January 14, 2013

ጥር 6 ይኸው ደረሰ

·         የፓትርያርክ ምርጫን ከዕርቀ ሰላሙ ጎን ለጎን ለማካሄድ የታሰበው ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለ አባት፣ ምእመኑም ያለ እረኛ ተበትነው እንዳይቀሩ” ነው፤ (ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል)
·         በሽምግልናው ሂደት የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ተጨምረውበት የዕርቀ ሰላሙ ድርድር ይቀጥላል፤
(ደጀ ሰላም፤ ጥር 5/2005፤ ጃኑዋሪ 13/2013/ PDF)፦ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ ሊካሄድ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረው። ጥር 6/2005 ዓ.ም ይኸው ደረሰ። ምንም እንኳን ሌሎች አጀንዳዎች አንሥቶ ሊነጋገረ እንደሚችል ቢጠበቅም በዋነኝነት ግን የጉባኤው ዓላማ ዕርቀ ሰላሙ እና የፓትርያርክ ምርጫው ጉዳይ እንደሚሆን እየተጠበቀ ነው።

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ስምዐ ጽድቅ ለተሰኘው የማኅበረ ቅዱሳን ጋዜጣ እንደተናገሩት ከሆነ “የፓትርያርክ ምርጫውን ከዕርቀ ሰላሙ ጋር ጎን ለጎን ለማካሄድ” የተቆረጠ ይመስላል። ለዚህም በምክንያትነት የቀረበው “ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለ አባት፣ ምእመኑም ያለ እረኛ ተበትነው እንዳይቀሩ” ነው። ነገር ግን በዕርቁ መፍረስ የሚበተነውን እና ያለ እረኛ የሚቀረውን ምእመን አስመልክቶ ምንም የተናገሩት ነገር የለም።

ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ያሉ እጆች በጽኑዕ በተጫኑት በዚህ የአበው ዕርቅና የቀጣዩ ፓትርያርክ ምርጫ ጉዳይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚበጅ ውሳኔ በጥብዓት ያሳልፋሉ ብለን እንጠብቃለን። በርግጥ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል እንዳሉት የፓትርያርክ ምርጫ ደንብ “ቀድቋል” ተብሏል። የመቀበሉም ሆነ የመሻሩ ሥልጣን የምልዐተ ጉባኤው ስለሆነ በተጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ዳግም ሊታይ ይችላል ብለን እንጠብቃለን።
   
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
10 comments:

Anonymous said...

የመቀበሉም ሆነ የመሻሩ ሥልጣን የምልዐተ ጉባኤው ስለሆነ በተጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ዳግም ሊታይ ይችላል ብለን እንጠብቃለን።
Do yo guys (deje slam) accept the decision given by synod? You are always against the decision of synod.

Unknown said...

ምንም አዲስ ነገር አጠበቅም። ምክንያቱም ለቤተ እግዜብሔር ይልቅ ለበቤተ መንግሥቱ ቅርበትና ትስስር ያላቸው ጳጳሳትና የቤተ ክህነት ባለ ሥልጣናት እስካሉ ድረስ የምዕመናን ፈቃድና ፍላጎት ሊሳካ አይችልም። ላለፉት 21 ዓመታት ይህ የማይሆንበትን ፥ ማለት status quoው እንዳይለወጥ የሚያስችለውን ሥራ ሁሉ ደረጃ በደረጃ ሳያዋቅሩ ነው የቆዩት። ለዚህ ተልዕኳቸው መሳካት ታማኝ የሆኑ ''ሊቃነ ጳጳሳትን'' ሲሾሙ ቆይተዋል። ለዚህ ነው በምልአተ ጉባኤው ውስጥ እርቀ ሰላሙን በሚመለከት አንድ አይነት ስምምነት ላይ ሊደረስ ያልተቻለው። የታጠቀ ኃይል በጀርባቸው ደጀን ሁኖ የሚጠብቃቸው የቤተ ክህነቱ ክፍሎች ያሉት ሁሉ ይሆናል እንጅ ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና ይጠበቅ ፥ እርቀ-ሰላም ይሁን ፥ ላንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድ ፓትርያርክና ኣንድ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚለው የተቀደሰ ሃሳብ ተቀባይነት አይኖረውም። ስለዚህ እንዲያው ብቻ 'እንዳያማ ጥራው ፥ እንዳይበላ ግፋው' እንደተባለው አይነት ነው እርቅ የሚሉት እንጅ ከልብ አይደለም። አኮ ለጽድቅ ማኅበረ ሲኖዶስ ለግብረ ተርእዮ ዳዕሙ ፥ መያሲያኒሁ አግብርት እስመ ሕሱማን ነዮሙ።

Anonymous said...

Zim bilachihu atinchachu. Abatochachin girana kegnun agenazbew yemihonewun yiwesnalu. Lij Abatu yemilewun mesmat alebet. Lelij yemaytay bizu neger le Abat yitayalina. Ke enersu belay enawkalen yemitlu kehone gin...egziabher yigetsitsachihual.

Anonymous said...

aba Hizkeal please do not mention our name!!!!!!!!!We the belevers never ask to have father first We have asked you to make peace first otherwise God will revange you for mentioning our name to finish woyane agenda.
try to be with the Fathers who want to create peace first.

Anonymous said...

Menga yemilun eko be kiristinaw agbab aymeslegnm. Be ergit lenesu 'yekebit' menga sanhon ankerim. Ye kutrachin enji yemininetachin neger aygedachewim. Silitane-kihinet ke kiristos be adera yewesedu bihon andu beg bitefa lemefeleg wedebetu lememeles ena lemetebek neber. Enegnih mengawin lemetebek yemilun siltane-kihinetun ke mileyayen mengist yetekebelut eskimeslen direse yegna meleyayet aygedachewim. Eirk yemibalewm bewich yalutin 'kis' enji lijinetachewn almo yetenesa aydelem.

Anonymous said...

We are not expecting anything new until every Ethiopian Pops stop leaving for their interest which they suppose to leave a life for their faith to protect and defend our church but they feared to face realities whenever our government interfere their duty. how can expect something while many of those father have no fear doing for will of God but the do have fear to government. we didn't choice this life for them its fact it God will so they should carry on their duty. I hope one day we will have father who can go jail or by stand until to death for this church.its so unbelievable that bitsu abun Abraham just involved in such things it is hard to believe anyone in those fathers. its good to have God that never leaves us whenever we are unfaithful to to him. almighty give us the true Father!!!

Anonymous said...

Wegenoche it is the time to pray deep from inside "kelebachen" directly to God. Wedemechereshaw gize eyetekareben nw. Amlak geta zare kireb nw.Tageso Tageso kebekaw mitu hayelegna nw.

Kersu mit yadenen Amelak Ethiopian and hizebuan becherenetu yitebek. Amen

Anonymous said...

ከበደ ቦጋለ ሆይ!ያገር ቤት አባቶችም እኮ የርሶ አባቶችም ጭምር ናቸው ። ሊያከብርዋቸው ሊሳሱላቸው ይገባል። እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያኒቱን እየመሩ እዚህ አድርሰዋታል። ችግራቸውን መረዳት ያስፈልጋል። አሜሪካ ቴምፑር ፔዲክ ላይ ተንጋለን፤ ወተት በጋሎን፤ ዘይት በጀሪካን፤እየገዛን፤ የቡና ቁርሳችን ጎረድ ጎረድ፤ መክሰሳችን ጥሬ ክትፎ በቆጮ የሆን መመናን ያዙን ልቀቁን አላበዛነውም?

Anonymous said...

Having all these uncomfortable issues in the church is awful. From the very beginning our church fathers have to be a great example for us by forgiving eachother. The issue is more of politices and corruption than christanity. It has nothing to do with spritual life. The congregations of the church has to unite together and ger rid of all the leaders of the church who are starving of power.

Unknown said...

Bemejemeria egziabeher ethiopian kehezbochua gar yetebek elalehu yehin kalku zenda yeh mengest eyale betekiristaniachen leamagnochua fekerena andenet tametalech malet yefesesen wuha endemafes yekoteral mengesten kegnachew bebetekeristuana tealka endigebanna endiamessen yeaderegu andand abatoch endalu yemitaweke new selezihe yeh mengest eskaltewegede besteker seltanune lemarazem mekefafelunena kaderewechune bebetekeristuana sego bemasegebat selemmayakob yehen mengest tebabero kebetekerstiano endeweged kaltederege besteker menem selam yelem.
egziabeher agerachen yetebeke

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)