December 1, 2012

የአባቶችን እርቀ ሰላም አስመልክቶ ከጀርመን ፍራንክፈርት ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተላከ መግለጫ

(READ THIS NEWS ARTICLE IN PDF) 

(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 22/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 30/2012)፦ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አባቶች በእርቀ ሰላም ዙሪያ ለመነጋገር የአንድ ሳምንት ዕድሜ በቀራቸው በአሁኑ ሰዓት ከተለያዩ አካላት የሚላከው የድጋፍ መግለጫ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ቀደም ብሎ “ከጉባኤ ካህናት ወምዕመናን ለቤተክርስቲያን ሰላም ተማጽኖ ባሻገር አስመልክቶ ጀርመን አገር ፍራንክፈርት ከተማ የሚገኘው የሐመረ ብርሃን ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መግለጫው አውጥቷል። ሙሉውን ከዚህ ያንብቡ።

16 comments:

Anonymous said...

ጀር መን ፍራንክፈርት የቅዱስ ገብኤል ቤተ ክርስቲያን አለን?
ወይስ ደጀ ሰላም የማስታወቂና ሥራ እየሰራች ነው
በጳጳስ ያልተባረከ አንድ ስብስብ እንዳለ ይሰማል ለማስተዋወቅ ሲባል ሥመ ታዋቂ የሆኑ መምህራን እየጋበዘ ለማስተዋወቅ ሲሞክር ነበር
እስከ ዛሬ ደግሞ ገለልተኛ ነን ሲኖዶስን እንቀበላለን ጳውሎስን ነው እምንቃወመው ሲባል ነበር አሁን ምዕመኑ ጳውሎስ አርፈዋል ምን ትጠብቃላችሁ ሲላቸው ደግሞ እርቀ ሰላም ብለው ጀመሩ
ሱሪ መጣፊያ ቢደራረብበት ድሪቶ ነው የሚሆነው እባካችሁ አዳራሽ አታለማምዱን ደጀ ሰላማውያንም እባካችሁ መጠቀሚያ ከመሆን ተቆጠቡ እዚህ ፍራንክ ፈርት ያለ ምዕመን ለራሱ ግራ ገብቶታል ከውስጥ መናፍቃን አባት ተብየዎች መከራ እያበሉት ነው ዛሬ ደግሞ ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የተሳባሰቡ ሰዎችን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ትላላችሁ በጀርመን ሃገር በኢትዮጵያ አርቶዶስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር ያለችው የሙኒክ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንብቻ ነው ።

Anonymous said...

eske zarem mesebaseb yechalale mechem teru abate nachew bezu sera
eyseru yegegalu bergetem sehtet benorem gen ategabe sera eyseru yegegalu.yalfewen teten le wedefetu mensate new aye frankfurt sentune cheger teschkemalech.

Anonymous said...

ቅዱስ ገብርኤል እንደሆነ እኔ እስከ ሚገባኝ ድረስ ምንም ዓይነት ምንፍቅናም ሆነ ጥቅም ብሎ የቆመ ሰው የለም።
በእርግጥም ገለልተኛ ናቸው ወይ አላውቅም። ዛሬ እዛው አስቀድሻለሁ የ 6 ወር ሪፖርት ሰምቻለሁ።
ሰው ሁሉ የሚሰጠው አስተያየት በጣም ውስጥ የሚነካ ነው።
ይህ ቤተ ክርስቲያን አለተባረከም አያሰኘውም ድሮ የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን መገልገያ ነበር። ስለዚህ ተባርኳል ነው ነገሩ።

በመሰረቱ ይህን የመሰለ አስተያየት ሳነብ የሰውን አመለካከት በጣም ይገርመኛል።
የትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው ማኅሌተ ጽጌን በማኅሌት ያሳለፈው? ታዲያ ይህ ምንፍቅና ያሰኛል? ጥቅምስ ከተባለ የሚያገኙት ደሞዝ አለ?
በየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው ጀርመን ውስጥ በዓመት ንግሥ ላይ ማኅሌት የሚቆመው?
የትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው ተአምረ ማርያም የሚነበበው?
ተው እባካችሁ የነገን አናውቅምና እንዲህ አይነት አስተያየት አንስጥ።
ይህ ሁሉ የማያደርጉ ቤተ ክርስቲያናት ሲወቅሱ ይገርማል።በገብርኤል ግን ሁሉም ነገር አለ። አገልግሎቱ በትላልቅ አድባራት ያለ ዓይነት ነው።ይህ ከምንል ምን አለ አባቶ ቹን ቀርበን ብንጠይቃቸው። ለነገሩ ፍራንክፈርት ውስጥ ወሬ እንጂ ለቤተ ክርስቲያን የሚቆረቆር ያለም አይመስለኝም።
ያለው ጠንካራ ጎን ይዞ ያለው ድክመት ለማስተካከል ነው፡ የሚሻለው ባይ ነኝ።
ልብ ይስጠን።

Anonymous said...

አቤት አቤት እንዲህ ነው ለሐይማኖት መቆርቆር!
በመጀመሪያ ይህ ቤተክርስቲያን ምን እየሰራ ነው ያለው:እውነተኛ ኦርቶዶክስ አማኝ ይህን አስተሳስብ ከመስንዘሩ በፊት ቆም ብሎ ማሰብ አለበት፣ ቤተክርስቲያኑ ከተመሠረተ ጀምሮ በየጊዜው የታወቁ የኦርቶዶክስ አባቶችን በመጋበዝ በግልጽ እውነቱን ስለሐይማኖታችን በደንብ እንድናውቅ አድርገውናል፣ ታዲያ እውነቱ ይህ ሳለ, continue writting
"እዚህ ፍራንክፈርት ያለ ምዕመን ለራሱ ግራ ገብቶታል...." ምን ሆኖ ነው ግራ የሚገባው? እውነቱን ተከትሎ ነው መሄድ! (follow the truth)ጸሀፊው ራሱ ግራ የገባው መሆኑ ግልጽ ነው

1.በጳጳስ ያልተባረከ አንድ ስብስብ እንዳለ ይሰማል..... ይህ አይነት አነጋገር ከእውቀት ማነስ የተነሳ ሰለሆነ የበለጠ አባቶችን ቀርቦ መጠየቅና ትምህርት ማግኘት ያስፈልጋል::
2.መናፍቃን አባት ተብየዎች መከራ እያበሉት ነው......፣ ታዲያ መፍትሄው ምንድነው? ከመፍትሄው ፈላጊው አንዱ ነህ ወይስ ተረት እየተረቱ መቀመጥ፣ ሰለ ሀይማኖታቸው ማወቅ የሚፈልጉ ሰዎችን ማከላከል፣ በቂ ትምህርት እንዳያገኙ ማድረግ. መፍትሄ መስሎህ ታይቶህ ነው
3. ደጀ ሰላማውያንም እባካችሁ መጠቀሚያ ከመሆን ተቆጠቡ........፣ የዚህ ድህረገጽ ትርጉም ያልገባህ ሰለሆነ እስቲ መጀመሪያ እንማር, መጀመሪያ learn, learn , learn it is not too late!
4. ዛሬ ደግሞ ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የተሳባሰቡ ሰዎችን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ትላላችሁ ....
ጥቅም? የምትጽፈው ለመሆኑ መልሰህ ብታነበው ይገባሀል?
ቆም ብለህ አስብ! ወይንስ ትንሽ ሳንጽፍ እንዴት ዝም እንላለን ነው
በፍራንክፈርት ውስት ብዙ አባቶች አሉ ትክክለኛውን ትምህርት ሊሰጡህ የሚችሉ የኔ ምክር እስቲ ጠጋ በልና ጠይቃቸው የበለጠ መማር ይቻላል
Anonymous said...

የሚገርም አስተያየት ሰጭ ነው በእውነት ለመናገር ሁሉ ነገር አስጠልቶን በየቤታችን የተቀመጥን ሰዎች የተጽናናንበት ቤተ ክርስቲያን ነው ጳጳስ አልባረክውም ለሚባለው ደግሞ በሀገራችን ስንት የገጠር ቤተክርስቲያን ነው ጳጳስ ያልባረከው ታዲያ የእነዛም አገልግሎት ከንቱ ነው ማለት ነው ነገር ግን ይህንን ደካማ ሀሳብ መተው አለብን ጳጳስ የባረካቸው ቤተክርስቲያኖች ምን ሰሩ ምንፍቅና ዘረፉ ፖለቲካ ብቻ ነው ታዲያ እዚህ ቤተክርስቲያን ግን ይህንን አላየንም ከሀገሬ ከወጣሁ 10 አመት ሆኖኛል ብዙ ቤተ ክርስቲያን እሄድ ነበር እግዚአብሄር በሚያውቀው እውነተኛ የሀገሬ ቤተ ክርስቲያን ሄጄ የመጣሁ ነው የሚመስለኝ እዛ ሄጄ ስመጣ ምክንያቱም አገልግሎታቸው ከልብ መሆኑን እያየን ነው ትላንት ከተቃወሙት ወገን ነበርኩ አሁን ግን በአገልግሎታቸው እረክቻለሁ ፍጻሚያቸውን እግዚአብሄር ያሳምርላቸው ነው የምለው በተረፈ ግን እንደመናፍቃን ጥሩ ነገር የሚካሄድባቸው ቤተክርስቲያን ጉዳይ የሚያመው ሰው ግን ራሱን ይመርምር በዚህ አጋጣሚ ለገብርኤል ቤተክርስቲያን ካህናት እግዚአብሄር የአገልግሎት ዘመናችሁን ይባርክላችሁ እላለሁ

Anonymous said...

ሰላም ደጀ ሰላሞች

ለምታነቡ ሁሉ ከተቀመጥኩበት ብድግ ከቆምኩበት ሸብረክ ጎንበስ ቆቤን ውልቅ አንገቴን ዝቅ አድርጌ ሰላምታዬን ለግሻለሁ።

እኔ ጀርመን ውስጥ ለብዙ ዓመታት ኖሬያለሁ አሁንም።

በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ሥር ያለውም የጀርመን ቤተ ክርስቲያን በምንፍቅና የተከበበ ነው(በርሊን ፤ኑረንበርግ፤ ሙንሽን፤ ካስል ሳይጨምር)
በውጭ ሲኖዶስ ያለው ምንፍቅና እና ዘረኝነት፤ ፖለቲካ ያለበት ነው።

ገብርኤል ገለልተኛ ነው ከተባለ ከማን ነው ገለል ያለው? የሚለው ጥያቄ አለኝ።
ኧረ ባካችሁ ተውን ተጽናንተንበታል ይህ ቤተ ክርስቲያን።
ሌላ ቢቀር በየሳምንቱ የምንሰማው የካህናቱ ዝማሬ ረጋ ያለው ቅዳሴ ተአምረ ማርያም ትታችሁ ወደምንፍቅና እና ፖለቲካ ወይም ዘረኝነት ልትማሩ ሌላ ቦታ ሂዱ ነው የምትሉኝ።
ይህ የናንተው ውሳኔ ነው። እዛ ሳስቀድስ ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና ሰላምን አድለን ይላሉ ሁሌም ካህናቱ ሲያሳርጉ እናም ጽሎታቸው ይስማቸው።
ወገን ትንሽ እያሰብን አስተያየት እንስጥ።

እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያናችን ሰላሙን ያድል አሜን!

Anonymous said...

እንዴት አይነት የምትገርሙ ገለልተኞች ተከታይ አስተያየት ሰጭዎች ናችሁ ባካችሁ???

ለካ ሌሎቹ በሕገ ቤተ ክርስቲያን የተመሰረቱት ቤተ ክርስቲያናት ከ10 እና 30 አመት በላይ አገልግሎት እየሰጡ ያሉት ቤተ ክርስቲያናት ለ እናንተ ቤተ ክርስቲያናት አይደሉም ? ንግስ ላይ ማኅሌት የሚቆም ደግሞ ከእናንተ ማኅበር ወጪ የሚቆም የለም ? ተአምረ ማርያምም ሌላ ቦታ አይነበብም ?

እውነትም በሁሉ ነገር ገለልተኞች ናችሁ! ወይ ታሪክ!!!
ቤተ ክርስቲያን እያሉ ማውራታቸው ሲገርመን ጭራሽ ሌሎቹን መኮነናቸው!

Anonymous said...

አይ የኛ ነገር ይህንን ሁሉ አስተያየት ከመስጠት መጀመሪያ ሄዶ ማየት ይሻላል:: ስብስብ የተባሉበት የአንድ ብሄር ተወላጅ ስላልሆኑ ነው? ወይ የጎንደር ወይ የትግራይ ተወላጆች መሆን ነበረባቸው? በሌላ በኩል ሊቃውንት የተሰበሰቡበት ቦታ ለመሆኑ እያየነው ነው:: አዎን አመታት ያስቆጠሩትን አየናቸው ምን ሰሩ? በእውነት ለመናገር በፍራንክፈርት መምህራንን መጋበዝ ያሳዩን እነሱ ናቸው:: ስለዚህ እነሱን የሚቃወሟቸው እነማን እንደሚሆኑ መገመት አያዳግትም:: ስለዚህ እባካችሁ ተውን ልባችን ከእግዚአብሄር ተገናኝቷል:: መጽናኛችንን አግኝተናል:: ቤተክርስቲያንን ቤተክርስቲያን የሚያሰኘው አገልግሎቱ ነው:: እግዚአብሄር ይመስገን አይተን የማናውቀውን አገልግሎት አይተናል:: ከላይ አንድ ወንድም የጻፈው አስተያየት ገርሞኛል:: በእርግጥም 10እና 30 አመት ያስቆጠሩት ያልካቸው ማንኛው ቤተ ክርስቲያን ነው? ተአምረ ማርያም የሚነበብበት ሰአታት እና ማህሌት የሚቆምበት ጻፍልን እስቲ በእውነቱ ጥቂት ግለሰቦች ቢኮንኗቸው ብዙ ፍሬ አፍርተዋል:: ሰይጣን ገና በቃለ እግዚአብሄር ይነዳል:: ማህሌቱ ሰአታቱ ታምረ ማርያሙ ያ ረጋ ያለው ቅዳሴ ሁሉ አስደስቶናል:: እኔን ብቻ ሳይሆን ብዙሃኑን ምእመን እያስደሰተን ነው:: ምን ጊዜ እሁድ ደርሶልኝ ባስቀደስኩ የሚያሰኝ ቤተ እግዚአብሄር ነው:: በክፉ የሚያዩትን ቅዱስ ገብርኤል ዝም አይልም መቼም ብቻ ልብ ይስጠን አሜን!!!!!!!!!!!!!

Anonymous said...

ከጀርመን
በትንሿ ሀገር ሁለት የገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አለ አልሽ እኛ የምናውቀው አንድ ነው። እናንተ ዕውቅና ሰጥታችሁት እንደሆን እንጃ፦ ገለልተኛም ቢባል ቢያንስ በጳጳስ በየትኛውም ይሁን ተባርኮ ነው። አሁን ባለው በዘመናችን ችግር አኳያ ፧ እርሱስ ቢሆን አሁን እስቲ ሀሳባቸውን ይግለጹ በእውነት የቤተ ክርስቲያን ነገር የሚገዳቸው ከሆነ። አምላክ ምክንያት አሳጣቸው ወደ አንድነቱ እንዲመጡ ይልቅ አስተዋጽዖ አድርጉ። ገለልተኞች ወይም ገመምተኞች ሳትሆኑ ገድለኞች ሁኑ እንሁን ለአንዲት ቤተክርስቲያን። አልያ ሀገረ ስብከት የሌለው ጳጳሰ የሌለው ቤተክርስቲያን ካኀንም የለውምና ምሥጢራት ለመፈጸም አይችልምና ቤተክርስቲያን ሳይሆን ቤተማኩረፊያ ነው።

ከኮለኝ ከተማ ጀርመን

Anonymous said...

ለኮለኝ ጸሐፊ፡
በትንሿ ሀገር ሁለት የገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አለ አልሽ እኛ የምናውቀው አንድ ነው።ያልከው? ይገርማል እስቲ አንድ ጥያቄ ለጠይቅ በአንድ ሲኖዶስ ውስጥ ያሉት የዳርምሽታድት እና የሐምቡርግ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያንስ ምን እንበለው?

ገለልተኛም ቢባል ቢያንስ በጳጳስ በየትኛውም ይሁን ተባርኮ ነው። ላሉት ከዚህ በፊት የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ነበር ተባርኳል ነው። ደግሞ ቆሞስ ያለበት ቤተ ክርስቲያን ነው እኮ።ቆሞስ አይባርክም ያለው ማንነው?

ገለልተኞች ወይም ገመምተኞች ሳትሆኑ ገድለኞች ላከው
ገለል ያሉት ከማንነው ጥያቄው!!!
1 ከምንፍቅና
2 ከዘረኝነት
3 ከሌብነት

ያኮረፈ ሰው ቤቱ አርፎ ይቀመጣል።እንጂ ምዕመናን በነፃ ጉልበቱ አያገለግልም።

ገድል ስሩ ላለከው እያየኽው ነው የእናንተን ምንፍቅና ወሬ ዘረኝነት ትቶ ዝም ብሎ ማገልገል ገድል አይደለም ?

እስቲ በሥጋ ሳይሆን በመንፈሳዊ መንጽር እየው።የነገው እግዚአብሔር ያውቃል።
የሚገርመው እኮ እስላሙም ፈጣሪን አመልካለሁ ነው የሚለው ግን እውነት አይደለም።ሌሎችም የእምነት ድርጅቶችም ቢሆኑ እንዲሁ።እናንተ ደግሞ ከእነሱ ጋር ትብብር ስላላችሁ ቅዳሴ የምትገቡትም እንደ እነሱ ነው።
ስለዚህ አቃጠላችሁ ነደዳችሁ። የዘመኑ ምዕመን ሁሉንም ጠንቅቆ ያውቃል።ምንም ብትጽፉ ቅም አለች ዶሮ የተበተነላት ጥሬ ቢያንሳት። ለማንኛውም በገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የምሰጠው አገልግሎ ት ያረካኛል ያስደስተኛል።
ስለዚህ አትንኩት ቤተ ክርስቲያኑ ተአምረ ማርያም ይነበብበታል ገድላትም ጨምሮ ስለዚህ ቅዱሳኑ አሉበት።መልአኬን በፊትህ እሰዳለሁ ይቅር አይልምና አታስመርሩት ነው ።

ሰው ልብ ይሰጠን ይላል። ለእናንተ ግን ለእያንዳንዳቹ ልቦች ይስጣቹ


Anonymous said...

it's so funny from Köln

I think this message not from Köln
I am really aware who can give such comment!!!

Why we have Two KidaneMeheret church in Ethiopian Synod?

People I see everyone wanna attack them as far as I know they have good service let's to talk them they come to Unity.

there was a time some people started to bring to Unity but there was the first Question from Gibreal church side by saying "
ለምንፍቅና ቅድሚያ እንስጠው የቀረው መነጋገር እንችላለን"so if all guys do you they have wrong?
I don't think so
guys don't hurry to judge!

ዝም ብሎ መንጫጫት ጥሩ አይደለም።
በኢትዮጵያ ፓትርያርክ ተሾመ ተብሎ ሲታወጅ መጥራት ይጀምራሉ።የዚያኔ የምታሳብቢ መናፍቅ ሁላ ጉድሽ ፈላ። ገብርኤል ያሉ አባቶችጋ በእምነት ቀልድ የለም እነ አባ ወልደ ትንሣኤ ሁሉ ጸጥ ያስደረጉ ናቸው።

Dawit from Munich said...

እውነትም "ቤተ ማኩረፊያ"!!!

አንድ ካህን ባኮረፈ ቁጥር ካህንነቱን የሚያሳይበት ሌላ ቤተ ክርስቲያን በራሱ ስልጣን መክፈት አለበት ነው የምትሉት ገለልተኞች ? ፍትሐ ነገስቱ ለመሆኑ በሊቀ ጳጳስ ያልተባረከ ቤተ ክርስቲያን ስጋ ወደሙ ይፈተትበት ይላል ?
እስኪ ገለልተኞች ነን ባዮች መልሱልኝ! የቅዱስ ገብርኤልን ታቦትስ በየትኛው ጳጳስ አማካኝነት ሊገባ ቻለ ?

እኔ የሚገርመኝ ማህበረ ቅዱሳን በዚህ ዙሪያ እንዴት ዝም ይላል ?hailu ke Nürenberg said...

ያኮረፉ ቄስ እና ዲያቆን ተጠራርተው ያለ ሊቀ ጳጳስ ያለ ሃገረ ስብከት ያለ ሲኖዶስ ያለ ፓትርያርክ "ቤተ ክርስቲያን" ከፈተናል እያሉ እንደ ሱቅ በደረቴ በቅዱስ ገብርኤል ስም የምትቀልዱት እናንተ እነማን ናችሁ?

የቤተ ክርስቲያኗ አንድነቷ ተመልሶ እንደ እናንተ ያለው መሃል ሰፋሪ( ገለልተኛ/ፍናፍንት) ቤተ ክርስቲያኗን መጠቀሚያ እንዳያደርጋት የአምላክ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን!


Anonymous said...


ሰላም ለደጀ ሰላም አንባብያ ን በሙሉ

ሰዎች የሚያቀርቡት የተለያየ አስተያየት ሳይ ለመፃፍ ተነሳስቼ ነው።
እኔ የፍራንክፈት ቅድስት ማርያም ምዕመን ነኝ። ብዙ ጊዜ አልሄድም እዚሁ ቅድስት ማርያም ነው የማስቀድሰው። ግን የእነሱን አካሄድ በጣም ያስደስተኛል።እነሱ እኮ የጳጳሱ ስም ነው የማይጠሩት ለዚህ ብቻ ልንቦጭቃቸው አይገባም። ባይሆንስ አሁን የያዙትን አገልግሎት እንዳለ ሆኖ ወደፊት ምን እናድርግ ብለን አባቶ ቹን ቀርበን እናነጋግራቸው። እንዲያውም በጀርመን ተስፋፍቶ ላለው ምንፍቅና አፍ የሚዘጉ ይሆናሉ።

Dawit from Munich ፤Dawit hailu ke Nürenberg
"ቤተ ማኩረፊያ" ብላችሁ አስተያየት ለሰጣችሁ
የሚያኮርፍ ሰው አርፎ ቤቱ ይቀመጣል እንጂ ምዕመናንን አያገለግልም።ይህን ከግምት አስገብታችሁት ነው? ወይስ እንዲያው አስተያየት ለመስጠት ነው?
ከላይ አንድ ሰው ይህን መልሶላችኋል ።
በምን አይነት ቋንቋ ቢነገራችሁ ይገባችኋል? ያኮረፈ ቤቱ ቁጭ ይላል።ከማንም አየገናኝም!!!!!!!!!
የቅዱስ ገብርኤልን ታቦትስ በየትኛው ጳጳስ አማካኝነት ሊገባ ቻለ ? ላልከው ቆሞስ ባርኮ አያስገባም ያለህ ማን ነው?ቀድመህ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ተማር እሱ ነው የሚያዋጣህ።ምክንያቱም አታውቀውምና!!!ልክ የማንቸስተር ወይም የቸልሲ ቡድን ደጋፊ ይመስል ዝም ተብሎ አይጮህም!!!!!!
የአንተ አስተያየት ለምን እንደሆነ ግልፅ ነው ሙኒክ ላይ ገብርኤል ስላለ ለምን እዛ ተከፈተ ነው።ይህ አስተያየት ከየት እንደሚመነጭ የታወቀ ነው።ባለፈው ለምን ሁለት ገብርኤል ሲባል ነበር።ለምን 2 ኪዳነምሕረት አለ?
ሙኒክ ገብርኤል ላለፉት 20 እና ከዚያ በላይ ዓመት የተሰበሰበው ከ 165,000 (ከአንድ መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ዩሮ በላይ) ለማንም አስበልታችሁ ስትቀመጡ ለምን የፍራንክፈርት ገብርኤል ሲከፈት የተቃወማችሁት ያህል አልተቃወማችሁም።ተቃወመን ልትለኝ ትችል ይሆናል ግን አስመልሳችሁታል ወይ ነው ጥያቄው።ለሃያ ዓመታት የት ነበራችሁ?
ሽቱትጋርት ሂድ ምዕመናኑ በብሔር ተከፍለዋል። የራሳቸው ቤተ ክርስቲያን ሆኖ ግን የሚቀደስበት ቀናት ቁጠረው።ቤተ ክርስቲያን ሆኖ ሳለ መከፋፈል የሚያስተምሩት ማን ናቸው?
የዚሁ ተመሳሳይ እኛጋ ቅድስት ማርያም ና እና እየው የሽቱትጋርቱ ዓይነት ነው።
ኮለኝ ሂድ የምንፍቅና ሃሳቦች መፈልፈያ ነው።
ቤተ ክርስቲያን ሆኖ በሲኖዶስ ስር ሆኖ ሳለ የወንበዴና የቀማኛ ቤት እንዲሁም ምንፍቅና መፈልፈያ ከሆነ ምኑ ቤተ ክርስቲያን ያሰኘዋል?
ስንት ምዕመናን መጥተው አልቅሰው በዚያው ቀርተዋል? የፀኑት ችግሩን ተሸክመው ቆመዋል።ያልበረቱት ደግሞ ጠፍተዋል ምናልባትም እምነታቸውም ቀይረው ይሆናል። ይህ ለምን አያሳምማችሁም?
ምናልባትም አንድ ካህን ነው ያደረገው ትለኝ ይሆናል።ግን እናንተ የትነበራችሁ?አሁንስ የራሳችሁ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት የምታደርጉት ጥረት ምንድን ነው? አሁንስ ያሉት አባት ወደፊት እንዳለፈው እንዳይፈጥሩ ምን እየሰራችሁ ነው?
ጥቅም ላላችሁት እመአምላክ ትፍረድ።እንዲያው በስደቷ ሰዓት የእርሷን ሥቃይ ለማሰብ ነውና ማኅሌት ዝማሬው ሲያቀርቡ አንድ ቀን ሄጄ ደስ ብሎኛል። ታድያ ይህ አገልግሎት የርሷን ስደት ለማሰብ ነውና እሷ ትፈረድ።
ጥቅምን በተመለከት ሁሉም እኮ የራሳቸው ስራ ያላቸው ናቸው።እንዲያውም ከካህናት ውስጥ እስከ እኩለ ሌሊት ሥራ ቆይተው እንደደከማቸው ለማኅሌት የሚመጡ አሉ ።እስቲ እናንተ እንኳን ማኅሌት ለመቆም ውዳሴ ማርያም ለመድገም ትተጋላችሁ ወይ ?
ልብ የሚመረምር አምላክ ይፍረድ። በአንድ ጣት ጠቁሞ መውቀስ ቀላል ነው የተቀሩት 4 ጣቶቻችሁ ግን እናንተን መልሰው ይጠይቋችኋል። መልሱን ለኅሊናችሁ ስጡት። እርገጠኛ ነኝ ይህን ስታነቡ ምን ያህል ኅሊናችሁ እንደሚረበሽ።
በመሰረቱ ካህናቱ መንፈሳዊነት የገባቸው ስለሆነ ማንም ከዚያች ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎ ት ክፍያ አይፈልግም። እንዲያው ነፃ እያገለገሉ የአባልነት ክፍያ ይፈፅማሉ። እስቲ ዝም ብላችሁ ከምትጮሁ ከእነሱ ተማሩ።
ይህ ቤተ ክርስቲያን ከተከፈት 2 ዓመት ተኩል ቢሆነው ነው። በጣም ገርሞኝ የሰማሁት ወሬ ነው። ባለፈው እሁድ ለ3ኛ ጊዜ የ6ወር ሪፖርት አቅርበዋል እናም በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ31 ሺህ ዩሮ በባንክ ይገኛል። ይታያችሁ የእመቤቴ ቤተ ክርስቲያን ስንት ዓመቱ ነው?ምን አለ? ኑረን በርግ ከተከፈተ ስንት ዓመቱ ነው? ስንት ብር አንሶት ነው መላው ጀርመን ሲለመን የነበረው ምን አለበት እንዲህ ዓየነቱ በጎ ነገር ብንማር? ለምን ክፉውን ብቻ እናያለን? ያልታደልን ትውልድ!!!ለነገሩ እኛ ኢትዮጵያውያን ለመነቃቀፍ እንጂ ተደጋግፈን ደካማ ጎናችን ለማስወገድ ልምዱም ስለሌለን ብዙም አይገርመኝም።
ኑረንበርግስ ቢሆን የዘንድሮው ገቢ ማሰባሰብስ ከማን ነው የተማረው?እንዲያውም የኑረን በርግ ቤተ ክርስቲያን ገብርኤል ያለው ምዕመንስ ሄዶ ይረዳ ዘንድ በደብዳቤ ጠይቀው የለም? ገብርኤልስ አላስተባበረም?
ሙኒክም ቢሆን ገብርኤሎች ከጋበዙት መምህር ተምራችሁ የለም ለ20 ዓመታት መምህራን ጋብዛችሁ ታውቃላችሁ?እነሱ ግን አሁን 5ተኛ ጊዜያቸው ነው።ወይ ምዕመኑን አስተምራችሁ ለፍሬ አታበቁ ወይ አርፋችሁ አትቀመጡም።
በጣም የሚገርመው አባ ገብረ ሕይወት እንኳን ወደ ቅድስት ማርያም ይመጡ ነበር።እንባችን ይታበስ ነበር። ደስ ይለን ነበር እርሳቸውም ቀሩ። ምነው ስንላቸው ካህናቱ እኔ ደብር ስላልመጡ እኔም አልመጣም ነው ያሉት። ታድያ እኔ አሁን ምንም ዓይነት ስብከት ቢሰብኩኝ ይገባኝ ይሆን?ሰው እራሱ ሳይፀና ሰውን ማፅናት ይቻለዋል?እርሱ ሳይማር ማስተማር ይቻላል።እሳቸውም ለካ ቲፎዞ ነው የሚፈልጉት።የሳቸውንም መጨረሻ ለማየት ያብቃን ግን ክፉውን አለመኝላቸውም። ወደፊት ብዙ የምናየው ይኖራል እድሜ ይስጠን።
በመጨረሻ ሃሳቦችን ላቅርብ
እስቲ እውነትም ልብ ካላችሁ ለሃይማኖታችሁ የምትቆረቆሩ ከሆነ ፍራንክፈርት መሃል አገር ነው ለጀርመን።
ሁላችንም ተሰባስበን ስለ ተንሰራፈፈው ምንፍቅና እንነጋገር።ጉባኤ ኒቂያ በጀርመን ይደረግ ።እስቲ ልብ ካላችሁ ይህን አስተባብሩ። ይህ ከሆነ በኋላ ገብርኤል ያሉ አባቶች እስቲ ገለልተኛ ነን ሲሉ እንስማቸው። ከሲህ በፊት እባካችሁ አንድ ሆነን እንስራ የሚል ጥያቄ ቀርቦላችው እነሱም ያሉት ይህ ነው።
የሚገርመው ጳጳሱም ቢሆኑ ዶክተር መራዊ ካልተስማሙ ምንም ማድረግ አይችሉም።ጳጳሱም ቢሆኑ አንድ መናፍቅ ላይ ሥልጣኑን ይዣለሁ አሉ እንጂ ተሰብስቦ የተሰጣቸው መጽሐፍ የት አደረጉት?ተባባሪ አለመሆናቸው በምን ማረጋጋጥ ይቻላል? ታድያ ይህ ቀኖና አልፈረሰም?መናፍቅ ገብቶ ሲቀድስ ይህ ሥርዓት አልፈረሰም? የኑረን በርጉ መሪጌታ ዳዊት መናፍቁን አይዞህ ከሚሉት ውስጥ አንዱ አይደለም? ከዚህ በፊት የኑረን በርግ ምዕመናን ያሰባሰቡት የተቃውሞ ፊርማ እንዲሰጥ ተልኮ አልሰጥም ብሎ የተሳደበውን ረሳችሁት?
በቅርቡ የሚሰማው ደግሞ ገብርኤል የአባቶች እርቅ እንዳለቀ የፓትርያርክ ስም ሊጠራ ነው ይባላል። እና የዚያኔስ ምን ሊውጣችሁ ነው?
እባካችሁ በፍቅር እንጂ በጥላቻ የሚሆ ን የለም።

በሲኖዶስ ስር ሆነው የሚሰሩት ስራ ግን የዲያብሎስ ስራ ነው።ክርስቶስ ቤቴስ የጸሎት ቤት ትባላለች ብሎ ሻጮችን ገርፎ እንዳወጣ ለእያንዳንዳችን አይቀርልንም።
ሊቀ ካህናት ተብለው ሊቀ መናፍቅ ሆነዋል።
ጣዖት የሚያመልከም እኮ ጣዖት አመልካለሁ አይልም። አምላኬን ነው የሚለው። ለማንኛውም አስተዋይ ልቦና ይስጠን ብዬ ልሰናበት።

Anonymous said...

ይገርማል ብቻ!

እውነት እኮ እግዚብሔር ነው! እግዚአብሔርን እየሰበክን ለምን እውነትን እንፈራለን!

በቤተ ክርስቲያን ላይ ደግሞ ገለልተኝነት ምን ማለት ነው ? በሲኖዶስ ስር አልሆንም፣ ሲኖዶሱ እኛው እራሳችን፣ ፈላጭ ቆራኝ እራሳችን እንሆናለን ብሎ ነገር ከየት የመጣ ነው ? ይህ መንፈሳዊ አካሄድ ነው ? ቤተ ክርስቲያን ከሆነ ቤተ ክርስቲያን የሚያሰኙትን ቅድመ ሁኔታዎች በፍትሐ ነገስቱ መሰረት ማሟላት አለበት::

የኛ ነገር እኮ እራሳችንን ዘወር ብለን ማየት እንችልም! እኛ እውነተኛ አማኝ ሌላው መናፍቅ:: ይገርማል!
ገና ቤተ ክርስቲያን ሳትመሰርቱ ከሁሉም በልጠናል ትላላችሁ! ቤተ ክርስቲያን ይሁን እና እሰየው ብለጡ!
ለማንኛውም እያስተዋላችሁ ተራመዱ!

Anonymous said...

እስከ አሁን ብዙ አስተያየት አንብብያለሁ።
መቼም በምንሮባት አሜሪካ ሀገር የገለልተኛ ነገር ከዚህ የተለየ ይመስለኛል።
እዚህ ጥቅም እና ስልጣን ጎሰኝነትም ጨምሮ።

ከላይ የተለያዩ ሃሳቦች ሳነብ ብዙ ነገር ለመገንዘብ ችያለሁ።ለምሳሌ ልጥቀስ።

እነዚህ ሲኖዶሱ እኮ አንቀበልም ያሉ አይመስለኝም እንደተረዳሁት ሲኖዶሱ እንቀበላለን ብላችኋል አሁን አቋማችሁ የሚል ነገር ትጽፎአል።ይህ ማለት ሲኖዶሱ ከተቀበሉ የተቃወሙት አሁን በአካል የሌሉትን ፓትርያርክ ነበር ስለዚህ ሌላ ሲመጣ ሊቀበሉ ነው ማለት ነው። ስለዚህ እውነትም ለሃይማኖታችሁ ተቆርቁራችሁ ከሆን መንገድ ላይ ናቸውና አትቦጭቋቸው።
ሌላው በሀገረ ስብከቱ እንኳን ሊቀጳጳሱ ሊቀካህኑኑ ማዘዝ ካልቻለ ይህም ሥርዓት ፈርሷል ብሏል አንድ ሰጪ።እውነት ነውም ፈርሷል።ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በሲኖዶሱ ሥር ያሉትም አልጠበቁም ማለትነው።

ሌላው በሰፊው የተፃፈው ስለምንፍቅና ነው። ሊቀካህኑ በምንፍቅና ሆኖ ሌላውም ስደተኛውም እንዲሁ እንዲያውም የባሰ ከሆነ እነዚህ ሰዎች ተጋፍተው የቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ መጠበቅ ካልቻሉ ምን አድርጉ ነው የምትሏቸው? ምንፍቅና እና ዘረኝነት ካልተዋጋችሁ አንድ ሲኖዶስ ውስጥ ብትሆኑም ሌላ ሰው ሳይረዳችሁ ከገለልተኞች ብሳችኋል። ምክንያቱም እኔ እስከገባኝ ድረስ ሰው አንዲት እምነት የሚለውን የሐዋርያው የጳውሎስ ትምህርት ይዞ እንዳይኖር ምንፍቀና ከበዛባችሁ
በሌላ በኩል ቅዱስ ዳዊት በመዝ 132 ላይ ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ ያማረ ነው የሚለውን ደልዛችሁ በጎሳ እና በብሔር ከፈላችሁት ምኑ ቤተ ክርስቲያን ያሰኘዋል?
ቤተ ክርስቲያን የሚለው አንደኛው ትርጉም የክርስቲያኖች በአንድነት ተሰብስቦ አንድ ሆኖ አንድ እግዚአብሔርን ማምለክ ነው። እናንተ ግን ከፋፈላችሁት። ክርስቶስ የጳውሎስ የጴጥሮስ ተብሎ ተከፍሏል ወይ?
እስቲ እናንተ ከላይ የተጠቀሱት የተጸናወታችሁ ነገር አስወግዱ እና ከዚያ በኋላ ብትወቅሷቸው መልካም ነው።

ካልሆነ ግን በሲኖዶስ ስም ቁጭ ብላችሁ ሸቀጥ የከፈታችሁ፤ሱቅ በደረቴ ያነገታችሁ እናንተ እንጂ እነሱ አይመስሉኝም።ስንት ሰው ጉዳችሁ እየፃፈ ማንበብ አቃታችሁ። ይህ ማለት መስታወት ላይ ቆሞ እፊቱ ልጥፍ ጭቃ የሚያክለውን እድፍ አይቶ "ማርያም የሳመችው ነው" እናም ውበት ነው እንደማለትነው።

መፍትሄ ይሆናችኋል የሚለም ልዝርዝር፡
1 ምንፍቅናን አጥብቃችሁ ተዋጉ
2 ዘረኝነት ይብቃችሁ
3 1 እና 2 ከፈጸማችሁ በኋላ ምዕመኑ ወደ እነሱ አይደርስም የዚህ ጊዜ እነሱ ብቻቸው አይቀድሱ ብቻቸው ማኅሌት አይቆሙም።
3 ተሰባስባችሁ ለመነጋገር ሞክሩ

ገለልተኞች ለተባላችሁት ደግሞ።
ሲኖዶሱ ከተቀበላችሁ ታድያ ችግሩ ምንድን ነው?ከአስተያየቶች እንደ ተረዳሁት ከሆነ የውጩ ሲኖዶስ አይነካካችሁም ይህ ደግሞ እሰይ ያሰኛል ምክንያቱም ምንፍቅና እንደ ሌለባችሁ አብዛኛው ሰው ጽፎአል ከላይ። ይህ ማለት ኢትዮጵያ ያለው ሲኖዶስ ትቀበላላችሁ ማለት ነው።

ይህ ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ ፓትርያርክ ሲሾም የፓትርያርክ ስም ልትጠሩ ነው ማለት ነው። ይህ ባይሆን ግን ሰዎች እንዳሉትም የተሳካለት ሸቀጥ ነው።

እናንተም ያላችሁ ጥሩ ጎናችሁ አጥንክራችሁ ያዙና ምንፍቀናው ድባቁን ምቱ። ዘረኛን ደግሞ ልክ አበበ ገላው መለሰ ዜናዊን አንገት እንዳስደፋው አነገታቸው የምታስደፉበት እሩቅ አይደለም በርቱ። የራሳችሁ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ጠንክሩ በርቱ።
በተለይ ምዕመናን በመንፈሳዊ እና በዕለተ ዕለት ኑሮአቸው እንዲጠነክሩ አስተምሩ። ዘረኝነት ትምክህት ምንፍቅና እንዳይገባባችሁ ጥንክሩ።
መቼም እርግጥ የሆነ አንድ ነገር አለ ልክ ገማልያል እንዳለው።አነሳሳችሁ ለአገልግሎት ከሆነ ምንም ቢወራ ቢፃፍ እንዳትሸበሩ ሰው ሊያጠፍችሁ ቢሞክርም አትጠፉም።አጥፊዎች ይጠፋሉ እንጂ።ካልሆነ ግን መጨረሻችሁ አያምርምና አስቡበት።

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሚወዳት እናቱ፤ ስለተመረጡት ቅዱሳን ብሎ ከመጣብን ፈተና ይሰውረን።አንድነትና ሰላሙን ያምጣልን።አሜን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)