December 9, 2012

የዕርቀ ሰላም ውይይቱ ተጠናቋል - ዛሬ መግለጫ ይሰጣል፤ በአቡነ መርቆርዮስ ጉዳይ ተጨባጭ ስምምነት ላይ የተደረሰ አይመስልም


(ደጀ ሰላም ኅዳር 30/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 9/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በአሜሪካዋ የቴክሳስ ግዛት ዳላስ ከተማ ከኅዳር 26/2005 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የሰነበተው የአባቶች ዕርቀ ሰላም ውይይት በመልካም ሁናቴ በመካሔድ ላይ ቆይቶ ቅዳሜ የተጠናቀቀ ሲሆን ዛሬ እሑድ መግለጫ በመስጠት ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል።

በአጀንዳዎቹ ላይ በመግባባትና በመከባበር ውይይቱን ያደረገው ጉባኤው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከሥልጣናቸው እንዴት ሊወርዱ እንደቻሉ በአገር ውስጥም በውጪው የሚገኙት አበው ልዑካን የታሪክ ምስክርነታቸውን ከሰጡ በኋላ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ኢትዮጵያ  መመለስ አስመልክቶ ረቡዕ ዕለት ሰፊ ውይይት መደረጉንና ሳይጠቃለል በይደር መገታቱን መዘገባችን ይታወሳል።


በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ባሉ አባቶች እና ምእመናን ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የአራተኛው ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ጉዳይ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ በሆነበት በዚህ ጉባዔ ከሁለቱም ወገን የተለያየ ሐሳብ ከመቅረቡ አንጻር ለጊዜው ከስምምነት ላይ የተደረሰበት አይመስልም።

ከአገር ቤት የመጣው ልዑክ “ቅዱስነታቸው በመረጡት ቦታ በጸሎት ተወስነው ይቀመጡ” ሲሉ በውጪ የሚገኙት አበው ደግሞ “ከነሙሉ ማዕረጋቸው ወደ መንበራቸው ይመለሱ” የሚለውን ሐሳብ አቅርበዋል። በሁለቱም በኩል ሐሳቡ ዕልባት ሳይሰጠው ቀርቷል። ጉባዔው ዛሬ መግለጫውን ሲሰጥ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ በሌላ ጊዜ ድጋሚ ተገናኝቶ ይወያይ እንደሆነ የደረሰበትን የውሳኔ ሐሳብ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ስለ አቡነ መርቆርዮስ መመለስ ግልጽ ደብዳቤ የጻፉትን የፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስን ሐሳብ አስመልክተው ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ ቃለ ምልልስ የሰጡት ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ አቡነ ናትናኤል ከትናንት በስቲያ አርብ “ፓትርያርኩ በተወሰነላቸው ቦታ እንዲቀመጡና ለአገራቸው አፈር እንዲበቁ” እንጂ ሌላ ነገር እንደማይጠበቅና እንደማይወሰን መናገራቸው የዕርቅና የሰላም ውይይቱ ሳይጀመር የተፈጸመ አስመስሎት ሰንብቷል። ለሰላም ውይይት ምንም ዓይነት በር መዘጋት እንደሌለበት ከማመን አንጻር አሁንም ውይይቱ እንዲቀጥል የሁሉም ተስፋ ነው። የመግለጫውን ሙሉ ሐሳብና ዝርዝር ጉዳዩን እንደደረሰልን እናቀርባለን።

“ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን - ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ”።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

41 comments:

Solomon Berhe said...

ጥሩ ዜና አይደለም::
ግን ሁላችንም ተስፋ አድርገን ነበረ፥፥

Anonymous said...

pirezdent Girima Melkam Aderegu Ahun
1 Mengisitu Hayile Mariam Keserawitu Ethiopia Gebito Menberun Meekeb Alebet Bilew Mefikedi Alebachew
Abune Merkorewos Kekibirachew Sinodos Asketilew Kegebu Mengisitu Hayile Mariam Lemin Yileyal ?

Anonymous said...

ከዚህ በፊት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በዚህ ጉዳይ እንቢተኛ እንደሆኑ ነበር የሚነገረን የነበረው ግን አይደሉም:: አባ ጳውሎስን እስካሁን ብዙ ስለወቀስኳቸው አምላኬን ከልቤ ይቅርታ እጠይቀዋለሁ:: አቡነ ጳውሎስን ነፍሳቸውን እግዚአብሔር በገነት ያኑርልን:: ምንም እንኳን ተሐድሶዎች የልብ ልብ የተሰማቸው በሳቸው ዘመን ቢሆንም መስራት የሚችሉትን ብዙ መልካም ስራዎችም ስለሰሩ ከልቤ ላመሰግናቸው ወደድኩ:: ለተሐድሶዎች የልብ ልብ እንዲሰማቸው ያረጉትም እሳቸው ተሐድሶ ስለሆኑ ሳይሆን በፍቅር ከቀረብኳቸው ይመለሱ ይሆናል በሚል ይመስለኛል:: አቡነ ጳውሎስ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው እኛ ጥቂት የምንለውን መልካም ስራ የሰሩት:: ለዚህም ታላቅ አክብሮት ይገባቸዋል:: ብዙ ተስፋ የጣልንባቸው የተቀሩት አባቶቻችን ግን ምንም ፈተና በሌለበት ቀኖናን ተከትለው “ይህች ሹመት (ፓትርያርክነት) በአንድ ዘመን በአንድ ሀገር ለሁለት ሰዎች ልትሆን አይገባም። ይህ በአንድ ሀገር ከተደረገ ግን አስቀድሞ ለተሾመው ትጽና።” (ፍትሐ ነገሥት ፍትሕ መንፈሳዊ ዐቢይ አንቀጽ 4 ንኡስ ቁጥር 70-78) በሚለው የቤተክርስቲያን ቀኖና መሰረት በህይወት ያሉትን ኣባ መርቆሬዎስን ከአስተዳደር ጉዳዮች ርቀው ግን መንበሩን እንዲይዙ ማረግ ሲችሉ አንድም ነገር ማረግ ባለመቻላቸው በጣም ነው የምናዝነው:: አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በፈለጉት ገዳም በጸሎት ተወስነው ይቀመጡ የሚለውንማ አቡነ ጳውሎስ እያሉም ተወስኖ ነበር:: አሁን የሁላችንም የክርስቲያኖቹ ፍላጎት የነበረው ድጋሚ ቀኖና እንዳይጣስ ነበር:: አቡነ መርቆሬዎስ ቡራኬ ላይ ብቻ እንዲሳተፉ ፓትርያርክ የሚለውን ስም እንደያዙ እንዲቆዩ: የጳጳሳት ሹመት ሲያስፈልግ ፓትርያርክ እንደመሆናቸው መጠን እሳሸው ሹመት እንዲሰጡና ሌሎች መንፈሳዊ ጉዳዮችን እንዲፈጽሙ ከአስተዳደር ጉዳይ ግን እንዲገለሉ ነበር የሁላችን ፍላጎት:: እሳቸው በህይወት እያሉ ስድስተኛ ፓትርያርክ እንዳይሾም ነበር ፍላጎታችን:: ሌላ የአስተዳደር ጉዳዮችን በተመለከት እንደራሴ ተሹሞ ከዋና ስራአስኪያጁ ጋር እንዲሰሩ ነበር የክርስትያኑ ፍላጎት:: ግን ምን ያረጋል ለቤተክርስቲያን ቀኖና እና ለመንጋው የሚጨነቅ አንድም አባት ባለመኖሩ ውሳኔው ሁሉ ያልጠበቅነው ሆነ:: ከዚህ በላይ መጻፍ አልቻልኩም:: በፍቅር ያሳደግችኝ ቤትክርስትያን ፍቅር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያስተማረችን እናት ቤተክርስትያን ግብረገብነትን ያስተማረችኝ ቤተክርስቲያን ዘሬ በውስጧ ፍቅርን በተግባር ማሳየት ሲያቅታት እጅግ ያንገበግባል:: ፍቅር ከውስጧ ሲጠፋ በፍቅር መጥፋት የተነሳ ልጆችዋ ሲበተኑባት እጅግ ያንገበግባል:: ሰይጣንን እንዴት አድርገን ድል መንሳት እንዳለብን ያስተማረችን ቤተክርስቲያን ጥንተ ጠላታችን ዲያቢሎስ በልጆችዋ መሃል ገብቶ መንጋውን ሲበጠብጥ እንዴት አድርጋ ድል መንሳት ሲያቅታት ማየት እጅግ ያንገበግባል:: አባቶቻችን ቢበትኑንም እኛ ግን እንዴት መሰባሰብ እንዳለብንና መበታተን እንደሌለብን መጻፍ ፈልጌ ነበር ግን እንባዬን መቆጣጠር ስላልቻልኩ ጽሁፌን በዚሁ ልግታው::

መኮንን (ዶ/ር)

Anonymous said...

What kind of talk of peace and reconciliation is expected hereafter? Do you mean you have to waite for the natural passing way of Abune Merkorios and then the harmful ego of those so-called Abatoch will be quinched and the Church will be reunited? This sounds very ugly ?

Anonymous said...

ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ዛሬም አቡነ መርቆሬዎስ በመንበራቸውም ባይሆን በሕይወታቸው አሉ፡፡
እኒህ አባት ላለፉት 21 ዓመታት ድምጻቸው በበጎም በክፉም ተደምጦ አያውቅም፡፡ የሚያውቅ ካለ ይናገር፡፡ 21ዓመት ቱርጁማንና ዲስኩረኞች ሲወጡ ሲወርዱ፣ሲዋረዱ ሲያልፉ ማየትን የመሰለ ድንቅ የእግዚአብሔር ሥራ ከየት ይገኛል፡፡ ከሳሾቻቸው የሉም፣ ሴረኞቹ ትቢያ ሆነዋል፣ አሉባልታ አናፋሾቹ ነፋስ እንደሚወዘውዘው ሸንበቆ ወዲህና ወዲያ ይማታሉ፤ ሺህ ቢታለብ በገሌ እንዳለችው ፍጥረት ሺህ ጊዜ ቢማስኑ አቡነ መርቆሬዎስን ከጽኑዕው መሠረት ማናጋት አልተቻለም፡፡
እኔን የገረመኝ በእነዚህ 21 ዓመታት የአቡነ መርቆሬዎስ አርምሞ ከእልፍ በላይ እየተናገረ መሆኑ ነው፡፡ የአርምሞ ስብከት፣ እርሳቸው ዝም ሲሉ እግዚአብሔር ሥራውን የሚሰራበት፡፡
ምዕመናንም ሆኑ፣ አባቶቻችን መሪዎቻችን ሊገነዘቡት የሚገባው ነገር ቢኖር በመቀባባት ማጠልሸትና ማስጠላት ይቻላል፣ ሕዝብን ማወናበድ፣ ሥልጣንን ማደርጀት ይቻል ይመስላል፤ ለጊዜው፡፡ ጊዜው ሲደርስ የእግዚአብሔርን ሥራ ማን ይሞግታል፤ ማንስ እንዳይሆን ሊከለክል ይችላል፡፡ አቡነ ጳውሎስ የሉም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የሉም፣ ታምራት ላይኔ የሉም፣ ሌሎች በአፍአ የማይታወቁ ሴረኞች የሉም፣ አቡነ መርቆሬዎስ ግን አሉ፤ ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ ብሎ እግዚአብሔርን ማመስገን ግድ አይልም፡፡ ሲወገዝ የኖረው፣ ሲጠላ የኖረው፣የክስ ዶሴ ሲከመረበት የኖረው አረጋዊው አቡነ መርቆሬዎስ ግን ዛሬም በእግዚአብሔር እስትንፋስ አለ፡፡ ይህ ነገር ከእግዚአብሔር ይሆንን? ብሎ የሚጠይቅ ልቡና ያለው ምዕመን ይኖር ይሆን?

Anonymous said...

Medhane Alem melkamun yasasebachew egnanim ger lib yisten. Ancient Ethiopia, yeEthiopia politica chigr kaltefeta yebetechrstian chigir ayifetam balew alesmamam. Yebetechrstian chigir ketefeta bicha new yeEthiopia chigir mefetat yemichilew. Chigiru systemic new. Gejiw party siltan bilek enquan yezeregaw mesmer yetefelegewin lewit lebetechrstian liameta aychilim. Betechrstian yerasuan yewist chigir kerfa sile hagerena hizib, sile selamena fikir meregagat, sile limatena equilinet,... mesbek menager timihirtuan menagnet sitichil bicha yeethiopia chigir yikerefal yemil hassab alegn. yebetechrstian chigir eko ye20 amet chigir bicha ayidelem, kenegestatu yijemiral. Lebetechrstian yetemechat alneberem, yahun base enji, mastekakel lewit mamtat yetemeche hone sale... Kesiltan yilik lemengaw yemiasib meri balemagignetua ayidel yetechegerechiw? It is not a matter of bringing Abune Merkorios back or electing a new one per se that matter. Degemos menfes kidus new yemimertew silu negerewin yele ende? Tadya yemenfes kidus fekad sint new? Minew lehawariayt yetelemene egziabiher ahun telewote ende! God forbid! I think we need to remember what has happened in Russian Orthodox church, but take some lessons from Coptic church.

Anonymous said...

All expected! they are gaming. both sides are not our fathers.

Anonymous said...

በጣም አሳዛኝ ዜና ነው። አባቶች የቤተክርስቲያን የባሰ ጥፋት እንዴት እንዳልታያቸው ግራ ይገባል። ማንኛውም መስዋትነት በመክፈል የቤተክርስቲያንን አንድነት፤ ሰላም ማምጣት ይጠበቅባቸዋል። ሌላ ጊዜ ፤ በሌላ ስብሰባ የሚለው ሃሳብ በፍጹም የማይመስል ነገር ነው። ይህን እየሰማን ምዕመናን ዝም ማለት ያለብን አይመስለኝም። አባቶችን በእንባ ሆ ብለን ወጥተን ልንማጸን ፤ ስብሰባው እንዲቀጥል ልናደርግ ያስፈልጋል። ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስም በአካል ቀርበው ስለትዕትና የአምላካቸውን ፈለግ እንዲከተሉ እና ሃሳባቸውን እንዲለውጡ ፤ በኢትዮጵያ ያለውም ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ዛሬውኑ ሃሳቡን እንዲያሻሽል ሊደረግ ይገባል። አሊያ ግን ሁለት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ለመመስረት እየተዘጋጁ እንደሆነ ይወቁት። ለእኔ የምዕመናን ድርሻ አሁን ነው። በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ ምዕመናን በሙሉ ሁሉንም አባቶች አሁን መፍትሔ ካላመጣችሁ (በሰላም ካልባረካችሁን) እንደ ኤልሳ አንለቅም ልንላቸው ይገባል።

Anonymous said...

ደጅ ሰላም እድሜ ይስጥልኝ። አኔ እንደው አዲሱ አበበ አቡነ ናትናኤልን ደውዬ አገኘዋቸው ሲል ስሰማው ሰውነቴን ውርር ነው ያደረገኝ። ለምን ቢባል፡- 1ኛ - ምነው አዲሱ ትንሽ እስከፍፃሜው ቢታገስ በሚል 2ኛ - አቡነ ናትናኤል የተጀመረውን የሰላም ውይይት የሚበርዝ ነገር ይናገሩና ሳይጀመር ሊጠናቀቅ ነው የሚል ስጋት ስላደረብኝ ነው። መቼም የፈሩት ይደደርሳል ሆነና፤ አዲሱም ትዕግስት አጣ። እርሳቸውም እስኪ ልዑካኑ የደረሱበትን ሰምቼ በኋላ እንነጋገር በማለት ፈንታ እንደፈራሁት የፈራሁትን ተናገሩ። እንደኔ እንደኔ ሁለቱም ደግ አላደረጉም።
ደጅ ሰላም ግን ምንም እንኳን ጉዳዩ አሁን ያለበት ሁኔታ ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢሆንም ተስፋ ሰጪ አድርጋችሁ በመዘገባችሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ሳልል ባልፈው እኔኑ እታዘዋለሁ። ምክንይቱም ቃለ ምልልሱን ከሰማሁ በኋላ ክፉ ክፉውን እያሰብኩ ነበርና ደጅ ሰላምን የከፈትኩኝ።

እስኪ አሁንም አሁንም ቸር ያሰማን።

Samuel said...

ከሃገር ቤት የመጡት አባቶች እኮ ላይስማሙ ተስማምተው ነው የመጡት!
አቡነ ናትናኤል ለVOA የተናገሩትን ሰምተናል፣ የሃገር ቤቱ ሲኖዶስ የወሰነውን ውሳኔ አይተናል!

እርሱ ሁሉን የሚያይ አምላክ የፈርዳል! ቢዘገይም የሚቀድመው የለምና ተስፋችን የድንግል ማርያም ልጅ ቸሩ መድኃኔዓለም ነው!!!

ለእውነተኛው እና ህጋዊው ፓትርያርካችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አምላከ ቅዱሳን አሁንም ጤናቸውን ሰጥቶ በህይወት አቆይቶልን ከነ መንበራቸው ለሚወዷት ሃገራቸው በቅተው ለማየት እኛን ያብቃን! የቅዱስነታቸው ቡራኬያቸው አይለየን!!!

Anonymous said...

እንደ ክርስትናማ ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያም ያሉት “አባታችን ይምጡና የበላይ አባታችን ሆነው ይባርኩንም ቤተክርስቲያኗንም ያስተዳድሩ ሰይጣን ይፈር” ማለትና ውጭ ያሉት የቀድሞው ፓትርያርክ ደግሞ “ሰይጣን ይፈር ስልጣን ስጡኝ ብዬ አልከራከርም ምዕመንም በኔ ምክንያት አይበተንም:: አንዱ ገዳም ዘግቼ በጸሎት ተወስኜ ዘመኔን እጨርሳለው” ማለት ነበር:: ግን የተገላቢጦሽ ሆነ ነገሩ ዘመኑ መቼም ዘመነ ምን ልበላችሁ አሳፋሪ ነው

Dawit said...

እኔን ያሳዘነኝ ለቤተክርስቲያን የሚያስቡ መስሎኝ እነሱን ተከትዬ የክፍፍል ሰለባ መሆኔ። አልቦ ጳጳስ።

Anonymous said...

ከእንግዲህ የኔ ማንነት መገለጫ አርቶዶክስ ብቻ ነውን? አይመስለኝም ኢትዮጵዊነቴም የማንነቴ መገለጫ ነው ከገለልተኝነት ወጥተን በግፍ ከተሰደዱት አባቶቸ ጋር ወያኔ እስኪወድቅ እግዚአብሄርን አመለካለሁ ቤተክርስቲያኔ ላይ የቀለዱትንም ወያኔወች ባለኝ እውቀትና ሀይል እስከመጨረሻው እፋለማቸዋለሁ እግዚአብሄርም ይረዳናል ሆዳሞችንም ያሳፍርልናል ትግላችንንም ኢሳትን በመደገፍ እንጀምር ሁላችንም የገጠር ቤተክርስቲያንንን ገዳማቱንና ድሀ ወከመርዳት ውጭ የቤተክህነቱን ኪስ ከመሙላት እንታቀብ ቤተክርስቲያናችን የወያኔ ስራ አስፈጳሚ ጳጳሳት የግል ንብረት ከመሆን ነፃ ትሆ ናለች ::

Anonymous said...

ወይ የቤተክርስቲያን ፓለቲካ! አባቶች ሆይ እባካችሁ የመንፈስ ቅዱስን ዕቃ ጦር ታጠቁ ሌላው ይቅርባችሁ!!!

Anonymous said...

ከዚህ በፊት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በዚህ ጉዳይ እንቢተኛ እንደሆኑ ነበር የሚነገረን የነበረው ግን አይደሉም:: አባ ጳውሎስን እስካሁን ብዙ ስለወቀስኳቸው አምላኬን ከልቤ ይቅርታ እጠይቀዋለሁ:: አቡነ ጳውሎስን ነፍሳቸውን እግዚአብሔር በገነት ያኑርልን:: ምንም እንኳን ተሐድሶዎች የልብ ልብ የተሰማቸው በሳቸው ዘመን ቢሆንም መስራት የሚችሉትን ብዙ መልካም ስራዎችም ስለሰሩ ከልቤ ላመሰግናቸው ወደድኩ:: ለተሐድሶዎች የልብ ልብ እንዲሰማቸው ያረጉትም እሳቸው ተሐድሶ ስለሆኑ ሳይሆን በፍቅር ከቀረብኳቸው ይመለሱ ይሆናል በሚል ይመስለኛል:: አቡነ ጳውሎስ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው እኛ ጥቂት የምንለውን መልካም ስራ የሰሩት:: ለዚህም ታላቅ አክብሮት ይገባቸዋል:: ብዙ ተስፋ የጣልንባቸው የተቀሩት አባቶቻችን ግን ምንም ፈተና በሌለበት ቀኖናን ተከትለው “ይህች ሹመት (ፓትርያርክነት) በአንድ ዘመን በአንድ ሀገር ለሁለት ሰዎች ልትሆን አይገባም። ይህ በአንድ ሀገር ከተደረገ ግን አስቀድሞ ለተሾመው ትጽና።” (ፍትሐ ነገሥት ፍትሕ መንፈሳዊ ዐቢይ አንቀጽ 4 ንኡስ ቁጥር 70-78) በሚለው የቤተክርስቲያን ቀኖና መሰረት በህይወት ያሉትን ኣባ መርቆሬዎስን ከአስተዳደር ጉዳዮች ርቀው ግን መንበሩን እንዲይዙ ማረግ ሲችሉ አንድም ነገር ማረግ ባለመቻላቸው በጣም ነው የምናዝነው:: አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በፈለጉት ገዳም በጸሎት ተወስነው ይቀመጡ የሚለውንማ አቡነ ጳውሎስ እያሉም ተወስኖ ነበር:: አሁን የሁላችንም የክርስቲያኖቹ ፍላጎት የነበረው ድጋሚ ቀኖና እንዳይጣስ ነበር:: አቡነ መርቆሬዎስ ቡራኬ ላይ ብቻ እንዲሳተፉ ፓትርያርክ የሚለውን ስም እንደያዙ እንዲቆዩ: የጳጳሳት ሹመት ሲያስፈልግ ፓትርያርክ እንደመሆናቸው መጠን እሳሸው ሹመት እንዲሰጡና ሌሎች መንፈሳዊ ጉዳዮችን እንዲፈጽሙ ከአስተዳደር ጉዳይ ግን እንዲገለሉ ነበር የሁላችን ፍላጎት:: እሳቸው በህይወት እያሉ ስድስተኛ ፓትርያርክ እንዳይሾም ነበር ፍላጎታችን:: ሌላ የአስተዳደር ጉዳዮችን በተመለከት እንደራሴ ተሹሞ ከዋና ስራአስኪያጁ ጋር እንዲሰሩ ነበር የክርስትያኑ ፍላጎት:: ግን ምን ያረጋል ለቤተክርስቲያን ቀኖና እና ለመንጋው የሚጨነቅ አንድም አባት ባለመኖሩ ውሳኔው ሁሉ ያልጠበቅነው ሆነ:: ከዚህ በላይ መጻፍ አልቻልኩም:: በፍቅር ያሳደግችኝ ቤትክርስትያን ፍቅር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያስተማረችን እናት ቤተክርስትያን ግብረገብነትን ያስተማረችኝ ቤተክርስቲያን ዘሬ በውስጧ ፍቅርን በተግባር ማሳየት ሲያቅታት እጅግ ያንገበግባል:: ፍቅር ከውስጧ ሲጠፋ በፍቅር መጥፋት የተነሳ ልጆችዋ ሲበተኑባት እጅግ ያንገበግባል:: ሰይጣንን እንዴት አድርገን ድል መንሳት እንዳለብን ያስተማረችን ቤተክርስቲያን ጥንተ ጠላታችን ዲያቢሎስ በልጆችዋ መሃል ገብቶ መንጋውን ሲበጠብጥ እንዴት አድርጋ ድል መንሳት ሲያቅታት ማየት እጅግ ያንገበግባል:: አባቶቻችን ቢበትኑንም እኛ ግን እንዴት መሰባሰብ እንዳለብንና መበታተን እንደሌለብን መጻፍ ፈልጌ ነበር ግን እንባዬን መቆጣጠር ስላልቻልኩ ጽሁፌን በዚሁ ልግታው

Anonymous said...

+++
"ወደ ቤትም ስትገቡ ሰላምታ ስጡ ቤቱም የሚገባው ቢሆን ሰላማችሁ ይድረስለት ባይገባው ግን ሰላማችሁይመለስላችኋል::" ማቴ. 10:12᎐3

Anonymous said...

Ahun Abirew Kedisewal begelelitega Debir Abirew Wilewal Wigizetu Tenesitowal temesigen Geleltega Debir Yemibal yelem Hulunim Eyewesedin Mebarek New Ahun Degimo Min Tametsu Yihon ? geleltega -yehager -yesidetega yemil neger kere

Unknown said...

ከጌታ ቃል በላይ ምን አምክንዮ/ሎጅግ ሊኖር ይችላል ? ጌታ ራሱ እኮ ግልጽ ባለ ቃል ተናግሮታል ፣"አልቦ ገብር ዘይክል ለክልኤ አጋእዝት ተቀንዮ ፤ ወእመ አኮ አሐደ ይጸልእ ፥ ወለካለኦ ያፈቅር። ወእመአኮ ለአሐዱ ይትኤዘዝ ፥ ወለካልኡ ኢይትኤዘዝ። " (ማቴ.6 ቁ.24)ታድያ ይህ ቃለ መለኮት እንዴት ሊሆን ይችላል ? በእውነት አገር ውስጥ ያሉት 'አባቶች' ለማን እየተገዙ ነው ? ለማንስ እየታዘዙ ነው ? ለዓለማዊው መንግሥት ወይስ ሰማያዊውን መንግሥት ለምትወክለው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ? ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ትላንትም ሆነ ዛሬ እየተጣሰ ያለው ለዓለማዊው መንግሥት መገዛትን በመረጡ የቤተ ክርስቲያኒቱ 'አባቶች' ነው። ታድያ እኔ እንደ አንድ ምዕመን እነዚህን 'አባቶች' 'ብፁአን' ብየ እንድቀበላቸው የትኛው ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ነው የሚያስገድደኝ ? 'ሲኖዶሳቸውንስ'በምን መስፈርት ነው 'ቅዱስ' በሚል ቃል እንድጠራው የምገደደው ? 'ቅዱስ' የሚለው ቅጽል እኮ እራሱ እግዜብሔር በአፈ መላእክት 'ቅዱዱስ ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ እግዜብሔር ፀባዖት ፍፁም ምሉዕ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ' እየተባለ የሚመሰገንብትን ቅዱስ ቃል እኮ ነው ለነዚህ አባቶች ጉባዔ እንድንሰጠው እየተጠበቀ ያለው። እረ እንዴት አድርገን ነው 'ሲኖዶሳቸውን ቅዱስ ' እያልን የምንጠራው ? አያስቀስፈንም ? ቅዱስ እግዜብሔርን እንደ መፈታተን አይሆንብንም? ይደልዎ ብሎ የመረጠውን ፓትርያርክ አሰድዶና ዓለማዊ መንግሥት የመረጠውን ታማኝ አገልጋዩን 'ፓትርያርክ ' ብሎ የተቀበለን ቡድን ፥ ሐዋርያት በ50 ዓ.ም እንዲሁም ሠለስቱ ምዕት በ325 ዓ.እ በመሠረቱት እውነተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ ስም እንዴት እንጥራው ? ሕግ አፍርሶ ሕጋዊነት በየት አገር ነው ያለው ? አዎ በእኛይቱ አገር ብቻ ! 'ወቀደምትኒ ይከውኑ ድኅረ'የተባለው ደርሶብናል !አንቲኒ ምድረ ኢትዮጵያ ! ዘተሰየምኪ ቅድመ ሀገረ እግዚአብሔር ፥ ለምንት ኮንኪ ዮም ሀገረ አላውያን ወሐሳውያን ? እስከ ማእዜኑ ታከብዲ ልበኪ ? ለምንት ታፈቅሪ ከንቶ ወተሓሢ ሐሰተ ? አእምሪ ከመ ተሰብሐ እግዚአብሐር በውሉድኪ ቅዱስ ያሬድ ወበቅዱስ ተክለ ሃይማኖት። ተመየጢ ፥ ተመየጢ ኢትዮጵያ ኃበ ጥንተ ክብርኪ ፥ ይሔይሰኪ ከመ ትኩኒ ሀገረ እግዚአብሔር ከመ ዘትካት! እንደኔ ልባችሁ በሀዘን የተሰበረ እንዲህ እያላችሁ በዜማ ቆዝሙ ፥ አልቅሱ ከማለት ሌላ ምን እላለሁ ?ሀዘናችንን ሰምቶ የሀገራችንንና የቤተ ክርስቲያንን ትንሣኤያቸውን ለማየት ያብቃን ። ዓሜን.

Anonymous said...

Ejig betam yemiyasazin sira newu yeteseraw. Ahunim betekristiyanua bepoletika yailoch teneksa endeteyazech yemiyamelakt newu! Gudayu sileabune merkorios aydelem. sile Betekristiyanua hig newu. ande gize yehone bota lay begulbet tetase...negeru alfo lela huneta tefetere. endegena higua metas albet? ewunet yihe wusane ahun silalune papasat sebe'a ayenagerem??? kelay Mekonen (dr.) tesemagna yalewu aynet simet newu yetesemagne. Bachiru abune merkorios wode menberu endaymelesu "mengist" akuam endeyaze yemiyamelaktewu yesemonu ye presidant Girma debdabe ena keziya behula yehonewu neger newu. Biyanse endet papasatu talqagebenetun endemikawomut endet mawok altechalem?! Papasnet mendin newu? Kristiyanenet mindin newu?

Anonymous said...

ለምን በግብጵ አንመራም የኛወቹ እንደሆኑ ተገንዘው ሳለ ገና ፎቅ በመስራት ላይ ናቸው ዘረኞች

የታደለ said...

ደጀሰላማዊያን ይሄንን የሰላም ሂደት በሚፈለገው መንገድ ሁሉ ስናግዝና ስናበረታታ ለነበርን ምዕመናን አባቶቻችን የምንጠብቀውን የአንድነት የምስራች ሊያሰሙን አልቻሉም። ምንም እንኳን ዝርዝሩን ለመስማት በመጠባበቅ ላይ ብሆንም እስካሁን የምንሰማው ነገር ሁሉ አባቶቻችን ጊዜ ማባከን የመረጡ ይመስለኛል። እንግዲህ አባቶቻችን ሊሲሙን ካልወደዱ ከአሁን ሰአት ጀምሮ ብጹዕ አቡነ መርቆሪዎስን በፕትርክናቸው እና በአባትነታቸው ተቀብለን በየቤተክርስቲያኑ መጥራት ብንጀምር ትልቅ ዘመቻ ይመስለኛል። እናት ቤተክርስቲያንን ብለን እስከዛሬ የተቀበልነው መስዋዕትነት በቂ ነው። አሁንም የሚገደን የቤተክርስቲያን አንድነት ነው እንጂ ሌላ አይደለም። በዚህ ሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የቤተክርስቲያን ልጆች ትክክል የሆነውን ነገር የማድረግ መንፈሳዊ ግዴታና ኃላፊነት ያለብን ይመስለኛል። ከአዲስ አበባ የሚሰማው ሁሉ የሰላሙን ሂደት የሚያግዝ አይደለም። መንበሩ ባዶ ሆኖ ሲያዩት ለሚገባው አባት ለመስጠት እንዳሳሳቸው ግልጽ ነው። ስለዚህ በእናት ቤተ ክርስቲያን ስር ላለን ኦርቶዶክሳዊያን ለዚህ ጥሪ መልስ እንዲሰጡ በቤተክርስቲያን ልጅነቴ ጥሪ አደርጋለሁ። የታደለ ነኝ ከደብረሰላም መድኃኔዓለም ዴንቨር

Anonymous said...

I strongly believe that there is no Ethiopian orthodox follower who could dare to speak against our fathers for simple reasons.
But what is really going on now?
Is this the time to still keep quit and see? I think the people has the right to ask and both sides has to explain it to the people.

Both sides are not working to the interest of the church or truth.This is just administrative issue and is all about prioritizing their own interest instead of what is best for the church.
we all know God's will is always unity and strength for the church. Here the obstacle is the lack of responsibility, carelessness and trying to look for personal benefit.
I would say everything has a limit.21 years is too much.
We as people of the church should act now.Both of them are not being responsible!!!!
IT IS SO SAD BUT TIME IS OVER FOR THE FATHERS!!! IN BOTH SIDES! BOTH, BOTH, BOTH ARE ALL WORRIED ABOUT THEMSELVES. NO ONE IS THERE FOR THE CHURCH.NO ONE!PEOPLE WILL ACT WITH THE HELP OF GOD.

Anonymous said...

WHY WHY WHY WHY ???? As a chruch preacher how could I stand now to represnet my church ? What kind of speech I have after this ? I had hope to sing for our unity but now just broken. Our fathers from Ethiopia must stand for the truth.
Dn.Sam from DC

Anonymous said...

ወገኖች ሁሉ እኮ ለበጎ ይሆናል። እዚህ ያሉቱ ጎዶች እስከ ጉዳቸው ወደ ሀገር ቢገቡ ምን እንደሚመጣ ከእናኛ ይልቅ እግዚአብሔር ያውቃልና ሁሉን እርሱ ይስራ እኛ ግን ጸልየናል፣ ተጨንቀናል.... እርሱ ቢታገስ እኮ ቁና እየሰፋ ነው። እኛ የምንለምነው ገና ሲጀምር ነው እርሱ ግን በሰፊው ሊፈርድ እስከአሁን ይሰፋል።

Anonymous said...

እንደሚነገረው ሆኖ ዕርቀ ሰላሙ በአሁኑ ጉባኤ ካልወረደ፣ ለሃያ ዓመት ተወጋግዘው የኖሩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እንደተወጋገዙ ይቆያሉ ናቸው ማለት ነው? በኢትዮጵያና በሰደቱ ዓለም የሚኖሩት የቤተ ክርስቲያኒቱ ምእመናን በአንድ ወጥ የፍቅርና የሰላም ሰንሰለት ተያይዘው ፊጣሪያቸውን እንዳያመልኩ የውግዘቱ ሰለባ ሆነው ይኖራሉ ማለት ነው? እስከ መቼ? ምን ሌላ ተአምር እስኪፈጠር ነው የሚጠበቀው? ተስፋ ላለመቁረጥ የሃያ ዓመቱ ልዩነት የአስተዳደር እንጂ የዶግማ አይደለም ሲባል ቆይቶ ነበር:: ከአሁን ወዲያስ? የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና እምነት በኢትዮጵያ፤ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና እምነት በ --- ሀገር፤ በ ---- ከተማ ሊባል ነው? ሁሉም ትክክለኛ ነኝ ካለ በቤተ ክርስቲያኒቱ ደኅንነትና አንድነት ላይ ለተከሠተው ስር እየሰደደ ለሄደው አደጋ ኃላፊና ተጠያቂው ማነው? የምእመናንስ የኃላፊነት ድርሻና የወደፊት ሚና ምንድነው? ከአሁን ወዲያ ተወጋግዞና ተበታትኖ መኖር ለቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ ለኢትዮጵያ ፍጽሞ አይበጅም። ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱ ለሁላችንም ቀናውን መንገድ ያሳየን። መመኪያችን እርሱ ነውና።

Anonymous said...

አስተያየት ከመስጠቴ በፊት ማሳወቅ የምፈልገው በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን በጎሳ ከፋፍሎ እየገዛ ያለው መንግሥት ደጋፊ አለመሆኔን ነው።

ከዚህም በላይ በጎሳ በሽታ የተለከፈውና በአባ ጳውሎስ ሲመራ የነበረው ሲኖዶስ ለኢኦተቤ/ክ መልካም መንፈሳዊ አመራር ይሰጣታል የሚል ከንቱ እምነትም የለኝም:: ስደተኛ ነኝ የሚለውም ሆነ ሀገር ቤት ያለው ቡደን ሁለቱም የመሪያቸውን የኢየሱስን ትዕዛዝ በግል ጥቅምና በገንዘብ የለወጡ መንፈሳዊነት የሌላቸው ቡድኖች መሆናቸውን ተረድቻለሁ::

ከዚህ ውጭ ግን አቡነ መርቆሬዎስ ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው ለሚለው ከሁሉ አስቀድሞ በደርግ አገዛዝ የጎንደር ክፍለ ሀገር ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ እነ ሻለቃ መላኩ ተፈራ በሕዝቡ ላይ ያን መሳይ መከራ ሲያወርዱበት ምንም ሳይናገሩ በዝምታ በማሳለፋቸው ላደረጉት መልካም ትብብር የተቸራቸው ስጦታ እንጂ ለቦታው የሚመጥኑ አባት ሆነው አልነበረም። ይህንንም አሁን በሕይወት ያሉት ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ ይመሰክራሉ።

የኢሕአዴግ አገዛዝ ሥልጣን እንደያዘ ምን ሊደርስባቸው እንደሚችል በመጠርጠር በነ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ አማካሪነት ታምሜአለሁ ብለው ከመንበረ ፕትርክና ረብሻ ሳያስነሱ ይውረዱ ተብለው በተመከሩት መሰረት ወደውና ፈቅደው ያለማንም አስገዳጅነት ለቀቁ። እውነቱ ይህ ለመሆኑ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ የጻፉትን መጽሐፍ ማንበብ በቂ ማስረጃ ነው። አሁን ወደ ኋላ ተመልሶ በሌለ ሥልጣን ሕጋዊው ፓትርያርክ ብሎ መጥራት የሕጻናት ጨዋታ ነው። እራሱ ሕጋዊው ፓትርያርክ የሚለው አጠራር የቀልድና የሃሰት መሆኑን ያሳያል። እውን አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመን እሳቸውን ፓትርያርክ አድርጎ ይቀበላል ብሎ የሚያምን ወገን አለ? በሕልም ዓለም መኖር ይፈቀዳል። አሜሪካ ሰው ያለመውን ሊያገኝ ይችላል ቢባልም እንደዚህ ያለውን ቅዠት ግን ሕልም ልንለው አይገባም።

Anonymous said...

Beka chigir yelewum! NO PROBLEM AT ALL! Hizbu andinetin le "abatoch" MSTEMAR alebet!

Anonymous said...

I AM SO SAD TODAY TO HEAR THIS BAD NEWS, I HAD HOPE TO BE UNITED IN OUR LOVELY CHURCH ,NOW IT'S BROKEN ,NOTHING TO HEAR GOOD NEWS ...SO PEOPLES(BLEVERS) OF ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH LET'S BE UNITED AND TELL TO OUR FATHERS "STOP THE DEVIL WORK" !!!!!!!!!!

Anonymous said...

After all,i Am not going to be call them "our holy Fathers" because they are not doing the right thing to be named holy Fathers and thy are not.spiritual. i do not expect this BAD NEWS!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
O LORD PLEASE HELP THIS PEOPLE AND OUR BELOVED HOLY CHURCH.

Anonymous said...

የተደበቀውን ሴራ አኮ ፕሬዘዳንቱ ዘርግፈውታል :: የመንገስት እጅ ምን ያህል ረጅም አንደሆነ በግልጽ ታይቷል :: አባቶች ተብየዎቹም ከምንግሥት ጋር ጠብቀን ልተብቅህ አየተባባሉ ነው :: እድሜ ለግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ..አሳቸው በግላቸው ለቤተ ክርስቲያን በማሰብ ሰላም እንዲመጣ የወሰኑትና ያደረጉት ነገር ሲዘከር የሚኖር ነው :: ነገር ግን ወሳኞቹ አካላት አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስትና ጳጳሳት ተብየዎች አመከኑት ምን ዋጋለው :: አቃቤ መንበሩ በዚህ እድሜያቸው አንዲህ መሆናቸው ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው ::ምናለበት ህዝበ ክርስቲያኑ ያገባዋል ብለው ብያማክሩት ወይ ድምጽ ቢሰበስቡ ነገሩን በቀምሳቸው ሸፍነው ይዘው አበላሹት አሁንም ይሄ ነገር ወደ ህዝቡ ይውረድ :: እኔ የማንኛውም አይደለሁም ግን የኢትይፕያው ሲኖዶስ በጣም የወረደና ቤተ ክርስቲያኒቱን አየጎዳ ያለ እንደሆነ አስባለሁ :: በአቡነ ጳውሎስ ስያሳብቡ ነበር አሁንስ ?????????? የተዋህዶ ልጆች ቸኮልክ እንዳትሉን እንጂ የቤተ ክርስቲያንትቱ ነገር አብቅቶላታል ::በእኔ በኩል ተስፋ ቆርጫለሁ :: ደጀ ሰላም ኃላፊነት በተሞላበት የዜና አቀራረብ ነው ያቀረባችሁት እናመሰግናለን በርቱ በርቱ

Anonymous said...

I AM SO SAD TODAY TO HEAR THIS BAD NEWS, I HAD HOPE TO BE UNITED IN OUR LOVELY CHURCH ,NOW IT'S BROKEN ,NOTHING TO HEAR GOOD NEWS ...SO PEOPLES(BLEVERS) OF ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH LET'S BE UNITED AND TELL TO OUR FATHERS "STOP THE DEVIL WORK" !!!!!!!!!!

Yenoah Merkeb said...

እኔ ከታላላቆች አውቃለሁ የሚል እምነት ባይኖረኝም እኝህ አባት በምንም ይሁን በምን ሁሉን ነገር መጋፈጥ ሲገባቸው ከመንበራቸው ተነስተው ለምን በስደት መኖርን መረጡ??? ቃለ-አዋዲውስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል??? አሁንስ እሳቸው የሙጥኝ ማለታቸውና አንዳንዶቻችን ደግሞ በማይመለከተን እየገባን መዘባረቅ ያስፈለገን ለምን ይሆን??? ለማንኛውም ፈጣሪ የፈቀደው መሆኑ ስለማይቀር ለአጓጉል ነገር ባንጣደፍና በማያገባን እየገባን በመዘባረቅ ትዝብት ላይ ባንወድቅ መልካም ነው።

Anonymous said...

oooooooooohhhhhhhh min yeshalal

Anonymous said...

ለመሆኑ ፈርኦን ልበ ድንዳና የማይመለስ መሆኑንን እግዚአብሄር ሳያውቅ ቀርቶ ነው እነዚያን ሁሉ ታአምራት እያደርገ የታገሰው ???አዎን እግዚአብሄር አዋቂ ነው ነገር ግን ለእያንዳንዱ የግፍ ጽዋው እስኪሞላ ይጠብቅለታል ጽዋው ሲሞላ ግን ውጤቱ ሰጥሞ መጥፋት ነዋ ስለዚህ የንጽህት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ምዕመናን ሃደራችሁን ቀቢጸ ተስፋ ውስጥ አንግባ ተግተን እንጸልይ ከዚህም የባሰ አሳልፋ ነው ይች ቤትክርስቲያን እዚህ የደረሰችው

Anonymous said...

Sibkete Abune pwlos yiqum.

Anonymous said...

1ኛ - ምነው አዲሱ ትንሽ እስከፍፃሜው ቢታገስ በሚል 2ኛ - አቡነ ናትናኤል የተጀመረውን የሰላም ውይይት የሚበርዝ ነገር ይናገሩና ሳይጀመር ሊጠናቀቅ ነው የሚል ስጋት ስላደረብኝ ነው። መቼም የፈሩት ይደደርሳል ሆነና፤ አዲሱም ትዕግስት አጣ። እርሳቸውም እስኪ ልዑካኑ የደረሱበትን ሰምቼ በኋላ እንነጋገር በማለት ፈንታ እንደፈራሁት የፈራሁትን ተናገሩ። እንደኔ እንደኔ ሁለቱም ደግ አላደረጉም።

Anonymous said...

"TWO WRONGS DOES NOT EQUAL A RIGHT." LET HIM WHO HAVE EARS TO HEAR HEAR THESE WORDS. I will say "us" because we are all one in our Lord. What is wrong with us is not what we think, its deeper, its complex (spiritual things), so let us not be quick to judge each other. The solution to fix our problem is simple, its not as complex as the problem; the key is being on the road to find the solution, this road is paved with forgiveness, humility, love, peace, generally all works of the spirit, once on this path, a solution will be reached ! question is what road are we on?

Anonymous said...

ወየው ቤተክርስቲያኔ! ወየው ቤተክርስቲያኔ! ወየው ቤተክርስቲያኔ! ወየው ቤተክርስቲያኔ! ወየው ቤተክርስቲያኔ! ወየው ቤተክርስቲያኔ! . . .
ኸረ ለመሆኑ ወደማን እንዙር
ኸረ ለመሆኑ ወደማን እንናገር
ጉዳቴን፣ እንባዬን ለማን ልተንፍሰው
ቢናገሩት ከንቱ ቢያለቅሱም ማን ሊሰማው
ታዲያ ክርስቲያኖች ከእንግዲህ ከማን ጋር እንቁም
ስለ አሃቲ ቢለን በአንድ ላይ እናዝግም
አሁንስ ይገርማል የአባቶች ጠባይ
እኔ ብቻ እንጂ የናንተንም አልይ
ለማለት ያስደፈራቸው በምን ተማምነው ነው?
አማራ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ ኦሮሞ በመባባላችን ነው
ስለዚህ ወገኔ እኔም አንተም አንቺም
እርሶም አዛውንቱ እና አዛውንቲቱ አንድላይ ሁላችንም
ይብቃችሁ እንበላቸው በዘር የከፋፈሉንን
እኛ ክርስቲያን ነን ዘራችንም ክርስቶስ
እምቢ ካሉም አንቅሮ መትፋት ነው እንዲደርሰን ጽድቁስ
በቃ እንበላቸው አንተ የጳውሎስ እሱም የኬፋ
በልቦናችን ውስጥ ክርስቶስ እንዲሰፋ
አለበለዚያ ግን ወገኔ ልምከርህ
የጠላታችን ዲያብሎስ መሳለቂያ እንደሆንህ
እኛም ክርስቲያኖች በአንድነት ሆነን
ለጽድቁና ለበረከቱ እንድንፈጥን ይሁን

እንደው የልቤን ስሜን የውስጤን ጭንቀት ለማለት ሞከርኩኝ እንጂ ገጣሚም ወይም የስነ-ጽሁፍም ሰው አይደለሁም፥ ወገኔ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በ40 እና በ80 ቀናችን ክርስቲያን የተባልን ዛሬ ትልቅ እና ከባድ አጣብቂኝ ውስጥ ቤተክርስቲያናችንን ለማስገባት የሞከሩት ከማንም በላይ አባቶችቻችን በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ የምንላቸው አባቶቻችን አንገታችንን አስደፉን፣ የጠላቶቻችን መሳለቂያ አደረጉን በሃገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያሉት አባቶች እግዚአብሔር በሚያውቀው የራሳቸውን የግል የዘራቸውን ጉዳይ ለማስፈጸም እንጂ ስለ ቤተክርስቲያኒቱ የተጨነቁበት ጊዜ አንድም ቀን እንደሌለ ማሳያ ይሄ ጊዜ መሆኑን በደንብ ያየንበት ጊዜ ቢኖር ይሄኛው የመጀመሪያው ነው። ከዚህ በፊት መቼም አቡነ ጳውሎስም በሕህይወት በመኖራቸው የእርቀ ሰላሙን ጉዳይ ለማስፈጸም ትልቅ ጋሬጣ የነበረው በአንድ ወቅት ሁለት አባት በመኖሩ ፈተና ሆኖብን ነበር፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ባወቀው አንዱን አስወግዶ ይልቁንም አቡነ ጳውሎስን መውሰዱ እራሱን የቻለ ምክንያት አለው ብዬ ነው የማምነው እርሱም ቤተክርስቲያንን አንድ ለማድረግ ብቸኛው መፍትሄ በመሆኑ ነበር እግዚአብሔር መንገዱን የከፈተው
አቡነ መርቆሪዎስ ቢሆኑ ኖሮ እኮ ይሄ የምንነጋገረው ሁሉ ዋጋ የለውም ነበር በውጪም ያሉት ወደ በለጠው ስህተት በገቡ ነበር፣ ነገር ግን እሱ ባወቀው መሆን የለበትን ለቤተክርስቲያን ሰላም ለምዕመኗ አንድነት ሆን ተብሎ የመጣ ትልክ የእግዚአብሔር መልስ ነበር ነገር ግን በሀገር ውስጥ ያሉት እንዴት ወደጎንደር ተመልሰን እንሄዳለን በሚል ርካሽ ፍላጎታቸውን እና የዘር እና የጎጥ ዘመቻ ውስጥ በመግባታቸው በውጪም ያሉት በውጪ ያለውን የተሻለ ኑሮ ጥሎ ለሀገር መብቃትን ስለማይፈልጉ አቡነ መርቆርዮስ በወንበራቸው ካልተቀመጡ በምንም መንገድ ድርድር የለም ብለው በመዝጋታቸው እንዲሁም በሀገር ውስጥ ያለውን ለፕትርክናው ቦታን ለመያዝ እንደማይችሉ በመረዳታቸው ይመስላል የበኩላቸውን መንገድ ወስደው እርቀ ሰላሙን እምንም ሳያደርሱ ትተውታል በቀጠሮ ቢባልም ዛሬ መንገድ ያልተገኘለት ሰላም ነገ የተሻለ ነገር ይመጣል ብሎ መጠበቅ በእኔ በኩል የዋህነት መስሎ ነው የሚታየኝ።
ለማንኛውም አባት የሚባሉትን በሙሉ ለራሳቸው ክብር እና ዝና ለዘር፣ ለጎጥ፣ ለወንዝ እንዲሁም ሌላውን ዝቅ አድርጎ እራስን ከፍ ለማድረግ ካልሆነ በስተቀር እራሳቸው ክርስቲያን ወገንተኝነታችን ከክርስቶስ ነው ሲሉን ቆይተው ዛሬ የዚህ ወገን ነን ያዛኛውን ወገን አንቀበልም በሚል መንፈስ መሄዳቸው በገዛ አባቶቻችን እንድናፍር እና አንገታችንን እንድንደፋ በመደረጋችን በጣም ያሳዝናል በእውነት በውጪ መናፍቃን፣ አክራሪዎች ዚገዘግዙን በውስጥም የመንግሥት ግብረ በላዎች እና ተሃድሶዎች ይገዘግዙናል ታዲያ እነዚህ አባቶች እውነት የቤተክርስቲያን አባቶች ከሆኑ ከዘራቸው እና ከዝናቸው በላይ ክርስቶስ እራሩ የማዕዘን ራስ የሆነላትን ደሙን አፍስሶ፣ ሥጋውን ቆርሶ ለሰጠን አምላክ እንዴት መንበርከክ አቃታቸው ዘራቸው ከክርስትናቸው ገዝፎ ነው ማለት ነው፣ ስልጣናቸው ከክርስትናቸው በልጦ እና ገዝፎ ይሆን እንዴ? ታዲያ እነዚህን ጠቦቶች ለአውሬ አውጥቶ መስጠትስ አያስጠይቃቸውም እንዴ? ሰፍሰ ገዳይ፣ ቋንዣ ቆራጭ እኮ በፈጣሪ በምድርም በሰማይም ፍርድ ይጠብቀዋል ታዲያ እነዚህስ አባቶች ካራ አውጥተው ምዕመናኑን አላረዱም እንጂ ቋንዣውን ቁረጠው አላሉም እንጂ እኮ ከዘ የተለየ ሥራ አይደለም የሰሩት ታዲያ ምዕመናን እንዴት ብለን ነው አባት ናቸው የክርስቶስ እንደራሴዎች ናቸው ለማለት በድፍረት መናገር የምንችለው እንደእኔ ከሆነ ያሁሉ ክብር እና መኮፈስ ሁሉ ለራሳቸው ክብር እና ዝና ብቻ ነው የሚለውን እውነት ነው ከሚሉት ወገኖች ውስጥ ደምሮኛል እና ትህትናቸውን፣ ፍቅረ ክርስትናቸውን፣ ለሰላም መሰዋታቸውን በተግባር ካላሳዩን እንዴት ነው አብረናቸው መጓዝ የምንችለው
እግዚአብሔር አምላክ ሰላመ ቤተክርስቲያንን የምዕመናን አንድነትን በተዓምሩ ያሳየን
በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን!

Unknown said...

የኖሕ መርከብ፣ ስለማያውቁት እየተናገሩ ያሉ እርዎ ነዎት። የትኛው ወንጌል ነው ፓትርያርክ በመሥሪያ ቤቱ ምክንያት ተጋፍጦ ይሙት የሚለው? ወንጌሉ የሚለው 'ለእመ ይሰድዱክሙ ሁሩ ወግዩ ውስተ ካልዕታ ሀገር''=በሚያሳድዷችሁ ጊዜ ወደ ሌላው አገር ሸሹ ነው የሚለው እንጅ ሙቱ አይልም። ሙቱ የሚለው በሃይማኖት ምክንያት ነው እንጅ በሥልጣነ መንበር አይደለም። ሥልጣናቸው የአንድ ሀገር ብሔራዊ ደንበር የሚገድበው ስላልሆነ የትም አገር ሁነው በሕይዎተ ሥጋ እስካሉ ድረስ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛውና ሕጋዊው ፓትርያርክ ናቸው። አባትነታቸውን ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የተቀበለ ይቀበላል ያልተቀበለና ልግል ጥቅሙ ያደረ ደግሞ በመንግሥት ፈቃድ የሚሾመውን ሹመኛ ጡት እየጠባ እናቴ ወይም አባቴ ማለት ይችላል። ግን አስመሳይ ክርስቲያን ሁናችሁ ባትቀርቡ መልካም ነው። ምክንያቱም ከየት እንደሆናችሁ በቀላሉ ነው የምትታወቁት። ክርስቲያኖች ከሆናችሁም እንደኔ በተፀውዖ ስማችሁ ጻፉ።

Anonymous said...

True! Most of the terrible actors are far away.it is the work of God.peace for our church!

Anonymous said...

KE ASMESAY KENTU MASASCHAK TETEBEK.WOYANE ADELEWM EYALU 21AMET WOYANE YAWERAWN POLETICA ENDE ADIS TAWERALEK.
WOYANE BEDEBDBE ENDASNESACHEW ERASU GELTSOTAL.
MIN BAY NEk ANTE!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)