December 27, 2012

የታዋቂው ሰባኬ ወንጌል የመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው የዕርቅና የሰላም ጥሪ ለብፁዓን አበው

"ወገኖቼ፥ ይህች ቤተክርስቲያን እስከ መቼ በልዩነት ትቀጥል? ዛሬ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በማረፋቸው ምክንያት ሌላ ፓትሪያርክ ከሾምን፥ ነገ ደግሞ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ቀናቸው ደርሶ ሲያርፉ ሌላ ፓትሪያርክ ሊሾም ነው ማለት ነው። እንዲህ እያለ ሊቀጥል ነው? “ለአንድ እረኛ አንድ መንጋ ይሆናሉ፤” የሚለውን የጌታ ቃል የት እናድርሰው? ዮሐ ፲፥ ፲፮ ። ስለዚህ በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ አባቶቻችን አንድ ሆናችሁ አንድ አድርጉን። የሃይማኖት ልዩነት ሳይኖራችሁ እንደ ተለያያችሁ አትቅሩ። የተወጋገዛችሁትን ውግዘት አንሡ። ውግዘቱ ለእናንተ አልተሰማችሁም ይሆናል። እኛን በተለይም በውጭው ዓለም ለምናገለግል ካህናትና ለሚገለገሉ ምእመናን ከባድ ቀንበር ሆኖብናል። ይህንን ቀንበር ስበሩልን። የልዩነቱ ምክንያት የታወቀ ስለሆነ ያለፈውን ትታችሁ የወደፊቱን አስቡ። ዓለምን ከናቁ መናኞች የሚጠበቀው ይኽ ብቻ ነው። .... በመሆኑም አንዳችሁ ተሸነፉና አሸንፉ፥ ወይም ሁለታችሁም  ተሸነፉና አሸናፊዎች ሁኑ። ያን ጊዜ እግዚአብሔር ቅን መሪ ለቤተክ ርስቲያን ይሰጣታል። ቤተ ክርስቲያኒቱም የጸጥታ ወደብ፥ የሰላም ማማ ትሆናለች።" የመልእክቱን ሙሉ ቃል ከራሳቸው የጡመራ መድረክ “ቤተ ደጀኔ” ላይ (CLICK HERE) ያንብቡ። ዕድሜ ይስጥልን መ/ሰላም። 
  


12 comments:

የታደለ ነኝ said...

ይበል ነው! ሰባኬ ወንጌል መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ። ትልቅ አርአያነት ያለው ጥሪ ነው። በዘመናችን ብዙ ማድረግ የሚችሉ፥ በደስታዋ ጊዜ የቤተክርስቲያን መድረክ አልበቃ የሚላቸው ሰባኪያነ ወንጌል አሉ። የሠርግ ቤት ልጆቿ! ! በአሁኑ ወቅት በገዛ ልጆቿ ድካም፥ ቤተክርስቲያን ቀራንዮ በምትገኝበት ሰዓት ላይ ዝምታን መርጠው የደስታዋ ቀን እስኪመጣ የሚጠብቁ! እነ ቀሲስ እከሌ ፣ እነ መርጌታ እከሌ፣ እነ አባ እከሌ፣ እነ መምህር እከሌ ….. መጻፍ አትችሉም እንዴ? የሚገርም እኮ ነው! ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በመከራዋ ቀን ትፈልጋችኋለች !! አቋማች ሁን እንወቀው!! ሥም እንጥራ እንዴ? ከዚህ በላይ ምን አለ? ምእመናንስ መምህራኖቻችሁን ለምን አትጠይቁም? ያስተዛዝባል።

Anonymous said...

ቃለ ህይዎት ያሰማልን አባታችን መላከ ሰላም።
አባቶቻችን ብጹዓን ጳጳሳት፦ አንዳችሁ ተሸነፉና አሸንፉ፥ ወይም ሁለታችሁም ተሸነፉና አሸናፊዎች ሁኑ።

Anonymous said...

ነጽሩ ከዲሲ
መልአከ ሰላም እግዚአብሔር ዕድሜ ይስጥልን፡፡ ይህ አቋም የብዙዎች እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ሃሳባቸውን በምን መልኩ እንደሚገልጡ አጥተው የተቀመጡ ብዙዎች ናቸው፡፡ እንደእኔ እንደእኔ ከላይ አስተያት እንደሰጡት ወዳጄ “የታደለ ነኝ” ባለ ስሜታዊነት እየከሰሱ እየወቀሱ ሳይሆን ሁኔታዎችን አመቻችተው አስተያየት በመስጠቱ እንዲበረቱ ማድረግ ይገባል፡፡ለምሳሌ፡- ደጀ ሰላም ጥያቄ አዘጋጅታ ለመምህራን በኢሜል አድራሻቸው መበተን የተሰጣትን መልስ ማውጣት ትችላለች፡፡ አገልጋዮቹ በየአገልግሎት መድረኩ እንዲሁም በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው ያሳዩትን አቋም በዜና መልክ በመሥራት በዚህ ጉዳይ ለእርቁ ተባባሪ መሆናቸውን ማሳየት ይቻላል፡፡ ሌላውን ደግሞ እናንተ ጨምሩበት ….፡፡ችግሩ የሁላችንም ስለሆነ መምህራኑ ዝም በሉ ቢባሉም ዝም አይሉም፡፡ካህናቱ በየሥፍራው ብዙ ሳይናገሩ አይቀሩም፡፡በርትቶ ሓሳባቸውን በመሰብሰብ በሕብረት እንዲጮሁ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

Anonymous said...

fana wegi abat melake selam egziabhr yistelen!

Anonymous said...

QHY Abatach Qesis Dejen
Always I have one doubt does our Bishops back home know about Dejeselam & others blogs I donot think they have access to read all our wishes I talked one father pls let us give a chance to be one specially in diaspora church they listen to me as a new issue please those who has a chance to met Sebkea members & Holly Synod let them !Here in North America & Europe we really suffering in there ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ቃለ ህይዎት ያሰማልን አባታችን መላከ ሰላም።
አባቶቻችን ብጹዓን ጳጳሳት፦ አንዳችሁ ተሸነፉና አሸንፉ፥ ወይም ሁለታችሁም ተሸነፉና አሸናፊዎች ሁኑ።

Anonymous said...

ውግዘቱ ለእናንተ አልተሰማችሁም ይሆናል።

ውግዘቱ ለእናንተ አልተሰማችሁም ይሆናል።

ውግዘቱ ለእናንተ አልተሰማችሁም ይሆናል።


እኛን በተለይም በውጭው ዓለም ለምናገለግል ካህናትና ለሚገለገሉ ምእመናን ከባድ ቀንበር ሆኖብናል።

Anonymous said...

"በሀገር ቤት ያላችሁ አባቶች ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዎስ ከሃያ ዓመታት ስደት በኋላ ወደ መንበራቸው ቢመለሱ የተከፈለው ተመልሶ አንድ እንደሚሆን፥ ልዩነቱም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደ ሚፈታ ይጠፋችኋል ብዬ አላስብም።" ቀሲስ ደጀኔ የእርስዎም አስተያየት እኚህ ሰው ወደ ስልጣን ይመለሱ የሚል ነው? ታዲያ ማነው ቤተክርስቲያንን ከግለሰብ የሚያስቀድም? ይህ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አጀንዳ መሆኑን ለይተው ያወቁት አልመሰለኝም:: እርስዎ በወንጌሉ ላይ ቢያተኩሩ መልካም ነው::

Anonymous said...

ለአባባሉ ቃለ ሕይወት ያሰማልን። ሰላም የሚያስፈራው ዲያብሎስ ብቻ ነው ምክንያቱም ቦታው አይደለምና እርስዎ እንደሚሉት አባ መርቆሬዎስ ወደ መንበሩ ቢመለሱ አንድነት ይመጣል ነው ይህ አባባል ለጊዜው ፖለቲካ ምላሽ ዪሆን እንደሆነ እንጅ ለቤተክርስቲያን እንደማይሆን ለእርስዎ እንግዳ አይደለም። ኢትዮጵያ በነበሩ ጊዜ ጉዳዩን በደንብ ሳያውቁት እንደማይቀሩ አልጠራጠርም። ይልቁንም አባ መርቆሬዎስ ከአባ መልክጼዴቅ መዳፍ ተላቀው በራሳቸው አንደበት እውነቱን ተናግረው ወደ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ቢቀርቡ ይህም የቤተክርስቲያንን ክብር ወደ ቦታው ይመልሳል። አባ መልክጼዴቅ በሕይወት እያሉ ይህንን ካየነው በውነት እግዚአብሔር ታርቆናል ማለት ነው። ሌላውን ትተን በጸሎት እንትጋ የሚሆነውን የሚሻለውን እግዚአብሔር ያውቃልና።

Anonymous said...

የተንጸባረቀው "አባ መርቆርዮስ ይመለሱ" የሚል ነው:: እባካችሁ የቤተክርስቲያን አንድነት ማለት የእኚህ አባት ወደ ስልጣን መመለስ አይደለም:: ይህ የተቃዋሚ ጎራዎች የያዙት ስትራተጂ ነው:: እውነት ለመናገር አባ መርቆርዮስን የማይፈልግ ህዝብ እጅግ ብዙ ነው:: የእርሳችው መመለስ ልዩነታችንን ያሰፋል እንጂ አንድነትን አያመጣም::ስልጣንንና አንድነትን ለይታችሁ እዩ:: አዲስ ፓትርያርክ ቢሾምም የቤተክርስቲያንን አንድነት ማምጣት የሚቻልበት ብዙ አማራጭ አለ:: ያጣነው ነገር ቢኖር መንፈሳዊነቱን ነው:: አባቶች የፓርቲና የቢዝነስ ዩኒፎርማቸውን እንደለበሱ ቤተክርስቲያን መምጣታቸው ነው ችግሩ::

የታደለ said...

እኔ እንኳን ትንሽ ማለት የምፈልገው በተደጋጋሚ የብጹዕ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ መንበራቸው ላሳሰባችው ወንድሜ መልስ ቢጤ ለመወርወር ነው። የኔ ጌታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለ ፖለተከኞች ተጽዕኖ ራሷን አስተዳድራ አታውቅም። ሁላችንም የምንስማማበት እውነት የአቡነ መርቆርዮስ ስደት በመንግስት ግፊትና በአባቶቻችን ድክመት መሆኑን ነው። ዛሬ ቤተክርስቲያቲያን መልሳ የተፋጠጠችው ከ20 ዓመት በፊት በትክክል መመለስ ካልቻለችው ጥያቄ ጋር ነው። ያንን ለማረም ሁለተኛ ዕድል አግኝታለች። የዚህ ጥያቄ መልሱ ተዋጠልንም አልተዋጠልንም የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ክብር ቦታቸው መመለስ ነው። ይህንንi እንድናይ የምንፈልገው የግንቦት ሰባት ወይም የተቋዋሚዎች አባል ወይም ደጋፊ፥ ወይም ፥የኢህአዲግ መንግስት ተቋዋሚዎች ስለሆን አይደለም። ቀኖናው የፈረሰው በትክክል በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ ሲሾም ነው። የሚስተካከለውም ፓትርያርኩ ቦታቸው ሲመለሱ ነው። ስለዚህ እርሶ እንደሚገምቱት አይደለም። ለ<> መቃርዮስም (መርቆርዮስ እንዳላልኩ ያስተውሉ) ሆነ ለአቡነ መልከ ጼዴቅ ያሎት አስተሳሰብ ትክክለኛውን ነገር ከመደገፍ ወደኋላ እንዳይጎትቶት እፈራለሁ። ሁላችንም ያንን አጥተነው ሳይሆን ለቤተክርስቲያን አንድነት የሚከፈል መስዋዕትነት እንደሆነ ስለተረዳን ነው። በተነጻጻሪ ደግሞ በአዲስ አበባ የሚገኙ አባቶቻችንም ከተመሳሳይ በሽታ ንጹህ እንዳልሆኑም ወዳጄ የሚረዱ ይመስለኛል። ቁም ነገሩ አሁን ምንም ይሁን ምን ቤተክርስቲያን መጀመሪያ አንድ ትሁን ከዚያ በኋላ በጋራ ወደ ንስሀና መፍትሔው እንመጣለን።

Anonymous said...

የታደሉ--- ህሳብዎ መልካም ነው። ስለ አባ መልከ ጼዴቅ ያለኝ አስተያየት እርስዎ እንዳሉት ትክክለኛውን ነገር ከማየት የሚከልል አንድም ነገር የለውም በዚህ አይስጉ። እንዳጻጻፍዎ ከሆነ የርስዎ ስጋት የሃያ ዓመቱ ሳያንሰን ሊደግመን ነው ይመስለኛል ይህ ደግሞ ከእምነት ያውጣልና በዚህ ላይ ጥንቃቄ ማድረጉ የሚሻል ይመስለኛል። የፈረሰውን ቀኖና እዚህም ያሉት ቤተክርስቲያንን ከፍለው አጽንተውታል። እስቲ ኢትዮጵያ ካሉት ክሊቃውንትም ሆነ ከምእመናን አንደበት እንስማ አባ መርቆሬስም ይናገሩ አንድ ጊዜ እንዳየሆቸው ከሆነ ህሳባቸውን ለመግለጽ ተጽእኖ እንድሚደረግብቸው ነው። ለኛ ግን ከሁሉ በላይ የሚጠቅመን አጥብቀን መጸለዩ ነውና እንበርታ።

yo said...

አለማወቃችሁን እግዚአብሄር ይቅር ይበላችሁ፡ የቤተክርስትያን ጉዳይ እኮ የጽድቅ እና የኩነኔ ጉዳይ ነዉ፡ ስለዚህ ሁሉም ክርስትያን በ ከፋፋዮች እና በዘረኞች ሳይደናገር የቤተክርስትያንን አንድነት መጠበቅ ይገባል። ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪወስ በሚያሳዝን ሁኔታ በመንግስት ጣልቃ ገብነት እንደተሰደዱ ለማንም ግልጽ ነዉ፡እኒህ አባት እኮ 21 አመት ሙሉ በጸሎት እና በዝምታ የአለምን ነገር በመተዉ ለእግዚአብሄር ሁሉን ሰጥተዉ በእግዚአብሄር ፈቃድ የሚኖሩ ናቸዉ፡የተሰደዱትም ለእዉነት እና ለጽድቅ ሲሉ ነዉ፡ ፓትርያሪክ በህይወት እያለ ሌላ እንዳይሾም ፍትሀሃ ነገስቱ ይደነግጋል፡ አሁንም ቢሆን ያለፈዉን ስእተት አርመን እና የተጣሰዉን ቀኖና አስተካክለን የመጭዉን የቤተክርስትያን ሁኔታ ለጳጳሳቱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የእምነቱ ተከታይ ስለሀይማኖቱ ሊነሳ ይገባዋል።አንዳንድ አላዋቂወች የቤተክርስትያን ጉዳይ የነብስ ጉዳይ እንደሆነ ባለማወቅ ወደ ፓለቲካ እና ወደብሄር ሊያጠጋጉት ይሞክራሉ፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)