- ከኢትዮጵያ የመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለም አቀፍ ቅርስ የመኾን ዕድሉን ካገኘ በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጥበቃና ክብካቤ ይደረግለታል፤
- የአ/አ ሀ/ስብከት አንዳንድ ሓላፊዎች ለዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል የሰጡት ትኩረት አከባበሩን በማዳከም የወቅቱን የቅ/ሲኖዶስ አመራር የማስነቀፍ ዓላማ እንደነበረው ተጋልጧል፤
- በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ፖሊስ በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራንና አባላት ላይ ያካሄደው ፍተሻና በኅትመቶች ሽያጭ ላይ የተደረገው እገዳ ተቃውሞ ገጥሞታል፤
- የአቶ መለስ ዜናዊ 40ኛ ቀን ተዝካር በታላቁ ቤተ መንግሥትና በጠ/ቤ/ክህነት ይደረጋል፤
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 14/2004
ዓ.ም፤ ሰምቴፕር 24/2012/ READ IN PDF):- የመስቀል - ደመራ በዓል አከባበር በዓለም ግዙፍነት ከሌላቸው ቅርሶች መካከል አንዱ ኾኖ እንዲመዘገብ ሲደረግ የቆየው ጥረት “በመልካምና ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መንገድ ላይ እንደሚገኝ”፣ በመጪው ዓመት ኅዳር ወርም ኢትዮጵያ ለዩኔስኮ ያቀረበቻቸው ማስረጃዎች ተቀባይነት አግኝተው የመስቀል - ደመራ በዓል የመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለም አቀፍ ኢትዮጵያዊ ቅርስ (World Intangible Heritage) ኾኖ እንደሚመዘገብ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡