December 29, 2012

የኢትዮጵያ መንግሥት ሊ/ካ ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁን በግድ ወደ አሜሪካ መለሳቸው

  •     Listen VOA Interview
  •    ዲፖርት አደረጋቸው፤ 
  •     ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ ናቸው ተብሏል፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 20/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 29/2012/ PDF)፦ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ መለሳቸው። እዚያው አስሮ ያላስቀራቸው አሜሪካዊ ዜግነት ስላላቸው ነው ተብሏል። ከእርሳቸው ጋር ለዚሁ ጉዳይ ወደ ኢትዮጵያ የሄደው የሰላምና አንድነት ጉባኤው ሌላ አባል ዲ/ን አንዱዓለም ዳግማዊ ስላለበት ሁኔታ አልታወቀም። ዝርዝሩን እንደደረሰልን እናቀርባለን። 
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።
  

4 comments:

Teklesilassie said...

This is the work of the devil.

How can a person who does this against his brother be called "Nibure ed"?

People like Nibure ed have dashed our hope to see a united Orthodox Church. As they have taken our hope for unity, may God also banish any pleasure and hope they may expect in keeping our church divided.

May God bless those who are persecuted for their effort for peace, unity and faith in God.

God help us. Please speak to us. Don't be quite when the worldly people are desecrating your house.

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኈዱ አምላክ አሜን !!!
ዘመኑ በሁሉም ቦታ ስንሄድ እከደከ ሰይጣን ማለት እንዳለብን የሚያመላክቱ ሁኔታወች በጣም በዝተዋል። ሰሞኑን ሞስሊም ኢትዮጵያውያን "መንግስት የለም ወይ?መንግስት የለም ወይ?”ሲሉ ሰምቸ ነበር። እንግዲህ በሀገራችን ዱርየ ወንበዴ እንጂ መንግስት የሚባል አለመኖሩን አረጋገጡልን። መንግስት እኛን ለሀይማኖታቸው አይሞቱም ብለው አስበው ከሆነ አሁን ያዩታል ። አባቶችም ይሄን አይነት አሰራር አሜን ብለው ተቀብለው አብረው የሚኖሩት ምን ያህል እድሜ ለመኖር አስበው እንደሆን እኔ እንጃ ይሄ የጤና አይመስለኝም ።
ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ የተባሉት ሳይጠሩ የመንግስት ጆሮ ሆነው ከአባቶች ጋር ተለጥፈው አሜሪካ ሄደው የተላኩትን ሰይጣናዊ ተልእኮ በተግባር አሳይተውናል የቤተክርስቲያን አምላክ ይፍርዳል ። ከዚህ በፊት እንደርስዎ ለጠፍ ሆነው የሄዱት አባት እንደተቀሰፉ እያወቁ ወደ እሳት ውስጥ መግባት አልነበረበወትም የእርሰወንም በቅርቡ እናየዋለን። የሰው ልጂ ለመኖርኮ ይሄን ያህል በእምነቱ መነገድ ብኩርናውን መሸጥ የለበትም እርሰዎ የመላ ህዝበ ክርስቲያኑንም መብትና ህልውና የሚነካ ነገር ውስጥም መግባት አልነበረበወትም ። ማንኛውም ነገር ቢሆን እግዚአብሄር ከፈቀደው ውጭ የሚሆን ነገር የለም።
እንግዲህ ለእኛ ለተዋህዶ ልጆች ጊዜው የሚጠይቀን ነገር ቢኖር የወንጌል ስብከት ወይንም ሌላ አገልግሎት ሳይሆን በሀይማኖታችን የምንፈተንበት የሰማእትነት ወቅት በመሆኑ ከኛ የሚጠበቀው ሰማእትነት ብቻ ነው።
ለሁሉም ጊዜ አለው!!!!!!
ጊዜውም የሰማእትነት ነው !!!
የሰማእትነት አገልግሎት ለሁሉም የሚሰጥ ሳይሆን እንደየ እምነታችን የጥንካሬ መጠን ለተመረጡ የሚሰጥ አገልግሎት ነው ። ማንም ተነስቶ ሰባኪ ልሁን ቢል ወይንም ዘማሪ ወይንም የማስታረቅ አገልግሎት ሌላም ሌላም ልሁን ቢል ከላይ ካልተሰጠው ሊሆን አይችለም። ለሁሉም አገልግሎት መመረጥና ለዚያ የተመደበ ሊሆን ይገባል እንደ ተሰጦውም እግዚአብሄርን ያገለግላል። በመሆኑም በአሁኑ ሰአት ሰባኪያን ልበ አምላ ዳዊት፡ ሀዋርያው ጳውሎስ ማለት ሳይሆን ለ21 አመት የተሰበክነው ወደተግባር የሚተረጎምበት ወቅት ነው። ዘመኑን ዋጁት ዘመኑ የነቅዱስ እስጢፋኖስ የነ ቅዱስ ጊዮርጊስ የነ አዛርያ አናንያና ሚሳይል ዘመን ነው።
ዘመኑ የሰማእታት ዘመን ነው።
ዘመኑ ለአውደምህረት የምንሽቀዳደምበት ሳይሆን በተግባር ስለ እውነት የምንመሰክርበት ዘመን ነው።
ዘመኑ እግዚአብሄር አምላክ አባታችን አብርሀምን ልጅህን ሰዋልኝ ያለበትን ዘመን ነው የደገመልን።
ዘመኑ የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል እምነት የምንጣየቅበት ነው።
ዘመኑ ክርስትናችን ከሰንበት ት/ቤት አዳራሺ ወጥቶ ለፈተና የሚቀርብበት ዘመን ነው።
ዘመኑ ቀራኒዮን የምናስብበት ማህበራት በማህበር የጠጣነው ጽዋ የክርስቶስ ደም መሆኑን የምንመሰክርበት ዘመን ነው።
አባቶቻችን የዝችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ፍቅር በውስጣችን እንዳልተከሉ፡ አብረን የክርስቶስን መንግስት እንዳልሰበክን ለናንተ ለአባቶቻችን ታዛዝዎች ሆነን እድሜ ሙሉ አብረን እንዳልደከምን በስተመጨረሻ ላላፊውና ለጠፊው ለምድራዊው መንግስት ማገልገል መረጣችሁ። እንግዲህ እግዚኦ ማህረነ እንጂ ሌላ ምን እንላለን። ስለእመብርሃን ስለ ወላዲተ አምላክ ከድቁና እስከ ጵጵስና ስላገለገላችኋት ቤተ ክርስቲያን በምትወዱት ታቦት ሁሉ በስላሴ ስልጣን ገዝቻችኋለሁ።
አሁንም አልመሸም ከፓትርያሪክ ከምርጫ በፊት የቤተክርስቲያን አንድነት ይቅደም !!!
የቀዳሚ ሰማእት ቅዱስ እስጢፋኖስ እረድኤቱና በረከቱ በሁላችን ላይ ይደርብን!!!
አሜን!!!

Anonymous said...

Those of you who do not know the so-called Bebure Ed Elias - he is a TPLF agent who has been destroying the EOTC since TPLF went to the bush to fight. Beure Ed Elias was hand picked by Sebhat Nega et al to divide and destroy the EOTC since Wayane launched war against Derg. Mind you TPLF believes that Amhara and the EOTC are enemies of Tigre, and thus the reason why they persecute Amharas and divide the EOTC.

Anonymous said...

I know L.K Hilselsie for sure, He is confidenced and one of an execellent spritual leader in our EOTC. He always cooperate with fact and the witness of the truth. I abilive he can make effective solution in our church.

But Woyane send him back with out reason because woyane always against the fact and mesleading
history. now we understand that woyane is on the top of our church .

Mengesha

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)