December 6, 2012

የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ለብፁዕ ወቅዱስ እንዲመለሱ በደብዳቤ ፈቀዱ፤ ደብዳቤውን አጠፉ

  • የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮን ዘገባና ቃለ ምልልስ አዳምጡ::
  •  ደብዳቤዎቹን ከዚህ ላይ ያገኟቸዋል።
(ደጀ ሰላም ኅዳር 27/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 6/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርርዮስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊት ሪፓብሊክ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ደብዳቤ ከጻፉ በኋላ ሐሳቡን ማጠፋቸውን ገልጸዋል:: በችኮላና የሚያስከትለውን “ጣጣና መዘዝ” ባለማገናዘብ በቀናነት የጻፉት ደብዳቤ መሆኑን ያብራሩት ክቡር ፕሬዚዳንቱ “መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ እንደማይገባ” በማስታወስ ደብዳቤያቸው መሳባቸውን አስታውቀዋል።


ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ አቡነ ናትናኤል ጋር መነጋገራቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ በሊቀ ጳጳሱ መገሰጻቸውን አልሸሸጉም። “ይቅርታ አድርጌልኻለኹ” መባላቸውን አብራርተዋል። ስለዚህ ትህትናዎ፣ ክቡር ፕሬዚዳንት ግርማ፣ እናመሰግንዎታለን። ፕሬዚዳንት ግርማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋዶ ቤተ ክርስቲያን 4ኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ሃገር ቤት ተመልሰው ከሁለት የተከፈለችው ቤተ ክርስቲያን አንድ እንድትሆን የሚያሳስብ ደብዳቤ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እና ለብፁዕ አቡነ ናትናኤል መጻፋቸው፣ ምንም እንኳን ዘግይቶ “ቢስቡትም”፣ ሐሳቡ ግን አስደስቶናል። ይበል ብለናል ክቡር ፕሬዚዳንት። እንደ መንግሥት ኃላፊነትዎም ባይሆን እንደ አንድ በሥልጣን ወንበር እንደተቀመጠ ኦርቶዶክሳዊ ሐሳብዎን መግለጥዎ ተገቢም፣ ጥሩም ነው።

ለማንኛውም የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮን ዘገባና ቃለ ምልልስ አዳምጡ።

ቸር ወሬ ያሰማን                                                                                                        


“ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን - ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ”።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡


10 comments:

tesfaye said...

ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ዛሬ ደስ የሚል ታሪክ ነው የሰሩት:: ይህንን ደብዳቤ የጻፉት የተከፈለችው ቤተ ክርስትያን አንድ ሆና ለማየት እንደሆነ ማንም ይረዳዎታል:: ነገር ግን ይሄ ከመቅጽበት ሃሳብዎትን ያስቀየረዎት የኢሕአዴግ ቁንጮ ባለስልጣናት ጥብቅ ማሳሰቢያ እንደሆነ ይገባናል…እርስዎ ግን ሃላፊነትዎን ተወጥተዋል እግዚአብሔር ይባርክዎ

Anonymous said...

ይህ ደብዳቤ ከቤተመንግስቱ ራሳቸውን የሽማግሌዎች የሰላም አፈላላጊ ኮሚቴ ብለው በመሰየም ትልቅ እይታ ለማግኝት በፕሬዝዳንቱ በኩል ደብዳቤ ሲያጽፉ በመጀመሪያ የተቃወሙት እና “እናንተ ይህ ጉዳይ አያገባችሁም” ብለው ቀጥተኛ ምላሽ የሰጡት አቃቤ መንበረ ፓትርያርክ አቡነ ናትናኤል መሆናቸው ደስ ያሰኛል፡፡ እንዲህ አይነቱን የውጭ ተጽዕኖና የማያገባውን ይህን ጉዳይ እናንተ አትወስኑልንም የናንተ ውሳኔ አያስፈልገነም የሚል አይነት አባት መገኘቱ መልካም ነው:: አቶ ግርማም ለአንድነቱ ያላቸውን አቋም ማሳየታቸው መልካም ነው:: ነገር ግን ከቤተ-መንግስቱ በኩልም ሆነ ከማንኛውም የውጭ አካል ቤተክርስቲያኒቱ ላይ ማንኛውንም አይነት ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ደብዳቤ መጻፉ አስፈላጊ አይመስለኝም:: የግላቸውን ሃሳብ ግን ይህ የግሌ ሃሳብ ነው ብለው እንደማንኛውም ክርስቲያን የሚሰማቸውን ነገር በቢሮአቸው ማህተም ሳይሆን በራሳቸው ፊርማ ብቻ ለሚመለከተው ክፍል ማሳወቁ በእጅጉ ያስመሰግናቸዋል::

አባቶች ወደ ስድስተኛው ፓትርያርክ የሚያረጉን ሩጫ እንዲያስቆማቸውና የአንድነቱን ጉዞ እግዚአብሔር እንዲያሳካው የሁላችንም ምኞት ነው:: ከአንድነቱ በኋላ ቀኖና ቤተክርስቲያንን ባገናዘበ መልኩና ከቁጥር ጋር (5 ተብሎ 4 አይባልም) ሳይሆን ከቀኖናው በማይጋጭ መልኩ ለመንበረ ፕትርክናው ቦታ ለቤተክርስቲያን የሚበጃትን በፍቅር ተነጋግረው እንዲወስኑ እግዚአብሔር ይርዳን::
M.M

Anonymous said...

ፕሬዘዳንቱ እነ ታምራት ላይኔ የዛሬ ሃያ አመት በፊት የሰሩትን ስህተት ሊደግሙት ነበር:: ግን ለጥቂት ተረፉ:: የግለሰብ ጉዳይን ከቤተክርስቲያን ጉዳይ ማስቀደም ይህንን የመሰለ ታሪካዊ ስህተት ሊያሰራ ይችላል:: ደጀ ሰላምም ትንሽ ወደ አባ መርቆርዮስ ዘንበል የምትሉትን አስተካክላችሁ ለቤተክርስቲያን ብቻ ስሩ::

Unknown said...

እኔ እንደገመትኩት ፕረዚደንት ግርማ የመንግሥታቸውን የሆነ አካል ስምምንት የተደረሰበትን ጉዳይ ነው የፃፉት ብየ ነው የማምነው። ነገር ግን ጉዳዩ የቤተ ክርስትቲያን ጉዳይ ስለሆነ መንንግሥት ፓትርያርኩ ወደ መንብራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማድረጉ ድሮም መንግሥት አባረራቸው የሚለውን ነገር እንደማመን ስለሚያስቆጥር ሁኖ ሌሎች ከደረሱበት በሁዋላ ፕረዚደንቱ እንዲያስተባብሉ ተገደዋል ብየ አምናለሁ። አሁንም በኔ ግምት ነገሩ ዳላስ ቴክሳስ በ2ቱም ወገኖች እየተደረገ ባለው በአባቶች ጉባዔ ይህ ፕረዚደንቱ ያሉት ነገር ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ብየ አምናለሁ። ከዚያ መንግሥት የድጋፍ መግለጫ ያወጣል እላለሁ። እንዲመለሱ ፈቃጁ ግን አገር ውስጥ ያለው ሲኖዶስ ነው ሁኖ መቅረብ የሚገባው እንጅ መንግሥት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጣልቃ መግባቱን በራሱ ማረጋገጥ አይችልም ነው የምለው። ለማንኛውም 'ተመነዩ ሠናየ ከመ ትረክቡ ሠናየ' ነውና መልካሙን እየተመኝን ውጤቱን ከባለቤቶቹ በዚህ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ እንረዳዋለን። እስከዚያው ድረስ ጸልዩ በእንተ ዛቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፥ አሐቲ ቅድስት ጉባዔ እንተ ሐዋርያት፣ ርትዕት በኀበ እግዜብሔር ። ወካዕበ ጸልዩ በእንተ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት፥ ወማኅበርነ በውስቴታ። ንበል ኩልነ ማኅበረነ ባርክ ወዕቀብ በሰላም። ዓሜን.

Anonymous said...

Minu New Des yemilew 20 Ametat Yekoye neger-Yehayimanot neger -yesirat neger Bepirezidan Girma tiezaz Yisitekakelal Malet new ?Meto Aleka Girma Betenagerutis Meche Koyu Yemilutin Ayawikutim Malet New Weyim Sile Betekirsityanachew Yemiyawkutt neger yelem Negeru Yasgermal Asastewg New Yalachew Sewch Maninetim Metawek Alebet Elalehu Leman Asibew New Melyayetin Lematsifat Abatoch ( Shimagilewoch ) Eyedekemu Sewn Sayanegagiru -Sadekumu - Sinodosun Saytseyiku Yemastarek Neger sayiseru Yigibu Malet Min Malet New ? Abune Natinaeil Talk Abat Mehonachew Teregagitsal

Anonymous said...

ቤተ ክርስቲያናችን ለ 20ዓመታት በ ሁለት ሲኖዶስ ስተመራ የቆየችው እኮ የቀድሞው ፓትርያርክ በህይወት እያሉ ለምን ሌላ ፓትርያርክ ተሾመ በሚል የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ነበር። እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ አንደኛው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድነት ለመመለስ ግልጽና ትክክል የሆነው እርምጃ (most logical approach) በይህወት ያሉትን ፓትርያርክ ለመላዋ ቤተ ክርስቲያን መሪ ማድረግ ነው። ይሄ ለምን ድርድር እንደሚያስፈልገውና ከባድ እንደሆነ ለህዝብ ግልጽ አይደለም።

Anonymous said...

እግዚአብሔር ልቦን ይባርከው፤ ቅን ልብ አሎት።

Anonymous said...

ከላይ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የፕሬዚደንቱ ሃሳብ ደግፈው ሲፅፉ ያላዩት ነጥብ አለ። ለሚደግፉት ነገር ሲሆን የመንግስት ጣልቃገብነትን ይበል ሊሉ፤ለማይደግፉት ነገር ሲሆን ደግሞ ሊቃወሙት ይሄ አያስኬድም። አቡነ ናትናኤል ግን አኮሩን። እንዲህ አይነት አባት ነው እሚያስፈልገው።የደጀሰላም ወደ አቡነ መርቆሬዎስ ዘንበል ማለቱ እኔም አሳስቦኛል። ምህረቴ

Alemneh said...

ከላይ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የፕሬዚደንቱ ሃሳብ ደግፈው ሲፅፉ ያላዩት ነጥብ አለ። ለሚደግፉት ነገር ሲሆን የመንግስት ጣልቃገብነትን ይበል ሊሉ፤ለማይደግፉት ነገር ሲሆን ደግሞ ሊቃወሙት ይሄ አያስኬድም። አቡነ ናትናኤል ግን አኮሩን። እንዲህ አይነት አባት ነው እሚያስፈልገው::


ፕሬዝዳንት ግርማ የጸፉት ደብዳቤ መስተካክሉ ትክክል ነዉ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በቤተክርስቲኑ ላይ የመወሰን ሥልጣን የሲኖደሱ ነው እንጂ የግለሰቦችም ሆነ የመንግስት አይደለም፡፡ከዚህ በፊት በጣልቃ ገብነት ቤተክርስቲን ለ21 ዓመት ተለያይታ ቐይታለች፡፡ ስህተት ደግሞ በስህተት አይታረምም፡፡ ሲኖደሱ የፕሬዝዳንት ግርማ እና የቨማግሌዎቹን መልካም ሀሳብ ተቀብሉ በፀ አባታችንን ወደ መንበራቸው ቢመልሳቸዉ የቤተክርስቲን አንደነት ለማምጣታ ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ መልካም የሚሆነው ቤተክርስቲን በራሷ በሆነው ሃይማኖታዊ መንገድ የሚመለከተው አካል ሲያስፈጽም ነው፡፡ለሁሉም ነገር ሰኬትማነት የሁሉም ምዐመን ተሰትፉ ከምንም በላይ ወሳኝ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ፕሬዝዳንት ግርማ እንደ አንድ ምእመን ላሳዩት እጀግ ለሚደነቅ ጥረት እግዚሔብሄር ይባርካቸው፡፡

እግዚሔብሄር ለሁላችንም የዕርቅ ልቦና ይስጠን!!!
አሜን፡፡

Anonymous said...

Abune Natnael Beewnet lebetekrstiyan yemiseru abat mehonachewn aweqn.Pre.Girmam beyewahnetna lebetekrstiyan bemeqorqor madreg yalebachewn adrgew neber behuala hasabachewn endiqeyru bigededum poletica wst slalu ayferedbotm.Abune natnael gn eskemechereshawa sekond dres lebetekrstiyan andnet sertew wtetunm aytew lemedeset yabqawot.Yagoresachhun ej yemtneksu hod aderoch ebakachhu lehlinachhuna legeta tazezu.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)