December 30, 2012

ቅዱስ ሲኖዶሱ የማን ነው? የእኛ ነው ወይስ?


(ከመልዕክተ ተዋሕዶ - ዘሮኪ/ PDF)፦ እንግዲህ ላለፉት 20 ዓመታት ከችግራችን ጋር ተወልዶ፥ ያደገው መንግሥት ፥ አቋሙን በግልጽ አሳውቆናል።  “ነገ ልትዳሪ ነው ሲሏት፥ ካልታዘልኩ አላምንም እንዳለችው ሙሽራ መሆኑ ይብቃን፥ እርማችንን እናውጣ። ስለ ነገ እናስብ፥ ስለ ቤተ ክርስቲያን እናስብ፥ ስለ አባቶቻችን እናስብ። የግዴታ ማክሰኞን መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም።
ቅዱስ ሲኖዶስ በመጪው ማክሰኞ  በሚያደርገው ስብሰባ ላይ፥ ካስታወሰን መልዕክታችንን መነጋገር ያለብን፥ ዛሬንና ነገ ብቻ ነው። የመንግሥትን አቋም ባይገርመንም የሚጠበቅ ስለሆነ ሰምተነዋል። የቅዱስ ሲኖዶስ ግን ማክሰኞ ይለይለታል። ቅዱስ ሲኖዶስ የማነው ወይ የኛ የኦርቶዶክስያዊያኑ ነው! አለበለዚያ፥ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለመንግሥት ነው። እንደኔ እንደኔ  የቅዱስ ሲኖዶስም ቢሆን፥ ግልጽ ይመስለኛል።  ይህንን ለመረዳት፥ ወደ ፊት ሁለት ቀን ጠብቆ ማየት ሳይሆን፥ ወደ ላ ብዙ ዓመታትን ማስታወስ ይበቃል። ያለፉትን ሁለት ሶስት ሳምንታት ብቻ እንኳን ስርመረምሩ፥ እውነታው ቅዱስ ሲኖዶስ ከመንግሥት ፍላጎት ውጪ አንድ ቀን እንኳን በነጻ አስተሳሰቡ ውሎ ማደር እንዳልቻለ ግልጽ ነው። ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ የቅዱስ ሲኖዶስ አካሄድን ነቅፈው፥ መሆን ያለበትን ተናግረው ውለው ሳያድሩ የደንነት ክፍሉ ኃላፊ “ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ ዝም ነው ሰኟቸው። በግዴታም ፈረሙ። ነገ ወደ አገር መግቢያ የላችሁም ተባሉ። ተስማሙም። ይህ በቂ አይመስላችሁምን? ጠብቀን እንስማው፥ ካላችሁ ግን ፥ ታገሱ።

የተዋሕዶ ልጆች፥ ዛሬ ቅዱስ አትናቴዎስ፥ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፥ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ፥ በአካል የሉም። ማን እነሱን ይሁን? ቡዙ የምንወዳቸው፥ የምናደንቃቸው ብጹአን ሊቃነ አልነበሩምን እንዴ? የት ሄዱ? ቢያንስ ካሉን ሊቃነ ጳጳሳት አንዳቸውስ !! እንኳን፥ ስለፍቅርና የቤተ ክርስቲያን አንድነት፥ በአደባባይ መናገር ይፍሩ? የተዋሕዶ ልጆች፥ ስለ አንቀጽ 39፣ ወይም ስለ ኢትዮጵያ አንድነት፥ ስለ ኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት፣ወይም ዘረኝነት እኮ አይደለም ጥያቄው! ያንን ያነሳ እማ መድረሻም የለውም። ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት መናገር ብቻ!! በግልጽ ቤተ ክርስቲያን አንድ ትሁን ማለት፤ ከፓትርያርክ ምርጫ በፊት ዕርቀ ሰላም ይውረድ ማለት፤ የፈረሰው ይስተካከል፥ የጠመመው ይቅና፥ ብሎ መናገር፥ መመስከር አስፈርቷቸዋል። በእናንተ ፍርሀት የተነሳ፥ ነገ መሥዋዕትነት ሊከፍሉ የተዘጋጁ፥ የተዋሕዶ ልጆች ያሣፍሯችኋል። ዛሬ እናንተ ለቤተክርስቲያናችሁ ብትቆሙ፥ ነገ ከእናንተ ጋር ቆመን ዋጋ ብንከፍል ያምርብን ነበር። ግና፥ ይህ የሚሆን አይመስለኝም።

ከዚህ በኋላ መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያለን ሁሉ፥ በየሰበካችን ነገ በዚህ ጉዳይ ላይ መወያየት ይጠበቅብናል። ምን ብናደርግ ይሻላል? የሚሰሙ ብፁዓን አባቶች አሉ ብሎ የሚያምን በስልክም፣ በኢሜልም እንዲሁም በአካል ተገኝቶ ያስረዳ። ሌላው፥ መላው ሰባያነ ወንጌል መምህራን ነገ ይህንን ጉዳይ አንስታችሁ ምን ማረግ እንደሚሻል፥ ተወያዩ። መምህራኑ ዝም ካሉ ደግሞ፥ ምእመናን ጠይቁ፥ መብታችሁ ነው። በየኤምባሲውና የመንግሥትና የቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ባሉበት፥ አቤቱታችሁን አሰሙ። ሰላማዊ ሰልፎች ከቤተ ክህነቱ ቢሮ ጀምሮ እስከ ሊቃነ ጳጳሳቱ መኖሪያ ድረስ፥ ይደረጉ። ማበረ ቅዱሳንም ሆነ ሌሎች መንፈሳያን ማበራት ከቤተ ክህነቱ ጋር ያላችሁ ግንኙነት እንዳይበላሽ በመጋት መደረግ የሚገባውን ሳትዘገዩ ዛሬ አድርጉት! ያለበለዚያ የእናንተም አስፈላጊነት አጠያያቂ ይሆናል። ትምህርተ ወንጌልን ማዳረስ፣ ገዳማትን ማጠናከር፣ አረጋያንን መርዳት፣ መምህራንን በሚያስፈልጋቸው መርዳት የሚቻለው ቤተ ክርስቲያን ሕልውናዋ ተጠብቆ፥ አንድነቷ ተከብሮ ሲገኝ ብቻ ነው። አር ባይነት በታሪክ ያስወቅሳል። ያስፈርድማል።

ለምርጫ ራሳችሁን ያዘጋጃችሁት አባቶቻችን ልብ ግዙ። እነ ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ እነ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ወዘተ የቤተ ክርስቲያንን ችግር ከውስጥም ከውጭም ሆናችሁ አይታችሁታል። ይህ ኃላፊ ወቅት አያታላችሁ። ነገ ይቆይ እንጂ፥ በኦርቶዶክሳያን መዋዕትነት፣ይነጋል።

በዚህ አጋጣሚ፥ ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዓለማየሁ፣ መልአከ መንክራት ቀሲስ አንዱዓለም፣ ዲያቆን አንዱዓለም፣ ቀሲስ ፋሲል ወዘተ ከገለልተኛው ወገንና በውጭው ዓለም የሚገኙትን አባቶች፥ የወከሉትን በአጠቃላይ፥ በመላው የሰላምና አንድነት ኮሜቴ ስም፥ ላደረጉት ታሪክ ማይረሳው፥ ቤተ ክርስቲያን የማትረሳው ትልቅ አርአያነት ያለው ሥራ እግዚአብሔር አምላክ በሰማያት ዋጋችሁን ይክፈላችሁ እላለሁ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

12 comments:

Kebede Bogale said...

ጥቂቶች አይደለንም ብዙዎች ነን ለቤተ ክርስቲያናችን የምንቆረቆር ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሥጋዊ ሕይዎታችንም የማንነታችን መታወቂያችን ናት ፤ ከዚህ ዓለም በምናልፍበት ጊዜም ወደ መንግሥተ ሰማያት የምንገባባት በራችን ናት። ስለሆነም የሁላችን የአማኞቿም ጭምር እንጅ የጳጳሳቱ የገል ንብረት አይደለችም። እነሱን የምናከብራቸውና ትእዛዛቸውን የምንቀበለው እነሱም የክርስቶስ ተወካዮች ሁነው እኛን መንጋውን ከነጣቂ ተኩላ ጠብቀው እስከተንከባከቡን ድረስ ነው። ተጠሪነታቸው ለማን ነው ? ለክርስቶስ ወይስ ለተኩላው ? ከተኩላው ነው ስለመንጋው ደኅንነት ጥበቃ መመሪያ መቀበል ያለባቸው ወይስ ከመንፈስ ቅዱስ? እርቅን ፥ ሰላምን ፥ ፍቅርንና አንድነትን አንፈልግም ብለው እንዴት እኛ አባቶቻችን ብለን አመራራቸውን እንቀበል ? የቱን አመራር ? የጥሉንና የከፈፍሉን ? ይህማ የጥንተ ጠላታችን የድያብሎስ ነው እኮ ! ይህማ መሆን የለበትም። እኛም እኮ እግዚአብሔር 'አእምሮ ' የተባለውን መልካሙን ከክፉው የምንለይበትን የማወቂያ መሳሪያ ሠጥቶናል ! እኔ በኒህ ይህን ጽሑፍ በደጀ ሰላም በኩል ባቀረቡት አባት/እህት ሃሳብ እስማማለሁ። እናንተስ ?

Wondwossen Kidanemariam said...

There is a time for everthing, and this is our time, a time given by God to fix our church problem. I feel sorry for those who are responsible did not do their job. How come we don't even have one holy father who stand for the truth? As christian what do we learn from all this? Is someone tell for those who running up down to grap church power is not the same as political power? This is my advice to them this time your are dealing with fire...........

Anonymous said...

le haymanotachine manenenetachine yemitayebete gizewe ahune new.Egzhabhere amlake yirdane.

Anonymous said...

We are in a cross road and we have to be vigilant enough on what measures we should take to help our fathers on both sides to resolve the deadlock. It is in such period of time, our elders, the likes of Prof.Getachew Haile should come forward and show directions. It is very regrettable for Ethiopian orthodox Christians to find ourselves in such shameful feud. Let’s be honest to ourselves, There is nothing that prevents our fathers at home to bring back abune merkorios to the throne, and at the same time, there is nothing for our fathers abroad to agree to elect a new Patriarch. Both have the key to open the closed door. But all stick to their interest, not of the church. This is a power struggle in its worst form. Most of all, the silence of Abune Merkorios, despite repeated appeals, is a puzzle. The one remaining issue to resolve is his return. It is very important to come out and talk to his kids.

Anonymous said...

Over 21 years Weyana (Collection of Devilish Group) has been destructor and # 1 enemy of Ethiopia,Ethiopianizm,Ethiopian ,Ethiopian History and EOTC. Destroying Ethiopia and EOTC are some of the ultimate goals of this internal colonizer ,burglar,cold blooded criminal and evil group."The time Shall Come"... "Ethiopia shall stretch forth her hands unto God"...Biblical Quotes.May our almighty of Lord Medhanialem Kirstose bless our holy nation Ethiopia.Amen!!!

Muluken Abera said...

Absolutely Agree with you great explanations!,so everyone must be praye our church. tnx

Anonymous said...

ከእባብ እንቁላል እርግብ አይፈለፈልም
ቢሰለቻችሁም ደጋግሜ እናገራለሁ

ከእባብ እንቁላል እርግብ አይፈለፈልም - ወያኔም ዓላማው ስለሆነ ኦርቶዶክስን ሳያጠፋ አርፎ አይቀመጥም

ተጠያቂ የሚሆነው ዓላማውን እየፈጸመ ያለው ወያኔ ሳይሆን ሃይማኖቱን ያልተከላከለው ኦርቶዶክስ ነኝ ባዩ ነው

መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ኢትዮጵያን ኦርቶዶክስን እና አማራውን ስለማጥፋት ቂመኛ እና ዘረኛ ድብቅ አጀንዳቸውን ሲገልጹ "ዓላማችንን አንረሳም - ቂማችንንም አንፈታም" ነበር ያሉት

ስናየው፣ ስንሰማው የኖርነው፤ አሁንም እየሆነ ያለው ይሄው ነው። አባቶችን ማሳደድ፣ ማዋረድ፣ በዘረኞቹ ትግሬዎች መሙላት እና የቤተክርስቲያንን አንድነት ማናጋት፣ ቤተክርስቲያናችን ዘርና ጎሳ ሳይገድባት በአንድ በእግዚአብሔር ጥላ ሥር እንዳትሆን፣ በዘረኝነት በተለከፈ የአንድ ጎሳ የበላይነት እና የወያኔ ጉዳይ ፈፃሚ የሆነች ቤተክርስቲያንን መፍጠር እንደሆነ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ የፈጸሙትና ያቀዱት ድርጊት፣ አሁንም የእነ አቦይ ስብሃት ዛቻ የሚያስረዳን ይህንኑ እውነታ ነው።

ሌላው ምዕመን ስለእናት ቤተክርስቲያኑ በተቆርቋሪነት አስተያየት በሚሰጥበት ጊዜ ለእነሱ /ለኢህአዴጋውያን ስለማይመቻቸው የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው የተቃዋሚዎች አስተያዬት ነው ወዘተ እያሉ ለማሸማቀቅ ይሞክራሉ። እነርሱ ቤበተክርስቲያን ላይ በስውር እና በገሃድ የሚያደርሱትን በደል ትተን፤ በቤተክርስቲያናችን እና በብጹአን አባቶች ላይ በድፍረትና በንቀት በአደባባይ የሚናገሩት ዘለፋ ምርቃት እየመሰላቸው ይሆን? ነው ወይንስ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለውን የቂሎች አባባል ሕዝብ አያውቅብኝም ለማለት ነው? ታዲያ ምነው መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ ካልገባ "ፓትርያርክ በሕይዎት እያለ ሌላ ፓትርያርክ አይሾምም" የሚለውን የቤተክርስቲያን ድንጋጌ ሲነሳባቸው የሚያንገበግባቸው ለምንድን ነው? አሁንም መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ ካልገባ እንኳን 4ኛውን በሕይዎት ያሉትን ፓትርያርክ ቀርቶ የአቡነ ጴጥሮስን አጽም አውጥተው በመንፈሳቸው እንመራላቸዋለን ቢሉ ምን ጥልቅ ያደርጋቸዋል?

ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደማይፈለፈል፣ ከኢህአዴግም ለሃይማኖታችን መጥፋትን እንጅ በጎ ነገርን ስለማንጠብቅ፤ መንግሥት በረጅም እጁ ቀደም ሲል በገዳማት መቃጠል፣ በንዋዬ ቅድሳት ዝርፊያ፣ በቤተክህነት ሙስና፣ በኋላም አንዴ በዋልድባ ገዳም መታረስ፣ ሌላ ጊዜ በአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት መነቀል እንደገና የወያኔ አፈቀላጤ ፓትርያርክ ለማስመረጥ በሚደረግ ሽኩቻ ሃሳባችንንም ጊዜያችንንም ሲበታትንብን ቆይቷል። ወደፊትም ይቀጥላል - ዓላማው ነውና።

እኛም አስተያየት ፖስት ከማድረግ ባለፈ አንዱንም ሳንከላከል ወደፊት የደገሱልንን የጥፋት በትር ገና ያወርዱብናል። የትናንቷ ቁስጥንጥንያ የዛሬዋ ኢስታንቡል እንደሆነች ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶም ዛሬ ራሷን መከላከልና ሃይማኖቷን ማስከበር ካልቻለች "በክርስቶስ ደም ስለተመሠረተች አትጠፋም" የሚለው ቃል ብቻውን አይበቃም። ታዲያ ቁስጥንጥንያ በክርስቶስ ደም አልነበረም ወይ የተመሠረተችው የሚል ጥያቄ ያጭራልና?

ወያኔዎች "ዓላማችንን አንረሳም - ቂማችንንም አንፈታም" እንዳሉት ዓላማቸውን እያሳኩ ነው። ስለዚህ ተጠያቂዎቹ ሃይማኖታችንን ያልተከላከልነው እኛው ራሳችን እንጅ እነሱ ወያኔዎች አይሆኑም።

ስለዚህ ወደድንም ጠላንም ዛሬ ነገ ሳንል ወያኔ/ህወሃት በሃይማኖታችን ጣልቃ እንዳይገባ የኦርቶዶክስ አማኞች በሙሉ ሃይማኖታዊ መብታቸውን ለማስከበር ከሚታገሉት ሙስሊም ወንድሞቻችን ጋር በመተባበርና በሰላማዊ መንገድ ሃይማኖታችን ይከበር ማለት አለብን።

"የቤተክርስቲያኔ ጉዳይ እኔንም ያገባኛል" የሚለውን ጥሪ ተቀብለን ተቃውሟችንን በህብረት ማሰማት ይኖርብናል። ይህም ተቃውሞአችን ፓትሪያርክ ከመሰየሙ በፊት መጀመር ይኖርበታል።

ይህንን ችግር ሕዝበ ክርስቲያኑ ገና በደንብ ስላላወቀው፤ የሚችል የተቃውሞ ድምጹን እንዲያሰማ፣ የማይችል በፀሎት እንዲያግዝ መላ ሕዝበ ክርስቲያኑ በየሰበካ ጉባኤው በይፋ ተነግሮት ማወቅ አለበት። በኋላ ግን ቁጭ ብለው የሰቀሉት ለማውረድ እንዳይቸግር እና ወደባሰ ፈተና ውስጥ እንዳንገባ እርምጃው አሁኑኑ መጀመር አለበት።

ልብ በሉ እያንዳንዷ የዝምታ ቀን ለወያኔ የድልና የስኬት ቀን ለቤተክርስቲያናችን ደግሞ የፈተናው መክበጃ ቀን ነች።

"የቤተክርስቲያኔ ጉዳይ እኔንም ያገባኛል" "ከፓትርያርክ ምርጫ እርቀ-ሰላም ይቅደም" የሚለውን ጥሪ ተቀብለን ድምፃችንን ማሰማት መንፈሳዊ ግዴታችን ይሆናል።

ስለዚህ በተጠናከረእና በተደራጀ መልክ መንፈሳዊ ጥያቄያችንን ለማቅረብ እንድንችል የማኅበረ ቅዱሳን፣ የሰንበት ት/ቤቶች፣ የሰንበቴነና ሌሎች እውነተኛ የተዋህዶ ማኅበራትና የሰበካ ጉባኤያት የመሪነቱን ሚና መጫወት ይጠበቅባችኋል።

በዓመት በዓል ጊዜ ከበሮ ይዞ ለመድመቅ ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያናችን አሁን ከገባችበት ፈተና እንድታወጧት ከምንጊዜውም በላይ እናንተን የምትፈልግበት ጊዜ አሁን ነው።

ይህ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ ቅድስት አርሴማ የእምነታችንን ጽናት የምናስመሰክርበት ወርቃማ ዕድል ነው ለዚህ ሰማዕትነት መብቃት ደግሞ ታላቅ መመረጥ ነው

እግዚአብሔር ቤቱን ይጠብቅ
ቸር ወሬ ያሰማን

Anonymous said...

ዝም ብሎ በወሬ የሚሆን አይደለም በእምነት ላይ ያለን እርግጠኝነትና ቁርጠኝነት የሚፈተንበት ጊዜ ነው፤ ለዚህም እስከዛሬ በዕውቀት ያለተገነባና የተወሰኑ ከላይ ያሉ አባቶች ነን ባዮች ብቻ አውቀውት መንጋው ዝም ብሎ በሞኝነት የሚመራበት እምነት ይህን ሊያመጣ አይችልም በእልህና በጥላቻ የተሞላ ዕምንት መፈተኛው ጊዜ መጥቷል፡፡

Anonymous said...

ወገኖቼ መጀመሪያ ስሜታዊነታችንን ቸል ብለነው በማስተዋል እንንቀሳቀስ:: በሁከትና በመጮህ የምናመጣው ነገር የለም:: ሃይማኖትም እንዲህ አይደለም:: የተነካብን የቤተክርስቲያን አስተዳደር እንጂ ንጽህት ተዋህዶ እምነታችን አይደለችም:: ሃይማኖታችን በልባችን ናት:: ቤተክርስቲያን ደግሞ ሃይማኖታችንን በማህበር የምናከናውንበት ቤት ናት:: ሁለቱን የነካብን የለም:: ቢሆን ሰው ለእምነቱ ይሞታል እንጂ ለአስተዳደር ጉድለት አይሞትም:: በቀላሉ ሊሰተካከል ስለሚችል:: ወያኔ ወያኔ የምትሉትን ነገር በደንብ ብታስተውሉት ወያኔ ከውጭ የመጣ አይደለም:: የእኛው ማህበረሰብ ያፈራቸው ናቸው:: ስለዚህ የማህበረሰባችንን የሃይማኖት ድክመትና ጥንካሬ የምንመዝንበት አንዱ የወያኔ አባላት ለሃይማኖታቸው ብሎም ለሀገራቸው ባላቸው አመለካከት ሊሆን ይገባዋል::

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይስጣቹህ፤ ይሄ ወሳኝ ሰአት ነው ለቤተ ክርስቲያናችን፤ ዓለም በቃኝ ካሉ በኋላ በምድራዊ ፍላጎት ምክንያት ለእርቅ ባለመፋጠናቸው በጣም አሳዛኝ ነው፤ ግን የሰላሙ እና የአንድነቱ መንገድ ኢትዮጵያ ባለው ሲኖዶስ ላይ ነው፤ በሁለቱ ሲኖዶሶች ስምምነት እንኳን ካልመጣ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ አዲስ ፓትርያርክ ሳይመርጥ አቡነ መርቆርዮስ እስኪያርፉ ጠብቆ ስደተኛውን ሲኖዶስ በአንድነት አዲስ ፓትርያርክ እንዲመርጥ ቢጋበዝ እምቢ የሚሉበት ምክኒያት አይኖርም።

Anonymous said...

December 31, 2012 11:52 AM "በስሜታዊነት የሚሆን ነገር የለም። ሃይማኖታችን አልተነካም - አስተዳደሩ ነው እንጅ! ……… እምነታችን በልባችን ነው። ሰው ለእምነቱ ይሞታል እንጅ ለአስተዳደር አይሞትም! - በቀላሉ ሊስተካከል ስለሚችል። ……. ወያኔ ወያኔ የምትሉት ነገር ወያኔ ከውጭ የመጣ አይደለም። የእኛው ማኅበረሰብ ያፈራቸው ናቸው።" ላሉት አስተያየት ሰጭ ቃልዎን ቃል በቃል ብናየው?

በመጀመሪያ ይህንን የሚሰብኩን እርስዎ ብጹዕ ወቅዱስ አባ በረከት ስምዖን ነዎትን? ወይስ የዋልድባው አሳራሽ ብጹዕ ወቅዱስ አባ አባይ ፀሐዬ ነዎት? አባ አቦይ ስብሃት ነጋ እንኳ የዘረኝነት መንፈሳቸው ገንፍሎባቸው በይፋ "ጳጳሳቱ አይረቡም" እያሉ ሲሳደቡ ቆይተዋል። አሁንም "ቤተክርስቲያኗ ትፈርሳለች" ብለው ቁርጡን ነግረውናል።

ከእነዚህ ብጹዓን ውስጥ ካልሆኑ ደግሞ የተኩላውን ለምድ ከለበሱት ከፕሮቴስታንታዊው ተሃድሶዎች ወገን ሳይሆኑ አይቀርም - "እምነታችን በልባችን ነው" የምትለዋ አባባል ትመሰክራለችና!

እኛም ኦርቶዶክሶያውያኑ እምነታችንን እና አስተዳደሩን ለይተን ሳናውቅ ቀርተን አይደለም። አስተዳደሩ እምነታችንን የሚያዛባ፣ ቤተክርስቲያናችንን የሚያፈርስ፣ ሕገ-ቤተክርስቲያንን የሚጥስ፣ አስተዳደር ሆኖብን እንጅ!

አባ ጳውሎስ ከመነሻቸው "ድንግል ማርያም ከአዳም የተላለፈ የውርስ ሃጢያት አለባት" ብለው እንደሚያምኑ በዶክትሬት መመረቂያ ጽሑፋቸው ግልጽ ባለ ቋንቋ አስፍረውታል። በጨለማው የፕትርክና አገዛዛቸው ዘመንም የተሃድሶ መናፍቃንን በመሾም ቤተክርስቲያናችንን ሲያስፈርሱ፣ ገዳማትን ሲያቃጥሉ፣ እምነታችንን ሲያስበርዙ፣ አባቶቻችንን ሲያሳድዱ፣ ምእመኑን በተለይም ወጣቱን ሲያስኮበልሉ አልቆዩምን? ማስረጃ የቀረበባቸውን የተሃድሶ መናፍቃንን ቅዱስ ሲኖዶስ ሲያወግዝ አባ ጳውሎስ በመቃወም እና መልሰው ሲሾሟቸው አልቆዩምን? በቤተክህነት ውስጥ ከላይ እስከ ታች የተንሰራፋውን የሙስና እና የዘረኝነት ችግርስ ምን ይሉታል? ይህ ሁሉ እንግዲህ ተራ የአስተዳደር ችግር ነው የሚባለው? "አስተዳደራዊ ችግር በቀላሉ ይስተካከላል" ያሉት እንዴት ብሎ ነው ይህ ሁሉ የሚስተካከለው? በእምነቱ የተፈተነና የፀና አስተዳደር ሲኖር አይደለምን?

የእኛም ጥያቄ ይሄው ነው! ለወያኔም ያልተመቸው ይሄው ነው!

"እምነታችን በልባችን ነው" የምትለዋም አባባል ተሃድሶያውያን መናፍቃን - ሲችሉ ምእመኑን ከቤተክርስቲያኑ የሚነጥሉበት፣ ሳይችሉ ደግሞ ሕገ-ቤተክርስቲያንን በማቃለል ምእመኑ ለቤተክርስቲያኑ ግዴለሽ እንዲሆን የሚጠቀሙበት አባባል እንደሆነ፤ ስንሰማው፣ ስናየው በመኖራችን እርስዎም ከእነሱ ወገን እንደሚሆኑ አያጠራጥረንም።

"ወያኔ ወያኔ የምትሉት ነገር ወያኔዎች ከውጭ የመጡ አይደሉም፣ የእኛው ማኅበረሰብ ያፈራቸው ናቸው" ያሉትም ከወያኔዎች ወገን መሆንዎን ራስዎ መሰከሩት። ወገናችን ስለሆኑ የፈለጉትን ያድርጉ ተዋቸው ነው የሚሉን? ለዚያ ነው ወያኔ ዓላማውን ለማሳካት ከተላላኪዎቹ ተሃድሶያውያን ጋር በመሆን "አፍቃሪ ወያኔ ፓትርያርክ ወይም ሞት!" እያለ ያለው።

ከዚህ በላይ የቤተክርስቲያንን መፍረስ እና መከፋፈል ፍፃሜውን ዝም ብላችሁ ተመልከቱ ነው የሚሉን?

ውድ አስተያየት፤ ሰጭ ለዛሬ አልተሳካለዎትምና ንስሃ ቢገቡ፣ ወይም የእርስዎን አይነቶቹን የበግ ለምድ ለባሽ ተኩላዎችን ወይም ራስዎ ነጣቂው ተኩላም ከሆኑ አሽከሮችዎን ቢመክሩልን፣ ቢያሳርፉልን ለቤተክርስቲያናችንም ለእናንተም ይበጃችኋል።

"የተዳፈነ እሳት ረመጡ አይጠፋም" - ሲቆሰቆስ አገር ሊያቃጥል እንደሚችል ይጠፋችኋል ብዬ አልገምትም።

እግዚአብሔር ቤቱን ይጠብቅ፣

Salaam said...

እኔ ሃጥያተኛው እንደሚገባኝ የማንኛውም ችግር የሚፈራው ከራስ ተጀምሮ ነው። የሃይማኖት አባቶች የምያስተምሩን ይህ ነው።

በውጭ አገር ያለነው የኦርቶዶክስ ምእመናን ለዚህ ችግር ትልቅ አስተዋጾ አርገናል። እንዴት? ለአመታት በቤተ ክርስቲያኖቻችን ጸብ በያይነቱ በማስተናገድና መከፋፈል። ብዙ ከተሞች ቤተ ክርስቲያኖች ለ2 ሳይሆን ስል3 ወይም 4 ተከፋፍለዋል።

ሁላችንም እንደምናውቀው እነዚህ ጸቦች በአብዛኛው መንጮቻቸው የሲኖዶስ ወይም የሃይማኖት ጉዳይ ሳይሆን የግል ጸብ ናቸው (ለምሳሌ በዋሺንግተን ገብራኤል በቅርብ ወራት የተከሰተው)። ከዛ በኋላ መናልባት የሲኖዶስ ጉዳይ እንደ ሽፋን ምክነያት ይቀርባሉ።

ይህ መጣላትና መከፋፈል የመንፋሳዊና የድርጅታዊ ሃይላችንን እጅግ በጣም አድክሞታል። አንድ ብንሆን፤ ብያንስ ሁለት ብንሆን፤ የገለልተኛና የውጭ ሲኖዶስ፤ የቤተ ክርስቲያናችን ችግር ልንፈታው እንችል ነበር።

አሁንም ከአግር ውጭ ያለነው ዋና ስራችን እርስ በርስ ያሉንን ቅሬታና ሽኩቻ ማስወገድና እንደ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በፍቅር አንድ ሆነን መጓዝ ነው።

ሁሉ መፍቴ ከራስ ነው የሚጅምረው።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)