January 28, 2013

ቤተ ክህነት የአዲሱን ፓትርያርክ ምርጫ የሚቃወሙትን እንደምትከስ አስፈራራች


(ደጀ ሰላም፤ ጥር 20/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 28/2013/ PDF)፦ ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ ሰላማዊ የሽግግር ጊዜውን ለማደናቀፍ የሚገኙ ቡድኖችን፣ የመገናኛ ብዙኅንና ግለሰቦችን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ማስጠንቀቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል የስድስተኛውን ፓትርያርክ አሿሿም በሚመለከት ሕገ ደንብ ወጥቶ ምርጫውን ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ውስጥ መሆኑን የሚያውቁ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኅን፣ ከውስጥ አፍራሽ ኃይሎች የሚቀበሉትን ፀረ ሰላምና ከእውነት የራቀ አሉባልታ ከድረ ገጽ ያገኙ በማስመሰልና ምንጮቻችን እያሉ በውጭና በአገር ውስጥ ያለውን ምዕመናን እያወናበዱ በሚገኙት ላይ ቤተ ክህነት ክስ መመሥረቷን የዘገበው ጋዜጣው መግለጫውን የሰጡት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሳይሆኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ መሆናቸውን አብራርቷል።

January 24, 2013

ሁሉም “የማንም አሿሿሚ አልሆንም! የሥልጣን ጥመኞችንም አላገለግልም!” ቢል


(መልዕክተ ተዋሕዶ - ዘሮኪ በተለይ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት/ PDF)፦ ደጀ ሰላማውያን እንደምን ሰነበታችሁ? ብዬ መጠየቅ፥ ዛሬ አልፈለኩም። እንዴት እንደሰነበትን፥ ሁላችንም እናውቀዋለንና። ለመላው የቤተ ክርስቲያን  ልጆች እያሳለፍነው ያለው ሳምንት የሐዘንና፥ ተስፋችንን አጨላሚ፥ ሆኖ ነው የሰነበተው። ይህ ሳምንት፥ ለሃያ አንድ ዓመታት ፥ መከፋፈል በተባለ በሽታ ፥ ታማ የነበረችው እናት ቤተ ክርስቲያን  ፥ ስትሰቃይ ኖራ ፥ ያረፈችበት ሳምንት ነው።  ነገር ግን አጥብቀን ከቀድሞው አብዝተን ከጮህን፥ ልክ በወንጌሉ እንደተጻፈው የሞተውን የሚያስነሳው ትንሣኤና ሕይወት የሆነ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ እስትንፋሷን ሊመልሰው ይቻለዋል። በእምነታችንም ጸንተን እያንዳንዳችን ማድረግ ያለብንን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ አንበል፤ በማለት ሰሞኑን አእምሮዬን ሲሞግቱኝ ወደ ከረሙት ጉዳዮች ተራ በተራ ልግባ።

January 23, 2013

ፓርላማው የላከው ቡድን የላሊበላ ቤተ ክርስቲያናት አደጋ ላይ ናቸው አለ

(Reporter Amharic):- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቅርስ፣ የባህልና የመገናኛ ብዙኅን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሰሜን የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የአገሪቱ ቅርሶችን እንዲታዘብና ሪፖርት እንደያደርግ የላከው የሕዝብ ተወካዮች ቡድን፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በአሳሳቢ አደጋ ላይ መሆናቸውን ሪፖርት በማድረግ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲደረግ አሳሰበ፡፡

የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለክልሉ መንግሥት አቀረቡ


·       የትግራይ ክልል ተወላጅ ካልሆናችሁ በዚህ ገዳም መኖር አትችሉም” ተብለናል፤
·       ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋልድባ የሚለውን ስም መጥራት ሁሉ የተለየ ይዘት እየተሰጠው” ነው፤
  •       መነኮሳት ይታሰራሉ፤ ይደበደባሉ፤
    • ከክልሉ ፕሬዚዳንት ጋር ተነጋግረዋል ተብሏል።
(ደጀ ሰላም፤ ጥር 12/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 20/2013/ PDF)፦ የዋልድባ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለአማራ ብሐየራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አቀረቡ። በመነኮሳት ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የዘረዘረው ደብዳቤው የክልሉ መንግሥት በሰላማውያን መነኮሳት ላይ የሚደርሰውን እንግልት እንዲያስቆም ጠይቀዋል። የታሰሩ፣ የተንገላቱ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸውን መነኮሳትም ዝርዝር አቅርበዋል። ሙሉ የደብዳቤው ሐሳብ ቀጥሎ ሰፍሯል።

January 22, 2013

አዳነ ግርማ - የቅ/ገብርኤል ወዳጅ - ግሩም ጎል


(ደጀ ሰላም፤ ጥር 14/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 22/2013/ PDF)፦ ኢትዮጵያ በአንድ እግሯ ቆማ ባመሸችበት በትናንትናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታ ግሩም ድንቅ ጨዋታ፣ ግሩም ድንቅ እግር ኳስ አየን። በዚህ ታሪካዊ ጨዋታ ላይ የማታ ማታ አቻ የምታደርገውን ጎል ያስቆጠረው የቅ/ገብርኤል ወዳጅ አዳነ ግርማ ነበር። እገሌ ሃይማኖቱ ኦርቶዶክስ ነው፤ እገሌ ሌላ ነው የሚል ከፋፋይ ሐሳብ ለማቅረብ ሳይሆን አዳነ የሚለብሰውን 19 ቁጥር ስንመለከት ቅ/ገብአርኤልን እንደሚወድ፣ የሐዋሳ ልጅ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የልጁንም ስም “ገብርኤል” ብሎ መጥራቱን ለማስታወስ ወድደን ነው።

January 20, 2013

“አንድ ጥምቀት፣ አንድ ሃይማኖት” የሚል ጥቅስ የያዙ ወጣቶች ታሠሩ


(ደጀ ሰላም፤ ጥር 12/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 20/2013/ PDF)፦ ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ ያለውን “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ጥምቀት” የሚል ጥቅስ ያለበት ቆብ ለሰንበት ት/ቤታቸው ገቢ ማስገኛነት በመሸጥ ላይ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ መታሠራቸው ታወቀ።

January 19, 2013

4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ስለ በዓለ ጥምቀት እና ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ያስተላለፉት መልእክት


4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ስለ በዓለ ጥምቀት እና ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ያስተላለፉት መልእክት:: 

አሜሪካ የሚገኙት አባቶች ሲኖዶስ መግለጫ አወጣ


(ደጀ ሰላም፤ ጥር 11/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 19/2013/ PDF)በትናንትናው ዕለት የአሜሪካው ሲኖዶስ  ያወጣው መግለጫ የተለያዩ ጉዳዮችን የያዘ ነበር፡፡ እነዚህም ጉዳዮች የቅዱስ ፓትርያርኩን መሰደድ በተመለከተ ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 4 ቁጥር 77 እስከሚድን ጠብቁት የሚለውን ቀኖናዊ ሕግ መሻሩን በመግለጽና ሌሎች ተጨማሪ እስከ 7ኛ ተራ ቁጥር የተዘረዘሩ አስረጅዎችን የሚጠቅሱ፣ የሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስን በስደት መቀጠል በተመለከተ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስን፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅና፣ ቅዱስ ዲዮስቆሮስን ስደት አብነት ያደረገ መሆኑን የሚተነትኑ እና የዕርቀ ሰላሙን ውይይት በተመለከተ ለምን? እንዴትና? በማን? እንደከሸፈ አስረጅዎችን በመጥቀስ የሚስረዱ ናቸው፡፡

ESAT Special on Ethiopian orthodox church current situation January 2013

Timket (Ketera) in South Africa


Video Courtesy of "ETHIOPIAN IN SOUTH AFRICA"

January 16, 2013

ከዕርቀ ሰላም ይልቅ ለ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ቅድሚያ የሰጠው የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ተስፋዎችን አጨላሚ ሆነ

(ደጀ ሰላም፤ ጥር 8/2005፤ ጃኑዋሪ 16/2013/ PDF) በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና ከመነሻውም በውጪ ተጽዕኖ ሥር የወደቀው የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ እንደተፈራውም ዕርቀ ሰላሙን አሽቀንጥሮ ወርውሮ 6ኛ ፓትርያርክ በመፈረሙ ላይ ጸንቷል። በብፁዕ አቡነ አብርሃም በተነበበው መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው ቅ/ሲኖዶሱ ያደረገው ሙከራ ያልተሳካው በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች ባቀረቧቸውና ከዕርቁ ጋር በማይገናኙ ሌሎች ምክንያቶች የተነሣ ነው። ይህ “ከእርቁ ጋር የማይገናኝ” የተባለው ምክንያት አሜሪካ ያሉ አባቶች የሚያነሧቸው “ፖለቲካዊ ጥያቄዎች” መሆናቸውን ደጀ ሰላም ትረዳለች። በተለይም ለብዙዎቹ የቅ/ሲኖዶስ አባላት የተነገራቸው ምክንያት “አገር አቀፍ ዕርቅ” ይውረድ ይላሉ፤ ውጪ አገር አሉት ፖለቲከኞችም አብረውን ካልገቡ ይላሉ የሚለው መልዕክት ነው።

የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ዘገባ


January 15, 2013

“ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ አገራቸው ይግቡ፣ ግን እንዴት ይግቡ?” የሚለው ቅዱስ ሲኖዶሱን አወያየ

(ደጀ ሰላም፤ ጥር 7/2005፤ ጃኑዋሪ 15/2013/ PDF)፦ ትናንት ሰኞ የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ  የተገኙ ብፁዓን አበው በዕርቀ ሰላሙ እና በቀጣዩ ፓትርያርክ ጉዳይ ሲነጋገሩ የዋሉ ሲሆን ዕርቀ ሰላም መቅደም እንዳለበት በደምሳሳው ግብብነት እንዳለ ተመልክቷል። ይሁን እንጂ አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን በተመለከተ ብፁዓን አበው በቀደመ አቋማቸው ማለትም “ወደ አገር ቤት ገብተው በጡረታ፣ በአንድ ሥፍራ ይቀመጡ” በሚለው እንደጸኑ በትናንትናው ስብሰባቸው አስረግጠዋል ተብሏል፡፡

የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ልኡካን ለሰጡት መግለጫ ከሰላምና አንድነት ጉባኤው የተሰጠ ማብራሪያ


 “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን”

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ያወጣውን መግለጫ አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የመጡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ልኡካን ለሰጡት መግለጫ ከሰላምና አንድነት ጉባኤው የተሰጠ ማብራሪያ
 ጥር 3 ቀን 2005 ዓ/ም (January 11/2013)
READ THIS FILE IN PDF
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ታኅሣሥ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ወቅታዊውን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ አስመልክቶ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫውን እንዲያወጣ ያስገደደው ዋነኘው ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለዕርቀ ሰላሙ ድርድር የላካቸው የሰላም ልዑካን ሳይመለሱና በዳላስ፤ ቴክሳስ የተደረገውን የሦስተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ውይይት ሪፓርት ሳያቀርቡ በአዲስ አበባ በኩል ስድስተኛ ፓትርያርክ ለመምረጥ አስመራጭ ኮሚቴ መሰየሙ በመሰማቱ እንደነበር ይታወቃል።

እርስዎስ ምን መፍትሄ አልዎት!?

January 14, 2013

ጥር 6 ይኸው ደረሰ

·         የፓትርያርክ ምርጫን ከዕርቀ ሰላሙ ጎን ለጎን ለማካሄድ የታሰበው ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለ አባት፣ ምእመኑም ያለ እረኛ ተበትነው እንዳይቀሩ” ነው፤ (ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል)
·         በሽምግልናው ሂደት የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ተጨምረውበት የዕርቀ ሰላሙ ድርድር ይቀጥላል፤
(ደጀ ሰላም፤ ጥር 5/2005፤ ጃኑዋሪ 13/2013/ PDF)፦ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ ሊካሄድ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረው። ጥር 6/2005 ዓ.ም ይኸው ደረሰ። ምንም እንኳን ሌሎች አጀንዳዎች አንሥቶ ሊነጋገረ እንደሚችል ቢጠበቅም በዋነኝነት ግን የጉባኤው ዓላማ ዕርቀ ሰላሙ እና የፓትርያርክ ምርጫው ጉዳይ እንደሚሆን እየተጠበቀ ነው።

Kesis Dr. Mesfin Tegegn on ESAT

January 12, 2013

የመጨረሻው መጀመሪያ እንዳይሆን

(መልዕክተ ተዋሕዶ -ዘ ሮኪ፤ በተለይ ደጀ ሰላም እንደጻፉት/ PDF)፦ በዚህ በውጭው ዓለም ለምንገኘው ለብዙዎቻችን፣ በተለይ ባለፉት 7 እና 8 ዓመታት ላቋቋምናቸው አጥቢያ አቢያተ ቤተ ክርስቲያናት፣ ምርጫችንን እናት ቤተ ክርስቲያናት አድርገን ስንጓዝ፣ መንገዱ እንደዚህ እንደ ዛሬው ቀላል አልነበረም፣ የተለያዩ ቅጥያ ስሞች እየተለጠፉብንና በአደባባይም ስንት ነቀፋ እየተቀበልንም ነበር። የወያኔ ቅጥረኞች እና የአባ ጳውሎስ አሽከሮች የሚሉት በተደጋጋሚ የሚዘወተሩ ሲሆኑ አጥቢያ አቢያተ ቤተ ክርስቲያናቱን ለማኅበረ ቅዱሳን አባላት ብቻ  እንደ ተቋቋመ የሚመለከቱም ቁጥራቸው ትንሽ አልነበረም።

January 3, 2013

አባቶች ሆይ አብነታችሁን አሳዩን

(መ/ር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ/ PDF):- በቀድሞ ዘመን ማዶ ለማዶ በመንደር ተለያይተው በቅርብ ርቀት ላይ  የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንደነበሩ ይነገራል፡፡ እነዚህ ህዝቦች ታዲያ ባልታወቀ ምክንያት ቅሬታ ፈጥረው በሆነው ባልሆነው ምክንያት እስከ መካሰስ ደርሰው ነበር፡፡ ልዩነታቸውም እየሰፋ ሲመጣ አንዱ ለሌላው መጥፎ ስም መስጠት ጀመረ፡፡ ከአሉባልታዎቹም መካከል፡- የታችኛው መንደር የላይኛዎቹን፤እዚያ ማዶ ያሉት ቡዳ ናቸው ሲሉ፡- በላይኛው መንደር ያሉትም በተራቸው፤ታች መንደር ያሉት ቡዳ ናቸው  እየተባባሉ እርስ በርሳቸው ይተማሙ ነበር፡፡ በሌላ መንደር የሚኖረው ሕዝብም ሁለቱን በቡዳነት ፈርጆ የሚቀርባቸው እስኪያጡ ድረስ ራሳቸው ባመጡት ጣጣ ገለልተኞች ሆነው ብዙ ዘመን ኖሩ፡፡

January 2, 2013

“ቤተ ክርስቲያንን ለፈተና አጋልጠን ወደ ገዳም አንገባም” (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ)

  • ከሰሜን አሜሪካ የተመለሱ የሰላም ልዑካን የጉዞ ሪፖርታቸውን ለሚ ሲኖዶስ ቅርበዋል።
  • የሰላም ልዑካኑ  ዕርቀ ሰላሙ መቀጠል እንዳለበት በአት አሳስበዋል፡፡
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 24/2005 ዓ.ም፤ January 2/2013/ PDF)፦ ላለፉት ሦስት ዓመታት  ሁለቱን ሲኖዶስ ለማስታረቅ ደፋ ቀና ሲል የነበረ አስታራቂ ጉባኤ ባወጣው መግለጫ መግለጫው ለሽምግልና ከተቋቋአካል አይጠበቅም በሚል  ተቃውቸውን የገለጡት ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጉባኤው ይቅርታ ካልጠቀ አብረውት ለመሥራት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)