December 29, 2012

የኢትዮጵያ መንግሥት ዓላማውን ግልጽ አድርጓል፤ እኛም አውቀናል

  • የመንግሥት ደጋፊ የጡመራ መድረኮች “አስታራቂ ኮሚቴው” ላይ ዘምተዋል፤
  • ከጳጳሰቱ መካከል የዕርቁ እንቅፋት የሆኑት አባቶች በግልጽ ታውቀዋል፤ ስማቸውን ከማውጣታችን በፊት አሁንም ሐሳባቸውን ይቀይሩ እንደሆነ እንጠብቃቸዋለን፤
  • ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ ናቸው ተብሏል፤
  • የአዲስ አበባው ልዑክ አባቶች ዲሲ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተጠሩ በኋላ ተገደው እንዲፈርሙ ተደርገዋል፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 20/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 29/2012/ PDF)፦ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ ከላካቸው ወዲህ ለዕርቁ ያለው የተስፋ ደጅ መዘጋቱ እሙን ሆኗል። መንግሥት የዕርቁ ድርድር ለይስሙላ እንጂ “ከምር” እንዲሆን አልፈለገም ነበር።
ነገሩ ከምር ሲሆን ግን “የጭቃ ጅራፉን” መምዘዝ ይዟል። ለዲፕሎማሲ ይጠቅመኛል ብሎ የፈቀደው ዕርቅ መሰካት ሲጀምር ከዲፕሎማሲው ከማገኘው ትርፍ በሩን መዝጋት ይሻለኛል ያለ መስሏል። የራሱን ፓርቲ አባል በፓትርያርክነት ለማስቀመጥ በጠራራ ፀሐይ ወረራውን ቀጥሏል።  

በተያያዘ ዜና አስታራቂ ጉባኤው አውግዘው መግለጫ እንዲሰጡ የተገደዱት የአዲስ አበባው ልዑክ አባላት ሐሳባቸውን በግድ እንዲቀይሩ የተገደዱት ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተጠሩ በኋላ መሆኑ ሲታወቅ ደብዳቤውን ያዘጋጁት ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ ከኤምባሲው ሰዎች ጋር በመሆን እንደሆነ ምንጮቻችን ገልጸዋል። ሦስቱ ብፁዓን አባቶች ደብዳቤውን ያለውድ በግድ እንዲፈርሙ ሲገደዱ ሐሳባቸውን ላለመቀየር ያንገራገሩት ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ በብዙ ማግባባት ፊርማቸውን እንዲያኖሩ ተደርገዋል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ መግለጫው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ኢላማ የተደረገው አስታራቂ ጉባኤ በመንግሥት ደጋፊ የግል ጦማሪዎች ሳይቀር በመወገዝ ላይ ይገኛል። “መጀመሪያውኑም ገለልተኛ አልነበረም” የተባለው አስታራቂው ቡድን ከመ-አርዮስ የታየበት ምክንያት ዕርቁን ከግብ ለማድረስ በመቃረቡ ነው።

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።
  
15 comments:

Hailu said...

May God the Almighty erase the TPLF conspirators from the face of the earth so that his house,EOTC, live in Peace and Unity.

The 6th Cadre 'Patriarch' will be only and only for the TPLF. It wont be a dime for the Ethiopian Orthodox believers.

I hate to see the continued disunity of our church because of the medling of the government of the athiests and menafkans.

We are not blessed with courageous spiritual fathers who can say no to the unorhtodox and unspiritual interference by the government in the affairs of our church.

Anonymous said...

ከእባብ እንቁላል እርግብ አይፈለፈልም

መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ኢትዮጵያን ኦርቶዶክስን እና አማራውን ስለማጥፋት ቂመኛ እና ዘረኛ ድብቅ አጀንዳቸውን ሲገልጹ "ዓላማችንን አንረሳም - ቂማችንንም አንፈታም" ነበር ያሉት

ስናየው፣ ስንሰማው የኖርነው፤ አሁንም እየሆነ ያለው ይሄው ነው። አባቶችን ማሳደድ፣ ማዋረድ፣ በዘረኞቹ ትግሬዎች መሙላት እና የቤተክርስቲያንን አንድነት ማናጋት፣ ቤተክርስቲያናችን ዘርና ጎሳ ሳይገድባት በአንድ በእግዚአብሔር ጥላ ሥር እንዳትሆን፣ በዘረኝነት በተለከፈ የአንድ ጎሳ የበላይነት እና የወያኔ ጉዳይ ፈፃሚ የሆነች ቤተክርስቲያንን መፍጠር እንደሆነ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ የፈጸሙትና ያቀዱት ድርጊት፣ አሁንም የእነ አቦይ ስብሃት ዛቻ የሚያስረዳን ይህንኑ እውነታ ነው።

ሌላው ምዕመን ስለእናት ቤተክርስቲያኑ በተቆርቋሪነት አስተያየት በሚሰጥበት ጊዜ ለእነሱ /ለኢህአዴጋውያን ስለማይመቻቸው የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው የተቃዋሚዎች አስተያዬት ነው ወዘተ እያሉ ለማሸማቀቅ ይሞክራሉ። እነርሱ ቤበተክርስቲያን ላይ በስውር እና በገሃድ የሚያደርሱትን በደል ትተን፤ በቤተክርስቲያናችን እና በብጹአን አባቶች ላይ በድፍረትና በንቀት በአደባባይ የሚናገሩት ዘለፋ ምርቃት እየመሰላቸው ይሆን? ነው ወይንስ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለውን የቂሎች አባባል ሕዝብ አያውቅብኝም ለማለት ነው? ታዲያ ምነው መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ ካልገባ "ፓትርያርክ በሕይዎት እያለ ሌላ ፓትርያርክ አይሾምም" የሚለውን የቤተክርስቲያን ድንጋጌ ሲነሳባቸው የሚያንገበግባቸው ለምንድን ነው? አሁንም መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ ካልገባ እንኳን 4ኛውን በሕይዎት ያሉትን ፓትርያርክ ቀርቶ የአቡነ ጴጥሮስን አጽም አውጥተው በመንፈሳቸው እንመራላቸዋለን ቢሉ ምን ጥልቅ ያደርጋቸዋል?

ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደማይፈለፈል፣ ከኢህአዴግም ለሃይማኖታችን መጥፋትን እንጅ በጎ ነገርን ስለማንጠብቅ፤ መንግሥት በረጅም እጁ ቀደም ሲል በገዳማት መቃጠል፣ በንዋዬ ቅድሳት ዝርፊያ፣ በቤተክህነት ሙስና፣ በኋላም አንዴ በዋልድባ ገዳም መታረስ፣ ሌላ ጊዜ በአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት መነቀል እንደገና የወያኔ አፈቀላጤ ፓትርያርክ ለማስመረጥ በሚደረግ ሽኩቻ ሃሳባችንንም ጊዜያችንንም ሲበታትንብን ቆይቷል። ወደፊትም ይቀጥላል - ዓላማው ነውና።

እኛም አስተያየት ፖስት ከማድረግ ባለፈ አንዱንም ሳንከላከል ወደፊት የደገሱልንን የጥፋት በትር ገና ያወርዱብናል። የትናንቷ ቁስጥንጥንያ የዛሬዋ ኢስታንቡል እንደሆነች ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶም ዛሬ ራሷን መከላከልና ሃይማኖቷን ማስከበር ካልቻለች "በክርስቶስ ደም ስለተመሠረተች አትጠፋም" የሚለው ቃል ብቻውን አይበቃም። ታዲያ ቁስጥንጥንያ በክርስቶስ ደም አልነበረም ወይ የተመሠረተችው የሚል ጥያቄ ያጭራልና?

ወያኔዎች "ዓላማችንን አንረሳም - ቂማችንንም አንፈታም" እንዳሉት ዓላማቸውን እያሳኩ ነው። ስለዚህ ተጠያቂዎቹ ሃይማኖታችንን ያልተከላከልነው እኛው ራሳችን እንጅ እነሱ ወያኔዎች አይሆኑም።

ስለዚህ የመጀመሪያው እርምጃ ወያኔ/ህወሃት በሃይማኖታችን ጣልቃ እንዳይገባ የኦርቶዶክስ አማኞች በሙሉ ሃይማኖታዊ መብታቸውን ለማስከበር ከሚታገሉት ሙስሊም ወንድሞቻችን ጋር በመተባበርና በሰላማዊ መንገድ ሃይማኖታችን ይከበር ማለት አለብን።

"የቤተክርስቲያኔ ጉዳይ እኔንም ያገባኛል" የሚለውን ጥሪ ተቀብለን ተቃውሟችንን በህብረት ማሰማት ይኖርብናል። ይህም ተቃውሞአችን ፓትሪያርክ ከመሰየሙ በፊት መጀመር ይኖርበታል።

ይህንን ችግር ሕዝበ ክርስቲያኑ ገና በደንብ ስላላወቀው፤ የሚችል የተቃውሞ ድምጹን እንዲያሰማ፣ የማይችል በፀሎት እንዲያግዝ መላ ሕዝበ ክርስቲያኑ በየሰበካ ጉባኤው በይፋ ተነግሮት ማወቅ አለበት። በኋላ ግን ቁጭ ብለው የሰቀሉት ለማውረድ እንዳይቸግር እና ወደባሰ ፈተና ውስጥ እንዳንገባ እርምጃው አሁኑኑ መጀመር አለበት። እያንዳንዷ የዝምታ ቀን ለወያኔ የድልና የስኬት ቀን ነች።

"የቤተክርስቲያኔ ጉዳይ እኔንም ያገባኛል" "ከፓትርያርክ ምርጫ እርቀ-ሰላም ይቅደም" የሚለውን ጥሪ ተቀብለን ድምፃችንን ማሰማት ግዴታችን ይሆናል።

ስለዚህ በተጠናከረእና በተደራጀ መልክ መንፈሳዊ ጥያቄያችንን ለማቅረብ እንድንችል የማኅበረ ቅዱሳን፣ የሰንበት ት/ቤቶች፣ ሌሎች እውነተኛ የተዋህዶ ማኅበራትና የሰበካ ጉባኤያት የመሪነቱን ሚና መጫወት ይጠበቅባችኋል።

በዓመት በዓል ጊዜ ከበሮ ይዞ ለመድመቅ ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያናችን አሁን ከገባችበት ፈተና እንድታወጧት ከምንጊዜውም በላይ እናንተን የምትፈልግበት ጊዜ አሁን ነው። ይህ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ ቅድስት አርሴማ የእምነታችንን ጽናት የምናስመሰክርበት ወርቃማ ዕድል ነው ለዚህ ሰማዕትነት መብቃት ደግሞ ታላቅ መመረጥ ነው

እግዚአብሔር ቤቱን ይጠብቅ
ቸር ወሬ ያሰማን

We Ethiopian have to learn from the past 20 years.
Woyane is not just a history, it is an up front deed that we have been seeing for 20 years. Let us stop simple talks. It become an addiction to all Ethiopians to see each event as new happening when ever Woyane does something we give an issue as new. Woyane is always Woyane neve hesitate doing what they are planning.

The only solution would be to unite. UNITE, UNITE and bring our freedom back. We don't have to worry on pieces of issues. The Enemy should have to go.

Anonymous said...

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት 'ሁሉም ወደ በአቱ ይመለስ' ያለበት ጽሑፍ በተለይም አርቃቂው ጉባኤ ላይ የሰጠው ትችት ሌሎች ካሉት ጋር ያለው ተመሳሳይነት ምን አንድምታ አለው?

እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

Anonymous said...

Who is trustworthy ???

Anonymous said...

Who belived the gov't announcement first.no one will never ever belive the gov't talk. Even every one knows the way how they will make false for every activity going on.even at this critical time making drama for their own. Please make us aware of the enemies of the church among the papasat.

Anonymous said...

እኔ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ አባላት ክፍተኛ ተጋድሎ በኦርቶዶክሳዊነቴ ኩራት ተስምቶኛል፤ ከአባቶቻችን የሚፈለገው ይህ አይነት አቋም ነው፤ በርቱ ቤተ ክርስቲያን ድካማችሁን አትረሳውም፤ እግዚአብሔርም ምንእንደ ሚያደርግ አናውቅም። መንግሥት ግን እርቃኑን ቀርቷል፤ በሀገራችን የሰላም ልዑካን፤ ከዚያም በላይ ካህናት በሰላም ወጥተው መግባት አለመቻለቸው ያሳዝናል፤ አሁንም ጎበዝ ያለው አማራጫ 1በኢትዮጵያ እውነተኛ አባቶች ካሉ ከነሱ ጎን ተሰልፎ በመቃብር አፋፍ ላይ ያለው ሰላም አፈር እንዳይለብ ይልቁንም ነፍስ እንዲዘራ ምእመናንን ማስተባበር፤ ያካልሆነ ደግሞ በውጭ ያሉ አባቶችን በማጠናከር ቤተ ክርስቲያንን ማደራጀት፤ ልዩነትን በማጥበብ ነጻነት ለሌለው ሕዝባችን አንድ ሁነን በጎ ሥራ መሥራት ነው የሚጠበቅብን፤በውጭ ያሉ አባቶች ሁሉን ሊያቅፉ ይገባል፤ ቤተ ክርስቲያንን የመደረጀት ሥራ፤ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የመስማር አገልግሎት በሰፊው ሊሰጥ ይገባል እላለሁ።
ንቡረ እድ ኤልያስ የሚባሉትን ሰው ግን ባጣም ያሳዝኑኛል፤ ምንያክል ዘመን ሊከብሩ ነው ወንድሞቻቸው ላይ ይህን ያክል በደል የሚፈጽሙት።

Anonymous said...

I don't understand the idea that they were forced... How many lives do they live? two, three, four, or ten? The fact is all Bishops are considered dead for this world. The bishops, including Abune Atnathewos, could have said NO, and face whatever consequence there may be. Why would they go to the Embassy to dicuss this issue in the first place?

Death to TPLF Weyane and its agents! God willing, we will overcome all these difficulties with our concerted effort and the help of God Christ Jesus.
Those worldly bishops, who are helping weyane destroy the Church of Christ, will be tormented in eternal fire along with their father, the enemy of God.

Anonymous said...

“ይድረስ ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት” የሚለውን አንብቡት (http://www.zehabesha.com/archives/15194)
አሜሪካን የምቀረው የኢትዮጵያ መንግሥት አትግባ ሲለኝ ብቻ ነው ብለህ መናገርህን፤ ከዓመታት በፊት ሰምቼ ነበር፡፡ ታዲያ እንዲህ የምትመላለስባት አሜሪካና በዚያ “ሲዖል” ውስጥ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን አቀባበላቸውንና አክባሪነታቸውን መቼም የምትገድፈው አይደለም፡፡ እነዚሁ ለአንተ ጠብ ርግፍ የሚሉት ምዕመናን ናቸው በመለያየት አጥር ውስጥ ተቆልፎባቸው መንፈሳዊ ዝለትን፣ ሥጋዊ ውጥረትን ሁሉ ታግሰው አባቶቻችን ሆይ በቃ እያሉ የሚጮኹት፡፡

Mebratu _ hawassa said...

Ebakachihu yihch betekrstian yalechbetn chigr yehulachinm guday new. Tigre ena amara malet min ametaw? Hulum tigre Tplf aydelem bizuwn hizb sile haymanotu tekorkuari new. Silezih Tplfn lemenkef eyalu menager elama mesat new yemihonew. ... Mebratu_ hawassa

Anonymous said...

Beletera adelu yamisun engi. It is us today and it will be them tomorrow (Hail Selassie).

Anonymous said...

ዳንኤል ክብረት ማን ነው?ስራው ምንድን ነው?ከማህበረ ቅዱሳን እንዴት ሊባረር ቻለ?ከማህበሩ የወሰደው ገንዘብ አለ የሚባለው እውነት ነው ወይንስ ውሸት?
ዳንኤል ክብረትን ሰወችስ እንዴት ይመለከቱታል? እርሱ ሰወችን እንደሚያየው የጎሪጥ እንደማትሉኝ ተስፋ አለኝ።
ስሙንስ ማን እያሉ ይጠሩታል?አምባሳደር ምናምን ምናምን የሚሉትን ሳይሆን ዳንኤል ክብሪት ውይንም ዳንኤል ክስረት የሚባለውን ነው የምላችሁ ለምን ሰወች እንደዚህ አንዴ ክብሪት አንዴ ኩራዝ እንዴት ይሉታል?።
የዳንኤል ክብረት ዲያቆን አይደለም የሚባለው ለምንድን ነ ው? ሰወች ያልሆነውን ለመሆን በመሞከሩ ምክኒያት እርኩስ መንፈስ ተጠናውቶታል የሚሉት እሱ እንደሁ አይቀድስ እንዴት ሊሆን ይችላል በርግጥ ሰወች የሚሰጡት አስተያየት እንዳለ ሆኖ ‹ሁሉም ወደየበኣቱ ይመለስ› ባሚል እርእስ ለሰላምና ለአንድነት የሚደክሙትን አባቶች ወያኔን ወግኖ የሞነጫጨረውን ያዩ ብዙ ሰዎች ውነትም ዳኒን እርኩስ መንፈስ እየተጫወተባት ነው ብለው ደምድመዋል ። እኔም እንዴት ሊሆን ይችላል በማለት ከዚህ ጋር የተያያዘ ማንኛውንም ኢንፎርሜሺን ማወቅ ፈለኩ ምክኒያቱም ለቤተክርስቲያናችን ብቻ ሳይሆን ለሀገራችንም በጣም ጠንቅ ስለሆነ እባካችሁ ስለዚህ አወዛጋቢ ፍጡር የምታውቁትን ሁሉ ፖስት አድርጉልን ።
እግዚአብሄር አምላክ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ከተኩላዎችና ከከሀድያን ይጠብቅልን!!!
አሜን!!!

Anonymous said...

"ከጳጳሰቱ መካከል የዕርቁ እንቅፋት የሆኑት አባቶች በግልጽ ታውቀዋል፤ ስማቸውን ከማውጣታችን በፊት አሁንም ሐሳባቸውን ይቀይሩ እንደሆነ እንጠብቃቸዋለን፤"...

እንደው ጳጳሳቱ ላይ ያነጣጠረ ይመስላል እንጂ ምንና ማን ተረፈ?

ምነው ደጀሰላም? ወዴት እየሔድን ነው?
ለተ.ራ፤ ተ.ራ.ማ እነ "አባሰላማም" ያጠግቡን የለ።
አ.ረ ለፍርድም አይመችም!። ብስጭትም ከሆነ ግድ የለም መረጋጋትንና ጊዜ መውሰድን የመሰለ ነገር የለም። ዘራፍ ከሆነም መጨረሻው በዕርገጠኝነት እያምርም።
ደግሞ "ዕርቁ" የተባለውም በምን መስፈርት ተመዝኖና ተፈርዶ የ"ደጀ ሰላሙ ዕርቅ" ብቻ ትክክል?

እንዳማረብን ቤተክርስቲያናችንን በጋራ እንመልከት!

ዳላስ-ቲክሳስ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)