አትሉም። አቡመ መርቆሪዮስ ይመለሱ ካላችሁ ትግራይ የራሷን ፓትርያርክ ሾማ የራሷን ሪፐብሊክ ትመሠርታለች” በማለት አባይ ፀሐዬ አሁንም ወያኔ ከእቅዱ ወደ ኋላ እንደማይል አርድተውናል http://www.zehabesha.com/archives/15936 ይመልከቱ። ቀደም ሲልም አቦይ ስብሃት በቅዠት ሳይሆን በእቅዳቸው ላይ ያለውን "ጳጳሳቱ አይረቡም፣ ቤተክርስቲያኒቷ ትበታተናለች" ብለው በድፍረትና በንቀት እቅጩን እንዳረዱን

"እረኞቹ ከተበተኑ መንጋውን ለመበተን ቀላል ይሆናልና፣ለቤተመንግሥት ሕግ የማይጠቀምበትን የእድሜ ገደብ በፓትርያርክ ምርጫ መስፈርት አስገብቶ አባቶችን ከጨዋታ ውጭ አድርጎ ማሰደዱ አይቀሬ ይሆናል። እንወዳታለን የምንላት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የተሃድሶያውያን መፈንጫ ትሆናለች። ወደዳችሁም ጠላችሁም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሚለውን ስም ብቻ ወርሰን እንዳሉትም ከፈቀድን እንታደሳለን ካልፈቀድንም በውጭ አገር ያለነው ብቻ ሳንሆን በአገር ውስጥም የምንኖረው ተበትነን እንቀራለን።

ስለዚህ ይህ ከመሆኑ በፊት የጥምቀት ዕለት ድምፃችንን ከፍ አድርገን በማሰማት ሃይማኖታዊ ግዴታችንን መወጣት ይኖርብናል። እስከ ጥምቀት ድረስ እያንዳንዱ ሰው ለሚያውቀው ሕዝበ ክርስቲያን ይህንን ሃይማኖታዊ ጥሪ ማስተላለፍ እና በቂ መንፈሳዊ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል።

ኦርቶዶክስ ነኝ ያላችሁ - እስኪ እንያችሁ?
ተሃድሶ አንሆንም ያላችሁ - እስኪ እንያችሁ?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)