December 2, 2012

በጀርመን የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካህናት “ግልጽ ደብዳቤ” አወጡ

(ደጀ ሰላም ኅዳር 23/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 1/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በጀርመን አገር ኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን ኃላፊ የሆኑት ሊቀ ካህናት / መርዓዊ ተበጀ “  ስለ  ነገዋ ቤተ ክርስቲያን ስንል ዕድሉ ዛሬ ባያመልጠንስ? “   ሲሉ “  ግልጽ ደብዳቤ”   አወጡ። የእናት ቤተ ክርስቲያን መካፋፈል የራስ ምታት፧ የሆድ ቁርጠት፧ የልብ ሕመም ወዘተ ሆኖ 21 ዓመታት  “   እኽ እኽ››  እያሰኘ መኖሩ በውስጡ ላለፈበት ትውልድ ሁሉ ግልጽ”   መሆኑን የጠቀሱት ሊቀ ካህናቱ እርሳቸውም የበኩላቸውን ሐሳብ ለመስጠት እንደፈለጉ ጠቅሰዋል። ይህንን ደብዳቤ አሁን መጻፍ የፈለጉት ጊዜው “የተመቸ” ነው በሚል ወይም በርሳቸው አገላለጽ ሲመች በእጅ፣ ሲፈጅ በማንካ ለማለት ሳይሆን ከዚህ አስቀድሞ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከመሾማቸው አስቀድሞም ተመሳሳይ ሐሳብ ማቅረባቸውን ማስረጃ ጠቅሰው አብራርተዋል።

ደጀ ሰላም ይህ መሠረታዊ ጽሑፍ ለአንባብያን ቢደርስ ያለውን ጥቅም በመረዳት፣ እንዲሁም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ይህንን አስተያየት ከግምት እንደሚያስገቡት በማመን አቅርበነዋል። መልካም ንባብ።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡ግልጽ ደብዳቤ
ስለ  ነገዋ ቤተ ክርስቲያን ስንል ዕድሉ ዛሬ ባያመልጠንስ?
በዚህ ርእስ ለመጻፍ ስነሣሣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ደሙ ስለ መሠረታት፣ እስክ ኅልፈተ ዓለም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስለ ሚመራት፧ ከሁሉም በላይ ስለ ሆነች፧ ሐዋርያት ስለ ሰበሰቧት፧ ስለ አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትንሽ መናገር ፈልጌ ነው። አንዲት የሚለው አሐዳዊ ቅጽል ሦስት መቶ አሥራስምንት (318) ሊቃውንት እንደወሰኑት ዓለም አቀፋዊነቱን እንደያዘ ሆኖ ስለ እኛዋም ቤተ ክርስቲያን  “   አሐቲ» አንዲት የሚለው ቅጽል ከሀገርና ከሃይማኖት አንጻር ይስማማታል። ስለዚህም ነው አንዲት እናት ቤተ ክርስቲያን የምንለው።

ለብዙዎቻችን የእናት ቤተ ክርስቲያን መካፋፈል የራስ ምታት፧ የሆድ ቁርጠት፧ የልብ ሕመም ወዘተ ሆኖ 21 ዓመታት  “   እኽ እኽ››  እያሰኘ መኖሩ በውስጡ ላለፈበት ትውልድ ሁሉ ግልጽ ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊ ያውም ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ፧ በሁለቱ ወገን ተከፋፍሎ  የአለ ሁሉ  “   ይህ ባይሆን ኑሮ» በማለት ሀሳቡን ያልገለጸና የማይገልጽ አለ ማለት አይቻልም።

“   ቀን ሲደርስ አምባ ይፈርስ» እንደሚባለው ሆነና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አርፈው፧ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሕይወተ ሥጋ በመኖራቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዴት ይምምጣ በሚለው ቃለ መጠይቅ ዙሪያ በመገናኛ አውታሮችም ሆነ ወይም በግል የመነጋገር ርእሰ ጉዳይ ከሆነ አራተኛ ወሩን በማስቆጠር ላይ ይገኛል። በሕዝብ የመገናኛ አውታሮች በተለይም በጀርመንና በአሜሪካ ራዲዮ ጣቢያዎች ቃለ መጠይቅ የቀረበላችው አባቶችና ወንድሞች የሚናገሩት አስታያየት በከፊል የመለያያ ነጥብ በማንሳት ሀቁን ለመጠቆም ሲፈልጉ፥ የተወሰኑት ደግሞ ሀቁን በመተው ጊዜውን ብቻ ለመዋጀት የሚፈልጉ ሆኖ ተገኝቷል።

ከዚህ ላይ አንተ ከማን ወገን ሁነህ ነው? እንዲህ የምትጽፍ የምትሉኝ ከሆነ፧  ችግሩ እንደተከሠተ ገና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሳይሾሙሳይቃጠል በቅጠል እንደሚባለው በአውሮፓ ደረጃ   ከጥቅምት 13-16.1984/23-26,10.1991/ በኮለኝ ከተማ ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን ተካሂዶ ስድስት ዐበይት ውሳኔዎችን ሲያስተላልፍ በሁለተኛ ተራ ቁጥርየብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጉዳይ ኖዶሳችን ብቻ ፍትሕ ርትዕ በተመላበት ሆኔታ ታይቶ በመጀመሪያ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማንያን፥ ቀጥሎም ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት /ቤት ማኅበር እንዲገለጽ የሚል ውሳኔ በጊዜው ረዳት ፓትርያርክ ለነበሩት ለብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስና ለቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት እንዲደርስ ሲያደርግበሕመም ምክንያት የተባለውን ግን በቂ ምክንያት ነው ብሎ አልተቀበለውም። 

ሰሚ ጠፍቶ በኃያላኑ ጣልቃ ገብነት  ሹመቱ እንደተፈጸመ 1985/1992 . ላይ ስህተት ሲደጋገም በሚል ርእስ በሰባት ገጽ የተጠቃለለ ከቅዱሳትና ከቀኖና መጻሕፍት ማስረጃዎችን በማጣቀስ የጻፍኩበትና በግልጽ ተቃውሞ ያሰማሁበት ስለሆነ ነው እንጂሲመች በእጅ፣ ሲፈጅ በማንካ እንደሚባለው አይደለም። ብዙዎች በፍርሃት ይሁን ወይም በይሉኝታ መንፈስ በተሸበቡበት ዘመን   ይህ የቀኖና ድንጋጌ እስከ ተሻረ ድረስ የሚከፈለው መሥዋዕት ቀላል እንዳልሆነና አንድ እልባት ሊደረግለት እንደሚገባ አበክሬ ተማኅጽኖ አቅርቤአለሁ። ጽሑፉ በጊዜው ጊዜ ብዙ የተባለለት ከመሆኑም ባሻገር፧ በኢትዮጵያ የመጻፍና የመናገር ዕድል እንዳሁኑ ሳያከስም የተለያዩ የግል መጽሔቶና ጋዜጦች አንዱ ካንዱ እየተቀባበሉ አውጥተውት ነበር። ሰሚ ግን አልተገኘም።

አሁን እንዲህ በአለ ጽሑፍ ላይ እንዳለፈው ስለ ነገረ ፓትርያርክ ምዕራፍ ከምዕራፍ፧ አንቀጽ ከአንቀጽ እያጣቀሱ ማስረጃ ለማቅረብ መሞከሩ የአንባቢን ጊዜ መሻማት መሆኑን በመገንዘብ፧ ሁሉን መዘርዘር ባያስፈልግም ፓትርያርክ እያለ ፓትርያርክ አይሾምም የሚለው ዐቢይ መሠረታዊ አንቀጽ ግን እንዲህ ይነበባል። ይህች ሹመት (ፓትርያርክነት) በአንድ ዘመን በአንድ ሀገር ለሁለት ሰዎች ልትሆን አይገባም። ይህ በአንድ ሀገር ከተደረገ ግን አስቀድሞ ለተሾመው ትጽና። ካለ በኋላ ስለታመመ ፓትርያርክ ሲናገር ግንአእምሮውን ያጣ እንኳን ቢሆን ይድናል ብለው ተስፋ የሚያደርጉ ከሆነ ይጠብቁት። ይድናል ብለው ተስፋ ባያደርጉ ግን፧ የታመመበት ዘመን በጣም ጥቂት ቢሆን ከሹመት አይሻሩት። ከመዳን ቢዘገይ ግን ይሻሩት። ... (ፍትሐ ነገሥት ፍትሕ መንፈሳዊ ዐቢይ  አንቀጽ 4 ንኡስ ቁጥር 70-78)

ቀኖናው በዚህ መልኩ ተቀምጦ ሳለ፣ ሀቁን ይዞ ችግሩን  በጋራ ውይይት መፍታት እስካልተቻለ ድረስ መልአክ ከሰማይ እስከ ሚመጣ ድረስ መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም። ከአኃት እብያተ ክርስቲያናት የሚበጀውን ልምድ መውሰድ፧ በጋራም ከስምምነት ላይ መድረስ  ነው። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ መዘጋጀት ለማገገም የቀረበውን ስብራት እንደገና ሰባብሮ ለመጣል ከመጣደፍ የተለየ አይሆንም። ያለው ልዩነት በስምምነት ሳይፈታ፥ አጉራ ዘለሎች በሦስትኛና በአራተኛ ረድፍ በቆሙበት ሰዓት ሌላ ፓትርያርክ ከተሾመ እምቀዳሚቱ የሀኪ ደኃሪቱ ነውና ከቀደመው የባስ ይመጣል ብሎ መናገሩ ነቢይ የሚያሰኝ አይደለም።  እንግዲያውስ  ጌታ የሚለው  ኢትአብስ ዳግመ» ዳግመኛ አትበድል አይደል? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የፈጸመውን ጥፋት በጥሙና እንመልከተው።

1. በዘመነ ደርግ ከቀኖና ውጭ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ከመንበራቸው ሲወርዱ፥ ብሎም ለሞት አልፈው ሲሰጡ  ምንም ድምፅ አላሰማም።
2. በዘመነ ኢሕደግ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው ሲወርዱ ከላይኛው ስህተት አልተማረም። እንዲያውም ስሙን ለውጦ ስህተቱን የሚያስፈጽሙለት አባቶች ሲመርጥ ኮሚቴ የሚል ተራ ( የዓለም) ስም አውጥቶየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ስኖዶስ በ፭/5/ ሊቃነ ጳጳሳት ኮሚቴነት እንዲመራ ወሰነ። ብሎ መግለጫ ከሰጠ በኋላ፧ አቃቤ መንበር እንኳን ሳያስቀምጥ  የሚሆነውን ሁሉ አደረገ። ቅዱስ ሲኖዶስ የራሱን ሕግ በራሱ ሲያፈርስ እጅግ ያሳዝናል።
3. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሞተ ሥጋ ሲለዩ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ 21 ዓመታት የቆየውን ከባድ ፈተና እግዚአብሔር አምላክ ሲያቀል እንደገና ወደ ፈተና ለመግባት በሩን ከፍቶ በመጠበቅ ላይ ይገኛል። ያው ቅዱስ ቃሉ እንደሚያዘው ለሦስተኛው ስህተት ግን ዕድል ሊሰጠው አይገባም። “   ንግራ ለቤተ ክርስቲያን» ነውና ማኅበረ ምእመናንና ማኅበረ ካህናት በአንድ ላይ ሁነው እግዚኦ በእንተ አንድነት የሚሉበት ጊዜ አሁን ነው። የግለሰብ ጉዳይ ቢሆን ኖሮ እንደ ልማዳችንቢሰማህ ምከረው፣ ባይሰማህ ግን መከራ ይምከረው» ብለን እናልፈው ነበር። ይህ ግን ከምንም በላይ ነው። ጉዳቱና መዳከሙ፥ በወንዝ መከፋፈሉ እንዳለ ሆኖ ቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናዋ ተጥሶ እስከ መቼ የባዕዳን መሳለቂያና የብዕር ማሟሻ ሁና ትኖራለች።የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለልጆቻቸው የሚያስተምሩትን እነርሱ ሠርተው ካላሳዩን ማነን ልንከተል እንችላለን? አሁንም ኢትአብሱ ዳግመ ዳግመኛ አትበድሉ እንበላቸው።  አንተስ ለምን ዳርዳር ትላለህ የሚለኝ ካለ በስደት ያሉት ፓትርያርክ በዘመነ ደርግ የፈጸሙት በደል ኖሮ ከመንበረ ፐትረካናቸው የሚያሰወርድ በደል ከተገኘባቸው እንደ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ  በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይታይባቸው ባይ ነኝ።    

በዚህም ሆነ በሌላእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን  አንቅደም እያልን የምናሰተምር መምህራነ ወንጌል  በሕመም ምክንያት ከዛሬ 21 ዓመት በፊት ከመንበረ ርክናቸው የወረዱት አባት በሕይወተ ሥጋ እያሉ፣ የቁጥር ዶግማ እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ አንድ ሲሆን ሦስት፣ ሦስት ሲሆን አንድ ነው ከሚለው ከምሥጢረ ሥላሴ ውጭ ሌላ የቁጥር ዶግማ ያለ ይመስል ነገሩ ስለ አራተኛውና ስለአምስተኛው ፓትርያርኮች ቅደም ተከተል ለመግለጽ ተፈልጎ ነው አራት ተብሎ አምስት እንጂ እንደገና አራት ስለማይባል ስድስተኛውን ፓትርያርክ እንመርጣለን በሚል በቁጥር ስድስት ምክንያት የተጣሰውን ቀኖና ላለመቀበል የአዲስ አበባው ቃል አቀባይ የማይሆን ምክንያት እየደረደሩልን ነው። የቅዱስ ሶኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ይህች ሹመት (ፓትርያርክነት) በአንድ ዘመን በአንድ ሀገር ለሁለት ሰዎች ልትሆን አይገባም። ይህ በአንድ ሀገር ከተደረገ ግን አስቀድሞ ለተሾመው ትጽና። የሚለውን በማናበብ እንዴት ከግንዛቤ ውስጥ እንዳላስገቡት የሚያስተዛዝብ ነው። ምን አለ! እንደ አባቶቻችንእውነትን ተናግሮ ከመሸበት ማደርየሚለውን ዘይቤ በክህነታዊ ሥራችን ብንተረጉመው።? ካላይ እንደገለጽኩት እንዲህ በጠጠር ኃይለ ቃል የምናገረው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወርደው፥ በመንግሥት ሞተር የሚንቀሳቀሰው ሲኖዶስ ገና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ከመሾሙ በፊት ስለተናገርኩት ብቻ ነው።
 

መቸም ሀቅ እንደ አሥር ቁጥር ነቁጥ ነጠላ ሠረዝና ድርብ ሠረዝ የላትምና ሀቁን መፈለጉ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የምትመራ ቤተ ክርስቲያን እንድትኖረን ብሎም በየቦታው አኩርፈው የተበታተኑትን  ሁሉ በአንድ ጥላ ሥር እንዲሰባሰቡ ያደርጋል። ያዘኑት ይጽናናሉ፧ የጠፉት ይገኛሉ። ባላገራ ሠይጣንም ለዘለዓለም ያፍራል።

ከዛሬ 21 ዓመት በፊት በበሽታ ምክንያት ከመንበራቸው የወረዱት አባት በሕይወተ ሥጋ እያሉ ሙሉ ጤነኛ ተብለው በመንበሩ የተቀመጡት አባት በሞተ ሥጋ ሲለዩ ያለሆነ ምክንያት ከማቅረብ ይልቅ ወይኩን ፈቃድከ እንደ ፈቃድህ ይሁን በሚለው አምላካዊ ትእዛዝ ተመርቶ መንበሩን ለባለ መንበሩ ማስረከብ ተገቢ ነው። በዚያውስ ላይ ማን ቀሪ አለና ነው? ከሀቅ የሚያሸሸን፧ ከዚህ ላይ የአገሬ አስለቃሽ የሙሾ ግጥም ትዝ አለኝ
                በሉ እናንተም ሂዱ እኛም ወደዚያው ነው።
                 ወትሮም መንገዳኛ ፊትና ኋላ ነው። /ከዚህ ላይ በገጠሯ ኢትዮጵያ ያለውን ቀጭን የእግር መንገድ ልብ ይሏል/
 
ወደ ተለመደው ስብከቴ ልመለስና ለማንም የማያዳላው የሞት ጽዋ ከፊታችን ተደቅኖ በሚያልፈው የማያልፈውን ፍቅር አንድነት እንዴት አናጣለንየእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ድምፅ እናዳምጥ። ከታሪክ ተወቃሽነትም እንዳን። ለአንዲቱ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ንጹሕ ኅሊና፧ ሰፊ ልቡና ይኑረን።ከመቶ ሃምሳ ዳዊት፣ አንድ የልብ ቅንነት ይሉየል አባቶች፧ ስለ  ነገዋ ቤተ ክርስቲያን ስንል ዕድሉ ዛሬ አያምልጠን እያልኩ እማጸናለሁ፣ እጮህ አለሁም።       
21 ዓመት ተሞክሮ ቀላል አይደለምና አሁንም ሕዝበ ክርስቲያኑና ማኅበረ ካህናቱ ያላወቁት የተለመደው ከባድ እጅ ካለበት ሀቁ ይነገረንና እርማችን እናውጣ። በጸሎትም እንበርታ። በሰው የማይቻለው በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላልና። እግዚኦ በእንተ አንድነት እንበል።

አባቶች እንደዚህ ያለ የጋራ መከራ ሲያጋጥማቸውየጨው ክምር ሲናድ ሞኝ ይልሳል ብልህ ያለቅሳል። ይላሉ። እንግዲህ እኛ ሁላችን ኦርቶዶክሳውያንና ኦርቶዶክሳውያት ምእመናትና ምእመናት በተለይም መንጋውን ለመጠበቅ የተሾምን ካህናትና ሊቃነ ካህናት መነኮሳትና ቆሞሳት አበወ ምኔታትና ኤጲስቆጶሳት፣ ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት  ከየትኛው ክፍል ነን? በዛሬዋ ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ሁነን ስለ ነገዋ ቤተ ክርስቲያን ምን ገዶን የምንል ከሆነ ለልጅ ልጅ የሚከፈል ዕዳ ገና አለብን።  ከዚህም እግዚአብሔር አምላክ ይሠውረን። ሴት አያቴጭንቅ አቃላይዋ የምትላት የሁላችን እመቤት ቅድሰተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን።  አሜን።

ሊቀ ካህናት / መርዓዊ ተበጀ
ጀርመን፧ ኮለኝ

ይህ ግልጽ ደብዳቤ
ለአቃቤ መንበረ ፓትርያርክ  ለብፁዕ አቡነ ናትናኤል
ለቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት
ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ /ክህነት /ቤት
ለመንበረ ፓትርያርክ  የውጭ ጉዳይ መምሪያ
ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ላልኩአቸው አካላትና ግለሰቦች እንዲሁም ለመገናኛ ክፍሎች ሁሉ ተልኳል።

15 comments:

Anonymous said...

thank you dr.merawi you did you part and i agree on your idea.

Anonymous said...

Dear Dr Merhatibebe

Most of us we agree what u wrote , it very important message. Excellent job.
I agree with u, Yes you are write Abune Melkesadik Yehaymanot Eses alebachew, The holy synod told him to come and explain about it,but he left to the USA, now he is the one make all this mess because he is the secretary of the exile fathers.
Few people knows about this reality including ESAT no idea how he left the country, they use it for the sake of their own personal benefit not for the church.

Dr Merhawi, I am very happy u mentioned about Abune Melkesadik, tanx for that. There are also others menafikan/tehadeso like Lueelekale, Kesis melaku and others they do their part the church not to go to the one UNITY, but GOD will make it. We all have to pray gfor that. MAY GOD HELP US

አንተስ ለምን ዳርዳር ትላለህ የሚለኝ ካለ በስደት ያሉት ፓትርያርክ በዘመነ ደርግ የፈጸሙት በደል ኖሮ ከመንበረ ፐትረካናቸው የሚያሰወርድ በደል ከተገኘባቸው እንደ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይታይባቸው ባይ ነኝ።

True said...

God be with you Dr Merhawi,
it is very clear message to all Ethiopian Orthodox Tewahido lijoch.
also thanks to Daniel for your resilient effort.

thank you.

Anonymous said...
This comment has been removed by a blog administrator.
Anonymous said...

ሊቀ ካህናት እግዚአብሐር ይስጥዎት። ባለፉት አራት ወራትና ከዚያም በፊት ስለ እውነትና ስለ ቤተ ክርስቲያኗ አንድነት የሚባለውን ቁም ነገር ሁሉ በግልጽ ደብዳቤዎ አጠቃልለውታል። አሁን የሚቀረው ቅንነትና ገንቢ ተግባር ብቻ ነው። በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ጫና ለማድረግ የሚያስብ ቢኖር ለራሱ ጭምር ሲል እጁን ይሰብስብ። ለሥልጣን የሚጓጉ አባቶች ቢኖሩ ሕግ ከተጣሰና ሕዝበ ክርስቲያኑ ከተከፋፈለ የማን አባቶች፣ የማን መሪዎች፣ የማን አግልጋዮች ሊሆኑ ነው? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስም እስካሁን በቤተ ክርስቲያኗና በምእመናኑ ላይ የደረሰው የሃያ አንድ ዓመት ግፍና ስቃይ ይበቃል፤ ልዑል እግዚአብሔር ፈርዷል በማለት ድምጻቸውን አጉልተው ቀኖናው እንደገና የማይጣስበትን ቸሩ አምላክ ጸሎታቸውን ሰምቶ ያመለከታቸውን ውሳኔ ለሕዝበ ክርስቲያኑ በይፋ የሚያበሥሩበት ሰዓት ደርሷል።

Anonymous said...

it is good idea

Anonymous said...

Dr Merawi yesafut debdabe tekekel bihonem sele haymanot hetsess ena hege bete kerestian mefres erasachew balubet hager eyetederege yalewun men adrgewut newu? Lelaw degmo debdabewun leman endesafut yemigels neger alayehum

hailu said...

I pray that God give us fathers like Like Kahnat Merawi.

May God give the wisdom for the fathers in Addis to put the Church's unity beyond anything else.

Now a days it is sounding to me a folk tale when I read about the sacrifice our forefathers paid to keep our faith and our country united. This is especially so when I realize the cowardice and earthly priorities that the current so called fathers have at the expense of our beloved Orthodox Tewahido Church.

What would they profit if they succeed to count "6th Patriarch" and yet leave our church divided and weakened? Tell me so called fathers, what will you benefit?

Let’s forget the bogus concern about counting numbers. Let’s go back to the righteous 4th and unite our Orthodox Tewahido at last!
God Help Us. Amen.

hailu said...

I pray that God give us fathers like Like Kahnat Merawi.

May God give the wisdom for the fathers in Addis to put the Church's unity beyond anything else.

Now a days it is sounding to me a folk tale when I read about the sacrifice our forefathers paid to keep our faith and our country united. This is especially so when I realize the cowardice and earthly priorities that the current so called fathers have at the expense of our beloved Orthodox Tewahido Church.

What would they profit if they succeed to count "6th Patriarch" and yet leave our church divided and weakened? Tell me so called fathers, what will you benefit?

Let’s forget the bogus concern about counting numbers. Let’s go back to the righteous 4th and unite our Orthodox Tewahido at last!
God Help Us. Amen.

Anonymous said...

"የቁጥር ዶግማ “እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ” አንድ ሲሆን ሦስት፣ ሦስት ሲሆን አንድ ነው ከሚለው ከምሥጢረ ሥላሴ ውጭ ሌላ የቁጥር ዶግማ ያለ ይመስል፤ ነገሩ ስለ አራተኛውና ስለአምስተኛው ፓትርያርኮች ቅደም ተከተል ለመግለጽ ተፈልጎ ነው፤ “አራት ተብሎ አምስት እንጂ እንደገና አራት ስለማይባል ስድስተኛውን ፓትርያርክ እንመርጣለን” በሚል በቁጥር ስድስት ምክንያት የተጣሰውን ቀኖና ላለመቀበል የአዲስ አበባው ቃል አቀባይ የማይሆን ምክንያት እየደረደሩልን ነው። የቅዱስ ሶኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት “ይህች ሹመት (ፓትርያርክነት) በአንድ ዘመን በአንድ ሀገር ለሁለት ሰዎች ልትሆን አይገባም። ይህ በአንድ ሀገር ከተደረገ ግን አስቀድሞ ለተሾመው ትጽና።” የሚለውን በማናበብ እንዴት ከግንዛቤ ውስጥ እንዳላስገቡት የሚያስተዛዝብ ነው። "
ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርዓዊን እግዚአብሄርእ ይስጥልን እያልኩ አምላካችን ክርስቶስ ስለ እውነት የሚመሰክር አባት በሀገራችንም ውስጥ ያስነሳልን አባቶቻችንን የመንፈስ ቅዱስ ሰይፍ ያስታጥቅልን:: መንጋውን ለመጠበቅ የተሾማችሁ ካህናትና ሊቃነ ካህናት፤ መነኮሳትና ቆሞሳት፤ አበወ ምኔታትና ኤጲስቆጶሳት፣ ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት ሁሉ መሪነታችሁ ለሰላሙ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለእንደዚህ አይነቱም ለመንፈሳዊ ጦርነትም መሆን አለበት ይህኔ ነው የእናንተ ትክክለኛ የሀይማኖታችን መሪወች እንደሆናችሁ የሚታወቀው ::
ከዚህ በፊት ምንም እንኴን ያስተላለፋችሁት ውሳኔው ተፈጻሚነት ባያገኝም ትናንት ስለ ሀውልቱ የወሰናችሁት ስርአተ ቤተክርስቲያንን የወገነ አቌም ሀውልቱ ባይፈርስም ውሳኔው ግን እንደተከበረ ይኖራል:: በመሆኑ አባቶች አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያንን እና ምእመናኖችዋን እያሰባችሁ ስለ አንድነት ቁሙ ካልቻላችሁ በገዳም ተወስናችሁ በጸሎት ቀሪ ህይወታችሁን ከአምላካችሁ ጋር ብትኖሩ ይሻላችኋል:: ጥለናት ለምንሄደው ለዝች አላፊ አላም አንወግን!!!

ጉባኤ ካህናት ወምዕመናን said...

ይበል :: እንዲህ በትክክል ሀቁን ፍርጥ አድርጎ የሚናገር ሰው ያስፈልጋል :: ቤተ ክርስቲያኒቱ ማዕከል መሆን ይኖርባታል:

http://peaceandunityforeotc.blogspot.com/2012/12/42-3-1.html

Anonymous said...

የዶክተር መረዓዊ ብሎግ ነው እንዴ?የሚያወያይ ሀሳብ በብሎጉ እስተዳደር ይሰረዛል ደጀ ሰላም ምነው?

Anonymous said...

+++
እናንተ ሀቅን ና ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም ሃሳብ ነው ወይስ ለግለሰብ የሚጠቅም የምታዩት ትክክለኞች ነን ካላችሁ የላክነውን የጀርመን ሀገር ም ዕመናንን ልብ ያደማውን ለምን አታወጡትም እሳቸውም ብሎ አስታራቂ መጀመሪያ እዚህ ያለውን ችግር ለምን አይፈቱም ነበር ???????????? እናተተስ ከ አንድ ጎን ነው እንዴ የምትመለከቱት ይገርማል ብቻ እግዚአብሔር ቀን አለው ለሁሉም እናንተ ባታወጡትም

Anonymous said...

Anonymous on December 3, 2012 7:44 AM
what do you know,that what was written needs to be erased.

Anonymous said...

ከናቡቴ
በእውነቱ ድንቅ ሀሳብ ነው።አሁን ስበሰባው የቀረው ጥቂት ቀናቶች ናቸው
እንግዲህ አባቶች በርቱና ቆራጥ ውሳኔ እንደምተደርሱ ተስፋ እናደርጋለን
ይሄ ሕዝብ እኮ ከሁለት አስርት አመት በላይ ያለመሪ ነው ያልፈው ማለት
ይቻላል እግዚአብሔር ደግሞ ትልቁን ስራ ሰርቶልናል አሁን ፍርሃት መሰበር
አለበት አርያም መሆን አለባችሁ ለኛ ለተራው ምእመናንና አባቶቻችን
እስካሁን ለአቆዩልን ቤተክርስትያናችንን ህልውና ስትሉ
እግዚአብሔር ፍርሃትን ይስበር፧፧
ቤተክርስትያናችንንም ያድን አሜንንን፨

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)