December 22, 2012

መኳንንት እጆቻችሁን ከቤተ ክርስቲያን አንሡ


“አንስኡ እደዊክሙ መንንት እም ቤተ ክርስቲያን
 (መኑ ከማከ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት/ READ IN PDF)፦ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጃት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአዳም ልጆችን ለሰማያዊ ርስት የምታዘጋጅ መንፈሳዊ ተም ናት፡፡ ባለቤቱ በማዕከለ ምድር ቀራንዮ የተሰቀለበት፣ እር ለጌታዋ ሙሽራ ሆና የምትኖርበት ምክንያት አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡፡ እርሱም በእንጨት ፍሬ የወደቀውን የአዳምን ዘር ወደ ቀደመ ክብሩ እና ቦታው መመለስ፡፡ ሰውን ከሞት ወደ ሕይወት ማሸጋገር ነው፡፡ በአርባ እና በሰማንያ ቀን ከተቀበልነው የልጅነት ሥልጣን አንሥቶ እስከ መጨረሻው የቤተ ክርስቲያን ማዕረግ /ፕትርክና/ ያለው ሥልጣንና ላፊነት ሁሉም አንድ ዲናር ለማግኘት የምንሰራባቸው ናቸው፡፡ አንድ ዲናር አንድ መንግሥት አንድ ክብር በማለት ይተረጎማል፡፡


ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅና ለመምራት የተሾሙ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ገዳማቱን ተጠግተው በማበር የሚኖሩ መነኮሳት፣ በየዋሻው በየፍርክታው የወደቁ መናንያን፣ በተቀደሰ ጋብቻ ፀንተው የሚኖሩ ሕጋውያን፣ በየአድባራቱ ለአገልግሎት የሚራወጡ ዲያቆናት ቀሳውስት፣ የቅኔ ማኅሌቱ መዘምራን፣ የወንጌልን ቃል ለማዳረስ የሚደክሙ መምህራን፣ እነዚህ ሁሉ በአንድነት ስለ አንድ ነገር ይደክማሉ፡፡ እርም መንግሥተ ሰማያት ናት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ስለ መንግሥተ ሰማያት ሲጽፍ “ዘዓይን ኢርእየ፣ ወእዝነ ኢሰማዕ፣ ውስተ ልበ ሰብእ ዘኢተሀለየ ዘአስተዳለወ እግዚአብሔር ለዕለ ያፈቅርዎ፤ ዓይን ያላየው ጆሮም ያልሰመው በሰው ልብ ያልታሰበ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ያዘጋጃት” ይላል፡፡

አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ “ኦ አንትሙ ሕዝበ ክርስቲያን በከመ ተጋባእክሙ በዛቲ ዕለት ከማሁ ያስተጋብእክሙ በደብረ ጽዮን ቅድስት ወበኢየሩሳሌም አግዓዚት እንተ በሰማያት። እናንተ የክርስቲያን ወገኖች ዛሬ በዚህች ዕለት እንደተሰበሰባችሁ እንደዚህ ክብርት በምትሆን በደብረ ጽዮንና በሰማይ ባለች ነጻ በምታወጣ በኢየሩሳሌም ይሰብስባችሁ።” /ቅዳሴ ማርያም ቁ.156/ በማለት ስለመንግሥተ ሰማያት ይመሰክራል። በዚህች ዕለት ያለው ቀድሶ ያቆረበባትን ነው። በዚህች ዕለት በቤተ ክርስቲያን እንደተሰበሰባችሁ ክብርት በምትሆን በደብረ ጽዮን ይሰብስባችሁ ከተፈጥሮተ እደ ሰብእ ነጻ በምትሆን በኢየሩሳሌም ሰማያዊትም ይሰብስባችሁ ሲለን ነው፡፡ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ንጉሠ ሰማይ ወምድር ኢየሱስ ክርስቶስ በስሙ አምነው በሃይማኖት ፀንተው፣ በምግረ ሰናይ አጊጠው ለሚያልፉ ቅዱሳን ክብርን የሚያድልባት ሥፍራ ናት፡፡

በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚደክሙ አበው በምድር ላይ የሚገጥማቸውን ፈተና አልፈው ወደ እርሷ ይገባሉ፡፡ ኃላፊነቱን ለሰጣቸው ጌታ ብቻ ሲታዘዙ ይህችን ርስት ገንዘብ ያደርጋሉ፡፡ እመናንም በሃይማኖት በምግባር ሲፀኑ “ንዑ ሀቤየ ቡሩካኑ ለአቡየ እናንት የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ” የሚል ድምጽ ይሰማሉ፡፡ ሐዋርያት ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባናል እያሉ የመሰከሩት ለዚህ ነው፡፡ በዓላውያን ፊት የፀኑት ን /መንግሥተ ሰማትን/ በማሰብ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚነግረን ቅዱሳን ሐዋርያት ቀጥሎም አበው ሐዋርያት፣ ከዚያም ሊቃውንት፣ ሁሉም በየዘመናቸው ቤተ ክርስቲያንን ያገለገሉት በብዙ መከራ ነበር፡፡ በእሳት ተቃጥለው፣በመጋዝ ተሰንጥቀው፣ ለአናብስት ተሰጥተው ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል፡፡ አደራቸውን በሚገባ ተወጥተዋል፡፡ ልቡናቸውን በሰማያት አድርገው ስለሚዙ በዓላማ በአም የፀኑ ነበሩ፡፡ ከእግዚአብሔር የሚያገኙትን ዋጋ እያሰቡ ሁሉንም በአኮቴት ይቀበሉም ነበር ፡፡

በዘመናችን እንደ ቀደሙ ሐዋርያት ያለ ናት፣ ስለ መንግሥተ ሰማያት ማሰብ፣ መሥራት ከመሪዎች ይጠበቃል፡፡ አላውያን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይቀርቡ፣ለመንፈሳዊው አገልግሎ እንቅፋት እንዳይሆኑ መሪዎች ትጉኅ እረኛ መሆን ይገባቸዋል፡፡ሐዋርያው “እንዲሁ ሰው እኛን እንደ እግዚአብሔር ምሥጢር መጋቢዎች ይቁጠረን፡፡ እንደዚህም ሲሆን በመጋቢዎች ዘንድ ታማኝ ሆኖ መገኘት ይፈለጋል፡፡” (1ቆሮ 4-1) እንዳለ መሪዎች ለተጠሩለት ዓላማ ታኝ ሊሆኑ ግድ ይላል፡፡ ይህ ካልሆ ግን ጠንካራ መሪ ሲጠፋ ቤተ ክርስቲያን የመናፍቃንና፣ የዓላውያን መረማመጃ፣ አጥር እንደሌለው ቤት የኃላፊ አግዳሚው መውጫ መውረጃ ትሆናለች፡፡ መንፈሳዊ ተም የሚለው በጽሑፍ የሚነበብ ብቻ ይሆንና በተግባር ግን ምድራዊውን ፖለቲካ መፈፀሚያ ማስፈፀሚ ወደ መሆን ትሸጋገራለች፡፡

ሰሞኑን በሁለቱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል የተጀመረው የእርቀ ሰላም ውይይት በብዙዎች ልቦና ተስፋን የጫረ ነበር፡፡ ውጤቱ እንዲሰምርም ሁሉም በየሥፍራው የተዋሕዶን አምላክ እየለመነ ነበር፡፡ ነገር ግን ችግሩን እግዚአብሔርና ጥቂት ግለሰቦች በሚያውቁት ምክንያት የታሰበው ሁሉ እንዳልታሰበ ሆኖ መምጣት ጀመረ፡፡ ታሪክ ሠርተው ቀንበራችንን ይሰብራሉ ያልናቸው አበው ሌላ የብረት ቀንበር ሊጭኑብን እየተዘጋጁ ለምርጫም እየተጣደፉ መሆናቸውን ሰማን፡፡ በጉዳዩም እጅግ እጅግ አዘንን፡፡ ሌላ ሠላሳና አርባ የልዩነት ዓመት ለማምጣት ከመቻኮል አንድነቱን ማስቀደም የመጀመሪያም የመጨረሻም አማራጭ መሆን ነበረበት፡፡ ግን ሳይሆን ቀረ፡፡

ለመሆኑ በዚህ ጉዳይ ማንን እንጠይቅ? እነዚያ ስለቤተ ክርስቲያን አንድነት ሲራወጡ የምናውቃቸው አባቶች በፍጥነት ሐሳባቸውን የቀየሩበት ምክንያት ምንድን ነው ብለን እንገምት? በብዙዎች እምነት ይህ ድርጊት ያልታወቀ እጅ ያለበት ነው፡፡ከአባቶች ጀርባ ሌላ አካል አለ እየተባለ ነው፡፡ ይህ እጅ የመንግሥት እጅ እንደሆነም መነገር ከጀመረ ውሎ አደረ፡፡ ጉዳዩ እውነት ከሆነ፣ እና የመንግሥት አካላት እጃችሁን አስገብታችሁ ከሆነ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን:: ንንት እጆቻችሁን አንሱልን እንላለን፡፡ እናንተ ከምትጋደሉለት ዓላማ በብዙ ሺህ እጥፍ የሚበልጥ ሰማያዊ ዓላማና ሥልጣን አባቶች እጅ አለ፡፡ እነዚህን አባቶች ከሰውም ከእግዚአብሔርም እንዳታጣሉ መንንት እጆቻችሁን ከዚህች ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን ላይ አንሱ፡፡ የሃይማኖት ነጻነት እንዳለ በሚነገርበት አገር ይህንን ማድረጉ ተገቢ አይደለምና መንንት እጆቻችሁን አንሱ፡፡

በእናንተ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ የሃይማኖት ሰዎችን አጥብቃችሁ እንደምትኮንኑ ሁሉ በሃይማኖታዊ ጉዳይ ጣልቃ ስትገቡ ቅሬታችን ወሰን የለውም፡፡ እነዚህን አባቶች የሾመ ሰማያዊ ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ለአገልግሎት የተጠሩት፣ የመነኮሱት፣ ለጵጵስና ማዕረግ የበቁት እርን ሊያገለግሉ እንጂ የእናንተ መሳሪያ ሊሆኑ አይደለም፡፡ እንደ ሰናኦር ሰዎች ተግዳሮታችሁ ከፈጣሪ ጋር እንዳይሆን መንንት እጀቻችሁን አንሱ፡፡ የቄሣርነት ድርሻ ለእናንተ ይበቃል የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር መልሱ፡፡ ይህ መልእክት እጃችሁ ካለበት ይድረሳችሁ፡፡ ከሌላችሁበት እንቀጥላለን ፈጣሪን በጸሎት እየተማፀንን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላትም የልጅነት ጥያቄያችንን እናቀርባለን፡፡ ለመሆኑ ይህች እጅ የማን ናት?፡፡ ለአንድነቱስ እንቅፋት የሆነ ማን ነው? የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ ጥያቄ፡፡
                                                               ወስብሐት ለእግዚአብሔር

7 comments:

Anonymous said...

መኳንንት እጆቻችሁን ከቤተ ክርስቲያን አንሡ

Anonymous said...

ግን ለምን የዕርቁ ጉዳይ አልተሳካም? ወይም አይሳካም?

ትልቁ ነገር እግዚአብሔር አልፈቀደም።

እንደስጋዊ ግን ብዙ ጊዜ አሁን ለደረስንበት የማልጨነቀው ነገር አለኝ። ጆሮ መስጠት ብዙ ጊዜ ይጠቅማል።
ገና የእርቅ ኮሚቴው ሲጸነስ ፤ በሰሜን አሜሪካ ሁለት ነገሮች የወቅቱ አነጋጋሪ የነበሩበት ወቅት ነበር።
1- የሰሜን አሜሪካ የሰንበት ት/ቤቶች እጣ ፈንታና
2- "የዕርቅ ኮሚቴ ወይም የሰላምና የአንድነት ጉባኤ" ጉዳይ

የመጀመሪያውን ልዝለልና ሁለተኛው ግን በወቅቱ በአህጉራቱ ባሉት በተለይ በሁለት አህጉር-ስብከት አባቶች የኮሚቴው ቅርጽም ሆነ ይዘት የጣማቸው ስላልነበር ተቀባይነት በጣም ዝቅተኛ ነበር። ከዚያም በሊቀ ካህናት መሪነት ወደ አዲስ አበባ ወደ "የበላይ" ወደ አቡነ ጳውሎስ ተገባ። ብዙም ሳያለፋ በአቡነ ጳወሎስ አመቻችነት "ዘመድን ለማስደሰት ሲባል" ኮሚቴውን በሲኖዶስ እውቅና እንዲያገኝ ተደረገ። ብዙ አባቶች ባፈጣጠሩ አዘኑ ግን በወቅቱ እንኳን ማዘን ድብደባም ደርሶባቸዋልና።
ከዚያም አቡነ ጳውሎስም ይሁኑ ሌላው "መኳንንት" ነገሩ ወደ አላስፈላጊ እንዳይሆንም እነ.... እገሌ በውስጡ እንዲካተቱ የተደረገውና የሚደረገው።
አሁን ኮሚቴው ነጻነቱን አወጀ፤ የሰሜን አሜሪካ አባቶችንንም ከማማከርና አብሮ ከመስራት ይልቅ ከ "ሌሎች" ጋር መማከርና መስራት ተመረጠ። ይህ ደግሞ እዚ ያሉትን አባቶች ብቻ ሳይሆን በሀገር ቤት ያሉትን በርካታ አባቶችንና በውጭም (ለምሳሌ ባለሁበት፤ በድፍን ቴክሳስ) በርካታ መእመንን ያሳሰበ ነበር።
ከዚያም አቡነ ፋኑኤል የአህጉሩ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ የቻሉትን ለማድረግ ቢጥሩም፤ ጊዜው ደግሞ ሌላ መዘዝ ይዞ የመጣ ስለነበር ጭራሽ በቁስል ላይ ቁስል ተፈጠረ።
- አቡነ ጳውሎስም አረፉ።
- ኮሚቴው ወዴት አቤት ይበል?
- 'ይህ አጋጣሚ' የሚለው አባባል በርካታውን የኢንተርኔት አምደኞችን አነጋገረና ኮሚቴውም የተቻለውን እንዲንቀሳቀስ አደረገ፤ ግን አብዛኛውን የሀገር ቤት ቀርቶ የውጩንም አማኝ አላነሳሳም/ አላሳመነውም።
- ሌላው በውጭ ያሉት አባቶች አንዳንድ ጊዜ በሚዲያውና በየ ዩብ-ቲዩብ እየደረሱና እየወጡ የሚሰጡት ሃሳቦች ለእርቁ የሚሰጠው ኔጌቲቭ እንዳሉ ሆኖ፤
- የፖለቲካ አይኖችንና ጭንቅላቶችንም ትቼ፤
-----------
ባጠቃላይ ነገሮችን እቅልለናቸውና በሩጫ አንመልከታቸው።
እውን የቤተ-ክርስቲያኗ 'ፕትርክና' ጉዳይ በበርካታ ደጀ ሰላማዌያን ፍላጎት ቢፋታ ሰላም ይፈጣራ?

ማን ያውቃል?። እኔ ግን የወጣትነቴን እድሜዬን ጨርሻለው!
አንዴ አይደልም ሁሌቴ እናስብበት። እንተኛበት። ከሁሉ በላይ እነጸልይበት።

ባልታዛርBaltathar said...

ለቅድስት ቤቱ የሚያውቅበት ከሃሊ አምላክ ይታገሳል፡፡ አዎን በማይነጥፍ ትዕግስቱ ይታገሳል፡፡ እርሱ የአማልክት አምላክ ፍርዱ ቅን፣ የእውነቶችም ሁሉ እውነት የሆነ ዛሬም ይታገሳል፡፡ ወዮ! እናንት አበሳችሁ የበዛ መሳፍንት፣ ከቀድምቶቻችሁ ስህተት አትማሩምን? የተክለሃማኖት አምላክ ይፋረዳችኋል፡፡ ጊዜው ሩቅ አይደልም፡፡ ወዮ! ነገርን ሁሉ ውብ አድርጐ ይሰራዋል ሃሌሉያ፡፡ ለእናተ መኳንንት ግን ወዮ፣ አቤቱ የድንግል ማርያም ልጅ ፍረድ፣ የመጀመሪያው ሁሉ መጀመሪያ ሕያው አምላክ ሆይ እባክህ ዝም አትበል፡፡ መንጋህን ሊበትኑ የዱር አናብስት ከበዋታልና፡፡ ልዑል ሆይ አትዘግይ! አሜን

ባልታዛርBaltathar said...

ለቅድስት ቤቱ የሚያውቅበት ከሃሊ አምላክ ይታገሳል፡፡ አዎን በማይነጥፍ ትዕግስቱ ይታገሳል፡፡ እርሱ የአማልክት አምላክ ፍርዱ ቅን፣ የእውነቶችም ሁሉ እውነት የሆነ ዛሬም ይታገሳል፡፡ ወዮ! እናንት አበሳችሁ የበዛ መሳፍንት፣ ከቀድምቶቻችሁ ስህተት አትማሩምን? የተክለሃማኖት አምላክ ይፋረዳችኋል፡፡ ጊዜው ሩቅ አይደልም፡፡ ወዮ! ነገርን ሁሉ ውብ አድርጐ ይሰራዋል ሃሌሉያ፡፡ ለእናተ መኳንንት ግን ወዮ፣ አቤቱ የድንግል ማርያም ልጅ ፍረድ፣ የመጀመሪያው ሁሉ መጀመሪያ ሕያው አምላክ ሆይ እባክህ ዝም አትበል፡፡ መንጋህን ሊበትኑ የዱር አናብስት ከበዋታልና፡፡ ልዑል ሆይ አትዘግይ! አሜን

Anonymous said...

ወይ የኢ/ት መንግስት የባልና የሚስት ጭቅጭቅም እኮ ወደፊት የወያኔ እጅ አለበት የዳቁኑና የቄሱ ጭቅጭቅ የወያኔ እጅ አለበት ለምንድነዉ ችግሩ የኛ ነዉ የማንለዉ ጭብጥ በሌለዉ ነገር ዝም ብሎ ባሉባልታ መንግስትን መኮነን ህዝብን ከህዝብ አባቶች ከአባቶች በመለያየት አንድነት እንዳይመጣ ማድረግ እኮ ነዉ በእዉነት አንድነቷን የምትፈልጉ እስቲ መጀመሪያ እናንተ የፖለቲካ ስሜታችሁን ዋጥ አድርጉት እንደሰዉ አመለካከት በግልጽየሚታየዉን ችግሩያለዉ አባቶች ጋ ነዉያለዉ ለምንድ ነዉ የማትሉት የምን የናታቸዉ መቀነትጠለፋቸዉ ማለት ያስፈለጋል እራሳቸዉ በሰሩት እዚህዉጭ ሃገር ያሉት አባቶች መች ለአንድነት ልባቸዉ ተከፈተ የእነሱም የወያኔ እጅ አለበት

Anonymous said...

ወይ የኢ/ት መንግስት የባልና የሚስት ጭቅጭቅም እኮ ወደፊት የወያኔ እጅ አለበት የዳቁኑና የቄሱ ጭቅጭቅ የወያኔ እጅ አለበት ለምንድነዉ ችግሩ የኛ ነዉ የማንለዉ ጭብጥ በሌለዉ ነገር ዝም ብሎ ባሉባልታ መንግስትን መኮነን ህዝብን ከህዝብ አባቶች ከአባቶች በመለያየት አንድነት እንዳይመጣ ማድረግ እኮ ነዉ በእዉነት አንድነቷን የምትፈልጉ እስቲ መጀመሪያ እናንተ የፖለቲካ ስሜታችሁን ዋጥ አድርጉት እንደሰዉ አመለካከት በግልጽየሚታየዉን ችግሩያለዉ አባቶች ጋ ነዉያለዉ ለምንድ ነዉ የማትሉት የምን የናታቸዉ መቀነትጠለፋቸዉ ማለት ያስፈለጋል እራሳቸዉ በሰሩት እዚህዉጭ ሃገር ያሉት አባቶች መች ለአንድነት ልባቸዉ ተከፈተ የእነሱም የወያኔ እጅ አለበት? እግዚአብሄር ይስጥህ ተቃዋሚዎች በተለይ እጃችሁን አንሱ ሊባሉ ይገባል የእነኝህ አባቶች ወደዉጭ መሰደድ በዉጩ ዓለም ለተፈጠረዉ ሁሉ ተጠያቂ ማን ነዉ ወያኔ? የገለልተኛ እርስ በእርስ አለመስማማት ተጠያቂ ወያኔ?እዉነት ካልተናገርን እግዜር እንዴት ይታረቀን መወቀስ ያለበትን ትተን ዝንብለን በጥላቻ ሌላ የምንወቅስ ከሆነ እንዲህ አይነትሁኔታ ቁጣ ነዉ የሚያመጣዉ በተለይ በአሁኑ ጊዜ አቡነ መርቆርዮስ ከነ ሙሉ ስልጣናቸዉ ካልተመለሱ የሚለዉ አንግበዉ የፖለቲካ ድል የሚመስላቸዉ ቤ/ክንም አንድነቷን ካገኘች ህዝቡን የሚያገኙበት ሌላ መንገድ የሌላቸዉ የሚመስላቸዉ ተቃዋሚዎች ከዚህ ፈቀቅ እንዳትሉ የሚሉ ተቃዋሚዎች እጃችሁን አንሱ ሊባሉ ይገባል [

Anonymous said...

thank you በተለይ ዛሬ ሳያምኑ ዓርብ ሮብ ሳያውቁ ትላንት ኢሃፓ ወይ ደርግ የነበሩ ያንን ህይማኖታዊ የዘዉድ አገዛዝን አማኙን ትዉልድ ገድለዉ ቤ/ክ በሯን ዘግተዉ አባቶች ገድለዉ ዛሬም ትዉልዱ እነሱን ተሻግሮ አያቶቹን መስሎ እግዚአብሄር አለ ብሎ ወደ ቤ/ክ ቢመጣ መግደል እንጂ ሰላምና መቻቻልን ያለመደባቸዉ ሳያምኑ ወደ ቤ/ክ ተከትለዉት መጥተዉ በማርኪስዝም ሌኒንዝም ምላሳቸዉ ቦርድ ሆነዉ ለዚህ ያደረሷት እነሱ ናቸዉ ዛሬም በሁለቱም አቅጣጫ ለቤተ/ክ ችግሮቹ በተለይ በዚህ በዉጩ ዓለም ያሉት የሃገራችን ፖለቲካ ሁኔታ የበላን ቦታ ያከኩልን እየመሰለን ለዚህ ሲያደረሷት እያየን እኮ ነዉ እዚህ ያሉ አባቶች እኮ ከአቡነ መርቆርዮስ ጀምሮ ኪድናፕ ነዉ ያደረጓቸዉ መንፈሳዊ ሳይሆኑ መንፈሳዊዉን ሲያስተዳድሩ እኛ ባልናቹ ነዉ እያሉ ክፋትን አለማምደዋቸዉ ከመኮራረፍ አልፈዉ ትላንት በሯን ከዘጉባት ፓትሪያርኳን ከገደሉባት በባሰ ሁኔታ በታሪኳ አይታዉ የማታዉቅ ክፋት ባባቶች ልብ ተክለዉ ገፋፍተዉ በዉጭ ሲኖዶስ የሚል ነገር የመጨረሻ የብጽእና ማረግ ያደረሰቻቸዉን እንዲክዱ አደረጓቸዉ ስለዚህ ሁላችንም እዚህ አጠገባችን ያሉት እጃችሁ አንሱ እንበላቸዉ እነ ኢሳትም ለቤ/ክ ዉስጣቸዉ መርዝ ነዉ አንድ ከሆነች ኢንተርቪ የሚያደርጉት መነኩሴና ድንጋይ የሚያጨባብጡበት መድረክ አያገኙም

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)