December 1, 2012

ግልጽ ደብዳቤ:- ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ

ዳር ፲፮ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
“በትሕትና፡ዅሉና፡በየዋህነት፡በትዕግሥትም፤ርስ፡በርሳችኹ፡በፍቅር፡ታገሡ፤
በሰላም፡ማሰሪያ፡የመንፈስን፡አንድነት፡ለመጠበቅ፡ትጉ።” ኤፌ 4:2-3
ግልጽ ደብዳቤ (PDF)
ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ
ዋሽንግተን ዲሲ
ለብጹዕ አቡነ ናትናኤል
ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ እና የአርሲ  ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
አዲስ አበባ: ኢትዮጵያ
ለብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
በያላችሁበት:
ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቆሬዎስ  : ብጹዕ አባታችን አቡነ ናትናኤል እና ብጽዓን አባቶች
ቡራኬያችሁ ይድረሰን !
ጉዳዩ :  በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ያለውን ልዩነት አስወግዶ ሰላምና አንድነትን ስለማምጣት 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ብላ አምና ርትዕት ሃይማኖትን ስታስተምርና ስትመሰክር ከመኖሯ በተጨማሪ ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያንና ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ መኩሪያ የሆኑትን ብዙ የታሪክ ቅርሶችንና ሀብታትን አበርክታለች:: ለመጥቀስ ያህል ሥነ ሕንጻ፣ ቋንቋ ከነ ሥነ ጽሑፉ፣ ሥነ ሥዕል፣ ዝማሬ፣ የሀገር ፍቅርንና ጀግንነትን ማንሳት ይቻላል:: ይሁን እንጂ ይህች ጥንታዊት፣ ታሪካዊትና ሐዋርያዊት የሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን፤ በአሁኑ ጊዜ፤ በፓትርያርክ ሲመት ምክንት በሃይማኖትና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሳይሆን በአስተዳደር ከሁለት በላይ ተከፍላለች ዚህም ምክንያት በሀገር ቤት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስና በውጪው ዓለም የሚንቀሳቀሰው ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሁም ገለልተኛ ነን በሚሉ አድባራት  በመከፋፈሏ፤ የምእመናን ሕብረትና ሰላም ጠፍቶ ልጆቿ ለነጣቂ ተኩላ ተጋልጠው እየዋለሉ ይገኛሉ።ዝሆንና ዝሆን ቢጣሉ ተጎጅው ሣሩ ነውእን አባቶቻችን አስተዳደር በመለያየታቸ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን  ታላቅ ጉዳት ደርሶባታል::  እናንተ አባቶቻችን  መለያየቱ ያስከተለውና እያደረሰ ያለው ጥፋት ይሰወራችኋል ባንልም እኛም ልጆቻችሁ ብናስታውሳችሁ መልካም ነው ከማለት አንጻር፤ ከብዙ ጥቂቶቹን እንከተለው እንጠቁማለን
1.    አስተዳደርና የተቋም ጥንካሬ
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋ ቤተ ክርስቲያን በክፍፍሉም ሆነ በተለያዩ የአስተዳደር ብልሽቶች ምክንያት ሕዝበ ክርስቲያኑ ተገቢውን መንፈሳዊ አመራር እያገኘ ነው ያለው ማለት አይቻልም::  ለምሳሌም የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል።
1.      የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መዳከ ( ግልጽነት፤ ተገቢ ቁጥጥር፤ ፍትሐዊነትና ቅልጥፍና አለመኖሩ፤ አንሙስናና ዘረኛነት መንሰራፋታቸው፤)
2.     ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን የሥልጣን እርከን፤ ግልጽ የሆነ፤ የተሟላ የደባ መስፈርት አለመኖሩ፤
3.     የቤተ ክርስቲያን መተዳደርያ ሕግ (ቃለ ዓዋዲው) በትክክል ተግባር ላይ አለመዋሉና ተዛማጅ ችግሮች
4.     የኦርቶዶክስና ሌሎች ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ዋነኛ መሠረት የሆነው ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ/APPOSTOLIC SUCCESSION/ እና ተዋረዳዊ/ ሰንሰለታዊ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር (Hierarchy) ለመጠበ::

2.   ገዳማትና አድባራት አብነት  ትምህርት ቤቶች ተገቢውን ድጋፍ ያለማግኘታቸው
5.     ለሀገርና ለወገን ጠቃሚ የሆኑ፣ የሊቃውንት መፍለቂያ የነበሩ የአብነት ትምህርት ቤቶችና ጉባኤያት እየተበተኑ ነው:: የብዙ መናንያንና ባህታውያን መጠ/ታዛ የነበሩ ገዳማትና አድባራት በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች እየተቃጠሉና እየፈረሱ ነው:: በከተማና በገጠር ያሉ ገዳማትና አድባራት በት እየተመካኘ ይዞታቸውን እየተነጠቁና ሕጋዊ መብታቸው እየተደፈረ ነው::
6.     ለኢየሩሳሌም ገዳማት  እንደ "ዴር ሡልጣን" እና ሌሎችም ገዳማት የሚያስፈልገው የዲፕሎማቲክና የሌላም እርዳታ ተዳክሟል፤
ከሀገር ውጭ በስደት ያለው ሕዝብ በአንድነትና በጋራ እየተመካከረ በሀገር ቤት ያለውን መንፈሳዊ አገልግሎት በማገዝ አድባራት፤ ገዳማትንና አብነት /ቤቶችበበቂ ሁኔታ መደገፍ እንዳይችል የውግዘቱና የአስተዳደር ልዩነቱ ሳንካ ሆኗል:: (እዚህ ላይ መጠቀስ የሚገባው፤ ውጭው ዓለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን፤ በየዓመቱ፤ ከ3-4 ቢሊዮን ዶላር ወደ ሀገር ቤት እንደምናስተላልፍ በጥናት የተረጋገጠ እውነት ነው። ነገር ግን፤ በተከሰተው የእርስ በርስ መለያየት ምክንያት ለቤተ ክርስቲያናችን የምናደርገው ርዳታ ከአቅማችን ጋር ሲነጻጸር እጅግ አናሳ ነው።)
3.   የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን መጠናከር
7.     በልዩ ልዩ ሥፍራዎች በአክራሪዎችና በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ላይ ግፍ እየተፈጸመ ነው:: በጅማ፣ በኢሉባቦር፣ በአርሲና በሌሎችም ቦታዎች ክርስቲያኖች በነጻነት ፈጣሪያቸውን እያመለኩ ባሉበት በሰይፍ ስለት እንደተቀሉ፣ እሳት እንደተለቀቀባቸው ሀገር የሚያውቀው እውነታ ነው::
8.     ያለውን አስተዳደራዊ ክፍተት በመጠቀም የቅድስት ቤተክርስቲያንን መሠረተ እምነት ለመለወጥ የሚታገለው የተሐድሶ መናእንቅስቃሴ ተጠናል:: በስማችን የሚጠሩ፣ የአበውን ስምና ማዕረግ የያዙ፣ የቤተ ክርስቲያናችንን እንጀራዋን የሚቆርሱ ነገር ውስጣቸው ቀሳጭና ኢ-ኦርቶዶክስ የሆኑ ሰዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ  ውስጥ እንክርዳድ እየዘሩ ይገኛሉ

4.   ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት በሚገባው መጠን ያለመስፋፋት
Ø  ምዕመናን የሚያስተምራቸው በማጣትና በልዩ ልዩ ሰው ሠራሽ ምክንያቶች ተስፋ እየቆረጡ ወደ ሌሎች የእምነት ድርጅቶች ፈልሰው እየሄዱ  መሆኑን በሀገራችን ዘመን አቆጣጣር ፲፱፻፺፱/፳፻ ዓ/ም የተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት ያሳያል:: በዚህ ቆጠራ መሠረት የኦርቶዶክስ ምዕመናን ቁጥር ከሌሎች እምነቶች ቁጥር ጋር በንጽጽር የነበረበት ሁኔታ ከአስር ዓመት በፊት ከነበረው በመቶ ቀንሶ ታይቷል::  
Ø  በቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ትምሕርት በተለይ ለወጣቱና ለሌሎች ዜጎችም በቂ አለመሆኑ (እንደ እንግሊዝኛ ባሉ የዓለም ቋንቋዎች አለመጠቀም ጭምር)፤
በዚህም ምክንያት፤ የዚህች ቀደምት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎትና ዕድገት እንዲሁም ሊበረክትላት የሚችለው ድጋፍ የሚፈለገውን ያህል ሊዳብር አልቻለም። ይህንን ከባድ ችግር በሚገባ በማጤን፤ በሀገር ቤትም ሆነ በውጭው ዓለም የሚገኙ የተለያዩ አካላት በቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ጉባኤዎች በማከናወን፤ መግለጫዎች በማውጣትና በደብዳቤዎች በመማጸን ሰላምን ለማምጣት ሰፊ ጥረት አድርገዋል እያደረጉም ይገኛ  
በሀገር ቤት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፭ / ባወጣው መግለጫ፤ ካካተታቸው ውሳኔዎች ውስጥ አንደኛው፤ የስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ ሕግ እስከ ኅዳር ፴ ቀን ፳፻፭ / ድረስ እንዲጠናቀቅና የፓትርያርክ ምርጫውም እንዲቀጥል ወስኗል። በአንጻሩ ደግሞ  በውጭው ዓለም በሀገረ አሜሪካ የሚገኘው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ  የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ 11/2/2012 ባወጣው መግለጫ 4ኛው ፓትርያርክ፤ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው የቀድሞ  መንበራቸው እንዲይዙና የቤተ ክርስቲያኗን አንድነት ወደ ቀድሞ ክብሯ ማምጣት የሚያስፈልግ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን አረጋግጧል።
ከላይ እንደ ተገለጸው፤ በሁለቱም አካላት የተነሳው የሃሳብ ልዩነት የቤተክርስቲያንን ዘላቂ ጥቅም በማሰብ በውይይት ሊፈታ የሚችል መሆኑን እናምናለን:: ለዚህም ኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፭  / አካባቢ፤ ለሶተኛ ጊዜ ዳላስ ሊከናወን የታቀደው የሰላምና የአንድነት ጉባኤ እንዲቀጥል የሁለቱንም ወገኖች ይሁንታ ማግኘቱ ሁሉንም የቤተክርስቲያን ልጆች ያስደሰተና በታላቅ ጉጉትና ተስፋ እንዲጠበቅ አድርጎታል
እኛም በሰሜን አሜሪካና ካናዳ በተለያዩ ግዛቶች የምንገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባላት የሆንን ካህናት፡ ዲያቆናት፡ የሰንበት /ቤት አባላት፡ በራትና በጠላላምዕመናን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት ሌት ከቀን ደፋ ቀና እያለ እር ሰላሙ እየሠራ ካለው የሰላምና እንድነት ጉባኤ ጎን በመሠለፍ በተለያየ መንገድ የድርሻችንን የድጋፍ ድምጽ እያሰማን እንገኛለን።
በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተጋረጡት ዘ ብዙ ችግሮች ሊወገዱ የሚችሉትና መፍትሔ የሚገኝላቸው ፤ ዕርቀ-ሰላም ወርዶ፤ በፍቅር፤ በሕብረት፤ ተቀናን ስንሠራ በመሆኑ አባቶቻችን ከሁሉ በፊት ለሰላምና አንድነታችን ቅድሚያ እንድትጡልን  ይህን በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ ላይ እየተጻፈ ያለውን መጥፎ ታሪክ የሚቀይር ተስፋ ለቆረጡ ምዕመናንና ምዕመናት የሚያጽናና ታላቅ ገድል እንድትሠሩልን እንለምናለን:: 
በማከተልም ይህ ያለየመለያየት ዘመን አቁሞ የአንድነት ዘመን እንዲሰፍን የተማጽኖ ድምጻችንን ስናሰማ በሁለቱም ወገን ያሉ አባቶቻችንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለያየትን ሰብረው አንድነትን እንደሚያበስሩን በመተማመን የሚከተሉትን የመፍትሔ ሃሳቦች በታላቅ ትህትና እናቀርባለን::
1.      የቤተ ክርስቲያን አንድነት መሠረት የሆኑ ካ ምእመናን በተፈጠረው ልዩነትና መከፋፈል ከፍተኛ ተጐጂ በመሆናቸው ቀደም ሲል በተደረገው የእርቅ ስምምነት መሠረት በሁለቱም በኩል የተላለፈው ውግዘት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲነሳ እንዲደረግ
2.     በአባቶች መካከል የተፈጠረው ችግር ሌላ 6ኛ ፖትርያርክ ከመመረጡ በፊት ጊዜ ተሰጥቶት ውይይት ተደርጐበት ወደ አንድነቱ እንዲመጣ፤
3.     በታሪክ አጋጣሚ በጥቃቅን ክፍተቶች በውስጥና በውጭ ችግሮች የመጡባትን ፈተናዎች በጥንቃቄ አጥንቶ አስቦና ግንዛቤን አዳብሮ ውሳኔ ለመወሰን : የቤተክርስቲያኒቱን ሁለንተናዊ ራዕይ: ስትራቴጂካዊ እቅድና ፕላን የሚነድፍ አባቶች የቤተክርስቲያን ልጆች የሆኑ ምሁራንን ያቀፈ ሁሉን አቀፍ ጉባዔ እንዲደረግ፤
4.     አባቶቻችን የፖለቲካውን ጉዳይ ለፖለቲከኞች ሰጥተው በሃይማኖት አንድነት ያሉትን ጥንካሬዎች ቅድሚያ በመስጠት አንድ መንጋ አንድ እረኛ የሚኮንበት ሁኔታ በአፋጣኝ እንዲወሰን፤
5.     ቤተ ክርስቲያናችን የምትመራበትን ሕገ ቤተክርስቲያን /ቃለ ዓዋዲን/ በውጪውም ዓለም ያለውን አስተዳደሯን የሚያማክል ይዘት እንዲኖረውና ለሁሉም ተደራሽ የሆነ አካሄድ እንዲኖረው እንዲደረግ፤ እንደዚሁም በየደረጃው ባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅሮች ውስጥ ግልጽነትና ተጠያቂነትን እንዲሰፍን የሚያደርግ አሠራር ለመዘርጋት የሚያስችል ሆኖ እንዲሻሻል እንዲደረግ
6.     በአስተዳደር ልዩነቱ ምክንያት ተዋረዳዊ/ ሰንሰለታዊ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር (Hierarchy) ወጥተው ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ወደ መዋቅሩ የሚገቡበት ሁኔታ እንዲመቻች
7.     በውጪው ዓለም ያሉ ምእመናን በቤተ ክርስቲያናቸው ጉዳይ ላይ በደረጃቸውና ኑሯቸውን መሠረት ባደረገ መልኩ ተሳታፊ የሚሆኑበት ኔታ እንዲመቻች፤

ጠቃላአባቶቻችን በሰውና በእግዚአብሔርም ፊት የሚከበሩበትን እርቀ ሰላምና አስተዳደራዊ አንድነትን በማምጣት አንድ ሃይማኖት፣ አንድ መንበር፣ አንድ ፖትርያርክ፣ አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ( ማለትም አንድ እረኛ አንድ መንጋ) እንዲኖረን የቻለውን ሁሉ እንዲያደርጉ በመስቀል ላይ ደሙን ባፈሰሰላት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምላክ ስም እንማጸናለን
በመጽሐፍ ቅዱስ “በገዛ ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቋት ዘንድ እናንተን ጳጳሳት አድረጎ ለሾመባት ለመንጋውና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ” ( ሐዋ 20፡28)። እንዳለ፤ አባቶቻችን ጥንቃቄ የተሞላበት፤ የትኛውንም ወገን የማይጎዳ በተለይ መንጋውን አንድ የሚያደርግ እና የሚያስደስት፤ ታሪክ የሚዘክረው ትውልድ የሚወሰው እርቀ ሰላምን በማድረግ የዘመናችን ሰማዕታት ትባሉልን ዘንድ በተማሕጽኖ እንጠይቃለን።
የአባቶቻችን አምላክ ቸሩ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነትን፤ ለሀገራችን ዕድገትና ብልጽግናን ያድልልን!
ከጉባኤ ካህናት ወምዕመናን ለቤተክርስቲያን ሰላም

3 comments:

tewahedo said...

yehe tsihuf le orthodox tewahedo emenet teketye hulu yemidrsbet menged befaleg ttu new dejeselam gebto yemyanabew betam tikit sew new memanu degmo eye hone yalewn kalaweke degmo yegenzabe etret yenorale seleze ezhe website lye yemiwetu tsihuf hulu lememanu yedrse.melkmune zemene egziabher yamtalen amane.

Anonymous said...

በአባቶች መካከል የተፈጠረው ችግር ሌላ 6ኛ ፖትርያርክ ከመመረጡ በፊት ጊዜ ተሰጥቶት ውይይት ተደርጐበት ወደ አንድነቱ እንዲመጣ፤

Anonymous said...

I completely agree with this article.
This is the time to influence ( or encourage) in some way our fathers to obey the church's teaching. I want to say to our fathers and concerned body we are in your side if you do the right thing. But if betray the church truth(God)) as the politicians wants you to do.
I tell you God will rectify it but you will have no place in our church. Respect politicians but fear God.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)