December 23, 2012

“ከፓትርያርክ ምርጫ - ዕርቅና አንድነት ይቅደም” ስንል ምን ማለታችን ነው?

(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 12/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 21/2012/ PDF)፦ እንደሚታወቀው ቤተ ክርስቲያናችን በመስቀልያ መንገድ ላይ እንደምትገኝ ተደጋግሞ የተገለጸ ነው ዋነኛዎቹ ርዕሰ ጉዳዮች ሁለት ናቸው። የመጀመሪያው ለ20 ዓመታት በውግዘት የተለያዩ አባቶች አንድ እንዲሆኑ፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን፣ አንድ አስተዳደር፣ አንድ ቅ/ሲኖዶስ እንዲኖረን ማድረግ ነው። ለዚህም “ተስፋ ሰጪ” ሁኔታ ላይ ተደርሷል። ይህ ዳር እንዲደርስ እናድርግ። ሁለተኛው ደግሞ 20 ዓመት ለቆየው መለያየት ዓምድና ምልክት የነበረው የፕትርክናው ሥልጣን አንዱ የመወያያ አጀንዳ ስለሆነ ከዕርቁ በፊት ሌላ እርምጃ አይደረግበት የሚለው ነው። ይህንን በሚጋፋ መልኩ በጥቂት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ግፊትና በመንግሥት ተጽዕኖ 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም “አስመራጭ ኮሚቴ” ተቋቁሟል። ሁለቱ አጀንዳዎች የሚገናኙት እዚህ ላይ ነው።

1.      ዕርቀ ሰላሙ ይፈጸም ማለት 4ኛው ፓትርያርክ የግድ ሥልጣኑን ይያዙ ማለት አይደለም። ሐሳቡ ውጪ በሚገኙት አባቶች በኩል የቀረበ መሆኑ ተደጋግሞ ተገልጿል። ለውይይት የቀረበ እንጂ ውሳኔ አይደለም። ውይይት የሚደረገው “ሰጥቶ በመቀበል ሕግ” አባቶች እንዲስማሙባቸው ሁሉንም አጀንዳዎች ጠረጴዛ ላይ ያስቀምጡ ማለት ነው።

2.     ምንም ቢሆን ከመለያየት አንድነት ይሻላል። ስለዚህ ዕርቁን ማስቀደሙ ተገቢ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን በመልዕክቱ አባቶቻችን ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ አንድነት የሚያመጣ ዕርቀ ሰላም መፈጸም ከሃይማኖታዊ ሥነ ምግባር አንጻር፣ ለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ከማሰብ አንጻር፣ መንጋውን ከማነጽና ሐዋርያዊ አገልግሎትን ከማቅናት አንጻር ለአባቶቻችን ግዴታ ይሆንባቸዋል፡፡ የሚፈለገው ዕርቀ ሰላም እውን እንዲሆንም ለእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ለእውነት፣ ለኅሊና ምስክርነት መገዛት አግባብ ይሆናል” ሲል በትክክል ያስቀመጠውን ሐሳብ እዚህ ላይ ብንጠቅስ ተገቢ ይሆናል።

3.     አንዳንድ ሰዎች ስለ 4ኛው ፓትርያርክ ሲነሣባቸው የሚደነግጡበት ዐቢይ ምክንያት “የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ታሪክ ይደመሰሳል” ብለው በመስጋት ነው። እንደሚታወቀው ይህ ዕርቀ ሰላም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ የተጀመረ እንደመሆኑ ዕርቁ መሳካቱ ማንንም “የርሳቸው የቅርብ ሰው ነኝ” ባይ ሊያስደነግጠው አይገባም።

4.     ደጀ ሰላም ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን  በሚያደርጉት ተግባር ለረዥም ጊዜ ስትቃወማቸው እንደቆየች የአደባባይ ምሥጢር ነው። ስንቃወማቸው የነበረው ግን “በትክክል አልተሾሙም፣ ቀኖና የጣሱ ናቸው” ብለን አልነበረም። አይደለምም። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከመንበራቸው ከተነሱ በኋላ “ባዶ መንበር አግኝተውና ተመርጠው” መሾማቸውን እናውቃለን። በወቅቱ ለተፈጸመው ጥፋት አቡነ ጳውሎስን ተጠያቂ ማድረግ ትክክል አይሆንም። በታሪክም በእግዚአብሔርም ፊት ሐሰተኛ ያስብላል። በመንግሥት ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት፣ በቤተ ክህነቱ ሰዎች ተባባሪነት 4ኛው ፓትርያርክ ሥልጣናቸውን ተቀምተዋል። አቡነ ጳውሎስ 5ኛ ፓትርያርክ በመሆናቸው አጠፉ ማለት ትክክል አይሆንም። ነገር ግን ቦታውን ከያዙ በኋላ በፈጸሙት ተግባር ግን (መሬት ይቅለላቸውና) ስንኮንናቸው ቆይተናል። አሁንም “እርሳቸውን እወዳለኹ” የሚል ቢኖር (በቤተ መንግሥቱ እንደሚባለው የርሳቸውን ራዕይ ለማስቀጠል) በእርሳቸው ዘመን የተጀመረውን ዕርቅ ማሳካት እንጂ ሌላ አማራጭ የለውም።

5.     የዘመነ አቡነ ጳውሎስ ግርግር ሳያንስ አሁን ደግሞ ሌላ የከፋ ልዩነትና ብጥብጥ እንዲፈጠር እየተደረገ ያለው ሩጫ በእጅጉ የሚኮነን ነው። ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ እንዳሉት “በፍፁም ተቀባይነት የለውም”። ብፁዓን አባቶች ከዚህ ታሪካዊ ስህተት ራሳቸውን ነጻ ማድረግ አለባቸው። እውነቱን ተናግረው መከራውን መቀበል ካልፈቀዱ ራሳቸውን ከዚህ ውሳኔ በማውጣት ከጥፋቱ ራሳቸውን ማዳን ይኖርባቸዋል። በዘመነ ደርግ ታላቁን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ለመከራ አሳልፎ ለመስጠት በተደረገው ስብሰባና ፊርማ ላይ የነበሩ አባቶች በሙሉ ዛሬ ስማቸውና ፊርማቸው ከነታሪካቸው ይፋ እንደሆነው ሁሉ አሁንም ቀን ሲያልፍ፣ ጊዜ ሲለወጥ በዚህ ድርጊት ውስጥ ያሉት አባቶች እያንዳንዳቸው አንገታቸውን የሚደፉበት ታሪክ እንዳይቆያቸው ቢያስቡበት መልካም ነው።

6.     ፓትርያርክ መሾሙ ያደርሳችኋል። መጀመሪያ አንድ ሁኑ።

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።
“እኔም የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል”
  
6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም የሚደረገውን ጊዜውን ያልጠበቀ ሩጫ አልደግፍም

11 comments:

Anonymous said...

we have to protest this idea for the next 5 sunday for 30 minutes after the end of kidase we the diaspora should start it first and it will go to ethiopia what do you think?

Anonymous said...

we the memenan has to help our fathers they have problem that they can't tell we can tell that there is some problem from govt let us stand to protest and save our church.

Anonymous said...

With the help of GOD, we can bring some difference. Let us pray and fight the good fight.

Anonymous said...

Our fathers can protest. If they do not support electing the 6th partiarc, they can go to GEDDAME and declare SUBAE. If two or 3 of them do this, there will be many to follw. Do as you are told by him, Matthew 16:18, remember Matthew 6:6, John 18:36-38, John 19:10, Matthew 16:23
To all E/O/T/C members, please read your bible Matthew 24 and pray.
There are many fathers falling at the church entrance. May GOD open their heart to obey him. Amen.

Anonymous said...

May almighty God have mercy upon us and our church!

Anonymous said...

እስከ ዛሬ ለአባቶች ስለ ዕርቀ ሰላምና ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ሊነገር የሚገባው ቁም ነገር ሁሉ ከአደራና ከጽኑ ልመና ጋር ቀርቧል። አንዳንዶቹ የሰሙ አይመስሉም። የተጫናቸው ነገር ሊኖር ይችላል (ጥቅም፣ ፍርሃት፣ ጎሰኛነት፣ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት፣ ወዘተ)።
አሁን የሚቀረው ልዑል እግዚአብሔር እርዱኝ እረዳችኋለሁ ባለው መሠረት ድርጊት በኅብረት ብቻ ነው። ለዚህም መንደርደሪያ እንዲሆን የሚከተለውን መርሐ ግብር እናቀርባለን።
1. ራሱ ባወጀው ሕገ መንግሥት በምዕራፍ 2 አንቀጽ 11 ንኡስ አንቀጽ 3 “መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡” የሚለውን ሕግ አክብሮ እንዲያስከብር ገዢውን ሥርዓት አበክሮ መጠየቅ። ይህም አንገብጋቢ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ምእመናን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ስለሚመለከት ከሌሎች ተመሳሳይ ችግር ካለባቸው ጋር ድርጊቱን በቅርብ ማስተባበር።
2. በየአጥቢያው፣ በየአድባሩ፣ በየገዳሙና በየመድረኩ፣ እንዲሁም በጋዜጣ፣ በድረ ገጽ፣ በሬዲዮና በመሳሰለው የመገናኛ አውታር ዕልቆ መሳፍርት የሌላቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሆኑ ተቆርቋሪዎች ስለቤተ ክርስቲያኒቱ ዕርቀ ሰላምና አንድነት ያላቸውን ጥልቅ ስሜትና ያቀረቧቸውን ሀሳቦች በብቃት ያልተረዱ ብፁአን አባቶች እንደሚኖሩ ስለሚገመት፣ አንኳር የሆኑትን ጉዳዮች በማጠቃል ከልዩ ማሳሰቢያ ጋር በአስቸኳይ እንዲደርሳቸውና የጉዳዩን ክብደት እንዲገነዘቡት ማድረግ።
3. በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የደረሰውን አደጋ ለማስረዳትና ዘላቂ መፍትሔ በማፈላለጉ ተግባር ምእመናን እንዲሁም በጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብና መላው ዓለም እንዲረባረቡ ትክክሉን መግለጫና ዜና እያጠቀሩ የመገናኛ አውታሮች እንዲያበሥሩ መተባበርና ማትጋት።
4. በጥቅማ ጥቅምና በልዩ ልዩ ጫና ምክንያት ለዕረቀ ሰላሙና ለቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ቅድሚያ መስጠት የተሳናቸው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ቢኖሩ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ አድባራትና እስከ ገዳማት እንዲሁም በመላው ምእመናን ዘንድ በትክክል ታወቀው እንዲጸለይላቸውና በየግላቸው ልዩ አደራ እንዲጣልባቸው ስማቸውን ፈጥኖ በይፋ ማሳወቅ።
5. የዕርቀ ሰላሙን ጉባኤ ማበረታታት፣ እንዲሁም በሚጠይቀውና አስፈላጊ በሆነው ሁሉ መተባበርና መርዳት።
6. የመርሐ ግብሩን አፈጻጸም በቅርብ የሚከታተል፣ የሚመራ፣ የሚያስተባብርና የሚቆጣጠር ልዩ ግብረ ኃይል በአስቸኳይ ማቋቋም፤ ካለም ማጠናከር። ለዚህም ማኅበረ ቅዱሳንና ደጀ ሰላም ታላቅ ሚና እንደሚኖራቸው ይታመናል።
ልዑል እግዚአብሔር ለብፁአን አባቶች ቀናውን መንገድ እንዲያሳያቸው፣ ቤተ ክርስቲያኑና መንጋውን እንዲጠበቅ እንማጸነዋለን።

Anonymous said...

I agree let us not go home on sunday after kidase let us raise our voice(ask in a polite way) to our debr astedadari I will do that in my debr with my brothers and sisters and you all as well please please please this is our time to act not only our fathers.

Anonymous said...

To all mimenan
where is our voice for our church
lets say "I care About My church"
lets say it all togother all the diaspora church should start this to show the church in ethiopia.if we don't say something they feel like we are dead so lets start
Sunday morning

Berhanu M. said...

አባት እና ልጅ
=========

ልጅ አባቱን ቢክደው እንቢ አሻፈረኝ ቢለው ፤
አባት ነው ልጅ ? እኮ ማነው የሚጐዳው ።

አባት በልጅ ቢያዝን ፣ ልጅም ቢያዝን ባባት፤
ከቶ በማን ፣ ለማን ይደርሳል ጉዳት ።

እንዲያው ፣ መለኪያ ቢኖረው ለሃዘን ፤
የየትኛ ትካዜ ይበልጥ ይሆን ቢመዘን ።

ልጅ አባቱን ባይሰማ ፣ አባት ልጁን ቢቆጣ ፤
ልጅም ባባቱ ቢያዝንና ቤቱን ለቆ ቢወጣ ።

ልጅ ስብርብር ቢል ቢሆን ቆማጣ ፤
ማን ነው ጥፋተኛ ለሚመጣው ጣጣ ።

የአባት ፍቅሩ አይሎ ፣ ና በእኔ ዳን ልጄ ብሎ ፤
ይኸው ስጋየን ብላ ደሜን ጠጣ ብሎ አባብሎ ።

ልጅ እንቢ መዳን አልፈልግም ካለው ፤
አባት ወይስ ልጅ ? ለዚህ ቂመኛ ማነው ።

አባት ደግሶ ሊድር ልጁን ፤
እልፍኝ አስጥሎ አጽድቶ ደጁን ።

ካልታረቀው ልጅ አባቱን ፤
ማን ሊመርቅ ነው ዘሩን ፤
በምድር የዘራውን ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ከብርሃኑ መልአኩ

Anonymous said...

እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
የምንኩስና ግብር ምን ነበር ምሥጢሩ
የክርስትና ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ
መቃብሩን ክፈቱና አበው ይመስክሩ፡፡

እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ
ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡

ነብያት በመጋዝ የተሰነጠቁት
ሐዋርያት ቁልቁል የተዘቀዘቁት
ሰማዕታት በእሳት የተለበለቡት
ቅዱሳን በገዳም ደርቀው የተገኙት
ምሥጢሩ ምን ነበር? አበው ይናገሩት፡፡

ይናገር ዝቋላ ግሸን ላሊበላ
የቅዱሳንን ዐፅም ለምን እንዳልበላ፡፡
ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር
እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡
ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት?
ወይስ ሀብት ንብረት የተሟላ ቤት?
ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት?
እናንተ ገዳማት ምሥጢሩን አውሩት፡፡

ጐበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና
ምግባር ሃይማኖቱ በእጅጉ የቀና፡፡
እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት
ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡
የጊዮርጊስ ወገን የት ነው የማገኘው?
በመሀል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው?
ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው?

ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ሰው አማረው
የሃይማኖት ጀግና የትነው የማገኘው?
ልግባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት
ማኅበረ ሥላሴ ከቅዱሳን ቤት?
አክሱም ግሸን ማርያም ከቃል ኪዳን ቦታ
ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ?
ፈሪሐ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ
ቤተ ክርስቲያንን ያልተደፋፈረ፡፡

የት ነው የማገኘው ለሃይማኖቱ ሟች
ለተዋሕዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች፡፡
የወገን መመኪያ የከሀዲ መቅሰፍት
ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሣ ቀስቅሱት፡፡
እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምሥጢሩ?
የክርስቲያን ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ?
መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡

ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ጀግና አማረው
በእምነቱ የፀና የትነው የማገኘው?
ብቅ ይበል እንየው እሱ ማነው ጀግና?

በጐችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ
መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ
የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ
እንደዚያ እንደ ጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ?
የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው
የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው
የዓለም አሸክላ ልቡን ያልማረከው
የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው?
ምሥጢርን ከምሥጢሩ አንድ አድርጐ ቀምሮ
ወልድ ዋሕድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ
እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ
ከአትናቴዎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡

ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር
መሆኗን የሚያምን ማኅደረ እግዚአብሔር
ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን
ትንታግ ምላስም ጭንግፍግፉን
ልሳነ ጤዛ መናፍቅን
ወልደ አርዮስ ዲቃላውን፡፡
በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ
ጀግና ማነው ዝቅ ይበላ፡፡

ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት
እስኪ ጎርጎርዮሰ ይምጣና ጠይቁት
ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ
ምሥጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ፡፡

የክርስቶስ ባርያ የአጋንንት መቅሰፍት
ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት
ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት
የጸሎት ገበሬ ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ይነሣ ቀስቅሱት
ይነሣ ጊዮርጊስ ይመስክር ምሥጢር
የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡

ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ
ዲያብሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ፡፡
ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ
መር ብለው የወጡት ከሥጋ ገበያ
ጾም ጸሎት ነበረ የሃይማኖት ጋሻ
መልከስከስ ምንድነው እንደ አበደ ውሻ፡፡

እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት
ዓላማው ምንድነው የዘመኑ ወጣት፡፡

እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ
ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡

ምንጭ፡- መለከት 1ኛ ዓመት ቁጥር 6

Unknown said...

ክቡራን ደጀሰላማውያን እንዲሁም ማኅበረ ቅዱሳን ፣ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ያለው 20 ዓመት የዘለቀውን የክፍፍል ችግር ለመፍታት በሚደረገው ርብርብ የምትጫወቱትን አወንታዊ ሚና እያደነቁ ከመጡት የቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን አንዱ ነኝ። አንዳንዴ ግን ግልጽ ያልሆኑ አቋሞች ስታንጸባርቁ አያለሁ። ያም ምንድንነው ? ካላችሁ፥ በመንግሥት ኃይል ከመንበራቸው የተሰደዱት ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው ይመለሱና የተጣሰው ቀኖና ይስተካከል በሚለው መሠረታዊ አቋም ላይ ያላችሁ እምነት ነው። አዎ ለእርቀ ሰላሙ ጠንክራችሁ እየሰራችሁ ነው። ግን ከመጀመሪያውም የጥሉና የክፍፍሉ ዋና ምክንያት የሆነው ፓትርያርክ በሕይዎት እያለ ሌላ ''ፓትርያርክ'' በመሾሙ ነው። ሌላ ምንም ምክንያት የለም። ይህን ከማስተካከል ሌላ ምንም መፍትሔ ሊኖርም አይችልም። በዚህ ላይ ያላችሁን አቋም "ይኩን ባሕቱ ነገርክሙ እመሂ 'እወ' ይኩን 'እወ'፤ ወእመሂ አልቦ ፥ አልቦ ። ወፈድፋደሰ እምእሉ እምእኩይ ውእቱ=ስለዚህ ንግግራችሁ 'አዎ' ከሆነ 'አዎ' ፥ 'አይደለም' ከሆነ ከሆነ 'አይደለም ' ይሆን። ከዚህ የተረፈ ቃል ግን ከሰይጣን ነው ።" ማቴ. 5 ቁ.37 በሚለው መሠረት አድርጉት። ይህ ነው የክርስቲያኖች አቋም መሆን ያለበት። ባንድ እውነታ ላይ ሁለት እውነት ሊኖር አይችልምና !።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)