- READ THIS ARTICLE IN PDF.
- ከአብረንታንት እና ማይ ለበጣ ሁለት መነኰሳት ወደ ማይ ፀብሪ ተወስደዋል፤ በዶንዶሮቃ ከ50 በላይ የመነኰሳት እና መነኰሳዪያት ቤት በፖሊስ ተፈትሿል
- ከፖሊሶቹ አንዲቱ ከጾታዋ የተነሣ ወደ ዋልድባ ለመግባት የማይፈቀድላት ሴት ናት
- የአብረንታንቱ አባ ገብረ ሥላሴ ዋለልኝ እንደታሰሩ ናቸው
- ከ49 ያላነሱ የቤተ ሚናስ መነኰሳት በፖሊስ ይፈለጋሉ
- ‹‹እናንት ምታታሞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመም ተጠያቂዎች ናችሁ›› /የማይ ፀብሪ ፖሊሶች/
July 31, 2012
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም የዋልድባ መነኰሳት ተጠያቂ ተደረጉ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
July 29, 2012
የአቡነ ጳውሎስ የማዕረግ ስም ላይ “ዓለም አቀፍ የሰላም አምባሳደር” የሚል ተጨመረ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- READ THIS NEWS FEATURE IN PDF.
- ስለ አቡነ ጳውሎስ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመት በክራውን ሆቴል ለሦስተኛ ጊዜ ይደገሳል።
- የመንበረ ፓትርያርኩ ሙስና ለጥቅመኛ የውጭ ቡድኖች ‹መስሕብ› ኾኗል - ራእይ ለትውልድ አንዱ ነው።
- የጠቅ/ቤ/ክህነቱ “የምግባረ ሠናይ አጠቃላይ ሆስፒታል” ኦዲት ተደርጎ አያውቅም።
- ሰሞናዊው ድግስ “ለመጨረሻው የአቡነ ጳውሎስ በዓለ ሢመት የቁም ተዝካር” በሚል እየተነገረለት ነው።
- “የሰውዬው [አባ ጳውሎስ] መታወሻ (legacy) አውዳሚነታቸው ነው። እርሳቸውም፣ እኛም እየበላን ያለነው ቀደምት ፓትርያርኮች ያስቀመጡትን ሀብት ነው።” (የቤተ ክህነቱ ታዛቢዎች)
July 28, 2012
July 26, 2012
የፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ በዓለ ሢመት - በሼራተን አዲስ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤
ሐምሌ 19/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 26/
2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የአቡነ ጳውሎስ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመት ሐምሌ አምስት ቀን 2004
ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተከብሯል፡፡ ሐምሌ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ምሽት በሼራተን አዲስ ለሁለተኛ
ጊዜ የተካሄደውና የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን፣ አምባሳደሮችንና ታዋቂ ሰዎችን ጨምሮ ከ500 ያላነሱ ሰዎች የታደሙበት የራት
ግብዣ በፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት እና “ራእይ ለትውልድ” በተባለ
አካል የተዘጋጀ መኾኑ ተገልጧል፡፡
July 23, 2012
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የፓትርያርክነት ማዕርግ የተቀዳጀችበት የነጻነት በዓል - በዓለ ሢመተ ፓትርያርክ - አከባበር የመንፈሳዊ ውርደትና የምዝበራ መንገድ ኾኗል
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 16/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 23/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በሙስና፣ ብኵንነት፣ ኑፋቄ እና ዐምባገነናዊ አሠራር የነቀዘው የአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና 20ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ዛሬ ምሽት ለሁለተኛ ጊዜ በሼራተን አዲስ ይከበራል። የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እና ራእይ ለትውልድ /Vision for Generation/ የተባለው አካል የጥቅም ትስስር የፈጠሩበት የሼራተኑ በዓለ ሢመት ዝግጅት በቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ይኹን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት አይታወቅም።
July 21, 2012
በዋልድባ መነኰሳት ላይ የሚካሄደው እስርና እንግልት ተባብሶ ቀጥሏል
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- አንድ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም መነኰስ ወደ ማይ ፀብሪ ተወስደዋል።
- የገዳሙ መነኰሳት የግዴታ መታወቂያ እንዲወስዱ ተደርገዋል።
- ፓትርያርኩ ዕግድ የጣሉበት የጀርመን የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሒዷል።
July 19, 2012
July 18, 2012
የሲያትል ምእመናን አቡነ ፋኑኤልን በይፋ ተቃወሙ፤ እንዳይመጡም ተስማሙ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 10/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 17/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በሰሜን ምዕራብ አሜሪካ በዋሺንግተን ሲያትል በሚገኙት በደብረ ሰላም ቅ/ሚካኤል
እና በደብረ መድኃኒት ቅ/አማኑኤል አብያተ ክርስቲያናት በድብቅ ሊመጡ ያሸመቁትን አቡነ ፋኑኤልን ሕዝቡ በይፋ ተቃወመ፡፡ እሑድ ከቅዳሴ በኋላ ምእመናን በይፋ ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ሕገ ወጡ ሊቀ ጳጳስ አባ ፋኑኤል ወደ
አብያተ ክርስቲያናቱ እንዳይመጡ በብርቱ ተቃውሞ ቀርቧል። በሌሎች አካባቢዎች የተጀመረው “ቤተ ክርስቲያንን ከነአባ ፋኑኤል እና
ከፕሮቴስታንቱ አጋራቸው ከኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የመታደግ” እንቅስቃሴ በሲያትልም ተጀምሯል። “ምንም አያውቅም” እየተባለ የሚናቀው
ምእመን ለቤተ ክርስቲያኑ የክፉ ቀን ደራሽ መሆኑን እና በሐዋሳ ያለው ሕዝበ ክርስቲያን እንባውና በተጋድሎው ቅ/ሲኖዶስ ኡኡታውን
ሰምቶ ያገኘውን ድል በአሜሪካ የሚገኘውም ምእመን እንደሚደግመው አረጋግጧል።
July 16, 2012
በጀርመን ስለ ዋልድባ ተጠርቶ የነበረ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ በፓትርያርኩ ታገደ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
ደብዳቤውን ይዘናል (PDF Page 5/6)።
(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 9/2004
ዓ.ም፤ ጁላይ 16/ 2012/ READ NEWS IN PDF)፦ በዋልድባ ገዳም ክልል ውስጥ መንግሥት እሠራዋለሁ ያለውን የስኳር ፋብሪካ ግንባታ በመቃወም በጀርመን
ያሉ ማኅበረ ካህናት እና ማኅበረ ምእመናን በፍራንክፈርት ከተማ ሐሙስ ሐምሌ 12/2004 ዓ.ም (ጁላይ 19/2012) በኢትዮጵያ
ቆንስላ ጽ/ቤት ተገኝተው የተቃውሞ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ በጀርመን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ኃላፊ ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርዓዊ ተበጀ አስተላለፈውት የነበረው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አግባብነት እንደሌለው እና ሕዝበ
ክርስቲያኑ ወደ ሰልፉ እንዲወጣ የማድረጉ ጥረት እንዲገታ ቅዱስ ፓትርያርኩ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፉ።
July 14, 2012
July 13, 2012
የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር እንደማይሠራ በድጋሚ አረጋገጠ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁን 21/ 2012/ READ THISARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሥር የሚገኘው የላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን “ከብፁዕ አቡነ ፋኔኡል ጋር እንደማንሠራ እና የሸቱትንም ሾመት የማንቀበል መሆኑን” እንገልጻለን ባለበት መግለጫው አቡነ ፋኑኤል “ከዚህ በፊት ለአህጉረ ስብከቱ ተመድበው አባታዊ መመሪያ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት አባቶች በተለየ መልኩ በመጓዝ ካህናት እና ምዕመናንንን በማሳዘን ለመናፍቃን በር የሚከፍት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓት ባልጠበቀ እና ባልተከተለ መንገድ መመሪያ በመስጠት እና በተግባርም በመፈፀም የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስጠብቅ አካሄደ በመጓዛቸው በሚሠጡት የተሣሣተ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የወጣ አመራር ጋር አብሮ መጓዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት ያለንን አቋም/ አቋማችንን እንገልጻለን” ብሏል።
July 12, 2012
ጠቅ/ቤተ ክህነት “ጉባኤ አርድእት” ነን ባዮች በመንበረ ፓትርያርኩ እንዳይሰበሰቡ አገደ
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
·
እገዳው የተላለፈው መንግሥት ለአባ ጳውሎስ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ
ከሰጠ በኋላ ነው ተብሏል።
·
በአባ ጳውሎስ ቀጥተኛ ይኹንታ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ
ለቀናት በኅቡእ ሲሰበሰብ የቆየው ቡድኑ÷ ከፊል መሥራች አባላቱ ከሸሹትና የስብሰባ እገዳ ከተጣለበት በኋላ÷ ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት
የ‹ዕወቀኝ› ጥያቄ ማቅረቡ ተነግሯል።
· የቅ/ሲኖዶስ እና የጠቅ/ቤ/ክህነት ጽ/ቤቶች÷ ቤተ ክርስቲያን
“ጉባኤ አርድእት” የተሰኘውን ኅቡእ ቡድን እንደማታውቀው ገልጸዋል።
· የኅቡእ ቡድኑ አስተባባሪ ፕሮቴስታንታዊው ኀይለ ጊዮርጊስ
ጥላሁን በአባ ጳውሎስ ትእዛዝ የያዘውን የጠ/ቤ/ክህነቱን መኪና እንዲያስረክብ ተደርጓል።
· አባ ጳውሎስ የእምነት ንጽሕናቸውን በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ
መሠረት ያላረጋገጡትንና ከቡድኑ ቀንደኛ አስተባባሪዎች አንዱ የኾኑትን አባ ሰረቀን በመንፈሳዊ ዘርፍ ም/ሥ/አስኪያጅነት ለመሾም
ማሰባቸው ተሰምቷል።
· “ለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ሲባል የቡድኑን ኅቡእ እንቅስቃሴ
በጥብቅ እየተከታተልነው ነው” /የጠ/ቤ/ክ መመሪያ ሓላፊዎች/።
· “ከጉባኤው አስተባባሪዎች አብዛኞቹ በሚሠሩባቸው ቦታዎች
ተቀባይነት ያጡ ግለሰቦች ናቸው” /የቋሚ ሲኖዶስ ምንጮች/።
July 4, 2012
የታሰሩት የዋልድባ መነኰሳት በነዋሪው ተቃውሞ ለተቃጠለው የፕሮጀክቱ ዶዘር እና ለተጎዱት ሠራተኞች ሓላፊነት እንዲወሰዱ እየተገደዱ ነው
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
·
የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሠራተኞች በአካባቢው ሕዝብ እየተሳደዱ ነው::
·
ነዋሪው ሠራተኞቹን እስከ ማይ ገባ
ከተማ ድረስ እንዳሳደዳቸው ተነግሯል::
·
የዓዲ አርቃይና ማይ ፀብሪ ወረዳዎች ሓላፊዎች በታሰሩት መነኰሳት እየተወዛገቡ ነው::
·
ከዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም የተወሰዱት አምስት መነኰሳት በዓዲ አርቃይ ፖሊስ ጣቢያ
እንደታሰሩ ናቸው::
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 27/2004
ዓ.ም፤ ጁላይ 4/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ሰኔ 23 ቀን 2004 ዓ.ም÷ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ከዋልድባ ሰቋር
ኪዳነ ምሕረት ገዳም የተወሰዱት አምስት መነኰሳት በዓዲ አርቃይ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ በአንድ ቆርቆሮ ቤት ውስጥ እንደታሰሩ መኾናቸውን
የስፍራው ምንጮች ለደጀ ሰላም ገለጹ፡፡
July 1, 2012
ሰበር ዜና - የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም በፌዴራል ፖሊስ ተከቧል
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
·
አራት መነኰሳት በፖሊስ ተይዘው
ተወስደዋል፤ ሌሎቹ መነኰሳት እየተደበደቡ ተበታትነዋል።
·
የገዳሙ የሱባኤ ወቅት በፖሊስ የኀይል
ርምጃ እየታወከ ነው።
·
በዛሬማ ወንዝ ላይ የሚገነባውን
የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ግድብ የሚሠራው ሱር ኮንስትራክሽን ለቆ መውጣቱ እየተነገረ ነው፤ በምትኩ የቻይና ተቋራጭ የገባ ቢኾንም በእርሱም
ላይ ተቃውሞው መቀጠሉ ተሰምቷል።
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 24/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 1/
2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ዓዲ አርቃይ ወረዳ የዋልድባ
ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም ከማይ ፀብሪና ዓዲ አርቃይ ወረዳዎች በአምስት መኪና ተጭነው በመጡ የፌዴራል ፖሊስ ኀይሎች ሥምሪት
ውስጥ እንደሚገኝ የስፍራው ምንጮች ለደጀ ሰላም ገለጹ፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)
Blog Archive
-
▼
2012
(270)
-
▼
July
(15)
- ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም የዋልድባ መነኰሳት ተጠያቂ ተደረጉ
- የአቡነ ጳውሎስ የማዕረግ ስም ላይ “ዓለም አቀፍ የሰላም አምባሳደር” የሚል ተ...
- ዝክረ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ /ሐምሌ 2003 ዓ.ም./
- የፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ በዓለ ሢመት - በሼራተን አዲስ
- የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የፓትርያርክነት ማዕርግ የተቀዳጀችበት የነጻነት በዓል...
- በዋልድባ መነኰሳት ላይ የሚካሄደው እስርና እንግልት ተባብሶ ቀጥሏል
- ልዩ የውይይትና የመረጃ ልውውጥ መድረክ፤ በሲያትል
- For Your Information
- የሲያትል ምእመናን አቡነ ፋኑኤልን በይፋ ተቃወሙ፤ እንዳይመጡም ተስማሙ
- በጀርመን ስለ ዋልድባ ተጠርቶ የነበረ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ በፓትርያርኩ ታ...
- What a Comedy!!!
- የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር ...
- ጠቅ/ቤተ ክህነት “ጉባኤ አርድእት” ነን ባዮች በመንበረ ፓትርያርኩ እንዳይሰበሰ...
- የታሰሩት የዋልድባ መነኰሳት በነዋሪው ተቃውሞ ለተቃጠለው የፕሮጀክቱ ዶዘር እና...
- ሰበር ዜና - የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም በፌዴራል ፖሊስ ተከቧል
-
▼
July
(15)








