December 7, 2012

የዕርቀ ሰላም ውይይቱ በመልካም ሁናቴ ቀጥሏል


(ደጀ ሰላም ኅዳር 27/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 6/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በአሜሪካዋ የቴክሳስ ግዛት ዳላስ ከተማ በመካሔድ ላይ የአባቶች ዕርቀ ሰላም ውይይት በመልካም ሁናቴ በመካሔድ ላይ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸውልናል። ትናንት የተጀመረው ጉባኤ በመጀመሪያ ቀን የጠዋት ውሎው በጸሎተ ኪዳን ጉባኤውን ጀምሯል።  ጸሎተ ኪዳ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ መሪነት ከተካሔደ በኋላ “ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በመልአከ መንክራት ቀሲስ አንዱዓለም ይርዳው ተሰምቷል።


ጉባኤው ቀጥሎ  ከዚህ ጉባኤ ምን እንደሚጠበቅ ባለ አምስት ነጥብ ማብራሪያ  በአስታራቂ ኮሚቴው አባል በቆሞስ አባ ጽጌ ደገፋው የቀረበ ሲሆን  የሰላምና  አንድነት ጉባኤው አባላት ትውውቅ አድርገዋል። አስከትሎም ሁለት መልእክቶች በተከታታይ ቀርበዋል።  ብፁዕ አቡነ ገሪማ ባቀረቡት የመግቢያ መልዕክት ስለ ኢትዮጵያ  መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረውን በመዘርዘር ኢትዮጵያ ገረ እግዚአብሔር መሆኗን አብራርተው ቤተ ክርስቲያን ለአገር ያበረከተችውን አስተዋጽኦ ዘርዝረው በተለያዩ ጊዜዎች ፈተና  እንደገጠማትና እንደተወጣችው  አብራርተዋል:: ሰላም ማምጣት  አስፈላጊ መሆኑንና ባፋጣኝ እንዲፈጸም እንደሚገባ አስረድተዋል::  ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅባቀረቡት ተመሳሳይ መልዕክት ታራቂዎችም አስታራቂዎችም እኛ ነን ብለዋል::

 ጉባኤው ውይይቱን ቀጥሎ ከኢትዮጵያው ሲኖዶስና ከሚገኙት አባቶች በኩል የቀረቡትን ሁለት የመወያያ አጀንዳዎች በማጣጣም  በሰላምና  አንድነት ጉባኤው የቀረቡ ስድስት  የዕርቀ ሰላሙ የውይይት አጀንዳዎች እና  የመወያያ ደንብ ስለማጽደቅ የሚገልፀው ሑፍ በንባብ በመርሐ ግብር መሪው  ተነቦ ጉባኤው አጀንዳውን አጽድቋል::

ከሰዓት በ ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዓለማየሁ መድረክ መሪነት በታካሔደው ውይይት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከሥልጣናቸው እንዴት ሊወርዱ እንደቻሉ በአገር ውስጥም በውጪው የሚገኙት አበው ልዑካን የታሪክ ምስክርነታቸውን በወቅቱ ሰጥተው ውይይቱ በሰላምና በፍቅር ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ኢትዮጵያ  መመለስ አስመልክቶ ሰፊ ውይይት ተደርጎ በይደር ተጠናቅቋል። ውይይቱ ሐሙስም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ዝርዝሩን እንደደረሰልን ለማቅረብ እንሞክራለን።

በተያያዘ ዜና በአገር ሽማግሌዎች ምክር አቡነ መርቆርዮስን መመለስ አስመልክተው ደብዳቤ የጻፉት ፕሬዚዳንት ግርማ ደብዳቤያቸውን ከሳቡ ወዲህ ጉዳዩ ትልቅ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ እንደቀጠለ ነው። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዛሬ ያነጋገራቸው የፕሬዚዳንቱ ልዩ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ ደብዳቤው በደብዳቤ እንደሚሻር ገልጸው አዲሱ ደብዳቤ “አቡነ መርቆርዮስ ከፈለጉ ተመልሰው ለፕትርክና መወዳደር እንደሚችሉ” የሚያትት ሐሳብ እንዳለው ተናግረዋል።

በእርግጠኝነት ይህ ሐሳብ የፕሬዚዳንቱ እንዳልሆነ መገመት ይቻላል። እንኳን በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ ለሚኖር ሰው የሰለጠነ ዓለማዊ ፖለቲካ የሚመራ ሰው እንኳን “ተርሙ ያለቀ መሪ” ድጋሚ ይወዳደር አይባልም። ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት የመራ ሰው ጊዜ ገደቡን ሲጨርስ ሥልጣኑን ለሌላ ሰው አስረክቦ በጡረታ ይገለላል እንጂ ድጋሚ ልወዳደር አይልም። መንፈስ ቅዱስ አንድ ጊዜ ፓትርያርክ ያደረጋቸውን ሰው ለሌላ ፓትርያርክነት ተወዳደሩ ማለት ምን ማለት ነው? ፕሬዚዳንት ግርማ ደግሞ ይህንን ስለሚያውቁ “እንዲህ ይላሉ” ብለን አንጠብቅም። ነገር አሳምር ያለ የመንግሥት ሰው ያመጣት ሐሳብ መሆን አለባት። አሁንም ቢሆን፣ በዚያም ይሁን በዚህ፣ እጃችሁን ከቤተ ክርስቲያን ላይ አንሡልን፤ ቤተ ክርስቲያን የራሷን ጉዳይ ለማስተናበር አታንስም።

ለማንኛውም የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮን ዘገባና ቃለ ምልልስ አዳምጡ።
                                                                        

“ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን - ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ”።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

15 comments:

ke.ya.seyoum said...

ልዑል እግዚአብሔር ፍጻሜዉን ያሳምርልን ለ21 ዓመታት የተለያዩት ብፁዓን አባቶቻችን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ምእመናን እና ምእመናት ይጠቀሙባት ዘንድ ዐለቱን አፍርሶ ይቺን የመጨረሻ ልዩ እድል የሰጠን አምላካችን ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን ።

ke.ya. seyoum said...

ልዑል እግዚአብሔር ፍጻሜዉን ያሳምርልን ለ21 ዓመታት የተለያዩት ብፁዓን አባቶቻችን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ምእመናን እና ምእመናት ይጠቀሙባት ዘንድ ዐለቱን አፍርሶ ይቺን የመጨረሻ ልዩ እድል የሰጠን አምላካችን ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን ።

Anonymous said...

Hey my brother:- Danny Mare,pleas if you have a proof that Deje selam is laying why don't you show us or let's read it,if you don't just be quite .Deje selam they doing there part for the ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH are you doing your part? (were is your's?)I don't think you will answer this question. DON'T LET THE DEVIL USE YOUR MIND ! GOD BLESS YOU!

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

"እንኳን በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ ለሚኖር ሰው የሰለጠነ ዓለማዊ ፖለቲካ የሚመራ ሰው እንኳን “ተርሙ ያለቀ መሪ” ድጋሚ ይወዳደር አይባልም።"
ምነው፡መንግሰት፡እጅህን፡ብታነሳ፡፡እስካሁን፡የደረሰባችሁ፡አይበቃም፡አትማሩም፡፡አቶ፡መለስ፡እና፡አቡነ፡ጳውሎስ፡ላይ፡የደረሰውን፡እስካሁን፡አልተገነዘባችሁም፡፡እነርሱ፡ሲነገራቸው፡አልሰማ፡ብለው፡በትዕቢት፡ወድቀዋል፡፡ተማሩ፡ተማሩ፡አሁንም፡ተማሩ፡፡
ለቤተ፡ክርስትያን፡ሰላም፡ሁላችን፡እንጸልይ!!!

Anonymous said...

First of all the letter that written by this old men that called president of ethiopia he is not wrote a letter to be genuine for our church but Ethiopia government trying to make some destruction to our peaceful meeting. I am warning including Deje Selam and Voice Of America to stay away from broadcosting any government comment or suggestion. it doesn't mean I am dislike what you guys doing but let us focus on main point and important to us now. which is our unity... Ethiopian government purposly doing such things because they are benefited by making the division. pls wake up everyone and let ignore those ppl or government etc do what is right for church future. we don't have any chance coming to us very soon this is only one. pls pls let us stop broadcasting government news he say she say trying to broadcast what is encourage ppl of ethiopian orthodox church.

Anonymous said...

ይህ እርቁን ለማደናቀፍ የተጻፈ በፍጽም አይደለም። ጉዳዩ መ/ር ልዑለቃል አካሉ ይመለከታል።

ለምን እርሱ እንደተወከለ ሊገባኝ አልቻልም፤ ምክያቱም አቋሙ እንደቀድሞ ከወነ የፕሮቴስታቶች ሰላይ ቢሆንስ ። እንዲህ ለማለት ያስቻለኝ 1989 አ.ም በአዲስ አበባ በገዳመ ኢየሱስ ቤተክርስቲያ ከግርማ በቀለ እና ጽጌ ስጦታው ከተባሉ "ፕሮተስታንቶ" ጋር የክረምት ኮርስ ሰጥቶኝ ነበር። ኮርስ የሰጣቸው የሰንበት ተማሪዎች የፕሮተስታንትን ካንፕ እንዲቀላቀሉ ምክንያት ወኖአል።

ከሁሉም ግን የማልረሳው ልዑለቃል አካሉ ለመዳን ምን ያስፈልጋል ብሎ ፈተና ላይ ለጠቀን ጥያቄ የሰጠውት መልስና፤ እርሱን ኤክስ አድርጎ የጻፈው መልስ እስካሁን ይገርመኛል። እኔ የመለስኩት በስላሴ ፤በክርስቶስ ኢየሱስ ስለማመን፤ ስልመጠመቅ፤ ስለቅዱስ ቁርባን፤፦ እሱ ሁሉም ላይ አንዴአስምሮ(አክስ አድርጎ) በጌታ ማመን ብሎ ጻፈበት። ኮርሱ ከተሰጠ በኃላ ከ 1-2 አመት ባለው ጊዜ ውስጥ ሁሉም የሰንበት ት/ቤት አባላት ማለት ይቻላል ፕሮተስታንት ቸርች ተቀላቀሉ።

ከዚያ ድርጊቱ ከታረመ መልካም። ካልታረመ ግን በአባቶች መካከል ምን ያደርጋል?

ኢየሱስ ክርስቶስ የጌቶ ጌታ ነው።

Blog by ROME Vehicle Towing Service said...

Hi Dejeselam,
I did comment on your 12/05/2012 dated article to be corrected. If you continuing with falsify information, it damaging your reputation. As children of our Church, we obligated to disseminate any information truthfully and be accountable. The way your choosing of ignorance bare a consequence paying un wanted price. My previous comment is as follows and hope you take the right step. Thanks,
'ውጪው በሚገኙት አባቶች ከሚተዳደሩ አብያተ ክርስቲያናት የመጡት ደግሞ ቆሞስ አባ ጽጌ ደገፋው፣ መ/ር ልዑለቃል አካሉና ዲ/ን አንዱዓለም ዳግማዊ'
Sorry Dejeselam, Dr. Deacon Andualem is employee of EOT Debere Mehret St. Michael Cathedral, Garland, Texas and the Church is Neutral. It means is not a part of neither Synods. A responsible media must exercise and it’s duty to check the fact, but yours short to exhibited it. We have witnessed in the past how our Church being painted at your site, especially during our worst day in our Church history. Again today labeling our Church with out any fact must be stop. And Dr. Andualem is not representing our Church and Congregation as the member of the Exile Synods as a full time paid employee. And our Church role is very limited on the affairs of this matter and never officiated it self to neither Synods. Hope you owe to your reader as well as to our Church and Congregation by correcting your article. Thanks,

Unknown said...

Dear last "Unknown",
Thank you for your comment. We apologize for the mere mistake in thanking you for the correction. Regarding our past reports, of course we do not accept that unnecessary comment. If you want to discuss that save it until the Peace and Reconciliation process is over. Ok? We know Dallas Michael Church is one of the leading geleltegna Churches in USA. The error is a simple mistake.

Ke-Gabriel Beate said...

አቡነ መርቆሬዎስ በህይዎት አሉ፤ መንፈስ ቅዱስ የሰጣቸው ስልጣን ነው፤ ከሃገር የወጡት ተገፍተው ነው፤ ሕዝባቸውን በሙያቸው እያገለገሉ ናቸው።
ታድያ ለምን ሌላ ፓትርያርክ መምረጥ አስፈለገ? እግዚአብሔር ያረመውን እኛ እንዳናበላሽ እናስተውል።
አቡነ መርቆሬዎስ ፈቃደኛ ከሆኑና በቀራቸው የእድሜ ዘመን መንጋውን ለመጠበቅ ፈቃደኛ ከሆኑ:-
፩ ወደ ኢትዮጵያ ይግቡ፣
፪ ማእረጋቸው ፬ኛው ፓትርያርክ እንደሆነ ይጠበቅ፣
፫ አሜሪካ ከ፬ ባላነሰ አህጉረ ስብከት ትከለል፣
፬ ቃለ አዋዲ በመላው የውጭ አገር ላሉ የኢኦተቤክ ባስቸኳይ ይሰራጭ፣
፭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ከሙስናና ከዘረኝነት ባስቸኳይ ትንጻ፣
፮ ስራችን ሁሉ ክርስቶስን ይምሰል፤ ቅድስትና ብጽእት ማርያምን እናስብ፥ የመላይክትን አገልጋይነት እንይ፥ ጻድቃንና ሰማእታት ትተውልን እንዳለፉ ጠብቀን እናስተላልፍ።

Anonymous said...

To the anonymous who diatribe about Memihir Leulekal

How do you start your view on claiming your comment is not to negatively view the peace and reconciliation and right of the bat started to cannonade an individual who was one of few(2 or 3) individuals who incepted the idea of the reconciliation few years back ?

There is so much flow in your post but this is not the time to defend an individual so I will leave your junk for later garbage pickup but I just have a message to you and your alike:

Anyone who in any form or shape influences, impact, comments on the recent peace and reconciliation is an enemy of my beloved church. I am to the view that whatever decision these fathers reach in Dallas, as long as it ends with peace and reconciliation; it is victory for the church, victory for the faithful at large and sad day for Protestants and heretics and enemies of the church.

God is great and God bless you DJ,

Blog by ROME Vehicle Towing Service said...

Hi Dejeselam,
I thank you for correcting your article posted on 12/05/2012 in regard to our Ethiopian Orthodox Tewhado Debre Mehret St. Mikael Cathedral of Garland, Texas and its employee Dr. Deacon Andulam Dagemawi. I also noticed on your above reply that you had bothered by and choose to postpone, hope you keep your statement. I do not have any intention or interest to spilling fuel on fire than do my best is truthful. And it is my daily pray that our Church be under one Synod and the division curtain be torn down for good. Thanks again for taking action in correction of your article.

hailu said...

Mr Unknown,
You seem to have taken a pride in being neutral "geleltegna". How can you be neutral in a series church affair? Where do you learn that an Ethiopian Orthodox church can call itself neutral and is not blessed by a bishop, then a Patriarch? I have a respect to those churches who associate to at least one of the synods and acknowledge a Patriarch. Neutral is not an orthodox tradition "twufit".

Blog by ROME Vehicle Towing Service said...

Hi Dejeselam,
I came to learnt that the VOA brodcat an interview with the Acting Chief of the EOTC Synod of Addis. I am puzzles with his Holiness statement. Is he going retreat as the President of that Nation decision or that is the official stand of the Ethiopia based Synod? What will be the future of the Peace and Reconcile group? If no reconciliation, are we going to have the two Synods? What will be the future of those Neutral (geleltenga) Church, are they going to have their Synod or practice without one?
I hope a scholar or any one for that matter give me a head up to the above concern I have stated. Thanks,

hailu said...

Mr Unknown,

If the fathers in Addis are gutless to stand against the government's interference in our church affairs and solve a two decade old division, then unfortunately we orthodox Christians don’t have righteous fathers in Addis. Therefore, the division may continue unless the Almighty God intervene.

As to the "geleltegna" churches, they must not deceive themselves as there is not “geleltegna” in the Orthodox tradition. They must utilize their God given brain to judge right from wrong and join one of the synods. If they are honest to themselves and understood the root cause of the division, they should join the synod which is lead by the righteous 4th Patriarch, His Holiness Abune Merkorios.


May God bless EOTC.

Unknown said...

ነገሩ ሁሉ በጉጉት እንደ ጠበቅነው እየሆነ አይመስለኝም። አቡነ ናትናኤል ለጋዜጠኛ አዲሱ አበበ(VOA)እንደተናገሩት ፓትርያርኩ ወደ ሀገራቸው ገብተው በመረጡት ቦታ መቀመጥ እንደሚችሉ እንጅ ፣ በውጭም ሆነ በዉስጥ ያለነው ብዙዎቻችን የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች እንደጠበቅነው፥ የተጣሰው ቀኖና ተስተካክሎ በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስና በአንድ ቅዱስ ፓትርያርክ የምትመራ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ትኖረናለች ብለን አስበነው የነበረው እንዳልሆነ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት። ምን ይደረግ ይህ የኔው ትውልድ ያልታደለ ነው። አንዲት ቤተ ክርስቲያን፥ አንዲት ሉዐላዊት ሀገርና አንድ ኢትዮጵያዊ ሕዝብ ነበር ከአባቶቹ የተረከበው። ትውልዱ ግን የተከፋፈለ ሕዝብና ቤተ ክርስቲያን ለቀጣዩ ትውልድ አስረቦ እያለፈ ነው። መቸስ ምን ይደረግ ድንቁርና እንደ ጥበብ ፥ መከፋፈል እንደ ስልጣኔ ቆጥረነው በጥፋት መንገድ መጉዋዝን መርጠናልና 'ግበ ከርየነ ወወደቅነ ኅበ ግብ ዘገበርነ' በቆፈርነው ጉድጓድ እየገባን መውደቅ ነው። አዎ ባለ አገሮቹና ዘመናውያኑም ሹማቸውን ይሹሙ። እኛም ስደተኞቹ ሕጋዊ/ቀኖናዊ ናቸው ብለን የምንከተለውን ስደተኛ አባትና በቅዱስነታቸው የሚመራውን ቅዱስ ሲኖዶስ አመራር እንደ ተቀበልን እንቀጥላለን። ''ከ2ቱም ገለልተኞች ነን '' የሚሉትም እንደተገለሉ ይቀጥላሉ ማለት ነው ፥ ወይም ከ2ቱ አንዱን መርጠው ይቀላቀላሉ። ከሁሉም አንሆንም የሚሉትንም 'የገበያ ግርግር ለሌባ ይመቸዋል'እንደሚባለው በዚህ አጋጣሚ ቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈስ ቅዱስ ተለይቷታል እያለ ልጆቿን እየነጠቀ የፕሮቴስታንቱ ሐሳዌ መሲሕ እያጰነጠጠ ይማርካቸዋል። አዎ ለዚህ ነው ''የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን'' ያጋለጡን !ባጭሩ 'ፈቀደ እግዚእ ያግዕዞ ለአቡነ መርቆሬዎስ ወያግብዖ ኅበ ዘትካት መንበሩ 'ብለን ተስፋ ጥለን ነበር ግን አልሆነም።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)