December 13, 2012

4ኛውን ፓትርያርክ በተመለከተ


4ኛውን ፓትርያርክ በተመለከተ የአስተያየት መስጫ ጥያቄ (ፖል) ማቅረባችን ይታወቃል። ጥያቄው “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀጣይ ፓትርያርክን በተመለከተ ድምጽዎን ይስጡየሚል ሲሆን መልሶቹም “ሀ/ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ፤  ለ/ አቡነ መርቆርዮስ በሞት እስኪያልፉ ድረስ መንበሩ በዐቃቤ መንበር ብቻ ይቆይ፤ ሐ/ 6ኛ ፓትርያርክ ይሾም፤ መ/ ሌላ መፍትሔ ካለዎት ይጻፉ፤” የሚሉ ናቸው። መልሳችሁን መስጠታችሁ እንዳለ ሆኖ “ተጨማሪ” አስተያየት መስጠት የምትፈልጉ ከሆነ እነሆ።

48 comments:

Anonymous said...

ግእዝ በመሥመር-ላይ

"አቡነ መርቆርዮስ በሞት እስኪያልፉ ድረስ መንበሩ በዐቃቤ መንበር ብቻ ይቆይ፤" What does this mean? Except: "let the division continue!" While appreciating the effort to collect our vote at least for awareness if not for any practical value, I was WORRIED to see this as one among the choices. All the more so as I see more people are voting for it, I think without understanding its implication. I would suggest DS reconsiders this choice and either cancel it altogether or qualify it in such a way it reflects that reconciliation and unity of the Church are not compromised. At the least, state clearly its divisive implication, if that is what you want to offer.
Also a more nuanced alternative of the re-enthronment of Abuna Merkorios--one that involves an appointment of a nominee for the administration--would be more attractive for many.

Anonymous said...

ጤናይስጥልኝ ወንድሞች እንደምን አላችሁ:: የምታደርጉትን ታላቅ መንፈሳዊ አገልግሎት እያደንቅሁ ልዑል እግዚአብሔር ጽናቱን እና ብርታቱን እንዲሰጣችሁ ከልብ እመኛለሁ:: ብጽኡ ወቅዱስ አቡነ ማርቆርዮስን በተመለከተ ከላይ ያዘጋጃችሁትን የድምጽ መስጫ አገልግሎት አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ የሚለውን በመመረጥ ተሳትፎ አድርጌያለሁ:: መፍትሔ ካለዎት ይጻፉ የሚለውን አይቼ ግን የሚጻፍበትን ቦታ ስላላገኘሁ ነው ይሄን አስተያየት እዚህ ርዕስ ስር የጻፍኩት:: ምናልባት ካሉት ምርጫዎች ውስጥ ቅዱስ አባታችን ወደመንበራቸው ተመልሰው የአስተዳደር ስራውን ግን በእንደራሴነት ለሌላ ሊቀ ጳጳስ መስጠት የሚለውን ማካተት ያስፈልግ ይሆን ብዬ አሰብኩ:: ምን ይመስላችኋል?

Anonymous said...

በአሁኑ አቀራረብ ከተወሰነና ቅጹን የሚሞሉት በመቶ ቢበዛም በጥቂት ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሆኑ የዳሰሳው (survey) ዘይቤ የራሱ ግድፈት ይኖረዋል። የእነዚህ ጥቂት ሰዎች መልስ እስከ ሃምሳ ሚሊዮን የሚገመቱትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ምእመናን ፍላጎት ያመለክታል ብሎ ለመደምደም ያስቸግራል። ስለዚህ ስለ ዳሰሳው ይዘት ማብራሪያ ቢሰጥበት ውጤቱ ድምዳሜ ሳይሆን ጠቋሚ ብቻ መሆኑን በቅድሚያ ለማስገንዘብ ይረዳል።

dl said...

There is not compromise in faith. Mistakes need to be corrected. Sin need to repented. Faith matter is not politics. The True patriarch, Abune Markorios, need to be restored to his place/power. He was persecuted by woyane. yayenewun eninageralen yesemanewun enmesekiralen.

Anonymous said...

abune merkoriwos ye akuwam sew aydelum kalu le min aynagerum abatin entachew le mengaw emaigedachew mindena nachew derg esepa siltan yizual bibalu yinageru yihone

Anonymous said...

6 patrairic yishome

Anonymous said...

አስተያየት ከመስጠቴ በፊት ማሳወቅ የምፈልገው በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን በጎሳ ከፋፍሎ እየገዛ ያለው መንግሥት ደጋፊ አለመሆኔን ነው።

ከዚህም በላይ በጎሳ በሽታ የተለከፈውና በአባ ጳውሎስ ሲመራ የነበረው ሲኖዶስ ለኢኦተቤ/ክ መልካም መንፈሳዊ አመራር ይሰጣታል የሚል ከንቱ እምነትም የለኝም:: ስደተኛ ነኝ የሚለውም ሆነ ሀገር ቤት ያለው ቡደን ሁለቱም የመሪያቸውን የኢየሱስን ትዕዛዝ በግል ጥቅምና በገንዘብ የለወጡ መንፈሳዊነት የሌላቸው ቡድኖች መሆናቸውን ተረድቻለሁ::

ከዚህ ውጭ ግን አቡነ መርቆሬዎስ ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው ለሚለው ከሁሉ አስቀድሞ በደርግ አገዛዝ የጎንደር ክፍለ ሀገር ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ እነ ሻለቃ መላኩ ተፈራ በሕዝቡ ላይ ያን መሳይ መከራ ሲያወርዱበት ምንም ሳይናገሩ በዝምታ በማሳለፋቸው ላደረጉት መልካም ትብብር የተቸራቸው ስጦታ እንጂ ለቦታው የሚመጥኑ አባት ሆነው አልነበረም። ይህንንም አሁን በሕይወት ያሉት ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ ይመሰክራሉ።

የኢሕአዴግ አገዛዝ ሥልጣን እንደያዘ ምን ሊደርስባቸው እንደሚችል በመጠርጠር በነ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ አማካሪነት ታምሜአለሁ ብለው ከመንበረ ፕትርክና ረብሻ ሳያስነሱ ይውረዱ ተብለው በተመከሩት መሰረት ወደውና ፈቅደው ያለማንም አስገዳጅነት ለቀቁ። እውነቱ ይህ ለመሆኑ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ የጻፉትን መጽሐፍ ማንበብ በቂ ማስረጃ ነው። አሁን ወደ ኋላ ተመልሶ በሌለ ሥልጣን ሕጋዊው ፓትርያርክ ብሎ መጥራት የሕጻናት ጨዋታ ነው። እራሱ ሕጋዊው ፓትርያርክ የሚለው አጠራር የቀልድና የሃሰት መሆኑን ያሳያል። እውን አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመን እሳቸውን ፓትርያርክ አድርጎ ይቀበላል ብሎ የሚያምን ወገን አለ? በሕልም ዓለም መኖር ይፈቀዳል። አሜሪካ ሰው ያለመውን ሊያገኝ ይችላል ቢባልም እንደዚህ ያለውን ቅዠት ግን ሕልም ልንለው አይገባም።

በአጭሩ ወደ ሃገራቸው ተመልሰው መንበሩ ላይ ይቀመጡ የሚሉት ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተማርያም ወርቅነህ ናቸው እንጂ (ይኸውም በእጅ አዙር የምቆጣጠረው እኔ ነኝ ከሚል ምኞት በመነጨ አሠራር) ራሳቸው አቡነ መርቆሬዎስ ቢጠየቁ እንደማይስማሙ የተረጋገጠ ነው:: አይ የምትለው ትክክል አይደለም የሚል ሰው ካለ እስቲ ከአቡነ መርቆሬዎስ አንደበት እውነቱን እንስማ::

Anonymous said...

Asiteyayet Sebisibu tebilachihu new Weis Yerasachihu Simet New Yihinin Agenda Makirebachu Min Lemalet Tefeligo New Enante Eneman Nachihu Patiriyarrik lememiretsim Hone Lemeshar Mebituna Siltsanu Yesinodosu new Enij Manim Tesebsibo Ayidelem Ahun Degimo Abune Merkorewosn Bemimeleket Hasabi Sitsu Yemitilut lemidinew ? Abune Merkorewos Wede Menberachew Bimelesu Akatsilachihu Yemirigedilachew Enante Nachihu

Anonymous said...

ሀ: አቡነ መርቆሬዎስ በህይዎት አሉ፤
ለ: ስልጣናቸው መንፈስ ቅዱስ የሰጣቸው ስልጣን ነው፤
ሐ: ከሃገር የወጡት ተገፍተው ነው፤
መ: ሕዝባቸውን በሙያቸው እያገለገሉ ናቸው፤
ሠ: እምነትን ያጎደሉበት ህጸጽ ካለባቸው ለምእመናን ግልጽ ይደረግ።

ምእመናን የምናውቀው፥ የምናየውና የምንሰማው ሀቅ ሕዝባቸውን በሙያቸው እያገለገሉ መሆናቸውን ነው፤ ይህ ሆኖ እያል፤ ታድያ አቡነ መርቆሬዎስ ተርማቸውን ሳይጨርሱ ለምን ሌላ ፓትርያርክ መምረጥ አስፈለገ? ውድ ወገኖቸ፤ ከኰሚዩኒዝም ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ እግዚአብሔር በሀገራችን ላይ ያደረገው ለሁላችንም ግልጽ ሳይሆንልን ቀርቶ አይደለም፤ እግዚአብሔር ያረመውን እኛ ፍጡሮቹ እንዳናበላሽ እናስተውል እንጂ፤ በማቴ ፮፥፲፬ -፲፭ ያዘዘው አባቶቻችን አይመለከታቸውምን?
ሁሉም ለማለት ብቸገርም፤ አብዛኛው ምእመናን ዛሬ ይቅር ለእግዚአብሔር እያል ይገኛል። ከአባቶቻችንም ይህንኑ ይጠበቃል። በጐች ተቅበዘበዙ፥ በጐች ጥሩ እረኛ ፈለጉ፥ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ሰግስገው ገብተው በጐችን እያመሱ ናቸው፤ የተኩላው መንጋ ራቅ ብሎ በጐች እስኪበተኑ ይጠብቃል። አባቶቻችን ሆይ ልጆቻችሁ ተኩላውን እናሸንፍ፤ እርዱን? ለቤተ ክርቲያኗና ለምእመናን አንድነት ስትሉ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን አድርጉልን?

አቡነ መርቆሬዎስ ፈቃደኛ ከሆኑና በቀራቸው የእድሜ ዘመን መንጋውን ለመጠበቅ ፈቃደኛ ከሆኑ:-
፩ ወደ ኢትዮጵያ ይግቡ፣
፪ ማእረጋቸው ፬ኛው ፓትርያርክ እንደሆነ ይጠበቅ፣
፫ አሜሪካ ከ፬ ባላነሰ አህጉረ ስብከት ትከለል፣
፬ ቃለ አዋዲ በመላው የውጭ አገር ላሉ የኢኦተቤክ ባስቸኳይ ይሰራጭ፣
፭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ከሙስናና ከዘረኝነት ባስቸኳይ ትንጻ፣
፮ ስራችን ሁሉ ክርስቶስን ይምሰል፤ ቅድስትና ብጽእት ማርያምን እናስብ፥ የመላይክትን አገልጋይነት እንይ፥ ጻድቃንና ሰማእታት ትተውልን እንዳለፉ ጠብቀን እናስተላልፍ።

የቅዱሳን አምላክ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፤ አሜን።

Anonymous said...

Hi Deje selamoch,
I have seen your post inviting us to vote for ''የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀጣይ ፓትርያርክን በተመለከተ ድምጽዎን ይስጡ''.

I think it doesn't address most Ethiopians opinion. ብዙ ሰው የሚፈልገው የአቡነ መርቆሬዎስን መመልስ ወይም በአቃቤ መንበር መቆየትን አይደለም:: አማራጭ ስለሌለን ግን ለምሳሌ እኔ ሁለቱንም ነው የመረጥኩት:: የኔና የአብዛኛው ክርስቲያን ፍላጎት ግን አቡነ መርቆሬዎስ የፕትርክናውን ማዕረግ እንደያዙ እንዲመለሱ ግን ከማንኛውም የአስተዳደር ጉዳዮች እንዲርቁ ነው:: ከአስተዳደር ስራዎች ውጭ ያሉትን ሁሉንም የፓትርያርኩን ስራዎች እሳቸው ያከናውናሉ:: ሌላ ፓትርያርክ መሾም አያስፈልግም:: መንበሩ በሳቸው ይያዛል ማለት ነው:: አቃቤ መንበር አያስፈልግም:: የአስተዳደር ጉዳዮችን የሚያከናውን አንድ ሊቀ ጳጳስ ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ተመርጦ እንደራሴ ሆኖ ከዋና ስራ አስኪያጁ ጋር እንዲሰራ ይደረጋል:: እንደ ፓትርያርኩ ሆኖ መፈረም ይችላል ማንኛውንም የአስተዳድር ጉዳዮችን ልክ ከፓትርያርኩ ስልጣን እኩል ማከናወን ይችላል:: ፓትርያርኩ ምንም እንኳን የአስተዳደር ጉዳዮችን አያከናውኑ እንጂ እንደራሴው የሚሰራውን ሁሉ ለሳቸው ማሳውቅ አለበት:: የሳቸውን ይሁንታም ማግኘት አለበት::

Anonymous said...

Hi, deje selamoch. I can't read your post today because of PDF. If it is possible please.

Anonymous said...

አቡነ መርቆሬዎስ የፕትርክናውን ማዕረግ እንደያዙ እንዲመለሱ ግን ከማንኛውም የአስተዳደር ጉዳዮች እንዲርቁ ነው:: ከአስተዳደር ስራዎች ውጭ ያሉትን ሁሉንም የፓትርያርኩን ስራዎች እሳቸው ያከናውናሉ:: ሌላ ፓትርያርክ መሾም አያስፈልግም:: መንበሩ በሳቸው ይያዛል ማለት ነው:: አቃቤ መንበር አያስፈልግም:: የአስተዳደር ጉዳዮችን የሚያከናውን አንድ ሊቀ ጳጳስ ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ተመርጦ እንደራሴ ሆኖ ከዋና ስራ አስኪያጁ ጋር እንዲሰራ ይደረጋል:: እንደ ፓትርያርኩ ሆኖ መፈረም ይችላል ማንኛውንም የአስተዳድር ጉዳዮችን ልክ ከፓትርያርኩ ስልጣን እኩል ማከናወን ይችላል:: ፓትርያርኩ ምንም እንኳን የአስተዳደር ጉዳዮችን አያከናውኑ እንጂ እንደራሴው የሚሰራውን ሁሉ ለሳቸው ማሳውቅ አለበት:: የሳቸውን ይሁንታም ማግኘት አለበት::

Anonymous said...

“6ኛ ፓትርያርክ ይሾም"
የሚለው ሀሳብ ከባድ አደጋ አለው:: ባጠቃላይ የወደፊቱን ትውልድ ያላገናዘበ ለቤተክርስቲያን አንድነትና ለመንጋው የማያስብ ይልቁንስ የራስን ወይንም የአንድን ቡድን የተሳሳተ ጉዞ መደገፍን ያመለክታል :: 6ኛ ፓትርያርክ መሾም ማለት እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እስካለን በልተን በሰላም እንኑር አይነት ነው:: ይህ ቀላል ጉዳይ አይደለም ቤተክርስቲያናችን አንድነቷንና ክብሯን ሊያስጠብቁ በሚችሉ ሰወች ልትመራ ይገባል :: በርግጥ በ“ዘሀበሻ ” ላይ እንዳነበብነው በቤተክርስቲያናችን አብላጫው አባቶች የትግራይ ተወላጆች ቢሆኑም በተወሰነ ደረጃ የምናውቃቸው መንፈሳውያንና ሃይማኖት ያላቸው አባቶች ናቸው ብለን ስለምናምን የቤተክርስቲያንን አንድነት ቅድሚያ ይሰጣሉ ብየ እኔ በበኩሌ ትንሺ ትንሺ ተስፋ አደርጋለሁ ::ነገር ግን ይዚህን ሁሉ ህዝበ ክርስቲያን ጭንቀት የማይታያቸው ከሆነ እውነት እውነት እላችኌለሁ የያዛቸው አባዜ ቀላል አይደለምና ሸክሙ ለነሱ ነው ::ጉድኮ ነው መቸም እኛን ከፋፍለው ስለ ስልጣን ብቻ ሲጨነቁ ያሳዝናል ያስተዛዝባል:: ቤተ ክርስቲያን የሰላም የመፍትሄ ምንጭ ካልሆነች የት ይደረሳል? አባቶቸ ስለ እግዚአብሄር ብላችሁ ሃጢያት ውስጥ አታስገቡን እንወዳችኌለን እናከብራችኌለን እባካችሁ እባካችሁ ከድቁና ጀምራችሁ እስከ ጵጵስና እድሜ ልካችሁን ባገለገላችኌት ቅድስት ቤተክርስቲያን ስም በወላዲት አምላክ በእመ ብርሐን ስም በመዳህኒያለም ይዥችኋለሁ ይችን ቤተክርስቲያን እንደተረከባችኌት አስረክቡን እኛም ልባችን አዝኖ አይቅር::

Anonymous said...

Nothing wrong in putting it us an option. There are, for sure, people who don't want the unity. If unity is the only option, there will be no need for voting. Tnx

Anonymous said...

አቡነ፡ መርቆርዮስ፡ ተገደው፡ መንበሩን፡ እንደለቀቁ፡ እየታወቀ፡ አሁን፡ በድምፅ፡ ብልጫ፡ አስተያየት ይሰጥ፡ ማለት፡ ስድብ፡ ነው።

Anonymous said...

“6ኛ ፓትርያርክ ይሾም"
የሚለው ሀሳብ ከባድ አደጋ አለው:: ባጠቃላይ የወደፊቱን ትውልድ ያላገናዘበ ለቤተክርስቲያን አንድነትና ለመንጋው የማያስብ ይልቁንስ የራስን ወይንም የአንድን ቡድን የተሳሳተ ጉዞ መደገፍን ያመለክታል :: 6ኛ ፓትርያርክ መሾም ማለት እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እስካለን በልተን በሰላም እንኑር አይነት ነው:: ይህ ቀላል ጉዳይ አይደለም ቤተክርስቲያናችን አንድነቷንና ክብሯን ሊያስጠብቁ በሚችሉ ሰወች ልትመራ ይገባል :: በርግጥ በ“ዘሀበሻ ” ላይ እንዳነበብነው በቤተክርስቲያናችን አብላጫው አባቶች የትግራይ ተወላጆች ቢሆኑም በተወሰነ ደረጃ የምናውቃቸው መንፈሳውያንና ሃይማኖት ያላቸው አባቶች ናቸው ብለን ስለምናምን የቤተክርስቲያንን አንድነት ቅድሚያ ይሰጣሉ ብየ እኔ በበኩሌ ትንሺ ትንሺ ተስፋ አደርጋለሁ ::ነገር ግን ይዚህን ሁሉ ህዝበ ክርስቲያን ጭንቀት የማይታያቸው ከሆነ እውነት እውነት እላችኌለሁ የያዛቸው አባዜ ቀላል አይደለምና ሸክሙ ለነሱ ነው ::ጉድኮ ነው መቸም እኛን ከፋፍለው ስለ ስልጣን ብቻ ሲጨነቁ ያሳዝናል ያስተዛዝባል:: ቤተ ክርስቲያን የሰላም የመፍትሄ ምንጭ ካልሆነች የት ይደረሳል? አባቶቸ ስለ እግዚአብሄር ብላችሁ ሃጢያት ውስጥ አታስገቡን እንወዳችኌለን እናከብራችኌለን እባካችሁ እባካችሁ ከድቁና ጀምራችሁ እስከ ጵጵስና እድሜ ልካችሁን ባገለገላችኌት ቅድስት ቤተክርስቲያን ስም በወላዲት አምላክ በእመ ብርሐን ስም በመዳህኒያለም ይዥችኋለሁ ይችን ቤተክርስቲያን እንደተረከባችኌት አስረክቡን እኛም ልባችን አዝኖ አይቅር::

ኤፍሬም ከዲሲ said...

ሰላም ደጀ ሰላም አቡነ መርቾርዮስ ከነ ሙሉ ክብራቸው ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ እፈልጋለሁ። ከነ ሙሉ ማአርጋቸው እንዲመለሱ ግን አልፈልግም። ምን ማለት ነው ትሉ ይሆናል እኚህ አባት አንዲም ቀን የሚፈሉጉትን ተናግረው አያውቁም።
ምን እንደተበደሉም አልተናገሩም ለምንድ ነው ሁሌ ስለሳቸው በሰው የሚነገረን መድረክ ላይ ወጥተው መናገር ባይፈሉጉ እንኻን ድምፃቸውን በቴፕ ቀርፀው ያሰሙን። ይህ ካልሆነ ለመፍረድ በጣም አስቸጋሪ ነው።
ከዚህ ሁሉ በሁለቱም በኩል ያሉ አባቶች ሰላም ለማውረድ ቅንነት ማሳየት አለባቸው ለስልጣን ተብሎ ሃይማኖቻችን መናድ የለበትም። ስለዚህ ቡፅዕ አባታችን ድምፃቸው ያሰሙን።

Anonymous said...

መጀመሪያ መቅደም ያለበት የቱ ነው ብለን ማሰቡ የሚሻል ይመስለኛል:: እንዳለመታደል ሆኖ ነው እንጂ እነርሱ ልጆቻቸውን ታረቁ ይቅር ተባባሉ እያሉ እያስተማሩ እነርሱ ይቅር መባባል ያቃታቸውን አባቶቻችን ወደ አንድ ማምጣት ነበር ትልቁና ዋናው መፍትሔ ከዚያ በኋላ ሁሉም በስምምነት ይሆን ነበር ግን ምን ይደረጋል ቢሆንም ግን ተስፋ አንቆርጥም:: ከላይ ያቀረባችኋቸው አማራጮች ብቻችውን መፍትሄ ሊሆኑ አይችሉም ግን ምንአልባት ቢስማሙልን አቡነ መርቆሪዎስ እንዲመለሱ እንፈልግ ይሆናል ዋናው ግን እርቀሰላሙ ነዉ ለሁሉም መፍትሄ ሊሆን የሚችለው::

Anonymous said...

አባታችን ወደ ወንበራቸው ተመልሰው ህዝቡን ይባርኩ፡ በተጨማርም የአስተዳደር ስራውን ችሎታ ካላቸው ጋር ተባብረው ይስሩ።

Anonymous said...

ye bizuhanu asiteyayet endihu new esachew ye ptrikinawin shumet yiketilu gin lela astedaderun yemisera abat yimeret

Anonymous said...

አንድ አይነት አስተያየት ደጋግመን ላለመጻፍ ስንል አንድ ሰው የሰጠውን አስተያየት ደግመን አንጽፍም:: ፌስ ቡክ ላይ እንዳለው አይነት 'like' ማረግ የሚቻል ቢሆን ኖሮ ከላይ የተሰጡት አስተያየቶች ላይ ብዙ 'like' ታገኙ ነበር:: ስለዚህ ከቻላችሁ ''ቅዱስ አባታችን ወደመንበራቸው ተመልሰው የአስተዳደር ስራውን ግን በእንደራሴነት ለሌላ ሊቀ ጳጳስ መስጠት'' የሚለውን ብታስገቡ አማራጩ ውስጥ ጥሩ ነበር::

Anonymous said...

Why talk abune merkoriyos?

Anonymous said...

Hi, deje selamoch. I can't read your post today because of PDF. If it is possible please.


Anonymous said...

stastics shows the church is losing members rapidly ... But other "menafek" churches are incresing from time to time rapidly...." Le ferusawuyan abatochachen amlak lib yistachew...."

Bisrat said...

I do completely agree with this opinion:
"አቃቤ መንበር አያስፈልግም:: የአስተዳደር ጉዳዮችን የሚያከናውን አንድ ሊቀ ጳጳስ ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ተመርጦ እንደራሴ ሆኖ ከዋና ስራ አስኪያጁ ጋር እንዲሰራ ይደረጋል:: እንደ ፓትርያርኩ ሆኖ መፈረም ይችላል ማንኛውንም የአስተዳድር ጉዳዮችን ልክ ከፓትርያርኩ ስልጣን እኩል ማከናወን ይችላል:: ፓትርያርኩ ምንም እንኳን የአስተዳደር ጉዳዮችን አያከናውኑ እንጂ እንደራሴው የሚሰራውን ሁሉ ለሳቸው ማሳውቅ አለበት:: የሳቸውን ይሁንታም ማግኘት አለበት::"
That is because:
1) There is need to appoint another patriarch while there is one who is alive.
2) Even if I don't consider him as the true father of the church (from his past experiance), I am sure that he won't accept someone who pro-EPDRF. That means one big problem has been resolved since most of the current church fathers are Abune Pawulos nominees (that means they are pro-EPDRF). We need to have someone who loves the people and the church. We need the unification of the church. We need someone who is free of politics and self interest. The church is facing many challenges from the inside (=corrupt fathers, pro-tehadiso, etc) and outside (the protestant church, the Muslims, etc).
May God bless our church

Bisrat said...

I do completely agree with the opinion:
"አቃቤ መንበር አያስፈልግም:: የአስተዳደር ጉዳዮችን የሚያከናውን አንድ ሊቀ ጳጳስ ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ተመርጦ እንደራሴ ሆኖ ከዋና ስራ አስኪያጁ ጋር እንዲሰራ ይደረጋል:: እንደ ፓትርያርኩ ሆኖ መፈረም ይችላል ማንኛውንም የአስተዳድር ጉዳዮችን ልክ ከፓትርያርኩ ስልጣን እኩል ማከናወን ይችላል:: ፓትርያርኩ ምንም እንኳን የአስተዳደር ጉዳዮችን አያከናውኑ እንጂ እንደራሴው የሚሰራውን ሁሉ ለሳቸው ማሳውቅ አለበት:: የሳቸውን ይሁንታም ማግኘት አለበት::"
That is because:
1) There is need to appoint another patriarch while there is one who is in service.
2) Even if I don't consider አቡነ መርቆሪዎስ as a true father(from his past experience), but he won't be willing to work with someone who is pro-government. The interference of the government has to be stopped (most of the current church fathers are nominees of አቡነ ፓውሎስ who was pro-government). We need to have someone who loves the people and the church. We need to see the unification of the church. We need someone who is free from politics and self interest. The church is facing many challenges from inside (corrupt fathers, pro-tehadiso ...) and outside (the protestant church, the Muslims ...).
May God bless our church

Anonymous said...

ሰላምን ስንመኝ በእውነት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት ይህ ከሆነ ውጤት ይኖረዋል ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ ደጀሰላም እውነቱን የማስረዳት ኃላፊነት ዪኖርባታል አለበለዚያ ግን ፍጹም የሆነ ስህተትን መደጋገም ስለሚሆን ቤተክርስቲያን ምንም ጊዜም ቢሆን ከችግር ትወጣለች ለማለት ያስችግራል። አብዛኛው አስተያየት ሰጪው አማኝ በቂ መረጃ ስሌለው የሚነበቡት አስተያየቶች ክበጎ አመለካከት አንጻር ሲታዩ መልካምነት ቢኖራችውም ትክክለኛነቱ አጠራጣሪ ነው። እውነቱ ምን ድነው ቢባል የአባ መርቆሬዎስ ሢመት የመንግሥትና አባ መልክጼዴቅ አሉበት ሲወርዱም ሁለቱም አሉበት። ይህ ነው እውነቱ ሊነገር የሚገባው። እርግጥ በሁሉም የፓትርያርክ ሢመት መንግሥት አለበት ዋናው ቁም ነገር ግን ለወደፊቱ ምን መደረግ አለበት የሚለው ሲሆን ለዚህም መልስ ሊሆን የሚችለው፤
1.ቤተከርስቲያንን በትክክል ማወቅ፤
2.መከብፋፈል ሳይሆን በአንድነት መቆም
3.መረጃን ከትክክለኛ ምንጭ ማግኝት፤
4.መልካሙን እረኛ እንዲስጥ በንጹሕ ልብ ወደ እግዚአብሔር ማመልከት ይህ ከሆነ ሰላምን ልናገኝ እንችላለን ብዬ አምናለሁ። አለበለዚይ ግን እኛው ራሳችን የችግሩ ተጋሪዎች ሆንን ማለት ንውና ከልብ እናስብበት።
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ዪጠብቅልን።

Unknown said...

ትላንትና በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ አዲሱ አበበ ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ ከሚባሉ ኢትዮጵያዊ ጋር በዚሁ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርጎ ነበር። ኮማንደሩ ስለቀደሙት ሊቃነ ጳጳሳቶች በፈተና መጽናት ያስታወሱን ከዚህ በፊት ቤተ-ክርስቲያኗ የነበራትን ጥንካሬ አንደኛው ምንጭ ነው ያስታወሱን። ከአቡነ ሚካኤል አና አቡነ ጴጥሮስ ተጋድሎ የማይተናነስ። ያንን ጥንካሬዋን ለመስበር ስለተፈለገ ነው ቤተክርስቲያኗ የፖለቲካ ዱላ ያረፈባት። አራተኛውም ፓትርያርክ አንደቀደሙት መሆን ሳይችሉ ቀርተው ሃገራቸውም ቤተክርስቲያናቸውንም ትተው ተሰደዋል። ነገር ግን ከዚያ ደሞ አጂግ የከፋውን ጥፋት ያጠፋ ወገን ነበረ (ወይንም አለ)። ጊዜ የሰጣቸውን የፓለቲካ ጉልበት አና ሃይል ተጠቅሞ የቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ህግ በተጣሰበት ሁኔታ የፕትርክናውን ቦታ አንዲይዙ የተደረጉት ሰው የክርስቲያናዊነት ስነ-ምግባር በውስጣቸው ቢያይል ኖሮ ፣ለቤተክርስቲያኒቱ ያላቸው ወገንተኝነት ቢያይል ኖሮ የቤተክርስቲያኒቷ መንፈሳዊ ህግ አደተጣሰ አያወቁ ፕትርክናውን መንበር ባልያዙ ነበር። ቀብተው የፕትርክና ስልጣን የሰጧቸው ጳጳሳትም ወይ የሚጠበቅባቸውን የተጋድሎ ስራ አልሰሩም። ወይ ደሞ ነገሩን ደግፈውት ነበር ማለት ነው።

ስለዚህ ማነጻጻር ካስፈለገ በመጽናት ደከም ማለት አና ክህደት በእኩልነት ሊዳኙ አይገባም። ቤተክርቲያኗ በፓለቲካ ጣልቃ አንደተገባባት በጊዜው በፖለቲካ አንጻር ጣልቃ የገቡት ሰው በህይወት ስላሉ በማያሻማ ሁኔታ የእምነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። "ይቅርታም' የጠየቁበት ጉዳይ ነው። የአሁኑም የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ጉዳዮን በህሊናቸው ዳኝተው ደብዳቤ አንዲፅፉ ያነሳሳቸው ምክንያት ይሄው ይመስለኛል። ያንን በማድረጋቸው ደሞ የደረሳባቸውን ነገር መገመት አንችላለን። የጻፉትንም ደብዳቤ አስርዘዋቸው ፣ "ያገር ክህደት ፈጽመዋል" አንደሚባሉት አስረኞች ፕሬዝዳንቱን "ይቅርታ" አስተይቀቃቸው ነገሩን በጫና አና በማስፈራራት ያኔ አማጺያኑ ሃገሪቱን ሲቆጣጠሩ ወደነበረው ሁኔታ አየወሰዱት ይመስላል።

ደበስበስ አድርገን ጉዳዮን በፓለቲካ መነጸር ያየነው አንደሆነ ---በእምነት ጣልቃ ገብነት መሆኑ ነው። ነ ፈረጥ አድርገን አንናገረው ከተባለ ደሞ በተጠና ሁኔታ ቤተክርስቲያኒቱ አንደጠላት ተፈርጃ ስለነበር አና መዳከም አንዳለባት ይታመን ስለነበረ ለዚሁ የማዳከም ስራ ይተባበራሉ ተብሎ የታሰቡ ሰው ወደ ስልጣን መተው የደረሰው ነገር ሁሉ ደረሰ። እግዚያብሔር ጊዜ አለው አንደሚባለው ጊዜውን ስራውን ሰርቶአል። የተጣሰውን የቤተ-ክርስቲያን ህግ ማስመለስ የሚቻልበት አጋጣሚ ተፈጥሮአል። ጉዳዮን አንደ ፕሬዝዳንት ግርማ በአቅም ማነስ ማስፈጸም ባይቻል አንኳን ጉዳዮን በሚያሳምን ሁኔታ የቤተክርሲያኒቷን ህግ ተከትሎ ፍርድ መስጠት ይገባ ነበር። የህዝብ አስተያየት መሰብሰብም ባላስፈለገ ነበር። ምክንያቱም ህዝቡ ፓትርያርኩ መንበራቸውን አንዲለቁ ስለተደረገበት ሁኔታ አና ኣምስተኛ ናቸው ተብለው የተነሱት ሰው አንዴት ወደ መንበሩ አንደመጡ በቤተክርስቲያን ሰዎች በኩልም( ጳጳሳት) በፍርሃት ወይንም ያለፍርሃት ጣልቃገብነቱን አንደችግር ሳይቆጥሩ አምነውበት ተባባሪ የሆኑበትን ጉዳይ ለህዝብ ይፋ ካልተደረገ - የሚሰጠው ሃሳብ የተዛባ አንደሚሆን አያጠያይቅም። ፓትሪያርኩ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አለባቸው! ከቤተክርስቲያኒቱ ህግ አንትጻር ፣ከተደረገውም ፓለቲካዊ ስህተት ፣ የእምነት ነጻነትን ከማስከበርም አንጻር ትክክለኛው ነገር ይሄ ነው። አራተኛው ፓትርያርክ በጉልበት የተነጠቁት መንበሩ ከተመለሰላቸው በኋላ ራሳቸው በእድሜም በጤናም ምክንያት የቤተክርስቲያኒቱን ጥቅም ግምት ውስጥ በማስገባት የሚወስዱት ነገር ይኖራል። የተደቀኑትንም አስቸጋሪ ሁኔታዎች አያነሱ መወያያት ይቻላል።

በሌላ በኩል ግን ፕሬዝዳንት ግርማ ደብዳቤያቸውን ከሰረዙ በኋላ ይዘውት የተነሱትን - አራተኛው ፓትርያርክ ወደ ሃገራቸው መመለስ ይችላሉ ነገር ግን በምርጫ አይወዳደሩም ወይንም መንበር አይዙም አይነት ኣስተሳሰብ -በቤተ-ክርስቲያን 'አባቶች' (ጳጳሳት) በኩል አንዲንጸባረቅ ማድረግ 'አልሸሹም ዘወር አሉ ነው' አንደሚባለው ይሆናል። አሁንም ቤተክርስቲያኗ በጉልበት አንደተያዘች ነው የሚያመላክተው። ከላይ አንደጠቀስኩት ጳጳሳቱም ተባባሪ ሆነው ለሌላ ሰው መንበር ሰጥተዋል። ምናልባት(ምናልባት!) የነሱ ሁኔታ ጠንካራ ቢሆን ኖሮ ያኔ ፓትርያርኩ እስክመሰደድ ላይደርሱ ይችል ይሆናል። ያኔ ስህተት ተሰራ። አለቀ ደቀቀ። የደረሰውም ነገር ደረሰ። አሁን ግን ተመልሶ በዛው በስህተቱ መንገድ መቀጠል በጣም አሳፋሪ ነው። በክህደቱም አንደመቀጠል ነው። የቤተክርስቲያኒቱንም ጥቅም አያስከብርም። ጉድዮ የጳጳሳት አና የሲኖዶሱ ብቻ አንዳይሆን የሰንበት ተማሪዎችም ምዕመኑም የሲኖዶሱን አባላት አጋጣሚ ፈጥሮ ይሄን ጉዳይ በአጽኖት አንዲይዙት ማድረግ ይገባል። የፖሉ ፋይዳ አልታየኝም።

ድሜጥሮስ

Anonymous said...

I think I am totally out of the way of spirituality or I am just trying to live by the words I heard; I confess that I don't have deep knowledge of the church's cannon. But, I believe that it was the Holy Spirit who elect St Paul the Apostle and other Saintly Fathers to the ministry of the Gospel; they were indeed true servants of the Lord and in their light they shined the world and in their suffering they showed their followers the straight way of salvation and the kingdom of heaven. I believe that the Holy Spirit that called these luminary stars to the service of the Gospel and worked with them is the same Holy Spirit who elect the Patriarchate to serve the true and holy church of God. We don't expect someone from another planet or continent to assume the seat of Patriarchate; He only knows who will be wise and diligent to take care of the Church, and her children from hypocritical thoughts and heretical teachings and to lead the believers towards a pious life. Our beloved fathers taught us that Christianity is a life of purity and humility. They also told us that the saintly fathers (st John Chrysostom, and others) run away and hide in a cave not to assume priesthood let alone Patriarchate. We also have been told about the story of that bishop who by the words of his beloved and wise mother remained faithful and diligent to the blessing he was entrusted by God... So what makes our fathers not to abide in the words they speak to the congregation?...If the Holy Apostles had period of fasting and prayers to ask God as to who would be replaced the place of Jude, what more prayers required in this generation!... if we are certain that the Holy Spirit has elected Abune Mekarious to the seat, then it is not our right to vote for him or to make preparation for electing the 6th one...If His Holiness Abune mekarios was expelled from the seat of the Patriarchate, he, by the will of God, and of course, if he thinks that he will be vigilant enough to shepherd the folks, will return back with out voting....I don't think that this is kind of Kebelle election.... It is really disgusting and I don't understand what really is the motive behind...To be honest, each one of us, if God will make decision on our vote, will not make rational and thoughtful voting, thinking of a better future for the church and its development in various aspect... We make our votes on different reasons; politics, race, etc. If Abune Mekarios was expelled because merely of political reason, then the ruling party should be responsible to apologize and inviting him to return back home and assume the seat again; if the vote is intended to help the ruling party back its decision on the results of the petition and vote, let it be mentioned openly and let all of us unanimously vote for him... I am not sure, given the overall accumulated problem in respect to administration and financial matters,..etc, the return of the Patriarchate or electing a 6th one with majority voting will bring any change... I don't know the will of God, but I am pessimist to electing the Patriarchate by voting over the internet via Deje Selam... Deje Selam has been doing a very great job for the last few years, I earnestly beg and advise her to keep on informing its audience and teach some individuals like me who don't have deep knowledge about the church's dogmatic and canonical teaching... I am not convinced of the legitimacy of voting over her web page... I would rather prefer to send petition to the fathers who dwell in the remote desert and the Holy monasteries, asking them, to ask in their prayers and let us know the will of God... If Deje Selam has come across with such information, she has to inform us...May the Holy Savior protect His church and resolve the problem we brought to ourselves by His Eternal Power. May the Intercession of our Lady, the Holy Virgin Mother of God be with us all!

Anonymous said...

Abune Merkoriwos wode neberew botachew yemelesu.

I voted for the first choice.which A. Or Ha.

Anonymous said...

I don't know the Ethiopian Ortodox Sinodos do. Let me ask you everyone in the Sinodos who are they. Are they believed really in Ortodxe Tewahedo. Are they believe in peace? Are they believed in UNITY? I don’t believe them because after the Sinodos meeting Abune Ysake told for journalist there weakness. Why don’t give time for peace? If Abune Merkorios take their position, we don’t know how long they live God knows. I think some of them want the position. If God wants Abune Merkorios, why don’t we wait until they go to God? Please Papasat think before your decision. We are waiting your decision for peace. Don’t give us untamed animal. Thank you our father. I believe one day he clears his House.

Anonymous said...

ሰላም ደጀሰላሞች ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና ሁለንተናዊ አድገት የምታደርጉትን ጥረት አደንቃለሁ። አሁን በሰፊው እያነጋገረ ያለዉን የፓትርያርክ ምርጫ በተመለከተ አስቀድሞ እርቁ እንዲፈጸም ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ በጸሎት፣በሃሳብ፣ ወዘተ አስተዋጽዖ እንዲያደርግ እያደረጋችሁ ያለዉ ያስመሰግናል። አሁን እያደረጋችሁት ካለው የድምጽ ድጋፍ በፊት የአገር ቤቱ ሲኖዶስ መከሪከሪያ ነጥብ ምን እንደሆነ ልናዉቅ የሚገባን ታላቅ እውነት ለብዙዎቻችን ግን የኢሕአድግ ቀጥተኛ ተጽእኖ ብቻ የሚመስለን ስለሆነ በዚህ ጊዜ ለቤተክርስቲያን ሁለንተናዊና ዘላቂ ሰላም ግልጽ ልታደርጉ ይገባል ብየ አምናለሁ።በተረፈ እግዚአብሔር የሁላችንንም ኃጢአት ሳይመለከት ለናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም ብሎ ለቤተክርስቲያናችን መልካም አባት እንዲሰጠን ሁላችንም መጸለይና አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጋችንን አናቋርጥ።

Anonymous said...

Ze Hamere Nohe said...
ሰላም ደጀ ሰላሞች ምንም ይሁን ምንም በከፍተኛ ጉጉት በጸሎትና በጭንቀት ስንጠባበቅ የነበረውን የእርቀ ሰላም መግለጫ አጠር ምጥን አድርጋችሁ ስላስነበባችሁን እግዚአብሔር ይስጣችሁ። የተከበራችሁ ወገኖቼ በቅድሚያ የሰላምና የእርቅ ኮሚቴው ብዙ ደክሞ ላደረገው ነገር ምስጋና ሲያንሰው ነው። ይህንን ችግር መሸምገል ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገመት የማይችል ጭንቅላት ጤንነቱ ያጠራጥራል። ውጤቱ እንደምንፈልገው ባይሆንም ጉባኤውን መዝለፍ በጣም ነውር ነው። ማንም ሰው የራሱን አስተያየት መስጠት ይችላል። ይሄ መሆን አለበት ብሎ መወሰንና መፍረድ ግን አይችልም ።ሃሳብ መስጠት ብንችልም ውሳኔውን ግን ለብፁአን አባቶች ብንተው መልካም ነው ። በሁለቱም ወገን ቀኖና መሻሩን በሁለቱም ወገን ስህተትና ጥፋት መኖሩን ተረድተናል ይህም በጥቅሉ ቀኖናው ማለትም የቤተ ክርስቲያን ህግ ፓትርያርኩ በህይወት እያሉ ሌላ ፓትርያርክ መሾም የለበትም ካለ የተሰደዱት ፓትርያርኩና ጥቂት አባቶች ብቻ እንጂ ሲኖዶሱ አልተሰደደም ሲኖዶስ እያለ ሌላ ሲኖዶስ ማቋቋም እንደማይቻል በህግ የታወቀ በመሆኑ ሁለቱም ወገኖች ይቅርታ ተጠያይቀው ሕዝበ ክርስቲያኑንም ይቅርታ ጠይቀው አንድ ሆነው አንድ እንዲያደርጉን መጸለይና የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማድረግ ተገቢ ነው። ደግሞም ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ በሕይወት እያሉ የብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ሲመት በወቅቱ በአገር ቤትም ሆነ አሁን በስደት የሚገኙት ብፁአን አባቶች ተስማምተው ያደረጉት ስለመሆኑ የተረዳን ስለሆን የጋራ ስህተታቸውን በጋራ እንዲያርሙት እንደ ልጅነታችን መጠየቅ ይቻለናል።
በአገር ቤት ያሉት አምስት ተብሎ ወደ አራት አንመለስም የሚሉትንና በውጭ ያሉትም ከነ ሙሉ ሥልጣናቸውና ክብራቸው ይመለሱ የሚሉትን እንዲያቆሙና ሁለቱም ወገኖች ለብዙሃን መገኛዎች ምንም አይነት መግለጫ ከመስጠት ተቆጥበው ወደ ሰላምና እርቅ እንዲመጡልን እንደ ልጅነታቸን መጠየቅ እንችላለን። ከጌታችን ከመድሃኒታችንና ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ እንደዚሁም ከነሱ ከአባቶቻችን የተማርነው ስለ ፍቅር እንኳን ሃላፊና ጠፊ የሆነውን ስልጣንና ክብር ይቅርና ሕይወትንም መስጠት እንደሚቻል ነው። ክርስቶስን የሚያክል ጌታ የኛ ፍቅር ገዶት በቃላት ሊገለጽ ከማይችል ዙፋኑና ሥልጣኑ ወርዶ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን ስቃይ ችሎና አሳልፎ ከሚገባው በታች ዝቅ ብሎና ተዋርዶ፣ ሞቶ፣ ተቀብሮ፣በትንሣዔው ድል አድርጎ፣ ሲዖል ድረስ ወርዶ ከዘላለም ባርነት ነጻ እንዳወጣን እሙን እንደ ሆነ ሁሉ ለፍቅር ሲባል ከአምስት ወደ አራት ይቅርና ወደ ዜሮስ ቢወረድ ? ከኔ ሃላፊና ጠፊ ስልጣን ይልቅ የቤተክርስቲያን አንድነት ይበልጣል ቢባልስ? ቤተክርስቲያን ከምትከፈል ሕዝበ ክርስቲያኑ ለቀበሮና ተኩላ ተላልፎ መሰጠቱ ከሚቀጥል፤ ለሕዝብና አሕዛብ መሳቂያና መሳለቂያ መሆናችን ከሚቀጥል፤ የኔ ሃላፊና ጠፊ ሥልጣንና ክብር ይቅርብኝ ቢባልስ? ወገኖቼ ሥርዓት ይበልጣል ወይስ ፍቅር ይበልጣል? በሰው ሰወኛው እንኳን « ስለ ፍቅር ሁሉም ይቅር ይባል የለም ወይ? የጌታ ቃል ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ ነው እያለን አይደለም ወይ ? ፩ኛ ቆሮ∕፲፫÷፩−፲፫ ። ጸብ፣ ክርክርና መለያየት የሥጋ ሥራ አይደለም ወይ? ገላትያ ፭፥፳፩ ። ይህንን ላስተማሩን አባቶቻችን በተግባር አሳዩን ብለን አንድ ሆነን በትህትናና በፍቅር ዝቅ ብለን መጠየቅ እንችላለን ።
የኢትዮጵያ መንግስት በአፍአ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አልገባም ቢልም ከጫካ ጀምሮ እስከ ዛሬ ደረስ ቤተክርስቲያናችንን እያጠፋ ስለመሆኑ እንኳን እኛ ዓለም የሚያውቀው ፀሐይ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። አሁን አሁንማ መንግስት እንዴት እንደሚዋሽ ጠፍቶታል ፕሬዘዳንት ግርማ « መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ ስለማይገባ እኔም ያለ ስራዬ ስለገባሁ የጻፍኩትን ደብዳቤ ስቤአለሁ ›› ባሉበት ማግስት እረዳታቸው ሲጠየቅ ግን በብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ላይ ቁርጥ ያለ ውሳኔውን ማሳለፉ መንግስት ጥንቱንም በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት አልፎ ወሳኝና ፈላጭ ቆራጭ መሆኑን ከማረጋገጡም በላይ ከላይ እንደ ገለጽኩት መንግስት እንዴት እንደሚዋሽ ጠፍቶታል። ስለዚህ በማንኛውም አጋጣሚ መንግስት ከቤተክርስቲያናችን ላይ የማይታይ የሚመስለውን እረጅም እጁን እንዲሰበስብ መልካሙን ገድል እኛም አባቶቻችንም በቆራጥነት ልንጋደል ይገባል። ዘመን ተገልብጦ ብዙዎች ከኛ መማር ሲገባቸው እስቲ እኛ ከነሱ እንማር። እስከ መቼ ሃይማኖታችን፣ ታሪካችን፣ ቅርሶቻችን የማንነታችን መገለጫዎቻችን ሲጠፉ፣ ገዳሞቻችን ሲታረሱ፣ ገዳማውያን አባቶቻችን ሲደበደቡ፣ ሲታሰሩ፣ ሲንገላቱ፣ ሲሰደዱ፣ ገዳማውያን እናቶቻቸን ጭመር በረሃብ አለንጋ ሲገረፉ፣ በቁማቸው በትል ሲበሉ፤ሲታረዙ እስከ መቼ ዝም ብለን እንመለከታለን ? ስለ ሃይማኖት ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም ተብለን ከታዘዘንና ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፈሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ። ሉቃ∕ ፲፮፥፲፫ ᎖ማቴ∕ ፲፥፳፰ ተብለን የለም ወይ?
ስለዚህ ከላይ ካሉ ብፁአን አባቶች ጀምሮ እስከ ታች ምዕመናንና ምዕመናት ድረስ እርስ በርሳችን ብንጠፋፋ ይሻላል ወይስ አንድ ሆነን መንግስትን ሳይሆን እግዚአብሔርን በመፍራት አጽራረ ቤተክርስቲያንን በመመከት ከታደልን በሰማእትነት አለያም እግዚአብሔር በፈቀደልን መጠን ሃይማኖታችንን ጠብቀን ለመጪው ትወልድ ብናስተላልፍ ይሻላል? ወይስ ተዋሕዶን ያለመንም ተጋድሎ ለተሃድሶ መናፍቃን ብናስረክብ ይሻላል? ወይስ እንደ ሞሮኮና ቱኒዚያ እንደ ቱርክና እንደ ሌሎችም አገሮች ስም አጠራራቸን ጠፍቶ ለአሕዛብ ተላልፈን ብንሰጥ ይሻላል? ገላትያ ፭፥፲፭። እንግዲህ ለሁላችም እሳትና ውሃ ከፊታችን ተቀምጧልና እጃችንን ወደ መረጥነው እንክተት።
December 11, 2012 5:38 PM

Anonymous said...

እግዚአብሔር በኣንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውልም፥፥ ጎበዝ እናስተውል፥፥


አቡነ መርቀርዮስ ሁሉንም ነገር ለእግዚኣብሔር ሰጥተዋል፥፥ እግዚኣብሔርም ሰማ

ከእርሳቸው ስደት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሚና ያላቸው ግለሰቦች ወይንም አካላት

ክንፈ ሞተ
ታምራት ታሰረ
አዲስ አበባ ሲኖዶስ ጳጳሳት ተከፋፈሉ አስከ መደብደብ ተደረሰ
ለእርቅ ዲሲ መጥቶ ... ሲመለስ ቦሌ ላይ አረፈ
አቡነ ጳውሎስ ኣረፉ
መለስ ሞተ

ቤተ ክርስቲያኒቱ ያሳለፈችውን አመታት እናስተውል፥

ዊኪ ሊክ አጋለጠ
በፕሬዘዳንቱ አንደበት እውነቱ ተገለጠ

ይህ ሁሉ አጋጣሚ ወይንስ የአምላክ ድምጽ?

በቀጣዩስ አቡነ መርቆርዮስ ምን ያዩ ይሆን። ክእርሳቸው ብዙ ተማርኩ
ፋአኦ

Anonymous said...

4 ተኛዉ pop ወደ መንበራቸዉ ተመልሠዉ በሥራቸዉ የአስተዳደር ሥራ የሚሠራ ሌላ ሊቀ ጳጳሥ በረዳትነት መሠየም ይቻላል ይህ ከሆነ አንድነታችንን መመለሥ እንችላለን

hana said...

wode abatochachin egziabehern fertachihu tewahedone amenachihu ye Ethiopiane wortodox tewhdo bet kerstiyane selamane melesulen enbawan abesulen kerstos feraje newona beyandandachihu heyewot liferde sayemeta begizi seru na elfu legnam ewonten astemerun yemenkorabachihu enhun. bekedusane amelke telemenune. tefatu enanetwo gar new egziabeher eymeskerbachihu yemeselalena begizi wode nesha temelsu erkunem afatenut. yebekachihu teshenefu alshenefe bayenet be abune bawolose yebeka yebetkrstiyanachine selame yemeles. amen

Anonymous said...

abune merkoriwos wode meneberachiwo yemelsu
betebke enasasebalen

Anonymous said...

emenet yalew sewo tegebar!
zemmmmmmmmm alu abatachine yehe ulu cihone meles eytebeku kefetariachwo.

Anonymous said...

ውድ ደጀሰላሞች፤

ስለ 6ኛው ፓትሪያርክ አሰያየም፤ የሕዝብ አስተያየት ለማግኘት ያደረጋችሁትን ጥረት አደንቃለሁ። የሕዝብ አስተያየት ዋጋ ያለው መሆኑን ለቤተ ክርስቲያናችን ጠቁዋሚ ትምህርት ነው!

በሌላ በኩል ግን፤ ስለ አንገብጋቢው የፓትሪያርክ አሰያየም ጉዳይ፤ በአስተያየት ደረጃ መወሰን እንደሌለበት እናንተም ብትሆኑ እንደምትገነዘቡ አገምታለሁ።

ከናንተ የሚብሰው፤ እጅግ አሳፋሪ የሆነው፤ በቪኦኤ አማካኝነት የቀረበው አስተሳሰብ ነው። ሰሞኑን በቪኦኤ የቀረበው አስተያየት፤ ለ6ኛው የፓትሪያርክ ምርጫ፤ "መንፈስ ቅዱስ" በተመራጭነት እንዲቀርብ ተጠቁሙዋል!!! እጅግ የሚያስገርም አባባል ነው! መንፈስ ቅዱስ፤ የእግዚአብሔር አካል መሆኑ ተረስቶ ይሆን? መንፈስ ቅዱስ የሚገኘው፤ በልባዊ ፀሎት፤ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃድ መሆኑ ተረሳ? እነአዲሱ አበበ የቤተክርስቲያን ልጆች መሆናቸው ቀረ እንዴ?

ቤተ ክርስቲያናችን፤ ስለ ፓትሪያርክ አመራረጥ፤ ግልጽ የሆነ ሕግ አላት። እባካችሁ፤ ደጀ ሰላሞች፤ በ1991 ዓ/ም ስለ ሲኖዶስ የወጣውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንና በፍትሕ መንፈሳዊ የተዘረዘረውን ሁሉ በጥንቃቄ ተመልከቱት። እውነተኛ ግንዛቤ ይኖራችሁ!!!

Anonymous said...

ገብረ ተአምረ ቅዱስ እግዚአ ብሄር በመዋዕሊሁ ለወያኔ
የተውደዳችሁ ደጀሰላማውያን ይችን አስተያየቴን ለመጽሐፍ ሳስብ አንድ ነገር ከተማርኩት ትምርት ትዝ አለኝና ገብረ ተአምረ ብየ ጽሁፌን ወይም አስተያየቴን መጽሐፍ ጀመርኩ።
እግዚ አብሔር በዘመነ ይኃዴግ ተአምር አደረገ። ሁላችንም እንደምናውቀው ታላቋ ቤተ ክርስቲያን ለሦት የተከፈለችው ያላግባብ መሆኑን ብዙ እውነተኞች አባቶች ሲናገሩ ቆ ይተዋል ነገር ግን ሐዋርያት ወመኑ የዓምነነ በእንተ ትንሳኤከ ስለትንሣኤህ ማን ያምነናል ብለው እንደተናገሩት የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆ ሬዎስን ተገዶ ከሥልጣን መውረድ ብዙው ክርስቲያን ለማመን ይቸገር ነበር ፓትርያርኩንም ፈርመው ነውሥልጣን የለቀቁት እያሉ የሚናገሩት ጥቂት የሚባሉ አልነበሩም ሎቱ ስብሐት ምሥጋና ይግባውና ቤተ ክርስቲያኗን ለመከፋፈል ያበቋት ሳይጠፉ እውነታው ለሁሉም ግልጽ ሆነ ታዲያ በዘመናችን ከዚህ የበለጠ ተአምር ያለ አይመስለኝም እግዚአብሔር ሲጣላ በትር አንሥቶ አይማታም እንደሚሉት በኢትዮጵያ ያሉ አባቶች እያንዳዳቸውን እግዚአ ብሔር ዱላ አንስቶ እንዲመታቸው መጠበቅ አይጠበቅባቸውም
አስቀድመው አርቀው ሊያስቡ ይገባል እላለው ምክንያቱም ይህ ሁሉ ህዝበ ክርስቲያን እያለቀሰ እነሱ ከዚህ በፊት የፈጸሙት በደል አንሶ አሁንም ለትዝብት ሊጥላቸው ለሰላሙ ጠንቅ ናቸው እያሉ ሲያሟቸው የነበሩት አምስተኛው ፓትርያርክ ወደማይቀሩበት አለም ሂደዋል አሁን የሰላሙ ጠንቅ ማንእንደሆነ እየታየነው እባካችሁ አባቶች በህይወት ያሉትን ፓትርያርክ ወደመንበራቸው መልሳችሁ እራሳችሁን ከትውልድ ወቀሳ አድኑ ነገር ግን እናተ ከዚህ በፊት ባያችሁት ተአምር
ካልተማራችሁ ፈርኦን ህዝቤን ልቀቅ ሲባል በለመስማቱ ምን እንደደረሰበት ለናተ መግለጽ ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብኛል እግዚአ ብሄር እናተንም ቤቴን ልቀቁ እንዳይላችሁ ዕፈራለው
የቤተክርስቲያን አምላክ ልብ ይስጣችሁ ። ለመሆኑ ለሥልጣን እምትሻሙት ከአጠገባችሁ ያሉት ሥልጣኑን ትተውት ሲሄዱ ከነሱ መማር እንዴት ይሳናችኋል

Anonymous said...

What is really wrong we Orthodoxs ..why donnt at least learn from the Muslims..we said we are more in % but just stay as an onlookers in our church's matter..The Late Abuna errects his figure and we kept quite..waldeba we kept quite..but until when?..let's join the movement and keep this parasite woyane mengist off of our religious matter...please wokeup guys..please enough sleeping!!!!!!

Anonymous said...

አለቀድሞው ፓትርያርክ ይገባል:: መንፈሳዊነት ሳይገባብት አንኳ ጉዳዩ በአለማዊ ስው አይን ቢታይ ትክክለኛው መፍትሄ የሚሆነው... ወንበሩ ለኔ ይገባኛል ብለው የሚቀናቀን ሌላ አባት እስከሌለ ድረሥ ለምን መንበሩ ለሚገባው ለባለቤቱ አይመለስም:: ይህ ብቻ ተቃዋሚ ጳጳሶቹ ለቤተክርስትያን ህግ አለመጋዛታቸውን ያሳያል::

Anonymous said...

መንበሩ ለቀድሞው ፓትርያርክ ይገባል:: መንፈሳዊነት ሳይገባብት አንኳ ጉዳዩ በአለማዊ ስው አይን ቢታይ ትክክለኛው መፍትሄ የሚሆነው... ወንበሩ ለኔ ይገባኛል ብለው የሚቀናቀን ሌላ አባት እስከሌለ ድረሥ ለምን መንበሩ ለሚገባው ለባለቤቱ አይመለስም:: ይህ ብቻ ተቃዋሚ ጳጳሶቹ ለቤተክርስትያን ህግ አለመጋዛታቸውን ያሳያል::

Unknown said...

ወደ፡ፈተና:አንዳትገቡ፡ ፀልዩ፡፡ ዛሬ፡በበተክርስቲያን፡ላይ፡የተጋረጠው፡ጋሬጣ፡ብዙ፡ነው፡፡ ቈሱም፡ዝም፡መ ጽሀፉም፡አንዲሉ፡አባቶቻችን፡ዝምታ፡መረጡ፡፡
ታረቊ፡ሲባሉ፡የናቴ፡መቀነት፡አደናቀፈኝ፡በተክርስቲያን፡ጠብቁ፡ሲባሉ፡ለህይወታችን፡አንፈራለን፡ታዲያ፡ክርስቲያኖች፡ምን፡ይበጀናል?
በበተክርስቲያን፡ላይ፡የወያኔ፡ባለስልጣን፡የነበረው፡ተፈራ፡ዋልዋ፡ያልታረመ፡ያልተገራ፡አንደበቱን፡በከፈተ፡ወቅት፡መልስ፡የሰጡት፡አባ፡ቀውስቶስ፡ብቻ፡ነበሩ፡
ሌሎቹ፡አባቶችስ? ኧረ፡ባካችሁ፡ፈጣሪያችሁን፡አክብሩት፡፡
በቅርቡ፡ደግሞ፡ስብሀት፡ነጋየተባለ፡ወያኔ፡ኣርቶዶክስን፡አንኮታክተን፡ሰብረነዋል፡ብሎ፡ሲናገር፡ሰማነው፡
ታዲያ፡አባቶች፡መግለጫ፡መስጠት፡አሁንም፡ትፈራላችሁ?
ልብ፡በሉ፡"ንሣር፡ተዘጋጅቷል፡ተቃጥቶዓል" ጆሮ፡ያለው፡ይስማ፡፡

Anonymous said...

ሰላም ደጆች እንደምን አላችሁ
ብዙ ሰዎች ለኛ ለሃጢአተኞች በአይናችን የሚታየንን እውነት ለዚያውም ከነማስረጃው ተደፍኖባቸው በድንግዝግዝ ጨለማ ተውጠው ላለፉት 21 አመታት ኖረዋል። ያም አልበቃ ብሏቸው ፓትርያርክ አቡነ መርቆሪዎስን ከደርግ ጋር ተባብረዋል መላኩ የተባለ ጨካኝን አልተቃወሙም የሚል የአሁኑን ፋሽስት መንግስት ፕሮፓግንዳ ሲረጩ እናያለን። በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን በስልጣን ላይ የነበረውን የደርግ አገዛዝ ምን አይነት አረመኔ እንደነበረ ሁላችንም የምናውቀው ነው። በምን አይነት መልኩ መቃወም እንዳለባቸው ሲታሰብ ከንቱ መሆኑና ይልቁንስ ቤተ-ክህነት በዚያን ዘመን እንድታድግ የራሷ የሆነ ነጻነት እንደነበራት እንደዛሬው ገዳማት ተደፍረው በቡልዶዘር የታረሱበት ላለመሆኑ ብዙ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል።ትልቁ ወንጀል አቡነ ቴዎፍሎስን በግፍ ከስልጣናቸው አስውግዶ መግደሉ ነበረ። ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ምንም እንኳን ላለፉት 24 አመታት አይናቸው ባላይም እና ድምጻቸውንም ባልሰማም ለእኔ ህጋዊው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ናቸው ብዬ አምናለሁ። እንደእኔ እንደእኔ ምንም ኢንተርቪ ሳይሰጡ ዝምታው እራሱ የእምነታቸው ምልክት በመሆኑ ውድጄዋለሁ።

Anonymous said...

ene ye mayigebain aba merkoriwos weyane abarereni kalu ahunim be siltani yalew engidih ye gender mengist ski meta ezaw yitebiku

Anonymous said...

I wish Abune Merkorios speak out abut this problem and make every thing clear how and why he left that people and the country on that bad time and what he like to be this time. our fathers please remember NO BODY WILL LIVE FOR EVER> DO GOOD THING TODAY>LEARN FROM Abune POWLOS. GOD BLESS OUR CHURCH AND SAVE US FROM THIS TREBLE TIME.

Anonymous said...

....it is obivious EPRDF will assign the next Pop (General)

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)