- ማኅበረ መነኮሳቱ አስቸኳይ ርዳታ ጠይቀዋል።
- ከብት ዘራፊዎችና ከሰል አክሳዮች የቃጠሎ መንሥኤዎች ናቸው ተብሏል።
- ‹‹ውኃ የለንም፤ የሚረዳን ሰውም የለንም፤ እሳቱ ወደ ትልቁ ደንና ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ሕንጻ
ቤተ ክርስቲያን እየተቃረበ በመሆኑ ከፍተኛ ርዳታ ያስፈልገናል›› /የገዳሙ መነኮስ/
- ገዳሙ በግራኝ ወረራ የመጥፋት፣ በኢጣልያ ወረራ የመዘረፍ አደጋ ገጥሞት ነበር፤ ከ20 ዓመት በፊት ‹‹የኦሮሚያ ነጻነት እስላማዊ ግንባር/ጃራ/›› ገዳሙን ወርሮ
በአካባቢው የሚኖሩ 16 ክርስቲያን አባ ወራዎችን አርዶ ነበር።
(ደጀ ሰላም፣ የካቲት 21/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 29/2012/READ THIS NEWS IN PDF)፦ እንደ ጥድ፣ ዝግባ፣ ወይራ፣ ግራር፣ ብሳና፣ ቀረሮ በመሳሰሉት
አገር በቀል እና ዕድሜ ጠገብ ዛፎች የተሞላውን በአጠቃላይ 13ሺሕ ሄ/ር መሬት ያህል ይሸፍን እንደነበር የሚነገረው የአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ እና አቡነ ሳሙኤል ገዳም በአራት ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ
በተቀሰቀሰ ሰደድ እሳት እየጋየ መኾኑ ተሰማ፡፡








