December 18, 2012

ምእመናን “ቅዱስ አባታችን” ብለው በሙሉ ልብና በፍቅር የሚታዘዙት አባት ይፈልጋሉ


  •  ቤተ ክርስቲያን “እንቁላልና ቲማቲም የሚወረወርበት ሌላ ፓትርያርክ” አያስፈልጋትም፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 8/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 18/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፕትርክና በ5ኛው ፓትርያርክ አረፍተ ሞት ባዶ ከሆነ ወዲህ ላለፉት 20 ዓመታት ሲያከራክር የነበረው ርዕሰ ጉዳይ እንደገና፣ እንደ አዲስ መወያያ መሆን ጀምሯል። በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃም፣ በግል ደረጃም የተለያዩ ሐሳቦችም በመንጸባረቅ ላይ ይገኛሉ። በምእመኑ ደረጃ “ነገረ ፓትርያርክ”ን ከማንሣት በፊት ዕርቀ ሰላሙ መቅደም አለበት የሚለውን አበክሮ በማቅረብ ላይ ይገኛል። የተለያዩ ደብዳቤዎችንም ለሚመለከታቸው አካላት በሙሉ አቅርበዋል። በሁሉም በኩል ሥጋት የሆነው ግን ክንደ-ፈርጣማው፣ እጀ ረዥሙ የኢሕአዴግ መንግሥት ለእምነቱ ተከታዮች ፍላጎት ሳይገዛ “የራሱን ፓትርያርክ” እንዳያስቀምጥ ነው።

በጥቅምት 6/2005 ዓ.ም ዘገባችን እንደገለጽነው መንግበኩል የመጀመሪያ የፓትርያርክ ምርጫው የምሥራቅ ሸዋ ሀገር ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ጎርጎርዮስ ሲሆኑ ይህ ካልሆነ በሁለተኛ ደረጃ የያዛቸው በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ መሆናቸው በብዙዎች ዘንድ የታመነ ነገር ሆኗል፡፡ የቀድሞው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለአንዳንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንደ እንደራሴያቸውም እንደተተኪያቸውም አስተዋውቀዋቸው ነበር የተባሉት የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስድስተኛ ፓትርያርክ ይኾኑ ዘንድ መንግሥት ወስኖ መግፋት ጀምሮ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ እንደ ምንጮቻችን ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ወደ ፕትርክናው መንበር መገፋታቸው÷ “የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን አቋም እና አሠራር (እነርሱ ራእይ ይሉታል) ያስቀጥላሉ፤ ለመንግሥት ለመታዘዝና ፍላጎቱን ለማስፈጸም ይመቻሉ” በሚል ሐሳብ ነው ተብሏል፡፡

የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልተሳካ ሁለተኛ አማራጭ ኾነው የተዘጋጁት በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ መሆናቸውን መዘገባችንም ይታወሳል፡፡ ብፁዕነታቸው ለበርካታ ዓመታት በውጭ የነበራቸው ቆይታ፣ ከቤተ ክህነቱ ችግር ጋራ ብዙ ንክኪና ትውውቅ የሌላቸው መኾኑና ከመንግሥት ጋራ አብሮ በመሥራት ረገድ አላቸው የሚባለው አቋም በጉዳዩ እጃቸውን ባስገቡት የመንግሥት ሓላፊዎች እና እነርሱን እየተባበሯቸው በሚገኙት የቤተ ክህነቱ ሰዎች ዘንድ በዕጩነት እንዲያዙ እንዳደረጋቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡ በአንድ ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣን የሚመራ ነው በተባለው በዚህ የ“ቀራቤ -መንግሥት” ፓትርያርክ ምርጫ ሂደት ድጋፍ እየሰጡ ናቸው የተባሉት የቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች’’ እንደሚገኙበት በጥቅምት 6/2005 ዓ.ም ዘገባችን ጠቅሰን ነበር፡፡

እንደ ምንጮቻችን ዘገባ ከሆነ በመንግሥት ዘንድ የመጀመሪያ ተመራጭ የነበሩት የምሥራቅ ሸዋው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ለፕትርክናው ተጠይቀው ባለመቀበላቸው ይሁን ወይም በሌላ ምክንያት ሹመቱ በኢየሩሳሌም  የኢትዮጵያ  ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሆኑት ወደ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ማጋደሉ እየተሰማ ነው። እንደ ታማኝ ምንጮቻችን መረጃ የመንግት ከፍተኛ ባለስልጣን በአካል ሄደው ጥያቄውን እንዳቀረቡላቸው፣ እርሳቸውም ሹመቱን ለመቀበል እንዳንገራገሩ ከስጥ አዋቂዎች የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

ይሁን  እንጂ  የመንግት ባለስልጣኑ ካነጋገሯቸው በኋላ  ከቤተክህነት  ተወክ  ይበራሱ ፈቃድ ባይታወቅም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ልዑካንን የያዘ ቡድን ከብፁዕ አቡነ ማትያስ ጋር መነጋገሩ ታውቋል። ኢየሩሳሌም ድረስ በመሔድ ሊቀ ጳጳሱን ያነጋገሯቸው፦     
  1.     ብፁዕ አቡነ ሕዝቅል የቅ/ሲኖዶ ዋና ጸሐፊ
  2.      አቶ ተስፋዬ ብሸት  ምክትል ጸሐፊ
  3.      አቶ እስክንድር ገ/ክርስቶስ ከሕዝብ ግንኙነት ክፍል እና
  4.      መምህር ሰለሞን ቶልቻ
ሲሆኑ ወደ እራኤል በመሄድ ሹመቱን እንዲቀበሉ  የማግባባት ሥራ እንደሠሩና እየሠሩ እንደሆነ ብፁዕነታቸፕትርክናውን ለመቀበል ከመግደርደር አልፈው ወደመቀበ ንደደረሱ ከውስጥ ምንጮ ለመረዳት ችለናል፡፡ ልዑኩ ኢየሩሳሌም የሄደበትን ምክንያት ቅዱሳት መካናትን “ለመሳለም” በሚል እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሏል።

አሁን ጥያቄው “እንቁላልና ቲማቲም የሚወረወርበት፣ በምእመኑ ዘንድ ተቀባኢነት የሌለው፣ የመንግሥት ወኪል ተብሎ የሚፈረጅ አባት በዚህ ወቅት ያስፈልገናልን የሚል ነው። በርግጥም ጥያቄው ከብፁዕ አቡነ ማቲያስ ቀርቦላቸው ከሆነ በምን ልብ ሊቀበሉት ይችላሉ? የቀድሞው ፓትርያርክ በአሜሪካና በሌሎች አገሮች በሚያደርጓቸው ጉብኝቶች የገጠማቸውን ችግር፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የደረሰውን መከራ፣ እርሳቸው ራሳቸውም በቁርጥ ሲተቹባቸው የነበሩትን ጉዳዮች በተመለከተ መፍትሔ ሳይገኝ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነቷና ሰላሟ ሙሉ በሙሉ ሳይጠበቅ ወደ ሹመት መሔድ በርግጥ ማንን ይጠቅማል?

ዘመኑ ለብፁዓን አባቶቻችን እና ለመላው ምእመን ከባድ ጥያቄ አቅርቧል። ቤተ ክርስቲያኒቱ በሕጓና በሥርዓቷ እንድትመራ ማድረግ ወይም ፈቃደ-ንጉሥ ፈጻሚት (መለካዊት) ስትሆን በዝምታ መመልከት። በተለይም የፕትርክናውን ሥልጣን “በምርጫም ይሁን በስመ-ምርጫ ለሚቀበለው አባት እጽፍ ድርብ ዕዳ ይሆናል ብለን እናምናለን። ምርጫውም ይሁን ሲመቱ ለጊዜው ደስታ ካልሆነ በቀር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ይረባታል ብለን አናምንም። የምእመኑ ድምጽ ከምንም ነገር በፊት “ዕርቀ ሰላሙ ይፈጸም፤ ቤተ ክርስቲአኒቱ አንድነቷ ይጠበቅ” የሚል መሆኑን በማያወላዳ መልኩ በመግለጽ ላይ ይገኛል። በዚህ ረገድ ደጀ ሰላም ያደረገችውን የአስተያየት መስጫ ዳሰሳ ውጤት እናቀርባለን፤ ተከታተሉን።

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን። 
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)