December 10, 2012

ዕርቀ ሰላሙ በሚቀጥለው ጥር ወር በሎስ አንጀለስ በድጋሚ ይካሄዳል


 (ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 1/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 10/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ከኅዳር 26 እስከ 30 (ዲሴምበር 5-9/2012) በሰሜን አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት የተደረገው ሦስተኛ ዙር የዕርቅ ድርድር ትናንት እሑድ መግለጫ በማውጣት እና ለሌላ ጉባዔ ቀነ ቀጠሮ በመስጠት ተጠናቋል። በመግባባት፣ በመከባበር እና በመደማመጥ ተደርጓል በተባለው በዚህ በአባቶች ውይይት ከቀደሙት ሁለት ጉባዔያት በተሻለ “ተስፋ ሰጪ” የአንድነት ምልክቶች የታዩበት መሆኑን ብዙዎች እየመሰከሩ ነው። ሙሉ መግለጫው በዳላስ ደ/ም/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በምዕመናን ፊት በተነበበበት ወቅት ከሁለቱ ወገን የመጡ ልዑካን ኮፒውን በእጃቸው ይዘው ታይቷል።

በዕለቱ የተነበበው መግለጫ በዋነኝነት በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ሐሳብ ሰጥቶ ያለፈ ሲሆን እኛም እንደሚከተለው ጨምቀን እኛም አቅርበነዋል።
  1. መለያየቱ ሁሉንም ወገን በእጅጉ ያሳዘነ እንደመሆኑ ቀጣይ አራተኛ ጉባዔ እንዲካሄድ፣
  2. አራተኛው ፓትርያርክ ወደ አገራቸው ስለሚመለሱበት ሁኔታ በሁለቱም ወገን የቀረቡት ሐሳቦች በሁለቱም በኩል ባሉ ምልዓተ ጉባዔዎች ታይተው ወደ ውሳኔ እንዲደረስ፣
  3. የቤተ ክርስቲያኑን ሰላምና አንድነት ለሚናፍቀውና ውጤቱንም በጉጉት ለሚጠባበቀው ሕዝባችን የሚፈለገውን ውጤት ማስገኘት እንዲቻል ሁሉም ወገን የበኩሉን በጎ ድርሻ እንዲጫወት አደራ፣
  4. የሰላሙ ጥረት ከፍጻሜ እስከሚደርስ ድረስ ሁለቱም ወገን ለሰላሙ ዕንቅፋት ሊሆን የሚችል ማንኛውንም ነገር ከመሥራት እንዲቆጠቡና ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠብቁ፣
  5. ይህንን ታላቅ የዕርቅ ሒደት ለማሳካት አላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኘውና የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን የሰላምና አንድነት ጉባዔ ማመስገን፣
  6. የሰላምና የአንድነት ጉባዔው ባቀረበው ሐሳብ መሠረት ቀጣዩና አራተኛው ጉባዔ ከጥር 16-18/2005 ዓ.ም (ጃኑ. 24-26/2012) በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ እንዲካሔድ፤ ከሰላም ጉባዔው ወደ ሁለቱም ተወያይ ወገኖች ምልዓተ ጉባዔዎች ልዑካን እንዲላኩና ስለተደረሰበት የውይይት ሁናቴ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተስማምተዋል።
  7. ይህ ጉባዔ ተጀምሮ እስኪፈጸም ድረስ በጸሎታቸው፣ በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸውና በጉልበታቸው የተባበሩትን የዳላስ ከተማና አካባቢውን ማኅበረ ካህናትንና ምእመናንን እንዲሁም የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን አመስግነዋል።
  8. አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ስዚህ ተስፋ ሰጪ ውይይት በሚያቀርቡት አሉታዊ ዘገባ ምክንያት ምእመናን እንዳይረበሹ የሚሉት ይገኙባቸዋል።   

ስለ ዕርቅ ሰላሙ የተሰማጨውን ሐሳብ እንዲያሰሙ ዕድል የተሰጣቸው የሰላምና የአንድነቱ ጉባዔ አባላት በበኩላቸው “የጥል ግርግዳው አልፈረሰም፣ ነገር ግን ተነቃንቋል”፤ እንዲሁም “የ20 ዓመት ችግር በአንድ ጊዜ ሊቀረፍ አይችልም ነገር ግን በትዕግስት ሁሉም ይፈታል”፤ “የሰይጣን ልቡ ተወግቷል ነገር ግን አልሞተም” የሚሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

ስለዚህ ታሪካዊ ጉባዔ አንዳንድ አስተያቶችና ቀጣይ ምልከታዎች በተመለከተ ደጀ ሰላም በሰፊው እንደምትመለስበት በማስታወስ የተስፋ፣ የአንድነትና የዕርቅ በር እንዲከፈት የጣሩትን ወገኖች ከልብ ታመሰግናለች።

“ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን - ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ”።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

17 comments:

Anonymous said...

ቸሩ እግዚአብሔር ይርዳን አንድ የምንሆንበትን ግዜ ያፍጥንልን

Anonymous said...

"Let your will be done". Amen FAO

Anonymous said...

yedihoch genzeb zim bilo le poletikegnoch mekelegna bayihon melkam new. mi'emenan gin erasachew andinetin lemefiter bitegu melkam new

Anonymous said...

It's very good news we can't give hand for devil because we have vision from God! EXCEPT MENAFICAN , POLITICAL PEOPLE AND WEDACEW AMLKACW YEONU SEWECH!

Anonymous said...

The MAIN PROBLEM is not that both sides can not work out a solution. The MAIN PROBLEM IS with the majority of MIDDLE MEN, so called "ASTARAQI'S". THEY ARE the ones who ARE fueling this fued, THEY ARE ones who in REALITY DO NOT WANT UNITY, THEY ARE the ones who are benefiting financially and politically from the disunity. I am not claiming all THESE "ASTARAQI'S" but MOST, remember it only takes ONE bad APPLE TO RUIN THE WHOLE BASKET OF GOOD APPLES, it took ONE HERETIC ARIUS to split the whole church. WHAT SHOULD BE DONE? ALL THE "ASTARAQI'S" need to be evaluated, each one, and make sure of their qualifications. For example, in Ethiopian tradition, if a husband and wife fight, one would never have a SINGLE or DIVORCED person to be astaraqi. How can that be possible? Our fathers were wiser than that. THE MAIN POINT IS the ISSUE is NOT WITH THE FATHERS OF EITHER SYNOD'S (God forbid I say this for there is only ONE SYNOD in God's eyes), the peace process is dragging not because of them, but because of those who claim they can bring they can bring peace and reconcilation between the two sides. A true shephard of the church opened my eyes to this fact a year ago, forgive my forwardness.

Anonymous said...

አሁንስ የጳጳሳት ፍቅራቸውና ክብራቸው ጠፋብኝ... ታዲያ ለምን በመመናን ይፈረዳል.... አሁን እነዚ ሰዎች ወደዚህ ሀገር ሲመጡ ያወጡት ብር እጀግ ብዙ ነው ያውም የቤተክርስቲያን ብር........አሁን ደግሞ ሌላ ብር

Unknown said...

''6ኛ'' የሚሉትን ነገር እስካልሾሙ ድረስ የፈጀውን ያህል ጊዜ ይፍጅ ለእርቀ ሰላሙ ጊዜ መስጠት አይቸግረንም። አባቶች የምንላቸው ጳጳሳት በእውነትም የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ከሆኑ፤ ዓለማውያን ገዥዎች የሚያሳድሩባቸውን ዓለማዊ ተጽእኖ ሁሉ ተቋቁመው፥ ከመንደርተኝነትና ጎሳዊ ስሜት ተላቀው፥ የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ በእጃቸው አድርገው፥ የዘጉትን ቤት ከፍተው ማኅበረ ምእመናን ባንድነት ይሰበስባሉ። ስለዚህ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ለማየት የቆየነውን ያህል አይዘገየም። ለሁሉም ቅዱስ አባታችን ሁሉንም ነገር አይተዋል እና ''ግፍዖሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍዑኒ " እያሉ የተለመደውን ለሰው ዝግ ለፈጣሪያቸው ክፍት የሆነውን ጸሎታቸውን መቀጠል ነው። 'ገሪማ ገረምከኒ ' እንል ይሆን ? መልሱ እንዳልኩት በቅርቡ ይሆናል!

Anonymous said...

Abune Natnael already told us. Don't you think it is a waste of time. Who will believe peace will come as long as there are 17 Tigray Papasat, with 7 from Wollo, 4 from Gojam and 2 from Gondar. 17 vs 13. Forget it, soon E/O/T/C will get another Pawlos. I lost my faith on these Fathers.

Anonymous said...

enko mendenew end abate mehon kakatachew egaw erasachen betkerstyanachn metebk alafenet aleben zemetaw eskmacha new enensa yebka

Ze Hamere Nohe said...

ሰላም ደጀ ሰላሞች ምንም ይሁን ምንም በከፍተኛ ጉጉት በጸሎትና በጭንቀት ስንጠባበቅ የነበረውን የእርቀ ሰላም መግለጫ አጠር ምጥን አድርጋችሁ ስላስነበባችሁን እግዚአብሔር ይስጣችሁ። የተከበራችሁ ወገኖቼ በቅድሚያ የሰላምና የእርቅ ኮሚቴው ብዙ ደክሞ ላደረገው ነገር ምስጋና ሲያንሰው ነው። ይህንን ችግር መሸምገል ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገመት የማይችል ጭንቅላት ጤንነቱ ያጠራጥራል። ውጤቱ እንደምንፈልገው ባይሆንም ጉባኤውን መዝለፍ በጣም ነውር ነው። ማንም ሰው የራሱን አስተያየት መስጠት ይችላል። ይሄ መሆን አለበት ብሎ መወሰንና መፍረድ ግን አይችልም ።ሃሳብ መስጠት ብንችልም ውሳኔውን ግን ለብፁአን አባቶች ብንተው መልካም ነው ። በሁለቱም ወገን ቀኖና መሻሩን በሁለቱም ወገን ስህተትና ጥፋት መኖሩን ተረድተናል ይህም በጥቅሉ ቀኖናው ማለትም የቤተ ክርስቲያን ህግ ፓትርያርኩ በህይወት እያሉ ሌላ ፓትርያርክ መሾም የለበትም ካለ የተሰደዱት ፓትርያርኩና ጥቂት አባቶች ብቻ እንጂ ሲኖዶሱ አልተሰደደም ሲኖዶስ እያለ ሌላ ሲኖዶስ ማቋቋም እንደማይቻል በህግ የታወቀ በመሆኑ ሁለቱም ወገኖች ይቅርታ ተጠያይቀው ሕዝበ ክርስቲያኑንም ይቅርታ ጠይቀው አንድ ሆነው አንድ እንዲያደርጉን መጸለይና የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማድረግ ተገቢ ነው። ደግሞም ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ በሕይወት እያሉ የብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ሲመት በወቅቱ በአገር ቤትም ሆነ አሁን በስደት የሚገኙት ብፁአን አባቶች ተስማምተው ያደረጉት ስለመሆኑ የተረዳን ስለሆን የጋራ ስህተታቸውን በጋራ እንዲያርሙት እንደ ልጅነታችን መጠየቅ ይቻለናል።
በአገር ቤት ያሉት አምስት ተብሎ ወደ አራት አንመለስም የሚሉትንና በውጭ ያሉትም ከነ ሙሉ ሥልጣናቸውና ክብራቸው ይመለሱ የሚሉትን እንዲያቆሙና ሁለቱም ወገኖች ለብዙሃን መገኛዎች ምንም አይነት መግለጫ ከመስጠት ተቆጥበው ወደ ሰላምና እርቅ እንዲመጡልን እንደ ልጅነታቸን መጠየቅ እንችላለን። ከጌታችን ከመድሃኒታችንና ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ እንደዚሁም ከነሱ ከአባቶቻችን የተማርነው ስለ ፍቅር እንኳን ሃላፊና ጠፊ የሆነውን ስልጣንና ክብር ይቅርና ሕይወትንም መስጠት እንደሚቻል ነው። ክርስቶስን የሚያክል ጌታ የኛ ፍቅር ገዶት በቃላት ሊገለጽ ከማይችል ዙፋኑና ሥልጣኑ ወርዶ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን ስቃይ ችሎና አሳልፎ ከሚገባው በታች ዝቅ ብሎና ተዋርዶ፣ ሞቶ፣ ተቀብሮ፣በትንሣዔው ድል አድርጎ፣ ሲዖል ድረስ ወርዶ ከዘላለም ባርነት ነጻ እንዳወጣን እሙን እንደ ሆነ ሁሉ ለፍቅር ሲባል ከአምስት ወደ አራት ይቅርና ወደ ዜሮስ ቢወረድ ? ከኔ ሃላፊና ጠፊ ስልጣን ይልቅ የቤተክርስቲያን አንድነት ይበልጣል ቢባልስ? ቤተክርስቲያን ከምትከፈል ሕዝበ ክርስቲያኑ ለቀበሮና ተኩላ ተላልፎ መሰጠቱ ከሚቀጥል፤ ለሕዝብና አሕዛብ መሳቂያና መሳለቂያ መሆናችን ከሚቀጥል፤ የኔ ሃላፊና ጠፊ ሥልጣንና ክብር ይቅርብኝ ቢባልስ? ወገኖቼ ሥርዓት ይበልጣል ወይስ ፍቅር ይበልጣል? በሰው ሰወኛው እንኳን « ስለ ፍቅር ሁሉም ይቅር ይባል የለም ወይ? የጌታ ቃል ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ ነው እያለን አይደለም ወይ ? ፩ኛ ቆሮ∕፲፫÷፩−፲፫ ። ጸብ፣ ክርክርና መለያየት የሥጋ ሥራ አይደለም ወይ? ገላትያ ፭፥፳፩ ። ይህንን ላስተማሩን አባቶቻችን በተግባር አሳዩን ብለን አንድ ሆነን በትህትናና በፍቅር ዝቅ ብለን መጠየቅ እንችላለን ።
የኢትዮጵያ መንግስት በአፍአ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አልገባም ቢልም ከጫካ ጀምሮ እስከ ዛሬ ደረስ ቤተክርስቲያናችንን እያጠፋ ስለመሆኑ እንኳን እኛ ዓለም የሚያውቀው ፀሐይ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። አሁን አሁንማ መንግስት እንዴት እንደሚዋሽ ጠፍቶታል ፕሬዘዳንት ግርማ « መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ ስለማይገባ እኔም ያለ ስራዬ ስለገባሁ የጻፍኩትን ደብዳቤ ስቤአለሁ ›› ባሉበት ማግስት እረዳታቸው ሲጠየቅ ግን በብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ላይ ቁርጥ ያለ ውሳኔውን ማሳለፉ መንግስት ጥንቱንም በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት አልፎ ወሳኝና ፈላጭ ቆራጭ መሆኑን ከማረጋገጡም በላይ ከላይ እንደ ገለጽኩት መንግስት እንዴት እንደሚዋሽ ጠፍቶታል። ስለዚህ በማንኛውም አጋጣሚ መንግስት ከቤተክርስቲያናችን ላይ የማይታይ የሚመስለውን እረጅም እጁን እንዲሰበስብ መልካሙን ገድል እኛም አባቶቻችንም በቆራጥነት ልንጋደል ይገባል። ዘመን ተገልብጦ ብዙዎች ከኛ መማር ሲገባቸው እስቲ እኛ ከነሱ እንማር። እስከ መቼ ሃይማኖታችን፣ ታሪካችን፣ ቅርሶቻችን የማንነታችን መገለጫዎቻችን ሲጠፉ፣ ገዳሞቻችን ሲታረሱ፣ ገዳማውያን አባቶቻችን ሲደበደቡ፣ ሲታሰሩ፣ ሲንገላቱ፣ ሲሰደዱ፣ ገዳማውያን እናቶቻቸን ጭመር በረሃብ አለንጋ ሲገረፉ፣ በቁማቸው በትል ሲበሉ፤ሲታረዙ እስከ መቼ ዝም ብለን እንመለከታለን ? ስለ ሃይማኖት ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም ተብለን ከታዘዘንና ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፈሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ። ሉቃ∕ ፲፮፥፲፫ ᎖ማቴ∕ ፲፥፳፰ ተብለን የለም ወይ?
ስለዚህ ከላይ ካሉ ብፁአን አባቶች ጀምሮ እስከ ታች ምዕመናንና ምዕመናት ድረስ እርስ በርሳችን ብንጠፋፋ ይሻላል ወይስ አንድ ሆነን መንግስትን ሳይሆን እግዚአብሔርን በመፍራት አጽራረ ቤተክርስቲያንን በመመከት ከታደልን በሰማእትነት አለያም እግዚአብሔር በፈቀደልን መጠን ሃይማኖታችንን ጠብቀን ለመጪው ትወልድ ብናስተላልፍ ይሻላል? ወይስ ተዋሕዶን ያለመንም ተጋድሎ ለተሃድሶ መናፍቃን ብናስረክብ ይሻላል? ወይስ እንደ ሞሮኮና ቱኒዚያ እንደ ቱርክና እንደ ሌሎችም አገሮች ስም አጠራራቸን ጠፍቶ ለአሕዛብ ተላልፈን ብንሰጥ ይሻላል? ገላትያ ፭፥፲፭። እንግዲህ ለሁላችም እሳትና ውሃ ከፊታችን ተቀምጧልና እጃችንን ወደ መረጥነው እንክተት።

Anonymous said...

ቸር ወሬ ያሰማን አሜን።

Anonymous said...

I do hope that we all desire to face the truth. If so, the following are the main results of the EOTC reconciliation meeting in Dallas during Dec. 4-8, 2012:

(a) It has failed completely as it did not result in the achievement of both fundamental objectives, namely:
(i) The lifting of the mutual "wugzet";
(ii)The prevalence of peace and unity.
(b) It was astonishing to note that the fathers were pretending to accept the principles of peace and partaking jointly in dining and the holy communion whereas, in accordance with church doctrine, they should have, first of all, resolved the formal wugzet on each other and Miimenan + Kahnat in general.
(c) In conclusion, it's obvious that after meeting three times, the current church leaders are continuing with their unholy design to sow and strengthen division within EOTC.
(d) It's time that Miimenan stop expecting much from them and think of taking an effective action themselves.

Forgive me said...

To Anonymous who stated their four points, thank you. I generally agree with all your points. Are you sure the fathers held kidase together? I believe the blame should not be only on the fathers, please refer to the comment above about the "middlemen", we too are to blame in many ways because the majority of us are supporting one side and accusing another. We need to stop if we are doing this, I am not saying agree with wrong doings; however hating the sin and loving the sinner is a better path to take. We all know there are wrongs on both sides, regardless of who done what and when, all we want to see today is unity. The Miimenan need to support unity, we need to encourage those around us whether Bishops, Priest, Deacons, other miimenan that regardless of the mistakes made within our fathers union in the past or present, what we want is their unity. They don't have to like eachother and agree; however,they need to stay together in order to please God, and also to show the world the true image of the Church. Our Lord Jesus Christ stated if two agree in my name I will grant their requests, so perhaps, there are children of God out there from both sides, who can truly agree on unity, please pray for our church. I am sure we will see a difference then.

Anonymous said...

ጤናይስጥልኝ ወንድሞች እንደምን አላችሁ:: የምታደርጉትን ታላቅ መንፈሳዊ አገልግሎት እያደንቅሁ ልዑል እግዚአብሔር ጽናቱን እና ብርታቱን እንዲሰጣችሁ ከልብ እመኛለሁ:: ብጽኡ ወቅዱስ አቡነ ማርቆርዮስን በተመለከተ ከላይ ያዘጋጃችሁትን የድምጽ መስጫ አገልግሎት አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ የሚለውን በመመረጥ ተሳትፎ አድርጌያለሁ:: መፍትሔ ካለዎት ይጻፉ የሚለውን አይቼ ግን የሚጻፍበትን ቦታ ስላላገኘሁ ነው ይሄን አስተያየት እዚህ ርዕስ ስር የጻፍኩት:: ምናልባት ካሉት ምርጫዎች ውስጥ ቅዱስ አባታችን ወደመንበራቸው ተመልሰው የአስተዳደር ስራውን ግን በእንደራሴነት ለሌላ ሊቀ ጳጳስ መስጠት የሚለውን ማካተት ያስፈልግ ይሆን ብዬ አሰብኩ:: ምን ይመስላችኋል?

Anonymous said...

እኛ ብንስማማም በነገሩ
አራትና ስድስት ቁጥር አስቸገሩ
እንዴት አምስት ደርሰን ወደ አራት እንውረድ
አንዴት ቁጥር ጠፍቶን ሊቃውንቱ እንዋረድ
ቁጥርን አሳስተን ታሪክ ከሚበላሽ
ደግሞስ ታላላቆቹ ከምንሆን ታናሽ
ለምን አንተወውም ነገሩን ጠቅለን
እኛ ወንደማማቾች በአንድነት ቀድሰን
ምእመን የዋሁን በውግዘት አሣሥረን
እያሉ ነው ብሎ እንዳይቀልድብን ሰይጣን
ታረቁልን እስቲ ተዉትና ቁጥሩን።

Anonymous said...

Dear "Forgive Me",

Thank you for your remarks and suggestions one of which is that, according to you, we should not side with either of the contending parties. You suggest a seemingly neutral approach to achieve a mutual reconciliation.

I regret, however, that your approach is unworkable for the following two major reasons:
(a) That after three supposedly sincere efforts towards unity and peace, none have succeeded so far. This is shocking especially in the context of our christian fathers who preach mutual forgiveness, tolerance, peace, and unity!
(b) That they have sullied and defied the EOTC doctrine by partaking in the holy communion as well as the Qddasie without removing the mutual "wugzet" in the first place.

Therefore, the question now is whether they deserve our confidence in achieving unity and peace during the fourth conference in Los Angeles in January. Since their primary interest is in power and worldly contentment, it's foolhardy to expect them to achieve spiritualy magnanimity.

Therefore, it's time that we, Miimenan including Kahnat, think of our options. Fortunately, we could apply the lessons of the Egyptian copts who said "enough is enough" when their spiritual leaders beheaved in a similar unacceptable manner.

It's time that we put a stop to the continued unchristian behaviour by our so-called church leaders!

Forgive me said...

Dear "Anonymous", I am thankful for your reply; it confirmed to me that I do not know anything regarding this subject matter, with the help of God I will refrain from commenting on the subject in the future. My main motivation came from a comment from my brother two nights ago, he said "This subject is too hard for me, therefore what ever I answer will be wrong." This is going to be my position from here on.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)