January 16, 2013

ከዕርቀ ሰላም ይልቅ ለ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ቅድሚያ የሰጠው የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ተስፋዎችን አጨላሚ ሆነ

(ደጀ ሰላም፤ ጥር 8/2005፤ ጃኑዋሪ 16/2013/ PDF) በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና ከመነሻውም በውጪ ተጽዕኖ ሥር የወደቀው የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ እንደተፈራውም ዕርቀ ሰላሙን አሽቀንጥሮ ወርውሮ 6ኛ ፓትርያርክ በመፈረሙ ላይ ጸንቷል። በብፁዕ አቡነ አብርሃም በተነበበው መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው ቅ/ሲኖዶሱ ያደረገው ሙከራ ያልተሳካው በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች ባቀረቧቸውና ከዕርቁ ጋር በማይገናኙ ሌሎች ምክንያቶች የተነሣ ነው። ይህ “ከእርቁ ጋር የማይገናኝ” የተባለው ምክንያት አሜሪካ ያሉ አባቶች የሚያነሧቸው “ፖለቲካዊ ጥያቄዎች” መሆናቸውን ደጀ ሰላም ትረዳለች። በተለይም ለብዙዎቹ የቅ/ሲኖዶስ አባላት የተነገራቸው ምክንያት “አገር አቀፍ ዕርቅ” ይውረድ ይላሉ፤ ውጪ አገር አሉት ፖለቲከኞችም አብረውን ካልገቡ ይላሉ የሚለው መልዕክት ነው።


ዛሬ በቅ/ሲኖዶሱ ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሳይሆን ከሰሞኑ በተለያዩ ዜናዎች ስማቸው ተደጋግሞ ሲጠቀስ በሰነበተው በብፁዕ አቡነ አብርሃም የተነበበው መግለጫ የብዙዎች ምእመናንና ካህናትን ተስፋ እንደሚያጨልምና ወደ ቀቢጸ ተስፋም እንደሚከታቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። ጥበብና አስተዋይነት በጎደለው፣ ከሃይማኖታዊነት ይልቅ ፖለቲካዊ አንድምታው ጎልቶ በሚሰማው በዚህ ውሳኔ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከ20 ዓመታት በኋላ ድጋሚ ልታገኘው ትችል የነበረውን የአንድነት መንፈስ ተኮላሽቷል። ለዚህም ከታዋቂ ሰባኪ ነን ባዮች እስከ አንዳንድ “ልጅግር” ጳጳሳት፣ ተሰሚነት አለን ከሚሉ ጦማርያን እስከ ፖለቲከኞች ያደረጉት ርብርብ በርግጥም ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድ እንዳትሆን የሚሠራው አካል እስከ ደም ጠብታ እንደተዋደቀ አሳይቷል፤ የብዙዎችንም አሰላለፍ በርግጥ ተረድተንበታል። የቤተ ክርስቲያን አምላክ ይፈርዳል!!

አንዳንዶቹ ጳጳሳትና ብሎገሮች እንዳሉት በርግጥ ለጳጳሳቱ ደሞዛቸውን የሚከፍላቸው አሜሪካና አውሮፓ፣ አረብ አገርና በሌሎች ዓለማት በስደት የሚገኘው ምእመን አለመሆኑ ብቻ የሚያስንቀው ከሆነ አገር ቤትም እያለ ጠቀም ያለ ገንዘብ መክፈል የማይችለው ደሃ ምእመን በእነርሱ ዘንድ ሞገስ የለውም ማለት ነው? በዚህ ደሃ ሕዝብ ገንዘብ ቤታቸውን አልሰሩምን? የሚንደላቀቁትስ በዚሁ ደሃ ምእመን ጥሪት አይደለምን? በሌላ ጊዜ ለዕረፍትም ለመዝናናትም የሚሆዱባቸው የአሜሪካና አውሮፓ አገራት ምእመናን አይሰሙ/ አይሰማቸው መስሏቸው ይሆን? ለማንኛውም በዚህ ውሳኔ አንድነምታ ዙሪያ ተከታታይ “ምልከታዎች” ማቅረባችን ይቀጥላል። ደጀ ሰላማውያንም ሐሳባችሁን እንድትሰጡ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።

የዚህን መግለጫ ሙሉ ቃል ከዚህ (PDF) ማንበብ ይቻላል።

41 comments:

Unknown said...

ዕሺ፥በጎ፥ በጄ፥ ይኹን፥ አደርጋለኊ ማለትን ብቻ ሳይኾን፤ እንቢ፥ አሻፈረኝ፥ አልስማማም፥ አልቀበልም፥ አይኾንም፥ አይኹን ማለትንም ታዘናል፦ "ኦሆ በልዎ ለእግዚአብሔር፤ ወእንብየ በልዎ ለጋኔን!" (ያዕ 4፡7)

ይህም በጨዋ ዐማርኛ እንዲህ ማለት ነው፦ "እ[ኽ]ንቢ በል!... እ[ኽ]ንቢ በል!" እንቢታውም ጋኔኑን ብቻ ሳይኾን፤ ጋኔን ያደረበትን ዐላዊ ኹላ ነው።

Anonymous said...

Very sad to here this and let the almighty judge us.

Anonymous said...

This is outright deceptive and misleading statement. The former Prime Minster, who was the highest official of EPDRF forced the Patriarch out of the Church.

The Patriarch knows if he didn’t comply he will be killed (Remember –Mengistu/ Derge killed the Second Patriarch and the bishops at the time they did not raise their voice- they actually collaborated with the Derge to eliminate him.

This time the 4th Patriarch didn’t want to be killed and he knows there won’t be any one to protect or defend him. So he left the country.

The bishops chose or took their order and put illegally Melese Zenawi’s bishop as Patriarch.
God mysteriously took aba Paulos and extended the life of the 4th Patriarch who is now well and alive.

መዝሙረ ዳዊት መዝሙር 2
4 በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።
5 በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።

Psalm 2:4 "He that sitteth in the heavens shall laugh: the LORD shall have them in derision."

12 ኃጢአተኛ ጻድቁን ይመለካከተዋል፥ ጥርሱንም በእርሱ ላይ ያንገጫግጫል።
13 እግዚአብሔር ይሥቅበታል፥ ቀኑ እንደሚደርስ አይቶአልና።
14 ኃጢአተኞች ሰይፋቸውን መዘዙ፥ ቀስታቸውንም ገተሩ ድሀውንና ችግረኛውን ይጥሉ ዘንድ ልበ ቅኖችንም ይወጉ ዘንድ፤
15 ሰይፋቸው ወደ ልባቸው ይግባ፥ ቀስታቸውም ይሰበር።

Psalm 37:13 "The LORD shall laugh at him: for he seeth that his day is coming….."

እነሆ፥ በአፋቸው አሰምተው ይናገራሉ፤ ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ፤ ማን ይሰማል? ይላሉ።
8 አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥ አሕዛብንም ሁሉ ትንቃቸዋለህ።

Anonymous said...

በጣም የሚገርም የሚያሳዝን .. ነው አባቶችን ምን ነካቸው? ምነው ለጊዛዊ ጥቅማጥቅም ተታለሉ? ምነው ክርስቶስን ቢያስቀድሙ? አሁን ምን ብለው ነው አውደ ምሕረት ላይ ቆመው ስለ እርቅ ስለ ሰላም ... የሚያስተምሩት? በጣም እራስ የሚያስደፋ የሚያሳፍር ተግባር ነው አቡነ መርቆርዮስስ ለምን ድምጻቸውን አያሰሙም ይሁሉ የቤተ ክርስቲያን ችግር መሻ እሳቸውና ነፍሳቸውን ይማር አቡነ ጳውሎስ ናቸው ምንአለ በሕይወት ያሉት አባት "ልጆቼ በእኔ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን አትከፈል ለእስከአሁኑም እግዚአብሔር ይቅር ይበለን አንድ እንሁን ..." ቢሉ? ስልጣኑስ ከእንግዲህ ምን ይሰራላቸዋል? መቼም ይህንን ሥራ የሰሩት ማን እንደሆኑ እናውቃለን እግዚአብሔር ይፍረድ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ሆይ ሰማይና ምድርን በዘረጋ በቀራንዮ አደባባይ ለሰው ልጅ ፍቅር ብሎ በተሰቀለው በመድኃኔዓለም ክርስቶስና በድንግል ማርያም ስም ብለው እባክዎ የተለያየችውን ቤተ ክርስቲያን ወደ አንድነት ይመልሱ!! ቀጣዬ ትውልድ ወቀሳ ይዳኑ የእኛንም እንባ ያብሱ አሁንም እርስዎ ዝም ካሉ ቤተ ክርስቲያናችም እስከመቼውም አንድ አትሆንም እባክዎ እባክዎ ለቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ይስሩና ይሙቱ በዙርያዎች ያሉትን ነገረ ሰሪዎች አይስሟቸው በቀራንዮ የተፈጸመውን ፍቅር ይመልከቱ ስለ እመብርሃን በለው ፍቅር ይስሩልን እኛ በቤተ ክርስቲያናችን አባቶች የሚፈጸመው ተግባር በጣም እያሳፈረን ነው ያለው በመናፍቃን ዘንድ እራሳችንን ነው የደፋነው ያፈርነው እባክዎ ከእፍረት ያውጡ ስለ ምዕመናኑ ልጆችዎ ብለው ይሸነፉ ቅዱስ አባታችን ይህች መልእክት በወሬ ደረጃም ቢሆን ትደርሶታለችና እኛም ተስፋ እናደርጋለን እግዚአብሔር ይርዳዎት

Anonymous said...

ከሁሉም የሚያሳዝነው ቤተክርስቲያኗን የሚመሩ አባቶች፣ ትእዛዝ ሊያገለግሉት ከመለኮሱለት አንድ አምላክ ሳይሆን ከፖለቲካ ድርጅት መሆኑ ከምንም በላይ ያሳዝናል። ለማስፈራራት እንደሞከሩትም ድምጻችን በብዙሐን የሚታቀብብን ከሆነ ትግራይ የራሷን ፓትሪያርክ ትመርጣለች እንዳሉት ሁሉ። እረቀሰላምና አንድነት በምንም መልክ እንዳይመጣ ታግለዋል። የፖለቲካው ቀኝ መሪ የሆኑት አቦይ ፀሐዬ አቡነ መርቆሪዎስ ይግቡ ማለት መንግስቱ ሐይለማሪያም ይግባ ማለት ነው ብሏል። ጎበዝ እነዚህ ሰወች ይህችን ቤተክርስቲያንም ሆነ አገር በነሱ መልክ ካልተጓዘች አጥፍተው ቢሄዱ የሚመርጡ ባእዳን ናቸው። ችግሩ ያለው ከነዚህ አገርና ሀይማኖት አጥፊወች ሳይሆን። ከብዙሀኑ አገሬን ሐይማኖቴን የሚለው ክፍል ወላዋይነትና አንድ አለመቆም ነው። ይህን ግልጥ ያለ ወሳኔ ካየ በኋላ ዞሮ የራሱን አባቶች ሲያወግዝ የሚገኘው ምእመን ሀይማኖቱን እየጎዳ መሆኑ አይታወቀውም። ከፊሉ ልክ እንደፖለቲካው ተከፍሎት የካድሬ ስራ የሚተገብር ነው። እዚህ ዳላስ እንዳየሁት፤ በእርቀ ሰላሙ ወቅት ንቡረእዱ እንደ አንድ የሀይማኖት አባት ሳይሆን ለምእመኑ የነበረው አስተያየት እጅግ ትህትና የጎደለው የመንደር ጎረምሳ ይመስል ነበር። ሌላው ቤተ ክርስቲያናችንን ከሁለት መከፈሏ አንሶ ገለልተኛ በሚሉ ወገኖች የሚካሄደው ነው። እንደኔ እነዚህ ከሁለት መሆን የሚፈልጉት የበለጠ ይጎዷታልና ወደ ወያኔው ሲኖዶስ ቢጠቃለሉ መልካም ይሆናል። ለምን ዳር ለዳር ይሄዳሉ? ከከባድ ይቅርታ ጋር ነው ቤተክርስቲያናችን በወያኔ የፖለቲካና ደህንነት መመራቷን በግልጽ ስለታዬ ነው ይህን ቃል የጨመርሁት። ባለፈው ሰሞን አቶ ስብሐት ነጋ የሚባሉት ትክለ ክፉ ሰው "ኦርቶዶክስና የአማራ ጊዜ አብቅቷል" ማለታቸው የሚታወስ ስለሆነ። የዛሬው ተግባር ሊገርመን አይገባም። ለሁሉም እባካችሁ በአንድ እንቁም። ሌላው ቢቀር ምንም ያህል ጊዜ ቢረዝም የአገርና የእምነታችን ምሰሶ የሆነችው ቅድስት ቤተክርስቲያን አንድ መሆኗ የማይቀር ነው።

Unknown said...

it's ok!

Anonymous said...

We don't have earthly holy fathers, we don't have spiritual fathers, we don't have monks,we don't have fathers like Abune Peteros and Abune Tewoflos any more.Ethiopia,now raise and stretch your hands not with happiness but with sadness,not to praise but to cry like Rachel weeping for her children because your children have no father and the holy synod converted to Judah. Tell to El Shaddai,He has strong arms to crush these evil doers.

Anonymous said...

'Seneger New' alech alu!!
A few weeks ago, i posted a comment about the determination of the TPLF lead government to divide us into peaces. If TPLF wants something, it'll happen whether we like it or not. Reason, TPLF knew us very well that we just talk, start creating noise here and there for a while where TPLF knew how to pass such very little wave of emotional talks and oppositions, just borrow elephant ear and ignore everything. Then our oppositions and even those little noise that we make for a week or so will evaporate sharply. TPLF knows us we are just paper (this time blog) talkers not action takers. Take a look at how money/(promised fame) can change anybody and totally forget what he/she used to believed in or said before. So, fellow EOTCan if we want change we need to be united sustainably and make deep down prying to the Almighty to bring peace and unification to our church we all love. (Tseleyu WeAhati BeteKerstian)

Anonymous said...

You guys should post all the commit people sending if you consider yourelf as journalism whatever it. that is what true journalist does. sometime I am have problems where you guys stand. or you start like Abun Abraham playing double game?

Anonymous said...

we all christians reject their decision since it is political decision.If it was spiritual it can conside with peace and unity.But not.therefore we shall not accept the coming new patriaric.He can only lead his supporters.

Anonymous said...

ለመሆኑ ይህ ሁሉ መጠፎ ታሪክ ሲፈፀም እያዩ እየሰሙ "ጆሮ ዳባ ልበስ አልናገር ምንቸገረኝ የኦርቶዶክስ እምነት ቢከፋፈል ሕዝቡ ቢበተን ... ብለው ዝም ያሉት አቡነ መርቆርዮስ በሕይወት አሉ? ምን ያህል ለመንጋው የማይራሩ አባት ናቸው ድምጻቸውን ያላሰሙት? እንደጽድቅ ይቆጠርላቸው ይሆን? ምን አለ አሁን ላልታሰረው ወደ ፊት ለሚታሰረው አንደበታቸውን አንስተወ "ልጆቼ ይብቃ ይቅር እንባባል ሀይማኖታችን እንጠብቅ ለሀገራችንም በአንድነት እንጸልይ... አይሉም? እንዲህ ከቀጠለ በእግዚአብሔርም በታሪክም ተወቃሽነት አለ አሁን እግዚአብሔር የሰጠው ጊዜ ነው ይጠቀሙበት አንድ ቀን ብቅ ይበሉና መንፈስ ቅዱስ ያሳሰብዎት ይናገረ እባክዎ የአዲስ አበባውን ሲኖዶስ የሚያሳፍር ተግባር ይፈጽሙ በጨበጡት መስቀል ብለው!!! ሥልጣንም አሁን ምንም የሚጠቅም አይደለም እባክዎ አባታችን የሰላም ድምጽ ያሰሙ መንጋውን አውሬ ሊበላው ነው ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ተሰፋ አጥተው ወዲያ ወዲህ የሚሉትን የአባ ሐብተ ማርያም (አባ መልከጼዴቅን) ነገር አይስሙ በትክክል እሳቸው ከኢትዮጵያ ሲወጡ የተናገሩትን ነገር በተግባር ነው ያዋሉት " የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ለሁለት ነው የምከፍላት...ብለው ነው የወጡት ማስረጃ አለ እሳቸውም ቢጠየቁ ያምናለሁ እንዳሉትም ለሁለት ሳይሆን ለሶስት ከፈሏት በጣም የሚያሳዝን ተግባር ሰው በስተ እርጅናው እግዚአብሔርን መንገድ ነበር መከተል ያለበት ግን ይህው እኛ በእነሱ ተግባር አፈርን ያስቡበት

Anonymous said...

ትክክለኛ ዉሳኔ ለመንደርተኝነትና ለፖለቲካ ስሜታቸዉ አይደል እንዴ በዉጭ ሃገር ሲኖዶስ ብለዉ ቤ/ክ የከፈሏት ከነኝህ አባቶች ማን ተከሰሰ ማን ተወቀሰ ከነሱ ጋር ያለዉ በዉጭ የሚኖር ወገኔ በተለያየ ተጽኖ ሃገር ዉስጥ በሰላም የሚኖረዉን ምእመንን የሚያደናግረዉ በዚሁ በነሱ በፖለቲካና በመንደር መንፈስ እያሰበ ነዉ በእዉነት ይህ ጥያቄ ከሌላቸዉ ለምንድነዉ ቢያርባቸዉም ቢመራቸዉም ስለቤ/ክ አንድነት በለዉ ለምንወደ ሃገር አይገቡም መቼም መንግስት የፈለገ አደረገ እንኳን ቢባል አባቶች ቤ/ክ ጥለዋት ይሰደዱ አይባልም እና የእምዬን ወደ አብዬ ሆነ እንጂ በዘርና በፖለቲካ ቤ/ክ ችግር ዉስጥ የከተቷት ዉጭ ሃገር ባሉት ይብሳል

Anonymous said...

Expected news from TPLF. Most racist, stubborn, narrow minded and short sighted organization.

Expected - because we know their inablity and unwillingness to learn from mistakes

http://www.ethiotube.net/video/24269/ETV-News--Ethiopian-Orthodox-Synod-says-could-not-come-to-in-agreement-with-the-ETOC-Synod-in-America--January-16-201

Lie after lie ....huhhhhh

Unknown said...

ለመሆኑ ከላይ ማንነታችሁን በሥራችሁ መደበቅ ባትችሉም ስማችሁን ደብቃችሁ የምትጽፉት ወገኖች የሚያስብ ህሊና ይኖራችሁ ይሆን ? እንዲያው ክርስትናችሁ ይቅርና እንደሰው ታስባላችሁ ? ማነው ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከ አሁኑ እየጣሰ ያለው ? ማን ነው በመንደርተኛነት ተደራጅቶ የፖለቲካ ሥልጣን ይዞ የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘር ከፋፍሎ ጳጳሳትን ሳይቀር በዘረኛነት መርዝ መርዞ እየበጠበጠን ያለው ? አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ቅዱስ ሲኖዶስ አለ ማለት ይቻላል ? ጳጳሳቱን ብፁአን ብለን የምንጠራቸው እየሆኑ ነው ? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ምን እንዲሉ ነው የምትፈልጉት ? ለፈጣሪያቸው አቤት እያሉ በግዞት ሁነው ከመንገር ሌላ ምንም ማድረግ አይችሉም። ለቅድስት ሀጋራቸውና ለሕዝባቸው ካሉበት ሁነው ይጽልያሉ። ለበደለኞቹም እራሱ እግዚአብሔር ፍርዱን እየሰጠ ቅዱስ አባታችንም ሆኑ እኛ ዐይናችን እያየ ነው። ገናም ይቀጥላል። ሌላ ምንም የሚደረግ ነገር የለም። በውጭ ያለው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱስ ፓትርያርኩ እየተመራ ሥራውን ይሠራል። ሰው የሆነው ሁሉ ማለፉ የማይቀር ነውና በሚያልፉበት ጊዜም ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ከአባላቱ መካከል አንዱን አባት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት መርጦ ይሾማል። አገራችን ኢትዮጵያ ነጻነቱዋን በምትቀዳጅበት ጊዜ ይሄው ሕጋዊው ፓትርያርክና ሲኖዶስ ወደ መንበሩ ይመለሳሉ። ይህ ደግሞ እሩቅ አይሆንም። እስከዚያው ድረስ ግን እነ አቶ ዐባይ ፀሐዬ የሃገር ቤቱን ቤተ ክርስቲያን እየገዙት ይቆያሉ። እኛ ግን የነሱን ሲኖዶስ የክስዮን ማኅበር አያልን እንጠራው እንደሆን እንጅ እግዚአብሔር እራሱ የሚጠራበት ቅዱስ የሚለውን ስም አንሠጠውም። ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስን እንደመስደብ ስለሚቆጠርብን። ገለልተኛ ሁነው የቆዩትም እርግጠኛ ነይ በሕጋዊው ሲኖዶስ አመራር ስር ይሆናሉ። ከዚህ የበለጠ ምንም ከሃገር ቤቱ አገዛዝ የሚጠብቁት ነገር አይኖርምና ! ባገር ውስጥም አሁን እነ አባይ ፀሐዬ የሚሾሙትን ''ፓትርያርክ '' አባቴ ብለው ከልብ እንደማይቀበሉት እርግጠኛ ሁኖ መናገር ይቻላል። ከአባ ጳውሎስ የከፋ ሕገ ወጥና የመንግሥት ሹመኛ ሁኖ የሚታይ ሰው እንደሚሆን መገመት ነቢይነትን አይጠይቅም። በዚህ ድርጊት ያዘናችሁ ፥ ይሆናል ብላችሁ በቅን ልቦና ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ስትጥሩ የነበራችሁ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆችም ተስፋ አትቁረጡ ። ምንአልባትም እግዚአብሔር ራሱ ያሰበው መልካም ነገር ሁኖ ይሆናል። አሁን ከመቸውም በበለጠ ማን ምን እንደሆነ ፥ ማለት ማን ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት መስፈን ከልብ እንደሚፈልግና ማን ደግሞ በአስመሳይነትና አታላይነት ሲጓዝ እንደቆየ ግልጽ የሆነልን ጊዜ አሁን ነው። ''በሥራ ፍሬአቸው ታውቋችው አላችሁ '' ብሏልና ። አይዞን እንበርታ ነው የምለው!ደጀ ሰላምም በያዘችው ቀጥተኛ መንግድ መጓዝዋን መቀጠል አለባት። እኛም ከጎኗ ሁነን እርምጃችን እንቀጥላለን። ሁላችንም አብረን ከቃል ኪዳኗ ምድር እንገባለን !!!!

Hailu said...

This is a non-sense and devilish act. I don't think a drop of any spirituality is left in these people's heart. As they have darkened our hope of seeing a united Orthodox Church, may the Almighty also vanish in front of their eyes all the earthly wealth, fame and authority they hope for.

Oh God! How can we call these people bishops if they fear AbayTsehaye and not the God they are supposed to serve?

We shall never accept or call their 6th cadre as a patriarch. Never.He will be yet another government operative we shall despise him as a curse on Our Church.

May God help you my beloved Orthodox Church. May God help you!

Dear fellow Orthodox Christians, please never deviate from your righteous Orthodox faith because of this political decision. Stay true Orthodox Christian by heart. The God we trust shall show us His Justice!

May God help you my beloved Orthodox Church. May God help you!


Tekle said...


YET ANOTHER FATEFUL DAY FOR MORTHER ORTHODOX CHURCH.

A DAY WHEN THOSE WHO ARE ENTRURSTED TO SAFEGAURD HER BETRAYED HER IN A BIG BIG WAY.

I AM LONGING FOR A RIGHTEOUS PERSON.

MAY GOD SHOW US THE WAY.

talker said...

Stop pointing your fingers at our fathers. There is nothing wrong with the decision of choosing the next Patriarch, no laws are broken. Who here is willing to die for that they believe? If you believe they are wrong, then leave everything you have and go protest. In addition, this is not a political move, a political move is like what "Hailu" wants, the reinstalment of 4 Patriarch, that is purely political, that is to say man made, and its wishful thinking.
The diaspora is full of Ethiopians who are full of it! They talk the talk but cannot walk the walk, just like me :) I think 90 percent of us belong to Amanuel hospital. We make baseless accusations. We call ourselves Orthodox but talk like pentes which is to mean stuff no one understands...we just talk and talk and talk...just like me, no fruit. Igzio.

Anonymous said...

ቅዱስ ሴኖዶስ እውነቱ ይህ ስለሆነ አሁን ወደ ፮ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ነው የምንሄደው አለ። ታዲያ አቡነ መርቆሬወስ ለምንድን ነው ለሕዝብ እውነቱን መናገር ያቃታቸው ምናልባት እውነቱ ይዅው የሀገር ቤቱ ሴኖዶስ ያለው ስለሆነ ይሆናል።
ታዲያ ሌላ ምን ይሆናል፣ ማንን ይፈራሉ፣ የሚኖሩት የመናገር ነጻነት በሚከበርበት ሀገር ነው፤ ከእግዚአብሔር ሌላ አለቃ አላቸው ብየ አላምንም። መንግሥት ገልብጦ ወደ ሀገር ቤት ለመግባት መሞከር በመንፈሳዊ ስልጣን መታሰብ የለበትም፤ ለሀገርና ለሕዝብ አይጠቅምም።

Anonymous said...

የአራተኛው ፓትሪያርክ ወደ መንበሩ መመለስ እማይቻል መሆኑ ሲኖዶስ ወስኖአል። የሰጠው አመክንዮ በርግጥ አከራካሪ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሲኖዶስ የሚመራው በመንፈስ ቅዱስ ብለን የምናምን ኦርቶዶክሳውያን ውሳኔውን በፀጋ ከመቀበል ውጭ አማራጭ የለንም። አንቀበልም እሚሉ ይኖራሉ እነሱ ግን አብዮታውያን እንጂ ክርስቲያኖች አይባሉም። ይሄ ቤተ ክርስቲያን እንጂ ትግል ሜዳ አይደለም “በፀሎታችን!” እንጂ “በትግላችን!” ቦታ የለውም። ምእመናን የሲኖዶስ ስልጣን መሻማት አንችልም። ከአቡነ ጳውሎስ ህልፈት ወዲህ በዚህ ጉዳይ ብዙ ተፅፎአል ብዙም ተብሎአል። “ቦ ጊዜ ለኩሉ” ነውና አሁን ልናደርገው እሚገባን በውጭ ያሉ አባቶች ጥሪውን ተቀብለው ካገር ቤቱ ሲኖዶስ ጋር በመዋሃድ አዲስ ፓትሪያርክ እንዲመርጡ መማፀን ፤ማግባባት ፤ወይም በፈረንጆቹ አነጋገር ሎቢ ማረግ ነው እሚጠበቅብን። አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበሩ እንዲመለሱ እሚወተውቱ ወገኖች በዚህ ውሳኔ እርግጥ ይከፋሉ። ለምን ሲኖዶስ ድምጣችንን አልሰማም እንደሚሉም የተረጋገጠ ነው። ነገር ግን አርቀው ማሰብ አለባቸው። ምመናን ዋናው ጉዳያቸው የቤተ/ክ ህልውናና እድገት ነው። የቤተ/ክ ስራትና ትውፊት መጠበቅ ነው። ምንም የዶግማ ልዩነት ሳይኖር በወንበር ምክንያት ሁለት ሲኖዶስ ሊኖረን አይገባም። ያገር ቤት አባቶች ባሁኑ መግለጫቸው እንዳስቀመጡት “የጥንቱ አባቶቻችን አትናቴዎስም ዲዮስቆሮስም ዮሃንስ አፈወርቅም ተሰደዋል ነገር ግን አንዳቸውም በሄዱበት ሲኖዶስን አላቋቋሙም” ብለዋል። ይህ ሐቅ ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሐይሌም ለረጅም ዘመን ሲሞግቱበት የነበረ ነው። በዝህ በኩል እነ አባ መልከፄዴቅ ደግ አላረጉም። በተፈጠረው ልዩነት ምክንያት አሜሪካ ቢሰደዱ ችግር አልነበረበትም ነገር ግን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር በህይወት እያለች ሌላ ሲኖዶስ ማቋቋማቸው ቤተ ክርስቲያኒቱን በድለዋል። አሁን አገራቸው እሚክሱበት ጊዜ ነው። በጌታ ወንዶሞቻቸው ከሆኑት ያገር ቤት አባቶች ፍቅርና አንድነት መስርተው፤ የተበላሸውን ነገር አሁን በሕይወት እያሉ አቅንተው ቢያልፉ ይሻላቸዋል። በታሪክም ተወቃሽ አይሆኑም። አገራችን በመልካ ምድራዊ አቀማመጥዋ፤ ደግ በእማይመኙላት መከበብዋ በታሪክ ያስከፈላት ዋጋ እምናውቀው ነው። አሁን ደግም ከግራ ከቀኝ ዶላር ኪሳቸው በሞላ መናፍቃን እና አክራሪዎች እየደረስባት ያለው ችግር ቀላል አይደለም። መጪውን ጊዜም ምን ይዞልን እንደሚመጣ አንድ እግዜር ነው እሚያውቀው ምልክቶቹ ግን አይስፈሩም አይባልም። ታዲያ በዚህ ዘመን በውጭም በውስጥም ያለን የተዋህዶ ልጆች በህብረት ልንቆም ይገባል።

Anonymous said...

Ben

ጥያቄ፡አለኝ? እውን፡ክርስቲያን፡ነን፡ወይስ፡የይስሙላ?

እውነተኞች፡ከሆንን፡ሁላችንም፡በአንድነት፡መንፈስ፡ተነስተን፡ይህን፡ክፉ፡መንፈስ፡እንቃወም፡፡አለበለዚያ፡መጪው፡ዘመን፡በጣም፡ያስፈራል፡፡
ጌታችን፡ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡እንዳስተማረን፡የተከፋፈለ፡መንግስት፡አይጸናም፡ነውና፡ለሃይማኖታችን፡መጥፋት፡በር፡እንዳይከፍቱብን፡አጥብቀን፡ልንታገለው፡ይገባል፡፡
መሰረታዊው፡መርሆ፡ሊሆነን፡የሚገባው፡-"የቤተ ክርስቲያን፡ወይም፡የምዕመናን፡አንድነት፡ሳይኖር፡በውጭም፡በሃገር፡ውስጥም፡ፓትሪያርክ፡የሚባል፡መኖር፡የለበትም፡ሰላም፡በቤተ-ክርስቲያን፡ከሰፈነ፡በኋላ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡መሪነት፡ወደ፡ፓትሪያርክ፡ምርጫ፡መኬድ፡ይኖርበታል"

ይህንን፡ለማድረግ፡እግዚዓብሄር፡ይርዳን፡፡

Anonymous said...

EPRDF knows how much ur determination and commitment… full of cowards.

Anonymous said...

እነዚህ አባቶች በህዝብ ሃብት አይደል የሚንደላቀቁት ለምንድን ነው በቃቹህ የማንላቸው እስከዛሬ ከጥንት አባቶቻችን የወረስነውን ሃብት ለብቻቸው ካለማንም ሃይ ባይነት ሲበሉና ሲንደላቀቁ (ቤተክርስቲያናችን ከያዘቻቸው መሬትና ከተገነቡቡት ህንጻዎች የሚገኘው ገቢ ማን ኦዲት አርጎት ያውቃል) አልበቃ ብሎአቸው ከተራው ህብረተሰባችንንም የግንባታና የተለያዩ ምክንያቶች እየሰጡ ሲበሉ ኑረው አሁን ከፖለቲከኞች ጋር መሆናቸው በጣም ያሳዝናል፡፡ አረ!!! ፖለቲከኛ ጳጳሳት ቆባቹህን አውልቁና የትግላችሁን ባርኔጣ አድርጉ፡፡ እውነተኛ እምነትና አማኝ በዚህ ጊዜ ነው የሚፈተነው

Solomon said...

በበኩሌ በአቡነ መርቆሪዎስ ላይ አንዳንድ የሀይማኖት ነቀፋ ያለባቸውን ሰዎች ሁሉ መደበቂያ እንዲያገኙ በማድረጋቸው ቤተክርስቲያኗን ጎድተዋል የሚል ቅሬታ ቢኖረኝም በርሳቸው በኩል ግን በዚህ ባሳለፍነው ረጅም ጊዜ አስችሏቸው ዝምታን መምረጣቸው ከሚያስደምማቸው አንዱ ነኝ። በዛሬ ጊዜ በየጥቅሙና በየዘሩ ተከፋፍሎ 'እኔ ልሰማ' የሚለው ጳጳስ በበዛበት ጊዜ አቡነ መርቆሪዎስ ሁሉን አስችሏቸው ዝምታን መምረጣቸው የእግዚአብሔር ጸጋ ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? እርሳቸው በዚህ አይነት ትእግስት፣ አርምሞና ዝምታ ለዓመታት ተቀምጠው እያለ የ"አዲስ አበባው ሲኖዶስ" መግለጫ ዛሬ የርሳቸውን ስም በማብጠልጠል የጻፈውን ስመለከት እርሳቸውን ይበልጥ እንዳከብራቸው አድርጎኛል። ሐዋርያ መሆን ማለት ከዚህ የተለየ አይመስለኝም። ይህ በዚህ እንዳለ መንግሥትና በቤተክርስቲያን ውስጥ የተሰገሰጉ የመንግስት ካድሬዎች በየመድረኩ እየተመሳሰሉ እየገቡ አቡነ መርቆሪዎስን እንዲናገሩ መገፋፋታቸው ያስገርመኛል። የሰይጣን የተንኮል ወጥመድ አድርጌም እወስደዋለሁ። ሁሉን ነገር የሚያመጣው ከዚያም የሚመልሰው ያው መንግሥትና ካድሬዎቹ በሆኑበት ሁኔታ እርሳቸው ምን እንዲሉ ነው የሚፈለገው? አንድ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደርሳቸው ፓትሪያርክ ለመሆን የበቃ ሰውስ በራሱ ፈቃድ 'እግዚአብሔርም ሕዝብም ቢፈልገኝ የፓትሪያርክነቱን ወንበር አልወስድም' የማለት መብትስ አለው ወይ? አልፈልግም ቢሉም አሁን እየሆነ ካለው ሁኔታ ጋራ የሚቀበላቸውም የለም። 'መንግሥት ጠንቸኛ ሆኖብን የእግዚአብሔርን ሳይሆን የስጋን ሥራ እንድንሠራ ስላደረገን እርስዎ ያን ተቀብለው ስልጣኑን አልፈልገውም ይበሉ' ማለትስ ተገቢ ነው? ይህን ቢቀበሉ እርሳቸውንስ የኀጢያቱ ተባባሪ አያደርጋቸውም? ይህ የክርስቲያን ጥያቄ ሳይሆን ክርስትና ዞሮበት የማያውቅ ሰው ጥያቄ መሆኑ በዚህ ይታወቃል። የርሳቸውን ጸሎትና ዝምታ፣ የምእመናንን ለቅሶና ዋይታ፣ የገዳማውያንን ስደትና መንከራተት አይቶ ጆሮን ጭው በሚያሰኘው በራሱ መንገድ እግዚአብሔር መልስ እንደሚሰጠን ቅንጣት መጠራጠር አያስፈልግም።

Anonymous said...

አባቶች ያመላከታችሁን አድርጋችኋል፤ እግዚአብሔር አሁንም እስከመጨረሻው ከእናንተ ጋር ይሁን

ካንሳስ

tersit said...

እስቲ እኛ ዝም እንበል እና እሱ አይስራ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

Anonymous said...

dear yetewahedo lejoche,

today my heart is broken. when i see abune abrehame on the tv screen, i was ashamed. where is the courage he showed us when he was in USA. was it for fake? it is hypocrisy, abune Abrehame seriously. i felt that and i said to myself Abune Aberham and Colonel Teka tulu, who was reading the derge's paper infront of Haileselase, are the same. no doubt about it. it is shame on you our fathers!!!!!

Anonymous said...

dear yetewahedo lejoche,

today my heart is broken. when i see abune abrehame on the tv screen, i was ashamed. where is the courage he showed us when he was in USA. was it for fake? it is hypocrisy, abune Abrehame seriously. i felt that and i said to myself Abune Aberham and Colonel Teka tulu, who was reading the derge's paper infront of Haileselase, are the same. no doubt about it. it is shame on you our fathers!!!!! it is outrageous!!! you are serving the mission of Christ and Holy church. you are not welcome to America anymore. you are betrayal us. you don't have any morality to tell us to do the right thing. History will judge you.
those who are residing in the North America, especially Aba melketsedik, congratulation for dissecting our holy church into two. i am sure you are the happiest person on earth at this moment. your mission is accomplished. you are the one kidnapped the holy father and are holding as a hostage him not tho tell us the truth what happened twenty years ago. history and God judge you till the end of the world.
you and your followers have begun worshiping in ethnicity and nufake. now our church is in wrong direction. you gave us to the enemy of our church and country.
shame on all of you you .

Anonymous said...

ዕሺ፥በጎ፥ በጄ፥ ይኹን፥ አደርጋለኊ ማለትን ብቻ ሳይኾን፤ እንቢ፥ አሻፈረኝ፥ አልስማማም፥ አልቀበልም፥ አይኾንም፥ አይኹን ማለትንም ታዘናል፦ "ኦሆ በልዎ ለእግዚአብሔር፤ ወእንብየ በልዎ ለጋኔን!" (ያዕ 4፡7)

እውነተኞች፡ከሆንን፡ሁላችንም፡በአንድነት፡መንፈስ፡ተነስተን፡ይህን፡ክፉ፡መንፈስ፡እንቃወም፡፡አለበለዚያ፡መጪው፡ዘመን፡በጣም፡ያስፈራል፡፡
ጌታችን፡ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡እንዳስተማረን፡የተከፋፈለ፡መንግስት፡አይጸናም፡ነውና፡ለሃይማኖታችን፡መጥፋት፡በር፡እንዳይከፍቱብን፡አጥብቀን፡ልንታገለው፡ይገባል፡፡
መሰረታዊው፡መርሆ፡ሊሆነን፡የሚገባው፡-"የቤተ ክርስቲያን፡ወይም፡የምዕመናን፡አንድነት፡ሳይኖር፡በውጭም፡በሃገር፡ውስጥም፡ፓትሪያርክ፡የሚባል፡መኖር፡የለበትም፡ሰላም፡በቤተ-ክርስቲያን፡ከሰፈነ፡በኋላ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡መሪነት፡ወደ፡ፓትሪያርክ፡ምርጫ፡መኬድ፡ይኖርበታል"

ይህንን፡ለማድረግ፡እግዚዓብሄር፡ይርዳን፡፡

Anonymous said...

why did not u post the full original document????????? why did you edit it???????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????

Anonymous said...

Seweyew, mejemeriya bedenb lemanbeb moker. የዚህን መግለጫ ሙሉ ቃል ከዚህ (in PDF https://docs.google.com/file/d/0B5ikXekolDC4aDQ5WUlTQTdyTkE/edit) ማንበብ ይቻላል።
Yemil Qal alayehem. Yejib Chekul honk.

Anonymous said...

Abetu Medhanite alem hoy kibrihn Gilets! Emebetie hoy Techenqenalna dreshilin!!!Amen.

Anonymous said...

በአሁኑ ወቅት በተፈጠረ ውኔታ አንዳንድ አስተያየቶች እውነታው ሳያገናዝቡ በጭፍን ተቃውሞን ብቻ ስለሚያስተጋቡ የሚከተለውን እንድጽፍ አነሳሳኝ።-

ስለአለፉት 20 አመታት፦
+ ወደዋላ ተመልሰን አቡነ መርቆሪዎስ እንዴት ከፓትሪያርክነት እንደተለዩ መማገት የለብንም፤ ሆኖም ግን የተለያዩ አስተያየቶች መልሰው በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ስለሚያጠነጥኑ ከእውነታዎቹ በመነሳት የሚከተለውን ማለት ፈቀድኩ። አዎን በታምራት ላይኔ(በመንግስት-"በወያኔ") ተጽኖ የቤተክርስቲያኗ በጀት ከመንግስት እንዲለቀቅ ሲባል አሁን ከሳቸው ጋር ያሉት ጭምር ተስማምተው ፕትርክናውን "እንዳስረከቡ " የወቅቱን መረጃ ያዩ ወገኖች የሚተነትኑት ጉዳይ ነው። ፓትሪያርክነት ደግሞ መንጋን የመጠመቅ ስራ ስለወነ፤ እንደዙፋን አንዴ እሺ እያሉ የሚለቁት ሌላ ጊዜ ደግሞ የሚናፍቁት ወንበር አይደለም። እውነተኛ የመንጋ ጠባቂ ነፍሱን ስለልጆቹ ነፍሱን አሳልፎ ይሰጣል እንጂ እያወቀ ለቤተክርስቲያን መከፈል ምክንያት አይወንም። (ማንያወቃል አባታችን ከ20 አመት በፊት ስለቤተክርስትያን ብለው ፓትራሪክነታቸውን አሳልፈው ሰጥተውስ ቢዎን)።

ከነዚህና ከሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ ወደመንበራቸው ይመለሱ የሚለው ሙግት፤ እውነታዎችን ያላገንዘበ ለቤተክርስቲያን ያለወገነ ጭፍን አመለከከት ነው።

ስለአሁኑ ወቅት፦
ከቀናት በፊት ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነው ወሳኔ እውነታውን ያገናዘበ ይመስላል ምክንያቱም በውጭ ያሉት አባቶችን ወደ ሂደቱ አስገብቶ አብሮ የሚቀጥለውን አባት ለመምረጥ የወሰነ ስለወነ። ለቤተክርስቲያን የሚያስቡ ወገኖች ይህ ወሳኔ የሰላሙን ሂደት ይበልጥ የሚያጠናክረው እንደወነ ይገነዘባሉ። እናም በውጭ ያሉ አባቶች ያለፈው አልፎአል ብለው ለቤተክርስትያን ቅን መሪ እግዚያብሄር እንዲሰጥ ከአገር ቤት አባቶች ጋር አብረው ለመስራት መነሳት አለባቸው።

ስለወደፊቱ፡-
ቤተክርስቲያን ከአሁን በዋላ የሚያስፈልጋት ዘመኑን የዋጀ በሁለት በኩል የተሳለ የአለምና የአካባቢያችንን ሁለንተናዊ ሁኔታ የተረዳ ፤የቤተክርስቲያንን ተልእኮ የማስፈጸም እና የማስተዳደር ጸጋ ያለው ቅን መንፈሳዊ አባት ነው። ስለወነም ዘር፤ቀበሌ፤አካባቢ በክርስትያኖች ዘንድ ቦታ ሊኖራቸው አይገባም።

የማይረባ ከንቱ፤ ሃይላችንን ያባከነ ያለፉት 20 አመታት ትርፍ የሌለው ክርክር ከእንግዲ ወዲህ ሊቆም ይገባል። ከማንም ወገን ይሁኑ ዘረኞችን እና ፖለቲከኞችን ይብቃቹ፤ ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ ወንጌል ሜዳ ነች ልንላቸው ይገባል።

እስቲ ከግብጽ ቤተክርስቲያን እንማር እንሱ ከአፍሪካ እስከ ላቲን አሜሪካ ለሰው ዘር ሁሉ መዳን ብለው ይሰራሉ ። እኛ ግን በሰሜን አሜሪካ ጠቅምጠን ከቀዬአንችን ያለውን ሰው እየፈለግን እንቆጥራለን፤ እንሾማለን ። በአንድ ወቅት በአንድ የውጭ ብሎግ ላይ አንዲት አፍሪካዊት ለምን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያ ሃዋሪያዊ ተልእኮ ለአፍሪካዊያን ወንደሞቻችን እንደማታደርስ መጠየቋን ማንቤን አስታወሳለው። በእውነት ግን መቼ ነው የኬንያ፤ የሱዳን፤የዛየር፤የጋና፤የጀማይካ... ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት እንዲቋቋሙ የምንረዳውና ሃዋርዊ ተለኮ የምናደርገውስ? ጌታ ያለን እኮ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በስሜ እያስተማራቹ ..እያሳመናቹ...እያጠመቃቹ ደቀምዛሙርቴ አድርጉ ነው። አንድ አባት ለምን መንበር ላይ አልተቀመጡም እያልን ዋናውን የክርስትና አላማ እየረሳን እንዳይሆን መንጠንቀቅ አለብን።
እስቲ አዲስ አበባ(ኢትዬጵያ)ስትሄዱየ አህዛብ የአምልኮት ስፍራዎችን እንዴት አዳዲስ እንደወኑ ተመልከቱ፤ መርካቶም ሂዱና ማን ንግዱን እንደትቆጣተረው፤ ስንትም ክርስቶስንና ወገኖቹን የሚሰድብም መጻፍት ገበያ ላይ እንዳለ አስተውሉ። ከአዋሳ እስከ ላንጋኖ(ሶደሬ) ፤ ለምን ቤተክርስቲያን እንደሌለ ግን በሳውዳረቢያ ቋንቋ ብቻ ደጃቸው ላይ የተጻፈባቸው ብዙ ህንጻዎች መንገድ ዳር እዳቆጠቆጡ እዩ። ባህርዳርም እንደገባቹ ቅ.ጊዮርጊስ ቤ/ክ እስከምትደርሱ ስንት አዳዲስ የአህዛብ ህንጻዎች እንዳሉ ተመልከቱ። ለምንስ ባላፉት 20 አመታት የቤተክርስቲያ አባላት ቁጥር(በመቶኛ) ቀነሰ ብላቹ እራሳቹን ጠይቁ? ከነዚ ሁኔታዎች የምንረዳው፤ ጊዜው፦ የቤተክርስቲያን ልጆች ተባብረው በፍቅር ከመቼውም ይልቅ የሚሰሩበት እንጂ አንድ አባት ለምን መንበር ላይ አልተቀመጡም ብሎ የቤተክርስቲያ ሃይል የሚባክነበት አይደለም።

ሃዋሪያው ቅ. ጳውሎስ በአንድ ወቅት እንዲ አለ... በጠላቶች ፈተና...በሃሰተኛ ወንድሞች ፈተና፤ እናም ቤተክርስቲያናችን እንደርሱ እየተፈተነች ይመስለኛል። ከቱርክ፤ ከሶሪያ፤ ከፍልስጤም፤ከየመን፤ ከሳውዲ ከነበሩ የቀድሞ ክርስቲያኖች እንማር፤እናስተውልም። አዎን ፤ አንተ የተኛ/ሽ ንቃ/ቂ! ያለሽ ይመስልሻል ተበልተሽ አልቀሻል የተባለው ወደኛ ሳይመጣ፦ አንተ የተኛ ንቃ!

በክርስቶ ወንድማቹ ከካናዳ።

Anonymous said...

EPRDF was, is and will never take his hand off our church as long as there is someone who steps up and dare to say no! enough! from our so called "fathers" in Ethiopia and then we will call him/them our father/s. It doesn't take to be a genius to know it's EPRDF who forces the 4th Pope to abandon and flee the country - their current statement about bringing back the 4th is like bringing back Mengistu speaks loud for itself. If they haven’t done that in the first place, they wouldn't have said it - period. What then now? The only real father, who laid his soul for his children, our lord and savior Jesus Christ- is our father- as he promised us He will never leave us at the hands of these “Melekawiyan” so called Abatoch. He will raise Abune Petros for us if we stay faithful to His words – don’t forget Elias and Henoke are yet to come. Don’t lose hope! We have greater hope ahead; look ahead of this dark cloud – there is light ahead, there are Abune Petros, Elias, Henock..etc waiting the time to come for us . It’s only about time!
May God keep us in His house to see His Grace region over His people! Amen.

Anonymous said...

In Ethiopian constitution, Religon and government are separated.
So, why we let the government to interfere in our religion?

Please we all chrstians are responsible to save our church.
a

Ameha said...

እግዚአብሔር ይፍረድ! ለምን ይዋሻል? 1ኛ) ኢሕአዴግ እንደ መንግሥት በተቀመጠ ማግስት ከአቡነ መርቆርዮስ በታች ያሉትን አንዳንድ አባቶች አቶ ታምራት ላይኔ አስጠርቶ፣ ከአቡነ መርቆርዮስ ጋር መሥራት እንደማይቻል እቅጩን ነግሮ አሰናብቷቸዋል። የሳቸውን መንበር ለመያዝ የሚቋምጡ አባቶች የመንግሥትን ውሣኔ ለማስፈጸም ደፋ ቀና ለማለት ጊዜ አልፈጀባቸውም። ይህንን የመንግሥት ውሣኔ ተቀብለው ወዲያው ለአቡነ መርቆርዮስ አርድተዋቸዋል። የመረጡበት ገዳም መቀመጥ እንደሚችሉ የተነገራቸው ያን ጊዜ ነበር። መንበራቸውን ራሳቸው እንደለቀቁ ተደርጎ የተገለጸው ነገር ውሸት ነው።

2ኛ) የአቡነ መርቆርዮስ ከመንበራቸው መነሳት እውን እየሆነ በመጣበትና አዲስ ፓትርያርክ መሾሙ አይቀሬ መሆኑ በተረጋገጠበት ወቅት፣ አቡነ መልከ ጸዴቅ ከዕጩዎቹ መካከል እንደሚሆኑ ቃል በተገባላቸው መሠረት ምድረ አሜሪካን ለቀው አዲስ አበባ ገቡ። ሆኖም እሳቸው እንዳሰቡት ሳይሆን ቀረና ኢሕአዴግ የራሱን ሰው በድርጅታዊ አሠራር አስመረጠ። ኢሕአዴግ እሳቸውን የፈለገው፣ ምርጫው ውጭ አገር ያሉትም ሆነ አገር ቤት ያሉት የኃይማኖት አባቶች አብረው መክረው እንዳስመረጡ ለማስመሰል በሸረበው ሤራ ውስጥ እንዲሳተፉ ለማድረግ ብቻ ነበር። አሁንም በዚህ ዘመን፣ ያንኑ ተመሳሳይ ተግባር ለመፈጸም "ውጭ አገር ያላችሁ አባቶች አገር ቤት ተመልሳችሁ 6ኛውን ፓትርያርክ እንምረጥ" በማለት ሲወተወት ይስተዋላል።

አቡነ መልከ ጸዴቅ መሸወዳቸውን ሲረዱ ድምፃቸውን አጥፍተው ወደ አሜሪካ ተመለሱ። በመጨረሻም፣ አቡነ መርቆርዮስን "አሞኛል ብለው መንበሩን ይልቀቁ፤ እኛ ከአገር እናስወጣዎታለን" በማለት ያሰኮበለሏቸው እርሳቸው ናቸው።

ወገኖቼ! ብዙ አስተያየት ሰጪዎች አቡነ መርቆርዮስ በይፋ ወጥተው ለምን አይናገሩም? እያላችሁ ትጠይቃላችሁ። አቡነ መርቆርዮስ አቅም የላቸውም። እርጅናው እንዳለ ሆኖ ሃሳብ እንኳ የመስጠት፣ የመወሰንም መብት ተነፍጓቸው በስደት አገር ግዞት ላይ ይገኛሉ። ስለዚህ ጸሎትንና ዝምታን መርጠዋል። እወነቱን ሳታውቁ አትፍረዱባቸው።

በመጨረሻ የዕርቀ-ሠላሙን ሂደት ያደናቀፋችሁቱ፣ ሥልጣን፣ ገንዘብንና የፖለቲካ ጥገኝነትን መከታ አድርጋችሁ ሕዝበ-ክርስትያኑንና ቤተ ክርስትያናችንን ያሳዘናችሁ አንዳንድ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ አዋርዳችሁንና አንገታችንን አስደፍታችሁ በተድላ እና በደስታ አትኖሩምና እግዚአብሔር የ 5ኛውን ፓትርያርክ ጽዋ ይስጣችሁ!

"እግዚአብሔር፡በአማልክት፡ማኅበር፡ቆመ፤ በአማልክትም፡መካከል፡ይፈርዳል። እስከ፡መቼ፡ሐሰትን፡ትፈርዳላችሁ? እስከ፡መቼስ፡ለኃጢአተኞች፡ፊት፡ታደላላችሁ? ለድሆችና፡ለድሃ፡አደጎች፡ፍረዱ፤ ለችግረኛውና፡ለምስኪኑ፡ጽድቅ፡አድርጉ፤ ብቸኛውንና፡ችግረኛውን፡አድኑ፤ ከኃጢአተኞችም፡እጅ፡አስጥሉአቸው። ...እኔ፡ግን፡-አማልክት፡ናችሁ፣ ሁላችሁም፡የልዑል፡ልጆች፡ናችሁ፤ ነገር፡ግን፡እንደ፡ሰው፡ትሞታላችሁ፤ ከአለቆችም፡እንደ፡አንዱ፡ትወድቃላችሁ፡ አልሁ። አቤቱ፡ተነስ፣በምድር፡ላይ፡ፍረድ፤ አንተ፡አሕዛብን፡ሁሉ፡ትወርሳለህና።" መዝ. 81(82)

Anonymous said...

I am very sorry to say this, EPRDF and the so called Ethiopian senodous in Ethiopia are trying to force the Ethiopian orthodox church to continue the legacy of abune Poulose.Jesus shows unconditional love on the cross . How on earth,these so called holly fathers choose
their ethnicity as a way of advancing their motive to get power and resources. How was the 21 years of abune Poulose patriarchy? Was it peaceful and blessing? I think it is high time to say no help to the churh until they fill it.othewise, they will continue to diminish our churh to the extent that we can't imagin .No more lies . May God bless Ethiopia!!!

Anonymous said...

I personally call everybody both inside and outside the country to follow Aleka Ayalew Tamiru's way. Just let's ignore both side, as they are not acting like a normal father. they both point fingers to each other. Let's focus on those independent church's and keep praying there. After all, these bishops are there because of the EOTC innocent people.

Defense? said...

To Anonymous who said...
“dear yetewahedo lejoche." Concerning your comments about Bitsu Abune Abrham, you asked where is the courage that his grace showed when he was Archbishop of Washington DC and Its Surroundings? I have an answer for you: his grace’s courage is still with him, just like his grace fought the devil's work of shaking the foundation of our church unity in the USA, he’s grace is doing the same in Ethiopia, just be patient and you will see, things are not always what they seem. Bitsu Abbatachin was removed from his position in USA against the will of the children his grace served; however, but both his grace and his children followed the church's cannon law and accepted the decision. At the same time, both presented their thoughts and feelings about the decision to the authorities at hand.
Bitsu Abbatachin Abune Abrham is a part of the Holy Synod, he is NOT THE SYNOD, he was reporting the resolution of the WHOLE SYOND decision. His grace taught us consistantly during his service in the USA that He will always stand for peace and unity; however, it must not come at the cost of breaking the church cannon laws. The law is there for us to follow, but today there are many in the church who break the laws to satisfy their own desires, this is wrong and is heretic. Bitsu Abbatachin does not need me or others as defense, did not our Lord say, "Blessed are you when others speak evil of you for my sake, rejoice!". I know first hand his grace understands it is an HONOR to be percecuted for the sake of the church, but woe to the one who percecutes the servants of the Lord Jesus Christ. Therefore, I guarantee you, God will be his grace's defense, so be careful about what you write or say, that goes for all of us here, this is not my advise but the teaching of our orthodox tewahedo fathers.

Birile said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን::

I completly agree with comments by anonyms on January 17/13 at 7:24AM and January 18/13 at 12:34AM.
The Holy Synod in Ethiopia has clearly announsed its decision on the current issues of the church. It has expressed its effort to unify the church. Its delegets has negotieted four times with the other synod.It has accecpted the members of the outside synod to be part of the church with their position and take part in the election of the sixth Patriarch of the church.The synod in Ethiopia has been trying this far.I haven't heard any about the efforts tried by the outside synod.Has it? How was it? How far? When? We need tangeble evidence. We have to comment based on facts not rumers.
The ouside synode wonts Abune Merkorios to take the Patriarch seat in Ethiopia. Is this really what he wonts? Has he been heard saying that he want his previous position in Ethiopia? If he has abondoned his seat previously (lets say that he has a political reason); how come that he is willing to take that same position in the same political system, for EPRDF is still the ruling party in Ethiopia? The Ethiopian Synod has clearly anounced their decisions; how come the outside synode hasn't responded to the facts presented in the decision? What is the reponsibility of a patriarch as a leader of the church specially in times like this? What do the church realy demand from Abune Merkorios at this time? Has he done what was expected of him? Did he even get a chance to express his feeling, his wishes in the exile? How often have we seen him, get his blessings, etc? Why?
Politicians here and there alway try to manupulate the church to fulfill their goals,this is true throughout history.The church united as one has to stand firm to achive its mission. We may have differences in politcal views but we are one family being born from the One Holy Spirit.There are two strong waves that we are swiming in, the wave of politics and a wave of faith in Christ Jesus.The wave of politics is getting stronger for we are helping it by pouring flood of hatread, envy, greed, division, etc.It is getting stonger and it is pulling us down deep into its center.It is dark thre, lots of confusion. Lets stop hatread, greed, etc. and rathe strengthen the wave of faith by pouring love, honesty, compasion, etc.
God bless us all! Praise to the Almighty God!Amen!

Birele said...

why cant we hear a response from the outside synod to the decisions made and facts presented by the synod from Ethiopia?

Birile said...

The political system is the same in Ethiopia. EPRDF is still a ruling party in Ethiopia. How can the return of Abune Merkorios to his privious position in Ethiopia, be a pivotal point for the unity of the chuech,for they claim that he had a political reason to abonden his position in the first place? How can be this be a reason separation? Has he claimed it? Has he said that he wont to be that seat in Ethiopia? Why dont the outside synod responded to the decision and facts presented by the synod in Ethiopia? What is most impotant for our cherch?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)