December 25, 2012

ከአዲስ አበባ ቅ/ሲኖዶስን ወክሎ የመጣው ልዑክ የሰላምና አንድነት ጉባኤውን መግለጫ ተቃወመ

  •     አስታራቂ ጉባኤው ይቅርታ ካልጠየቀ በውይይቱ አንሳተፍም ብሏል፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 16/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 25/2012/ READ THIS IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶች መካከል የተጀመረው ዕርቀ ሰላም ከግብ እንዳይደርስ “የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ” ጉዳይ እንዲቀጥል አስመራጭ ኮሚቴ መቋቋሙን ተቃውሞ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ራሱ ጠንካራ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በተለይም አዲስ አበባ ያሉት አባቶች ጉዳዩን በጥሙና እንዲያስቡበት ያሳሰበው ጉባኤው ይህ ሁሉ ልፋት መና እንዳይቀር ተማጽኗል።
ይህንኑ ደብዳቤ በጽሙና የተቃወሙት ከአዲስ አበባ የመጡት ልዑካን ዛሬ ለደጀ ሰላም በላኩት መግለጫ “የሰላምና የአንድነት ጉባኤ ያወጣው መግለጫ የተሳሳተ መሆኑን አበክሮ ገልጿል። “የሰላምና የአንድነት ጉባኤው ታሕሣሥ 12 ቀን 2ዐዐ5 . ያወጣው መግለጫ በዘለፋ የተሞላ፣ የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊነት የተዳፈረ፣ ሚዛናዊነትን ያልተከተለ፣ አሳሳች ትርጉም የሰጠ፣ የአደራዳሪ ወይም የአስታራቂ መርህን የጣሰ፣ የተጀመረውን የሰላም ጉዞ የሚያደናቅፍ” ነው ብሎታል። አክሎም “ከሁ በላይ የሚያስገርመው ነገር ቢኖር ሁለታችንም የጉዳዩ ባለቤቶች ከቅዱስ ዶስ ውሳኔ ሉዓላዊነት በመለስ የሰላሙ ጉዞ እንዳይደናቀፍ ጠብቀን በምንገኝበት በአሁኑ ጊዜ አስታርቃለሁ እያለ የሚገኝ አካል ሆን ብሎ የሰላሙን ሂደት ለማደፍረስ ይህን ያህል የቸኮለበት” ጉዳይ ምሥጢር እንደሆነበት የልዑካኑ ቡድን ጠቅሶ በውይይቱ ወቅትም ይኸው አስታራቂ ኮሚቴ ወገንተኝነት ሲያሳይ መቆየቱን ጨምሮ ጠቅሷል።

አክሎም “ኮሚቴው ይህንን ስህተቱን በግልጽ አምኖ ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነና ኃላፊነቱን በአግባቡ ካልተወጣ ከዛሬ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ኮሚቴ አማካኝነት ለመደራደር ፈቃደኛ እንደማትሆን ሊታወቅ ይገባል” የሚል ጠንካራ አቋም አንቀባርቋል። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች እንድትመለከቱ እንተይቃለን።

ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የኢትዮጵ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላምና የአንድነት ጉባኤ ያወጣውን የተሳሳተ መግለጫ አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ
ወአልቦ ማኅለቅት ለሰላሙ  ለሰላሙ ፍጻሜ የለውም፡ ኢሳ. 97

የኢትዮጵ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ልኡክ ሰላምና አንድነት ለመወያየት ከኅዳር 28 እስከ 3 ቀን 2ዐዐ5 . በዳላስ ቴክሳስ ጉሳኤ ተገኝቶ ስለሰላምና አንድነት ሥምረት በተካሄደው ስብሰባ የበኩሉን ጉልህ ሚና መጫወቱ ይታወሳል፡፡

ስለ ሰላሙ ሥምረት ያለውንም አቋም ሁለታችን ወገኖች በጋራ ባወጣነው መግለጫ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ለወደፊትም ለሰላሙ መሳካት ያለውን ፍላጎት በጋራ መግለጫው በሚገባ ተገልጿል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ የሰላምና የአንድነት ጉባኤው ታሕሣሥ 12 ቀን 2ዐዐ5 . ያወጣው መግለጫ በዘለፋ የተሞላ፣ የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊነት የተዳፈረ፣ ሚዛናዊነትን ያልተከተለ፣ አሳሳች ትርጉም የሰጠ፣ የአደራዳሪ ወይም የአስታራቂ መርህን የጣሰ፣ የተጀመረውን የሰላም ጉዞ የሚያደናቅፍ ሆኖ ስለተገኘ የቅዱስ ሲኖዶስ ልኡክ ይህንን መግለጫ ለማውጣት ተገዷል፡፡

በመሠረቱ የጉባኤው ኮሚቴ ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ እንደዚህ ያለ ሚዛናዊነት የጎደለው አዝማሚያ እየተከተለ እንደመጣ በየጊዜው ያወጣቸው መግለጫዎችና መፍትሔ ናቸው ብሎ ያቀረባቸው ሐሳቦች ምስክሮች ናቸው፡፡
ይህን ቅንነትና ሚዛናዊነት የጎደለው አካሄድና አመለካከት እንዲያርም በልኡኩ በኩል ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎች እንደተሰጡት በአንደበቱ ቢክድ እንኳ ኅሊናው እንደሚረታው እርሱ ራሱ አይስተውም፡፡

ከሁ በላይ የሚያስገርመው ነገር ቢኖር ሁለታችንም የጉዳዩ ባለቤቶች ከቅዱስ ዶስ ውሳኔ ሉዓላዊነት በመለስ የሰላሙ ጉዞ እንዳይደናቀፍ ጠብቀን በምንገኝበት በአሁኑ ጊዜ አስታርቃለሁ እያለ የሚገኝ አካል ሆን ብሎ የሰላሙን ሂደት ለማደፍረስ ይህን ያህል የቸኮለበት ምሥጢር ምን እንደሆነ ሊገባን አለመቻሉ ነው፡፡

ይሁንና እስከ አሁን ድረስ ባይገባንም አሁን ግን ከመግለጫው ይዘትና መንፈስ አንጻር ስናስተውል ሰላሙ እንዲመጣ ያልፈለገ የሰላም ጉባኤ ኮሚቴው ራሱ እንደሆነ በአንደበቱ መስክሮ አረጋግጦልናል፡፡

የጉባኤው ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ በሰነዘረው የድፍረት ድፍረት የሰላሙ ሂደት ቢሰናከል ተጠያቂው እርሱ ራሱ መሆኑን ሊገነዘብና በግልጽ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል፤ ኮሚቴው ይህንን ስህተቱን በግልጽ አምኖ ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነና ኃላፊነቱን በአግባቡ ካልተወጣ ከዛሬ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ኮሚቴ አማካኝነት ለመደራደር ፈቃደኛ እንደማትሆን ሊታወቅ ይገባል፡፡

ይህም ማለት የማስታረቅ ልምድና ብቃት ያለው፣ ፍጹም ገለልተኛና ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት በሐቅ የሚቆረቆር፣ ሚዛናዊነት ያልተለያቸው የተለያዩ የመፍትሔ ሐሳቦችን በማፍለቅ ማግባባት የሚችል ወገን ሲገኝ ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም በሯን ትዝጋለች ማለት አለመሆኑን የቤተ ክርስቲያናችን ተከታዮችና ወዳጆች ሁሉ በግልጽ ሊያውቁት ይገባል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ራሱ ለሰላም ፍጻሜ የለውም ብሎ ነግረናልና፡፡

በመጨረሻም ማንኛውም ለእውነት የቆመ ወገን ሁለታችን ወገኖች በጋራ ያወጣነው መግለጫ፣ የጉባኤው ኮሚቴ ካወጣው መግለጫ ጋራ ምን ያህል እንደሚቃረንና የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊ ሥልጣን እንዴት እንደሚዳፈር ቃል በቃል በማነጻጸር መረዳት እንደሚቻል እያስገነዘብን ቤተ ክርስቲያናችን ለሰላም ሲባል እስከአሁን ባደረገችው ጥረት ከግማሽ መንገድ በላይ እንደተጓዘች ሁሉ አሁንም ለሰላሙ ሥምረት እጇን እንደማታጥፍ ለሰላም ወዳጅ ወገኖቻችን ሁሉ አበክረን እንገልጻለን፡፡
ወአልቦ ማህለቅ ለሰላሙ
1.              አባ ገሪማ ዶክተር የብፁዕ ወቅዳስ ፓትርያርክ ልዩ /ቤት የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ፣
2.             አባ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎ /ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
3.             አባ ቀውስጦስ በሰሜን ሸዋ የሰላሌ /ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
4.             ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ የመ////ቤት መንፈሳዊ ዘርፍ //አስኪያጅ፣

ታህሣሥ 13 ቀን 2ዐዐ5 .
ዋሽንግተን ዲስ፣ አሜሪካ

55 comments:

Anonymous said...

ENDIWEM ZENBOBESH ENDEWEM TEZA NESH

Anonymous said...

I don't agree! The document seems forged. Compare the signature with the one that they put on the first agreement with those fathers in exile.
We'll see a counter attack for it from them.

May God give us Unity!

Anonymous said...

አይይይ !!! ከገቡበኝ እንዴት እንደሚወጡ ሲያወጡ ሲያወርዱ ከርመው አሁን ጥሩ ማሳበቢያ አገኙ። ይቅርታ ካልተጠየቅን አንደራደርም!!! ወዴት ወዴት። እባካችኹ እናንተ የሰላም ጉባኤ አባላት ሰብብ ነውና የሚፈልጉት በቶሎ ስለ እግዚአብሔር ስትሉ ይቅርታ ጠይቁ። እስካሁን ስትፉ ስትደክሙበት የነበረውን ጉዳይ አፈር ሊያለብሱት ናውና።
ወይ ጣጣ! መቼ ይሆን በቤተ ክርስቲያናችን እግዚአብሔር ብቻ የሚቀድመው?
ቸር ያሰማን

Anonymous said...

If this really is the way they want end the peace process, it is a clear indication of the level of meddling by the Ministry of Federal Affairs. That specific ministry is under total monopoly of Menafikan/Tehadso. Never thought they would dare to intrude this much though.

Anonymous said...

የኣባቶች መግለጫ ባለሁበት በዳላስ/ ቲክሳስ የብዙዎቻችንን ስሜት ነው ያንጸባረቁት።
በዕርግጠኝነት ኮሚቴው ብዙ ግድፈቶች ብቻ ሳይሆን እንደኔ እንዲህ አይነት አካል በእንደዚህ አይነት መቀጠሉ ጉዳቱ ነው የሚያመዝነው።
ልብ ላልነው። ያለጥርጥር!
ልብም እንበለው።

እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ሥራ ይባርክ።

Anonymous said...

Yates nawe yasalame gobayawe magelachea pls

Anonymous said...

I agree with them... all released information was one sided favering
"sidetegnaw synodos"...

Anonymous said...

Egizabehare macharashawen yasamerawe ega enetsaley

Anonymous said...

yeenate meknt adnakfgn hone negeru befsum yehea leerku meknyat ayhonm behultachu mekakel megbabatu kale leketl yechlal.seleweladtamlak belachu selame fterulen menfelgew yehenen becha new.

z frankfurt said...

የአባቶቻችን መግለጫ ትክክለኛ ቢሆንም ዘግይቶአል እላለሁ

ቀድሞውኑም አስታራቂ ከተባሉት አንዱ መ/ልዑለቃል voa ላይ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ከአድማጭ ለሚቀርብላቸው ጥያቄ ምን ያህል በቁጣና በወገንተኝነት ሲመልሱ ለሰማ ሩቅ ማሰብ አያስፈልገው ለዛውስ ቤተክርስቲያን ያስታራቂውን ኮሚቴ ማጣራት አለባት እላለሁ

frankfurt Germany

የሰላም ባለቤት የሰላም አለቃ የሰላም ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ የጠፋውን ሰላም ይመልስልን!
አሜን!

Anonymous said...

zare abatochcachen le segachew adeletewal .tarikem egzeabhairem yeteyekachewal.hizebe chrisitiyanun egzeabhair yetadegewal .abew bitsuan lekane papasat gin ye tarik teteyakewoche nachehu. yehche betekerestian eske alem fetsame tenoraleche enanete gin besbashe ergafewoche mehonachehun ateresu. abune paulose eko zare behiyewot yelum. yalefewn 21 amet yebetekerstian mekerawan asebu.zelalemawy ayedelachehum.

Anonymous said...

Abatoch lebetkrstiyan dersulat lgochow selame nafkochewl yeenatn andnt adera melkam zena asmun.

Anonymous said...

ahun yekerachu tensh new beft geleltegn yemibalew hasab eykernew dc rese adbarat kedst mareyam, dc kedus michael betekrstiyan metachu hezbun barkachu yehzbunm smet aytachhole ahun besost tekflo yeneberew wedhulet eyhone new kehulet degmo wedfsamew andnt endtmetu amlake yerdachu

Anonymous said...

Ahun Tikikil Nachew Shinagilewochu Abizitewt nebere mekakelega mehon neberebachew

Anonymous said...

በጣም ያሳዝናል

ታሪክ ይፋለሳል እያሉ ቤተ ክርስቲያን ነገር ፈጽሞ ዘንግተውታል።
እኛ በታሪክ አንኖርም የሚያስፈልገን በሰላም በፍቅር መኖር ነው።
እምቢ ብትሉ በተለያየ ጥቅም ወይም ዘረኝነት ወይም ስልጣን ወይም በፍርሃት መንፈስ ለተሞላችሁ ወይም ሰላም ሳይሆን ጥላቻ ብሎም እኩይ ምግባር ለተጸናወጣችሁ በሙሉ አንድ ነገር ቆም ብላችሁ ልታስቡ ይገባል እላለሁ።
አባ ጳውሎስም ሄደዋል መለሰም ሄደዋል እናንተም እንደ እነሱ ላትሄዱ ምን ጋራንቲ አላችሁ?
ስልጣን ለቋመጣችሁ ድምፃችሁን ለደበቃችሁ ሁሉ የሰማይ አባት ይከፍላል።ግድ የለም እድሜ ይሰጠን እናያለን።
ዮዲት ጉዲትም ግራኝ አህመድ ፋሽስትም ሌላም ቤተ ክርስቲያንን ጎዱ ግን እንሱ ጠፍተው ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ሰፍታ አብባ አለች እናድሳለን የሚሉትም ሆነ እኩይ ለሚሆኑባት ሁሉ እግዚአብሔር እጁን ያነሳል እንጠብቅ ግድ የለም።
ሠይፉን ብትረግጥ ያለውን እናስተውል።
ክርስቶስንም ክብር ይግባውና ፈጣሪ ሆኖ ሳለ ፍጡር ቢሉትም ሞተ ቢሉትም ወታደር ቢያሰልፉም ያች በትንቢት በቅዱስ ቃሉም የነገረን ቃል ነው። ውሸት ተወርቶ ሌላም ሆኖ 3 ቀን ሲሆን ግን ሞትን ድል ነስቶ ውሸቱን ሁሉ አጥፍቶ የማይጠፋ አምላካዊ ቃሉ ከልባችን ውስጥ ተክሎአል። ሁሉም ነገር ነገ መድኃኒዓለም ሁሉንም ያሳየናል።የሚሾም የሚሽርም ሕይወት የሚሰጥም ሕይወትም ቀጥፎ የሚወስድ እርሱ ነው።ስለዚህ ቆም ብላችሁ አስቡ።
ከቤተ ክርስቲያን ላይ እጃችሁን አንሱ።

አንሥኡ እደዌክሙ ከለባት እምቤተ ክርስቲያን።
እያልኩ ልሰናበታችሁ

መግለጫ said...

እኔ የምለው ምነው ይሄ መግለጫ አላባራ አለ አሁኑኑ ከኢትዮጵያ የሚወጡትን ማንኛውንም መግለጫ የሚያጣራ ኮሚቴ ይቋቋምልኝ!

Bushaga said...

ወያኔዎች እባካችሁ ቤ/ክርስቲያናችንንም ሀገራችንንም ልቀቁ ቋቅ ብላችሁናል ምርር ነው ያልነው ነቀርሳዎች

Anonymous said...

ጉዳዩ እኮ ግልጽ ነው።
1. የዳላሱ የዕርቅ ጉባኤ ኅዳር 30 ቀን ሲጠናቀቅ ሁለቱም ተደራዳሪ ወገኖች ተስማምተው የፈረሙበት መግለጫ ወጥቷል ተብሏል።
2. የሰላምና የእርቁ ኮሚቴ ከዚሁ ከጋራው ጉባኤ ጋር የተያያዘ መግለጫ ታኅሣሥ 12 ቀን አውጥቷል። በዚህ መግለጫ ውስጥ አራት አንኳር ነጥቦች አሉ። እነርሱም ሀ) ምንም እንኳ ገና ያልተቋጩ ጉዳዮች ቢኖሩ የዳላሱ ጉባኤ በሁሉም ወገን በመግባባትና በመልካም ሁኔታ ስለ መካሄዱ፤ ለ) ሁለቱም ተደራዳሪ ወገኖች ያልተቋጩትን ጉዳዮችና ከአስታራቂው ኮሚቴ የቀረቡትን የመፍትሔ ሀሳቦች ለመደቧቸው የበላይ አካላት አቅርበው ተጨማሪ መመሪያ በመያዝ እንደገና ለመሰብሰብ ስለ መስማማታቸው፤ ሐ) የሚሰበሰቡትም ከጥር 16-18 እንዲሆን ስለ መወሰናቸው፤ መ) የጋራው ጉባኤ በጥር ወር ተሰብስቦ የመጨረሻውን ውጤት ለበላይ አካላት ከማቅረቡ በፊት አዲስ አበባ ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ አዲስ ፓትርያርክ የሚያስመርጥ ኮሚቴ የሰየመ መሆኑ መወራቱና ይህም የዕርቁን ሂደት ሊያደናቅፍ ይችላል የሚሉ ናቸው።
3. በዕርቁ ጉባኤ እንዲሳተፉ ከአዲስ አበባ የተወከሉት ልኡካን ታኅሣሥ 13 ቀን ከዋሽንግተን ዲ.ሲ. ያወጡት መግለጫ የአስታራቂው ኮሚቴ መግለጫ የዳላሱን ጉባኤ የጋራ መግለጫ የሚቃረን ስለሆነ አነጻጽሮ ትክክሉን መረዳት ያስፈልጋል ይላል።
4. ታላቅ ተስፋ የተጣለበት የዕርቀ ሰላሙ ሂደት በዚህ አነታራኪና እጅግ አሳዛኝ በሆነ መልክ ይፋ ከወጣ ሁኔታውን በየደረጃው መመልከትና ትክክሉን ፈጥኖ መረዳት ያስፈልጋል። ጥልቅና ስውር የሆኑት ችግሮች ሁሉ በእግዚአብሔር ኃይል በወቅቱ ይታወቃሉ። አሁን ሊቀድም የሚገባውና ተጨባጭ የሆነው ጉዳይ የጋራውን ጉባኤ መግለጫና የአስታራቂውን ኮሚቴ መግለጫ ማነጻጸርና በትክክል መረዳት ነው። ስለዚህ እንደሌሎቹ ሰነዶች ሁሉ የዳላሱ የጋራ ጉባኤ የተፈራረመባቸው መግለጫም ለሕሊና እረፍት እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ ቶሎ ይፋ ሆኖ ሕዝበ ክርስቲያኑ ሊያውቀውና የራሱን ግንዛቤ ሊወስድ ይገባል።

Anonymous said...

those who are called themselves as Abba or papasat i just start predicted their death is on the way the maxim they can stay 3 or 5 years accusing bas less accusation to ye salam group for no reason. i hope God will judge on you. pls Deje Selam can you guys post all Papasat office phone number? it not illegal to post it please i need it i know lot of people are looking for the same question?????????????????????? this is not the first time to ask this question

Anonymous said...

በኔ አመለካከት ኣባቶቻችን በጣም ዘግይተዋል ይህውላቹ ወገኖቼ እኔ የምኖረው በዳላስ ቴክሳስ ነው የተሰራው ደራማ የሚያናድ ነበር ከአስታራቂዎቹ መካከል ለምሳሌ አንዱ ዲያቆን አንዱኣለም ነው በዚህ በዳላስ እና በአካባቢዋ ላሉ አብያተ ክርስቲያናት በጉባኤው ላይ እንዲሳተፉ ስጋበዝ አንኳን መረጦ ነወ የጠራው ግን ያልተጠሩት አብያተ ክርስቲያናት ካህናት የሰንበት ትምትርህ ቤት መዘምራን እና ምእመናን እሱ እንዳሰበው ሳይሆን እነሱ ግን የቤትክርስቲያኔ ጉዳይ ነው ብለው እንደዛ ባማረ መልኩ ኣባቶቻችንን ተቀበሏችው ይህንን ያደረገ እግዚአብሄር ይመስገን ይህንንም ላደረጋቹ እግዚአብሄር ይባርካቹ።ከዛም በዋላ አባቶች ወደሌላ አብያተ ቤተ ክርስቲያናት እንዳይሄዱ ተከላከለ ሁለቱን ኣባቶች ቢያግዳቸውም አቡነ ቀዎስጦስ ግን እዚህ ድረስ መጥቼ ሳላገኛቸው አልሄድም በማለት ሰኞ እለት በደብረ ፀሀይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወአቡነ አረጋዊ እንዲሁም በደብረ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ሊመጡ ቻሉ ወደ ማህበረ ቅዱሳን ፅህፈት ቤት መሄዳቸውንም ሰምቻለሁ ሽማግሌ ተብዬዎቹ ሲሰሩት ክነበረው ነገር ሌላም ሌላም ተጨማሪ ነገር ማለት ይቻላል ይሄ አኔ የምለው ግን ፍጥጥ ያለውን ኣድሎ ነው ሰዎች ግን የልጁ እንጂ የኮሚቴው ሃሳብ አይደለም እሱ የተወከለው በስደተኛዎቹ ስለሆነ ነው ሲባል ነበር አሁን ግን የሱ ብቻ አለመሆኑን ተረድቻለሁ ቢዘገይም ጥሩ ብላቹዋል ወገንተኛ ደጋፊ እንጂ ሽማግሌ ሊሆን አይችልም።

Anonymous said...

Hasabachun yele sidb maskemet yichalal abatochn, stupid,wushoch ejachun ke batekrstian ansu, eyilu
yemisfum, ejig yesaznal.sidb yesitan yediablos new.abatochn mesadeb awakinet aydelem.bemesadeb yesew kibr aykenesm.yerash teshenafinet dekamanet new yemigestew.lebetekrsianachn andnetn,selamn yiseten zend egziabhern bestelot melemen yishalal

Anonymous said...

I CAN'T BELIEVE THIS. THESE PEOPLE THEY JUST FIND A REASON TO FIGHT WITH EVERYBODY. THEY ARE FULL OF EGO AND I DON'T THINK THEY REALLY CARE ABOUT THE EOT CHURCH AT ALL. LOOT WHAT THEY WROTE. IT IS AMAZING THEY ARE LOOKING FOR
የማስታረቅ ልምድና ብቃት ያለው፣ ፍጹም ገለልተኛና ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት በሐቅ የሚቆረቆር፣ ሚዛናዊነት ያልተለያቸው የተለያዩ የመፍትሔ ሐሳቦችን በማፍለቅ ማግባባት የሚችል ወገን ሲገኝ

IF YOU DON'T KNOW HIM YET, HIS NAME IS LORD JESUS, THE HEAD OF THE CHURCH, i.e YOUR HEAD , JUST FOLLOW HIS COMMANDMENTS,
Mat 6:14-15 "For if you forgive men when they sin against you, your heavenly Father will also forgive you. But, if you do not forgive men their sins, your Father will not forgive your sins."

Matthew 12:25 Jesus knew their thoughts and said to them, "Every kingdom divided against itself will be ruined, and every city or household divided against itself will not stand.
MAY GOD ALMIGHTY PROTECT EOTC, AMEN
Berhanu Melaku said...

አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ አለች አህያ
===================
አህያና ጅብ ለረጂም ጊዜ ጓደኛሞች ሆነው ይኖሩ ነበር ፤ የሚኖሩባትም ሰፈር በምድር ላይ የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ተሟልቶ የሚገኝባት ነበለች። ከእለታት አንድ ቀን ኑሮ ሆነና ከሚኖሩባት ሰፈር የተሻለ ምድር ፍለጋ ብለው እረጂም መንገድ በስምምንትና በፍቅር ጉዞ ጀመሩ። ረሃብና የውኃ ጥም ከተቀላቀለበት ረጅም የበረሃ ጉዞ በኋላ ትልቅ ወንዝ በሩቁ አዩ፤ በደስታ ውኃ ሊጠጡ ወደ ወንዝ ወረዱ። ከወንዙም ጋ እንደደረሱ ጂብ ከላይ በኩል አህያ ደግሞ ከታች በኩል ውኃ መጠጣት ጀመሩ።
ጂብ ውኃ ከጠጣ በኋላ የሚበላ ነገር ፈለገ ። ቀና ብሎ ሲመለከት የሚያየው ጓደኛውን አህያን ብቻ ነው፤ አህያን ሊበላት ተመኘና የሰላም ጉዞ ስምምነቱን የሚያፈርስበት ዘዴ ፈለገና አንድ ነገር በህሌናው ብልጭ አለለት። ‘’ አሃ ስምምነታችንን ለማፍረስ ውኃ ልጠቀም ’’ አለና ‘’አህያ!” ብሎ በቁጣ ቃል ጠራትና “ለምንድን ነው እኔ እየጠጣሁ ውኃውን የምታደፈርሸብኝ?“ በማለት የጠብ አጫሪነት ጥያቄውን አቀረ፤ አህያም ሲመልሰ “ አንተ የምትጠጣው ከላይ በኩል ነው፤ አንተ ያደፈረስከው ውኃ ወደ እኔ ይመጣል፤ ውኃ ወደ ታች እንጂ ወደ ላይ አይሄድም፤ አያ ጂቦ ሳታመካኝ ብላኝ!” አለችው ። ብለው አባቶቻችን በነግርና ምሳሌ አሰተምረውናል።
ስለዚህ አባቶች ምክንያት መፍጠር አስፈላጊ አይደለም። ይልቁንስ የምዕመናንን የልብ ትርታ ብታዳምጡ መልካም ነው፤ በማለት ማሳሰቢያየን እቋጫለሁ።
ለኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን ኢ/ሀ/ደ/ግ የመረጠውን ሳይሆን እግዚአብሔር የመረጠውን አባት ይሰጣት። አሜን ።

Anonymous said...

ድሮም እኮ የተሰደደው "ሲኖዶስ" ሁለት አማራጭ ነው ያለው 1)የአዲስ አበባውን መንበር መረከብ 2)ስደተኛ ሆኖ መቀጠል:: ከዚህ ውጭ ለነሱ ሞት ነው ስደተኛ ተብሎ መቆየት ብዙም ስላላዋጣ ነበር እርቅ የሚል ነገር በሰላም ጎባዔው በኩል የጀመሩት :: እንደ እኔ አመለካከት ግን ለምን አይታረቁም የሚለው ሳይሆን ዋና ነጥብ መሆን ያለበት በያሉበት ሆነው ለምን የተሰጣቸውን አደራና ኃላፊነት አልተወጡም የሚለው ነው:: እነዚህ የሀይማኖት አባት ሳይሆኑ ህዝብን ከህዝብ የሚለያዩ የብጥብጥ አለቃዎች ናቸው:: ህዝቡ ግን በጨዋነቱ ተፋቅሮ ቢኖር መልካም ነው::

Anonymous said...

የት እንዳለ ሚናው ካልታወቀው ልዑለቃል እና ልደር ባዩ አንዱአለም የጠራ እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያን የተካተቱበት ኮሚቴ ይቋቋም። ከዳላሶች አንዱ።

Berhanu Melaku said...

<><><><><><><> ከእርቁ በኋላስ ? <><><><><><><><>
ከእርቁ በኋላ የኦርቶዶክስ ሃይማኖታችን በአስኳይ ልታተኩርባቸው የሚገባ አሥር ነጥቦች፦
1ኛ ተሃድሶን በንስሃና አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ በውግዘት ማጽዳት፣
2ኛ ሙስናን ከሁሉም አባቶች እጅ ላይ ማጠብ፣
3ኛ ዘረኝነትን ከቤተክርሰቲያንና አልፎም ከኢትዮጵያ ከርሰ ምድር ማጥፋት፣
4ኛ መነኮሳት በምድር ላይ የሚያካብቱትን ሃብት ለቤተክርስቲያ አስረክበው የሰማዩን ሃብት እንዲያካብቱ ማድረግ፣
5ኛ አባቶች የመኮብለያ ዜግነት ሳይሆን ሃዋርያዊ የሆነ የዓለም ዜግንትን እንዲያገኙ ማድረግ፣
6ኛ ቤተክርስቲያን በአንድ ፓትርያርክ በአንድ ጊዜ እንድትመራ ማድረግ፤ ቢቻል ደግሞ “ፓትርያርክ በሕይወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ አይሶምም የሚለውን ቀኖና በማሻሻል፤ አንድ ፓትርያርክ በሞት እስካልተለየ ድረስ ለአምስት ወይም አሥር አመት ብቻ በፓትርያርክነት እንዲያገለግል መወሰን፣
7ኛ እግዚአብሔር መንገስታትን ይገዛል እንጂ መንገስት የእግዚአብሔርን መንግሥት አይገዛም። ስለዚህ የመንግስትን በቤተክርስቲያን ጣልቃ ገብነት ማስቆም፤
8ኛ የቤተክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ (ቃለ አዋዲ) በዓለም ላይ ላሉ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ባሉብት አገር ቋንቋ ተተርጉሞ ማዳረስ፤
9ኛ ቤተክርስቲያኒቱ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን እንድትችል ቀኖናዋን ማሻሻል፤
10ኛ ባለንበት ዘመን በጣም ብዙ የቤተክስቲያኗ ሴት ልጆች ቤተክርስቲያንን በጤና ጥበቃና ትምህርት ዘርፎች ለማገልገል ብቁና ፍቃደኛ ናቸው፤ ይሁን እነጂ የቤተክስቲያኗ ቀኖና ስለሚከለክላቸው ችሎታቸው በቴተክርሰቲያን ውስጥ እንደተቀመጠ ጋን ውስጥ እንደሚብራ ጧፍ ሆኗል። ስለዚህ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘውን የሴት ልጆች ተሳትፎ የበለጠ ለቤተክርቲያን ጥቅም እንዲውል ቀኖናውን ማሻሻል፤

አብ የፈጠራትን፤ ወልድ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ የሰራትን፤ መንፈስ ቅዱስ የሚጠብቃትን ቤተክርስቲያን ሰይጣን እንዳያፈርስብን አጥብቀን እንጸልይ። በሩን በጸና ፀሎት እናንኳኳ፤ እግዚአብሔርን በጸና የልብ ፀሎት እንሻው፤ እርሱም ቃሉን ጠባቂ አምላክ ነውና ይሰጠናል።

የወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የጻድቃንና ሰማዕታት ፀሎት ከእኛ አይለየን፤ አሜን።

ከብርሐኑ መልአኩ

Anonymous said...

Offffffffffffffffffffffffffffffffff who is trustworthy

Anonymous said...

this is rubish politics, totally rubish and hostorical death to this church. i do concur with the selam committee which is true reflection of the truth. let them be responsible for this historical mistake.

Anonymous said...

It is so mind boggling to have to listen this so called “Abbatoch” do they even know their responsibility I seriously question it. This is what I am saying most of the EOTC followers understand what is going on, both MK and the synod back home please don’t confuse us and try to mislead with a multiple nonsense baseless story. Just go ahead and elect your cadres and you will see what will happen to the church next. You are not going to stay in power as much as you think. It has nothing to do with religion anymore; it has to do with power and greed. Most of us who live outside of the country will never follow the synod in Ethiopia anyway, because it is a collection of thugs and cadres! Yes I said it and called it as it is. The funny thing is that we know most of these Bishops personally. Some of them should not even be a priest let alone a Bishop. Well it is what it is, there is a saying in Amharic “Asa Gimatu Ke anatu”.

Anonymous said...

እናንተ ከሀደር ቤት ቅ/ሲኖዶስ የተወከሉት አባቶች ለምንድን ነው አሁን አቋማቸውን የቀየሩት አመሪካ እያሉ በቪኦ ኤ ራዲዮ ከተናገሩት እጅግ በጣም የተለየ ነው። የእርቁ ጉዳይ ፍጻሜ ሳያገኝ በሀገር ቤት ያለው ሲኖዶስ 6ኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ የሚየደርገውን ሩጫ ተቃውመው ብጹእ አቡነ አትናቴዎስ እንደማይቀበሉት ተናግረው አልነበረም እንዴ።በዚህ አይነት በየጊዘው እርቅ እያሉ አሜሪካ የሚመላለሱት ለማስመሰል ነው እንጂ የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት አይፈልጉትም ነበር ማለት ነው።

Anonymous said...

“በዘለፋ የተሞላ፣
የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊነት የተዳፈረ፣
ሚዛናዊነትን ያልተከተለ፣
አሳሳች ትርጉም የሰጠ፣
የአደራዳሪ ወይም የአስታራቂ መርህን የጣሰ፣
የተጀመረውን የሰላም ጉዞ የሚያደናቅፍ”
እግዝኦ ነው መቸም አሁን እስቲ የትአል ዘለፋው ?የቱ ነው ድፍረቱ?የትጋ ነው ሚዛናዊነት የጎደለው?ኧረ የቱ ነው አሳሳች ትርጉም የሰጠው?የትኛውስ መርህ ነው የተጣሰው?ማን የጀመረውን የሰላም ጉዞ ማን ነው የሚያደናቅፈው?
አይይይይ የሰው ጭንቅላት ዘግናኝ ነው።
ብትታረቁ ታረቁ ካልሆነ የራሳችሁ ጉዳይ ነው ባለጉዳዮች...4

Anonymous said...

ሳታምሀኝ ብላ
ሳታምሀኝ ብላ
ሳታምሀኝ ብላ
ሳታምሀኝ

Anonymous said...

ከመግለጫዎቹ ቃላቶች ጥቂቶቹ፡
1-የቤተ ክርስቲያንን የሰላምና አንድነት በር ለመዝጋት የሚተጉ ጥቂት ሊቃነ ጳጳሳት ....
2-"...ወደ ከፋ የችግር አዘቅት ውስጥ ለማስገባት ሲታገሉ ማየት"
3-"የሊቃነ ጳጳሳቱንም የአመራር ብቃትና የቅዱስ ሲኖዶስን አርቆ አሳቢነትም ጥያቄ ውስጥ አስገብቶታል።"

በተደጋጋሚ ሃሳቤን ለመሰንዘር እንደሞከርኩት፤ የሰላምና አንድነት ጉባኤው መስመር መሳት የጀመረው ጋና ከአምሰራረቱ ነው።
የእነ አቡነ አብራሃምን አባትነት አጣጥሎ፤ የእነ አቡነ ጳውሎስን 'ሰፈርተኝነት' ደጀን አድርጎና እነ አቡነ ፋኑኤልን እስከ አቡነ ጳውሎስ እረፍት(ነፍስ ይማር)ድረስ'አስተናጋጅ' ... አድርጎ የተነሳና ከቀደሙት መግለጫዎች ጀምሮ እዚህ ዳላስ የተደረገው ትርኢት የቅርቡ ትውስታችን ነው።
በኮሚቴው አባላት ላይ ምንም አይነት ግላዊ ጥላቻ የሌለኝ ከመሆኑ፤ ነገር ግን ለዚህ ትልቅና የተቀደሰ ዓላማ ግን የብዙዎቹን ብቃትና በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ልበ-እምነት በተልቅ ?????

ብዙዎች አ..ይ ..ገ..ባ..ቸ..ው..ም !!

ከዳላስ መዕመን

Anonymous said...

በማወቅም ሆነ ባለ ማወቅ፤ የሰላምና አንድነት ጎባኤ አባል ምናልባትም ሰብሳቢ ይመስሉኛል፤ ሊቀ ካህናት ኃይለስላሴ ከጥቂት ቀናት በፊት በቤተ ክርስቲያናቸው ስም የአቋም መቅለጫ ማውጣትስ ምን ይባላል?
ፈረንጅ conflict of interest እንደሚለው
የዴንቨሩን መግለጫ ደግመን እናንብበው።

Unknown said...

kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk that ia all I can say kkkkkkkkkkkk

Anonymous said...

ምድራዊ ኑሮን ንቀው ሕይወታቸውን በሙሉ እግዚአብሔርን በንጽሕና ለማገልገል፣ ቃሉን አክብረው ለዓለም ለመስበክ፣ መንጋውን በፍቅርና በሰላም ለመጠበቅ ቃል ኪዳን በገቡና መሥዋዕት ለመክፈል በተሰለፉ አባቶች መካከል እርስ በእርስ መወጋገዝና ሃያ ዓመት ሙሉ ቂም በቀል መያዝ ሊኖር ባልተገባ ነበር። ሰይጣን ገብቶና የሰው ልጅ ምድራዊ ባሕርይ አሸንፎ ስህተት ቢፈጸምም እንኳ በተለይ ለብፁአን አባቶች ከልዑል እግዚአብሔር በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት ይቅር ለእግዚአብሔር ለመባባልና ፍቅርን፣ ሰላምንና አንድነትን መልሶ ለመግንባት አስታራቂ ባላስፈለገ ነበር!
አሁንም ቢሆን አስታራቂዎች የፈጸሙት ስሕተት ቢኖርም እንኳ በእነርሱ ምክንያት በሩ ተቆልፎ ጉዳዩ ከእጅ ከመውጣቱ በፊት ወደ ዋናው ቁም ነገር ወደ ዕርቀ ሰላሙ ፈጥኖ መመለስ ትክክለኛው የእግዚአብሔር መንገድ ነው። ለዚህም የአስታራቂዎቹ ይቅርታ መጠየቅ በእርግጥ የሚያረካ ከሆነ ከሁሉም ቀላሉ እርሱ ነው። ከባዱና አንገብጋቢው ጉዳይ በብፁዓን አባቶች መካከል ከአሁን በኋላ ተወጋዞ መኖርና የቤተ ክርስቲያኒቱ መከፋፈል ነው።
ስለዚህ ብፁዓን አባቶቻችን በመካከላችሁ ያለውን ውግዘት አንስታችሁና ቀኑ ሳይጨልም ዕርቀ ሰላምን በአስቸኳይ መሥርታችሁ የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት መልሳችሁ እንድታንጹልንና የተበታተነውን መንጋችሁን በመሰብሰብ ከተኩላ እንድታድኑ ሥልጣኑን በሰጣችሁ በልዑል እግዚአብሔር ፊት ተንበርክከን እንማጸናችኋለን።
ለብፁዓን አባቶች ቅርበት ያላችሁ ካህናትና ምእመናን እንዲሁም የሚዲያ አውታሮች ሁሉ ይህንን ተማጽኖ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ሁሉ በአስቸኳይ እንድታደርሱልን አደራ እንላለን፡፡

Anonymous said...

አሁንም እባክዎ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ስለዋጃት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን፤ስለእማቤታችን፤ የቤተክርስቲያናችንን አንድነትና ሰላም ስለሚፈልጉ ሲሉ፤ የክርስቶስንና የሐዋርያትን አርአያነት ቅዱስነትዎ በሚጋባ ስለሚያውቁት ድምጾትንና ቡራኬዎን የሚፈልግ ብዙ ነው። ለቤተክርስትያናችን አንድነት ማጣት ሁላችን ክርስቲያኖች በቀጥታም ሆነ ወይም ...... ከተጠያቂነት አናመልጥም፤ በተለይም አባቶች፣ ሊቃውንት፣ .... በተለይም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በፓትርያርክነቶ አብዛኛው መፍትሄ በእጅዎ እንዳለ ፈጣሪያችንና የእርስዎ ልቦና ያውቁታል። ከሁሉም ባላይ አር አያነት ከርስዎ በእጅጉ ይጣበቃል። አምላክ ሁላችንንም ይታረቀን። አሜን!

Anonymous said...

እውነት ለመናገር የሰላምና አንድነት ጉባኤ ስሕተት አይታየኝም፤ ስህተት የሚሆነው የሚያውቀውን አፍኖ ይዞ ሰላሙ ሳይሳካ ቢቀር በው። እኔ ባለኝ መረጃ ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ ከኢትዮጵያ ኢምባሲ ሂደው ምክር ተቀብለብለው፤ ከሳቸው ጋር የመጡ ጳጳሳትንም ባለወቁት መነገድ ወደ ኢምባሲ እንዲዘሩ በመድረግ ለሰላሙ ማፋረሻ ሌላ ምክንያት ባለመገኘቱ በዚህ መንገድ በሩን ለመዝጋት የተነደፈ እቅድ ነው አሉ። አባቶች ባወጡት የጋራ መግለጫ ምክንያት ከኢትዮጵያ በኩል ወቀሳ ስላጋጠማቸው መውጫ ቀዳዳ ይፈለጉት በሰላም ጉባኤው መግለጫ በኩል ነው እየተባለ ነው። እንደኔ እንደኔ ለሰላም ጉባኤው አባላት ጠቃሚ መረጃዎችን በመለገስ ማገዝ የሚጠበቅብን ይመስለኛል።
እመቤታችን ትርዳን፤

Anonymous said...

ጎበዝ አንዘነጋ ለሰላሙ ቅድሚያ እንዲሰጥ አሁንም ደጀ ሰላም የማስተባባር ጥረቷን ልገፋበት ይገባል። ልዑካኑ በጋራ መግለጫቸው ያወደሱትን ጉባኤ ለምን መውቀስ ጀመሩ፤ ካጠፉስ ለምን እንደ አባት ጠርተው አልወቀሷቸውም። «አያ ጅቦ» የተባለው ይመስላል፤ ሰላሙ እንዲሰምር ከታሰበ ንቡረ እድ ኤልያስ በስራዋጽ ገብተው እንዲመጡ መደረግ አልነበረበትም፤ የሰላም ጉባኤውም ካለፈው መማር ነበረበት ይመስለኛል፤አሁንም ድምጻችንን ማሰማት አለብን፤ ችግሩ የሁላችን ነው የሰላም ጉባኤው ብቻ አይደለም፤ የተጀመረው «እኔም ለቤተ ክርስቲያኔ ያገባኛል» የሚለው ጥረትቢቀጥል ነው የሚጠቅመን።
ደጀሰላሞች በርቱ!

Anonymous said...

ወገኖቼ አንድ ሁነን ድምጻችንን ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም እናሰማ፣ እንዘን እንጸልይ፤ ድምጻችንን እናሰማ፤ የሰላም ኮሚቴዎችንም አይዟችሁ በርቱ ልንላቸው ይገባል፤ ይህን ያክል ሸክም ተሸክመው ይህ ቢከሰት አያስደንቅም፤ የሚያስደንቀኝስ ልዑካኑ እንደዚህ ያለ የመረረ ቃል በሚላላኩአቸውና በሚያውቋቸው ልጆቻቸው ላይ መናገራቸው ነው።
እግዚአብሔር እረኛ ይስጠን።

Anonymous said...

አቡነ መርቆሬዎስ እና ሌሎቹም አገራችን ቤተ ክርስቲያናችን
ያባረሩን አሁን የሉም ሞተዋል ስለዚህ ተመልሰን መጥተናል ብለው አገር ቢገቡ
ያዲስ አባው ጳጳሳት ኢሀደግን እሰሩልን ሊሉ ነው
ያን ጊዜ ክርስቲያኑ በነቂስ ወጥቶ
እነሱኑ እናንተ ውጡል ከናንተ መሃል የመንፈስ ቅዱስ ተገዢዎች ለሆኑ እንታዘዛለን ቢል ወዴት ያሄዳሉ

Anonymous said...

እኔ ድሮም ብያለሁ አይሆንም አስታራቂ ተብዬዎቹ
በኃይማኖታዊ ማንነታቸው ሲፈተሽ ለምሣሌ አንዱን ላንሳ ልኡለ ቃል እንዴት ለአስታራቂነት ተመረጠ እሱ ማነው የሚለውን ቢያንስ ከሀገርቤት የተወከሉት አስታራቂዎች እንዴት ዝም አሉ 1 በጣም ያሳዝናል

Anonymous said...

አዬዬዬ!!
ይህችማ የወያኔ ስራ ናት ፡

በውስጥ ባሉ ሰርጎ ገብ አባሎቹ አማካኝነት በአስተራቂዎቹ በኩል ሆኖ የሚያበሳጭ ደብዳቤ እንዲጻፍ ካስደረገ በኋላ ፡ በነአባ ገሪማ በኩል ዞር ብሎ በቆርጦ ቀጥል ዘዴው የመግለጫውን መንፈስ ገልብተው እንዲመለከቱ ካደረገና “ምን ቢንቁን ነው?...” እንዲሉና ይህን ደብዳቤ አዘጋጅቶ እንዲፈርሙ በማስደረግ ነገሩን ለማስቆም የፈነቀላት አንዲት ድንጋይ ናት ።
እባካችሁ አስታራቂዎች “እሺ ተሳስተናል” በሉና ነገሩን አብርዱት

Anonymous said...

6ኛ የፓትሪያሪክ ምርጫ????ያማቸዋል??? የኢትዮጵያ አምላክ ከኛ ጋር ነው ከፋፍሎ መግዛት ተለምዷል

Anonymous said...

የጥናትና ምርምር ማእከሉ ያዘጋጀው የጥናት ጉባኤ ተራዘመ
ታኅሣሥ 17 ቀን 2005 ዓ.ም.


በማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ማእከል ታኅሣሥ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የፓትርያርክ ምርጫና የአባቶች እርቀ ሰላም” በሚል መሪ ቃል አዘጋጅቶት የነበረው የጥናት ጉባኤ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ ሲሆን የሚካሄድበትን ጊዜ ወደፊት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Anonymous said...

“የቤተ ክርስቲያንን የሰላምና አንድነት በር ለመዝጋት የሚተጉ ጥቂት ሊቃነ ጳጳሳት ....”እውነት
"...ወደ ከፋ የችግር አዘቅት ውስጥ ለማስገባት ሲታገሉ ማየት"ይህችን ቤተክርስቲያን ወደዱም ጠሉም አንድ የማድረግ ሀላፊነቱ ያለው ከነሱ ላይ ነው ይህ ካልሆነ ወደ ከፋ የችግርና አዘቅት ውስጥ ለማስገባት እየታገሉ ነው ማለት ነው ።
"የሊቃነ ጳጳሳቱንም የአመራር ብቃትና የቅዱስ ሲኖዶስን አርቆ አሳቢነትም ጥያቄ ውስጥ አስገብቶታል።" አዎ የሰላምና የአንድነት ጉባኤው እውነቱን መናገር ስላለባቸው ። የሚደክሙትም ቤተ ክርስቲያኗ የሊቃነ ጳጳሳቱ ብቻ ስላልሆነች የነሱም ስለሆነች ነው ። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በምእመናን ባለቤትነት በጳጳሳት መሪነት የተመሰረተች እንጂ የግል ንብረት አይደለችም ስለሆነች የኛም የወደፊት እርምጃ የማያባራና የማይጠፋ እሳት ነው ። ዘመኑም ሰማእትነትን ይጠይቃልና ቤተክርስቲያናችንም ሀገራችንም የምታሳዝን ካደረጔት ሚጠይቅ ነውና!!!!


እባካችሁ አንድ

Anonymous said...

Thank you deje selam for sharing us the information.
I found it dissapointing to all tewahido christians to hear the "papasat" blaming the peace comitte. First of all , they are not ready to negotiate .
We all know they re gonna appoint the 6th pathriaric
No matter what.

Anonymous said...

ሃይማኖታችንን ራሳችን ካላስከበርነው ከወያኔ ምንም አንጠብቅም - ሌላ ምርጫም የለንም

ይድረስ ለማኅበረ ቅዱሳን፣ ለሰንበት ት/ቤቶች፣ ሌሎች እውነተኛ የተዋህዶ ማኅበራትና ለሰበካ ጉባኤያት!

"ከፓትርያርቅ ምርጫ - ዕርቅ እና ሰላም ይቅደም!" የሚለውን ጥሪ ተቀብለን፣ በየቤተክርስቲያናችን ተገኝተን ድምፃችንን ለማሰማት በተላለፈልን ጥሪ መሠረት እኛ ብንገኝም፤ ማን እንደሚጀምር እና እንዴት እንደምንጀምር ግራ ገብቶን ዝም ብለን ተመልሰናል።

ስለዚህ በተጠናከረ እና በተደራጀ መልክ መንፈሳዊ ጥያቄያችንን ለማቅረብ እንድንችል እናንተ የመሪነቱን ሚና መጫወት ይጠበቅባችኋል።

በአውደዓመት ከበሮ ይዞ መድመቅ ብቻ ሳይሆን እንደ እነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ እንደ ቅድስት አርሴማ፣ ለእምነታችን የምንጋደልበትና የእምነታችንን ጽናት የምናስመሰክርበት ወርቃማ ጊዜ አሁን ነው! ለዚህ መስዋዕትነት መብቃት ደግሞ ታላቅ መመረጥ ነው።


ጥያቄ "6ኛ"ውን ፓትርያርክ ለመምረጥ ለምትታገሉት የወያኔ አፈቀላጤ ጳጳሳትና ግብረ አበሮቻቸው!

በቅድሚያ ስለ ድፍረቴ ይቅርታ እየጠየኩ የሚከተለውን ጥያቄ እንድታብራሩልኝ እማፀናለሁ።

"5ኛ" ፓትርያር ሾመን ስናበቃ ቀጥለን "6ኛ" እንመርጣለን እንጅ፤ እንደገና እንዴት ወደ ኋላ ወደ "4ኛ" እንመለሳለን?" በማለት ያነሳችሁት ሃሳብ የጫረብኝ ጥያቄ ነው።

"ሃጢያት የሠራ - ንስሃ ከገባ ሃጢያቱ ይሠረይለታል" በማለት ቤተክርስቲያን ስታስተምረን ቆይታለች። ወደ ፊት ንስሃም አያስፈልግም ካልተባልን።

ታዲያ በትክክለኛው መንገድ ለመጓዝ፣ ከተጣመመው መንገድ ወጥቶ ወደ ኋላ ወደ መልካሙ መንገድ ተመልሶ ቀናውን መንገድ መያዝ ካልተቻለ፣ እንዴት ንስሃ መግባትስ ወደ ኋላ ተመልሶ ሃጢያትን ያስተሰርያል?

Unknown said...

የድሮ ሥላሴ ቅኔ ፤ ኦርቶዶክሳውያን ከመ ነሀሉ ቤተ ክርስቲያን ሐመት ሕማመ ወላዲት እም ፥ እስከ ፍፃሜሃ ለሠላስ ዓም፥ በዕለተ ልደታ ዐባይ ባሕቱ ላዕለ ዘክሮታ ሰላም ፥ ለእግዝእተ ኩልነ ማርያም ፥ ውፁአ ኮነ እምተስፋ ዓለም፥ ዘአምጽአ ለዛቲ ሕማም፡

Hailu said...

I am ashamed to call these kind of people "Bitsuan Papasat".

Why would they need excuses to continue with the effort to bring peace and unity in our church? How could they forget that their only and prime duty is to keep the church and its followers in peace and unity?

They sounded to me like a spoiled kid. It is absurd that they want excuse from the Committee whose only crime is to remind the synod in Addis to refrain from actions that will hinder the Peace and Reconciliation process.

I am tired of these so called Papasat. I will never accept whatever they would call 6th something .

Let them assign their cadre, and I shall have clarity to accept the 4th Patriarch His Holiness Merkorios as the legitimate leader of the EOTC.

I do think all of us in the Diaspora, who are disappointed by this childish behavior of some bishops in Addis, should rally behind Patriarch Merkorios more than ever. We shall not be subject to these unorthodox bishops and what comes out of their assembly.

Ameha said...

ያሳዝናል፤ ላለመታረቅ ሰንካላ ምክንያቶችን መደርደር። በአሪዞናው ስብሰባ ማብቂያ ላይ የዕርቀ-ሠላሙ ሂደት እንዳይደፈርስ ሁለቱም ወገኖች በግል ምንም ዓይነት መግለጫ እንዳያወጡ ተስማምተው የነበረ ቢሆንም፣ ከስብሰባው በኋላ በቨርጂንያ ግዛት አንድ ቤተ ክርስትያን ውስጥ (ለጊዜው ቦታውን በውል ባላስታውሰውም፣ ወይ ቅ/ት ሥላሴ ወይም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን ሊሆን ይችላል) አቡነ ገሪማ ስለ አቡነ መርቆርዮስ እንዴትና በምን ሁኔታ አገር ለቀው ሊወጡ እንደቻሉ ሆን ብለው ማብራሪያ ሲሰጡ አደመጥን። ያን ጊዜ ዕርቀ-ሠላሙ አደጋ ላይ እንደወደቀ ልቦናችን አወቀው። በዚህም ሳቢያ ሌላኛው ወገን፣ ከኢ/ያ የመጣው ቡድን ውል ማፍረሱን በማስረዳት በዕርቀ-ሠላሙ እንደማይቀጥል አስታወቀ። ለዚህ ስህተታቸው አቡነ ገሪማ እሰከ ዛሬ ይቅርታ አልጠየቁም።

ከዳላሱ ስበሰባ በኋላ፣ ኢ/ያ ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ "አባቶች" አስመራጭ ኮሚቴ ማቋቋማቸው ተሰማ። በዚህም ምክንያት የሰላምና አንድነት ጉባዔው በችኮላ መግለጫ አወጣ። መግለጫው መውጣቱንም ሆነ አዲስ አበባ አስመራጭ ኮሚቴ መቋቋሙን እነ አቡነ ገሪማ ታህሳስ 12/2005 ያውቁ ነበር። ስለማወቃቸውም በዚሁ ዕለት በዲሲ ቅ/ት ማርያም ቤተ ክርስትያን ተሰብስቦ ይጠብቃቸው ለነበረው ሕዝብ በተድበሰበሰ ሁኔታ ገልጸዋል። ለዚህም እኔ ራሴ ምስክር ነኝ። ይህ እየታወቀ ታድያ፣ በዕለቱ ስለ ዕርቀ-ሠላሙ ከመቀመጫው ተነስቶ ሲለምናቸው ለነበረው ሕዝበ-ክርስትያን አላስፈላጊ የተስፋ ቃል መናገርን ምን አመጣው? ታህሳስ 14/2005 በዚችው ቤተ ክርስትያን ውስጥ የሚገኙት የሰንበት ተማሪዎች የመሸኛ እራት በጋበዟቸው ወቅት ምነው ቅሬታቸውን አላሰሙ? አንዳንድ የጉባዔው አባላትስ የከረሙት አብረዋቸው አልነበር? ለነገሩማ ታህሳስ 12 ምሽት ጉባዔ ላይ ሊራገሙ ወደ ቤተ ክርስትያኗ እንደሚመጡ አስቀድሞ መረጃ የደረሰን ቢሆንም፣ ቀሲስ አቡኑ ባልተጠበቀ ሁኔታ መዘውሩን አሽከርክሮ ስለ ሕዝቡ ጥያቄ መልስ እንዲሰጡ ስላስገደዳቸው ያሰቡት ሳይሳካ ቀርቷል። በዛን ምሽት ባስተማሩት ትምህርት ወይም በሰጡት አስተያየት ከመንግሥት አካባቢ ሳይጎሸሙ የቀሩም አይመስለኝም።

በመሠረቱ፣ የሰላምና አንድነት ጉባዔው አባላት ወገነተኝነታቸው ለአንዲት ቤተ ክርስትያን እንጂ ከመግለጫው መረዳት እንደተቻለው ለውጪው ሲኖዶስ አይደለም። እንዲያውም አብዛኞቹ የውጪውን ሲኖዶስ የሚቀበሉ አይደሉም። የሰላምና የአንድነት ጉባዔው አባላት የማስታረቅ ብቃት እንደሌላቸው የታወቀው ዛሬ ነው? በነሱ አደራዳሪነት መሰለኝ እስከ ዛሬ ሲሰባሰቡ የቆዩት። ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ ዕርቀ-ሠላሙ የሚደናቀፍበት መንገድ ሲፈለግ የሰላምና አንድነት ጉባዔው ጎል ገባ። ድሮም ለይስሙላ ነበር የሚመላለሱት። የመግለጫው መውጣት የሠላም ሂደቱን ሊያደናቅፈው አይገባም። ምክንያቱም ውሉን የሚታረቁት ወገኖች አላፈረሱትምና። በመሠረቱ መልካም ፈቃድ ቢኖራቸው ኖሮ፣ ከነሱ በላይ ሽማግሌ የለምና፣ እርስ በርሳቸው በታረቁ ነበር እንጂ ከቁልቁል ሽቅብ የሚሄድ አስታራቂ ባላስፈለገ ነበር።

እንደ ክርስትያናዊ ዕምነቴ፣ ይህ ክስተት እንዲፈጠር እግዚአብሔር ፈቅዶ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ። ጉዳዩ አሳዛኝ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ሊሠራው ያሰበው ነገር ሊኖር እንደሚችል እገምታለሁ። መዝ. 81(82) ላይ የተገለጸው የእግዚአብሔር ቃል መፈጸሚያው ጊዜ የደረሰ ይመስለኛል። ለዚህች ቤተ ክርስትያን መከፋፈል ሁለቱም ወገኖች ከመጀመሪያው አንስቶ ተጠያቂዎች ናቸው። አንደኛው ወገን አቡነ መርቆርዮስን ገልብጦ ሥልጣን ለመያዝ በመጣደፉ (ታምራት ላይኔ “እሳቸውን አንፈልጋቸውም” ባለበት ወቅት የተከራከረ አልነበረም። በወቅቱ እርሱ ቢሮ ተጠርተው ትዕዛዝ የተሰጣቸው አባቶች አሁንም በሕይወት አሉ፤ አቡነ ገሪማን ጨምሮ)፣ ሌላኛው ወገን ደግሞ ቤተ ክርስትያኗን እና ሕዝበ-ክርስትያኑን ጥሎ ከአገር በመውጣቱ። ያም ሆነ ይህ፣ እኔ እንደ አቡነ ጴጥሮስ “ይግባኝ ለክርስቶስ” ብያለሁ።

Anonymous said...

እኔ እምለው እነዚህ ሰዎች እሚያመልኩት አምላክ፥ ሰላም፡ይቅር መባባልን፡ራስን ዝቅ ማድረግን፡ለእውነት መኖርን፡ለእርቅ ለአንድነት ለሰላም ማድላትን፡ለመንጋው እንጅ ለራስ አለመኖርን ካስተማረው እኔ ከማምልከው ጌታ ጋር አንድ ናችዉ? እንዳት አንድ ሊሆኑ ይችላሉ? በእዉኑ አለም መምበሩ ሆና አህያን በመምረጥ ራሱን ዝቅ ያደረገዉን ጌታን ያመልካሉ ?

እነዚህ ሰዎች አሁን አስታራቂዎች ምን አደረጉና ነው ይቅርታ ይጠይቁን የሚሉት ፧ እንዳት እነዚህ ሰዎች የሰቁሉትን የገረፉትን ይቅር በላችው ብሎ ራሱን አሳልፎ የሰጠውን ጊታን ያምናሉ ለማለት ያስችላል

አብዝቶ ዝም ያለው እግዚአብሔር ምን ያመጣ ይሆን ?

Anonymous said...

አቡነ መርቆሬዎስ ኧረ አንድ ይበሉ።
አልያማ በዝምታ የሚፈታ ነገር የለም። ኢትዮጲያ ያሉት አባቶችም 6ኛውን ጳትሪያርክ የመምረጥ መብታቸው ብቻ ሳይሆን ላወጡት ህግም ተገዢ መሆን አለባቸው። "ጳትሪያርክ ሳይሞት"... ለነበረው ሁኔታ ሁሉም የራሱ ግንዛቤ ያለው ሲሆን ማስፈራሪያ ሆኖ መድረስ ግን የለበትም።
ምነው አቡነ መልከጼዲቅ አቡነ ጳውሎስን ሲያስመርጡ የአስመራጭ ኮሚቴ አባል አልነበሩምን?

Maru said...

Sad day. I was optimistic to hear something good. I don't expect such type of reason from 'Papasat'. My understanding is that 'Papasat' are the pillars to keep the unity of our church even to death, no matter what happens.Really frustrating to see and hear such things from our pillars. Upset, worrisome, frustration in our heart.
Egziabiher ethiopian ena lejochuan Beyekertah Gobgnat.

Wondwossen Kidanemariam said...

As christian how in the world you turn your back from peace? The last twenty years there was no peace in our church, it seems we can not have peace in the near future either, this is not a good news those refused peace and unity.
If you belive that GOD is the one who put you in that position you better committ to it.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)